Get Mystery Box with random crypto!

ንቃት ''''' የልብ መቅረዝ በርቶ ነፍስ ሲኖር ለእምነት ቃል፤ በሺ እንቅልፍ መሀል | የግጥም ረመጥ✍️

ንቃት
"""""
የልብ መቅረዝ በርቶ
ነፍስ ሲኖር ለእምነት ቃል፤
በሺ እንቅልፍ መሀል
ልቡ ተቀስቅሶ አንድ ሰው ይነቃል!

ይነቃል...
ከሰመመን ሀሳብ እራሱን ያርቃል፤
የእውነት አታሞ ለዓለም ይደልቃል፤
ይነቃል...
ተስፋን ያ..ሰንቃል...!

ለአብነት

"ተመልከተው ኖህን"
የፈጣሪን ቁጣ ነቅቶ ቢጠረጥር፤
በኃጢያት ህላዌ
ዓለም ሲደነቁር፤
ጎንበስ ቀና ብሎ
መርከብ ሲቆረቁር...
ባበጃጀው መርከብ
ፍጥረትን ሲያሻግር
ወደመኖር ዓለም ጥፋትን ቀልብሶ፤
ግድ የለህም እመን
ንቃት ነው ምድርን ያቆማት መልሶ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@Abelaaaaam
@Abelaaaaam