Get Mystery Box with random crypto!

ያንተ ጥንካሬ ! አይንህ ወደ ብርሀኑ አቅጣጫ ከሆነ ሊጋርድህ የሚፈልግ ጥላ ከኋላህ ያርፋል ፤ ሀ | የግጥም ረመጥ✍️

ያንተ ጥንካሬ !
አይንህ ወደ ብርሀኑ አቅጣጫ ከሆነ ሊጋርድህ የሚፈልግ ጥላ ከኋላህ ያርፋል ፤ ሀሳብ መልካም ነገር ላይ ብቻ ካረፈ መጥፎ ነገሮች አንተ ጋር ሳይደርሱ ከጀርባህ ይወድቃሉ ።


ጨለማዉ ላይ ማፍጠጥ ብርሀን አይሰጥም ፤ ድክመትህን ብቻ አጉልተህ አትይ ! አንተ ባትሆን የማታልፋቸዉ ብዙ ችግሮች ነበሩ ፤ አንተ ግን ዛሬ ደርሰሀል ፤
ወዳጄ አሁን ያለህ ጥንካሬ የምታስበዉን
ሁሉ ለማሳካት ከበቂ በላይ ነዉ !