Get Mystery Box with random crypto!

ብእሬ ዝም ብል ወቀሰኝ ህሊናዬም ተቆጣ የለበስኳት ወረቀት አስበረደችኝ ተገልጣ ሰላም ነሳ | የግጥም ረመጥ✍️

ብእሬ
ዝም ብል ወቀሰኝ ህሊናዬም ተቆጣ
የለበስኳት ወረቀት አስበረደችኝ ተገልጣ
ሰላም ነሳኝ ቀለሙ በየጥጉ ተረጭቶ
ያበላኝ ብእሬ ወደቀ ገርጥቶ
እንቢኝ አለ ልቤ ሲያይ ይህን ሁሉ
እነዛ ሁላ ነበሩ ሲባሉ
አይበቅል ስር የለው አይታይ አብቦ
እንዴት ዝም በጀ ኧረ እንዴት ታስቦ
ወይስ ልኮትኩተው ከበቀለ ብዬ
ካዋፍ ልጠብቀው ወጥሬ በቆዳዬ
ግን ብእር ብእር ነው አንዴ የተፈጠረ
ሌት ከቀን ከእግዜሩ በምልጃ የመከረ
ሲነሳ አውለኝ ሲተኛ አሳድረኝ
በቀኝ እንዳዋልከኝ ለሊቱን ባርክልኝ
ነው ፀሎቱ ህዝቡንም ጠብቅልኝ
ግን ካፈር ተዋዋለ ላይመለስ ሄደ
ወደ ነበረበት እንደጉድ ነጎደ
ቀፎው ብቻ ቀርቶ ካፈር ተዋሀደ

ተገጣጠመ
በፊራኦል ለማ

T.me/Firaolled
T.me/Firaolled