Get Mystery Box with random crypto!

ትንሽ ብርሀን እግዜር ሆይ ትንሽ ብርሀን ብትሰጠን ጨለማዉ ለከት ስላጣ ፥ ስለሌለዉ መጠን ። | የግጥም ረመጥ✍️

ትንሽ ብርሀን
እግዜር ሆይ ትንሽ ብርሀን ብትሰጠን
ጨለማዉ ለከት ስላጣ ፥ ስለሌለዉ
መጠን ።

ትንሽ ብርሀን ፥ አለ አይደል
ሚያወጣን ፥ መንገዱን ከጠፋን
ከጨለማዉ ገደል ።
ትንሽ ብርሀን ፥ ለተስፋ እንዲሆነን
አለዚያማ
ተስፋ በሌለበት ፥ መኖሮ
እንዳይደክመን ።

ኬቲኤል