Get Mystery Box with random crypto!

Zehabesha

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabeshanews — Zehabesha Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabeshanews — Zehabesha
የሰርጥ አድራሻ: @zehabeshanews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 59.68K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian News

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 174

2022-05-27 13:15:10
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ላይ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።
ያየሰው የተጠረጠረው “ኹከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል” መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።
“ኢትዮ ፎረም” የተሰኘው የዩቲዮብ መገናኛ ብዙኃን አዘጋጅ የነበረው ያየሰው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ሥር የዋለው ትላንት ሐሙስ ግንቦት 18 ቀን 2014 ነበር። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያየሰውን ዛሬ አርብ ግንቦት 19 ፍርድ ቤት ያቀረበው ሲሆን የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቆበታል።
ጋዜጠኛ ያየሰውን ወክለው በችሎቱ የተገኙት ጠበቃው ታደለ ገብረመድህን፤ የተጠየቀው የምርመራ ጊዜ ውድቅ ተደርጎ ደንበኛቸው በዋስትና እንዲለቀቅ ጠይቀዋል።
የግራ ቀኙን አስተያየት ያደመጠው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፤ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የምርመራ ጊዜ በአራት ቀናት አሳንሶ 10 የምርመራ ቀናትን መፍቀዱን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።
በጽህፈት ቤት በኩል የተካሄደውን የዛሬውን የችሎት ውሎ ጋዜጠኛ ያየሰው በአካል ተገኝቶ መከታተሉም ታውቋል።
11.6K views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 10:15:25
በደቡብ አፍሪካ አንድ ኢትዮጵያዊ ሁለት ፖሊሶችን በሽጉጥ በማቁሰል ተጠርጥሮ ታሰረ፡፡
የኬፕታውን ፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል አንድሬ ትራኡት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያዊው በስርቆት ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረ ሲሆን በትላንትናው እለት ፖሊሶች አግኝተውት ሊያስሩት ሙከራ አድርገው እንደነበር አስረድተዋል፡፡ በዚህ ሙከራ ወቅት ተጠርጣሪው በሁለቱ ፖሊሶች ላይ ተኩስ በመክፈቱ ሁለቱም መቁሰላቸውንና አሁን በሆስፒታል እየታከሙ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የቆሰሉት የሰላሳ ስድስት አመቱ ሳጅንና የሀያ ስምንት አመቱ ኮንስታብል በአሁኑ ወቅት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ያስረዱት ቃል አቀባዩ የሰላሳ አንድ አመቱ ኢትዮጵያዊም በጥይት ተመቶ ቆስሎ በእስር ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
መግለጫቸውን ሲቀጥሉም ኢትዮጵያዊው ከሆስፒታል ድኖ ከወጣ በኋላ በመግደል ሙከራ፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በመያዝና በስርቆት ወንጀሎች በፍርድ ቤት ክስ እንደሚቀርብበት የገለፁት ቃል አቀባዩ ይዞት የነበረው ሽጉጥ ያልተመዘገበ መሆኑ መረጋገጡን አመልክተዋል፡፡
ምንጭ፦ ዘሐበሻ የዕለቱ ዜና
ZehabeshaOriginal
11.8K views07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 01:09:51

2.4K views22:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 20:11:52

6.7K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 19:34:33 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ግንቦት 18/2014 ረፋዱ ላይ "አድዋ ድልድይ" አጠገብ ከሚገኘው ቢሮው በሁለት መኪና በመጡ ሲቪሊ በለበሱ የደህንነት ኃይሎች ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ ቤተሰቦቹና የሙያ አጋሮቹ አድራሻውን ስናፈላልግ ውለናል።
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ፍለጋ በኋላ በተለምዶ 3ኛ የሚባለው ፖሊስ ጣቢያ አግንተነዋል::
ቀጥሎ የሆነው ትዕይንት
ከቀኑ 9:00 ሰዓት ገደማ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እጁን በካቴና ታስሮ ሁለት ሲቪል የለበሱና 4 መሳሪያ በታጠቁ ፖሊሶች ተከብቦ በዲፌንደር መኪና፣ ተከራይቶ ወደሚኖርበት መኖሪያ ቤቱ በማምራት በቤቱ ውስጥ ፍተሻ አካሂደዋል።
ፍተሻው ከ 9:15- 10:40 የቆየ ሲሆን፤ በፍተሻ ወቅት እንፈልጋቸዋለን ያሉትን የፍትሕ መፅሔት ዕትሞች ወሰደዋል።
በፍተሻው ወቅት፦

የቀድሞዋ ፍትህ ጋዜጣና ፋክት መፅሔት
ዕትሞች የተከማቹባቸው አምስት ሃርድ
ዲስኮች፣

ሳምንታዊ ህትመት የሚሰራባቸው የሥራ
ፍላሽ ዲስኮች፣

ሰባት ያህል የአሁኗ ፍትሕ መፅሔት ዕትሞችን በመለየት እንዲሁም የፅህፈት ጠረጴዛው ላይ የተገኙ ማስታወሻ መያዥያ የነበሩ ነጠላ ወረቀቶችን በመሰብሰብ ወስደዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ለፍተሻ ይዘውት የወጡ ፖሊሶች ከፍተሻው በኋላ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እስከምሽት 1:00 ሰዓት ድረስ ወደ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ አልመለሱትም።
ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ቤተሰቦቹ ቅያሪ ልብስና ራት ይዘን 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ በር ላይ እንገኛለን።
***
በፍተሻው ወቅት በኢትዮጵያ መጣ ለተባለው ለውጥ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ወደሥልጣን እንዲመጡ ላበቃቸው ለውጥ፣ ዜጎችን በማንቃት እና የአደባባይ ምክንያተኝነት እንዲፈጠር ጉልህ አበርክቶ የነበራቸው የቀድሞዎቹ የፍትህ ጋዜጣ እና የፋክት መፅሔት የተለያዩ ዕትሞች ያሉባቸው ሃርድ ዲስኮች፤ እንዲሁም ከለውጡ ወዲህ ይታዩ የነበሩ አገራዊ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት የመፍትሔ ሀሳቦች የቀረቡባቸው የፍትሕ መፅሔት ዕትሞችን ለይተው መውሰዳቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ዓለማቀፉ ማኀበረሰብ ልብ እንዲልልን እንፈልጋለን።
ቤተሰቦቹ እና የፍትሕ መጽሔት ባልደረቦች
7.8K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 17:54:19 ውድ የዘ-ሐበሻ ቤተሰቦች፤ ከዘ-ሐበሻ ኦሪጂናል ቻናል ውጪ፤ ዘ-ሐበሻ የጤና እና የህክምና መረጃዎችን የሚያጋራበት Zehabesha Health - Amharic የሚል ዩቱብ ቻናል አለው። በመሆኑም የጤና መረጃዎችን ስንለቅ ብታዩን የኛው ነው ለማለት ነው። የህክምና ባለሙያዎችን እያነጋገርን ስለምናቀርብ እንድንጠይቅላችሁ የምትፈልጉትን ጥያቄዎች ላኩልን።

ዕውነት ያሸንፋል
8.5K views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 17:47:25

8.6K views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 16:37:04

9.2K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 13:35:20 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፀጥታ ኃይሎች መወሰዱ ታወቀ!
የፍትሕ መፅሔት ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፀጥታ ኃይሎች መወሰዱን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ገለፀ።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቢሮው በነበረበት ወቅት በሁለት ተሽከርካሪ የመጡ መደበኛ (ሲቪል) የለበሱ የፀጥታ ኃይሎች ከቢሮው እንደወሰዱት ታውቋል።
10.5K views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ