Get Mystery Box with random crypto!

አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍

የቴሌግራም ቻናል አርማ adisnews — አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍
የቴሌግራም ቻናል አርማ adisnews — አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍
የሰርጥ አድራሻ: @adisnews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.65K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የዉጭ እና የሀገር ዉሰጥ አዳዲሰ
ዜናዎች የምናቀርበት ቻናል ነዉ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አለምአቀፋዊ 🌎🌏🌍
ወቅታዊ 🔊🔊🔊🔊
መረጃ የሚደርስበት ቻናል ነዉ
@Adisnews
@Adisnews
@Adisnews
እዉነተኛ የመረጃ ምንጭ

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-23 17:35:34
ህወሓት የቅድመ ግጭት ጩኸቱን እያሰማ ነው ሲል የመከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ

ህወሓቶች "የሰላም ድርድሩ ቴክኒካል ፈርሷል፣ መከላከያ ኃይሉን እያስጠጋ ነው፣ መከላከያ በከባድ መሳሪያ እየደበደበን ነው፣ ከላይ እስከታች የዕዝ ሰንሰለቱን ጠብቆ እየተፈፀመ ያለ ጥቃት ነው" ወዘተ በማለት የቅድመ ግጭት ጩኸታቸውን በስሙልኝ ፕሮፖጋንዳቸው እያስተጋቡ ይገኛሉ ሲል መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የሠራዊቱን ወቅታዊ ሁኔታ ባልተረጋገጡ፣ ባልተገቡ መረጃዎችና አሉባልታዎች የመዘገብ ወይም የማራገብ አሉታዊ ሙከራዎችም በአስቸኳይ እንዲቆሙ ሲል በጥብቅ አሳስቧል።

@Adisnews
@Adisnews
492 views14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 09:03:31
"የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲሰጥ ታቅዷል"

ትምህርት ሚኒስቴር

የ2ዐ14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በሁለት_ዙር እንዲሰጥ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለ42 ዩኒቨርሲቲዎች በተላከውን እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትክክለኛነቱን ባረጋገጠው ደብዳቤ መመልከት ችለናል።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዩኒቨርስቲዎች ፦

1. ምንም አይነት የመደበኛ ተማሪ በግቢ እንዳይኖር እንዲያደርጉ፤

2. በቀጣይ በሚገለጸው ተማሪ ቁጥር ልክ ምግብ እንዲቀርብ ዝግጅት እንዲያደርጉ፤

3. ለፈተናዎች ማቆያ ቦታ እንዲዘጋጅ እና

4. የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በፕሬዚዳንት የሚመራ ዋና ግብረ-ኃይልና በየካምፓሶቹ በዲን /ካምፓስ ኃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ-ኃይል እንዲያደራጁ መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የ2ዐ15 የአካዳሚክ ካላንደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወቅት (ከመስከረም 28 - ጥቅምት 17) ታሳቢ በማድረግ እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳስበዋል።

@Adisnews
@Adisnews
781 views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 09:03:10
የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ማስፈፀሚያ መመሪያ ፀደቀ

የከፍተኛ ትምህርትን አገራዊ ቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ማስፈፀሚያ መመሪያ ፀድቋል። መመሪያው በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦ እና ፀድቆ ለትግበራም ይፉ ሆኗል።

መመሪያው በመውጫ ፈተና ዝግጅት ሊካተቱ ስለሚገባቸው ሃገራዊ ዝቅተኛ የትምህርት ብቃት መመዘኛዎችን ፣ የሙያ ሥነምግባር ደምቦችን እና ተቋማት ሊከተሏቸው የሚገቡ የአሠራር ስነ- ስርዓቶችን አካቷል። ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መላኩ ተገልጿል፡፡

@Adisnews
@Adisnews
599 views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 17:45:49
#እኛም_አሐዱ_ብለናል

የመኖሪያ ቤት ሽልማት ለባለ እድለኞች ከአሀዱ ባንክ፡፡
ሰላም ፍቅር ጤና እንዲሆንላቹ እየተመኘን የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር #አቶ_መላኩ_ፋንታ ሀገራዊ ለዉጡን ተከትሎ ሀገራዊ ኢኮኖሚዉን ለማሳደግ የተከፈተ ባንኩ ሲሆን በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ አስተዋጽዎ ለማድረግ የተጀመረ #ባንክ ነዉ ብለዋል። በዚህም ባንካችን ስራ በመጀመሩ ምክንያት ለመላው ኢትዮጵያውያን መልካም ስጦታ ይዘን ቀርበናል እናም እድለኛ ለሆኑ 3 የአዲስ አበባ ወይም ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የመኖርያ ቤት አፓርታማ ልንሸልምዎ ዝግጅታችንን ጨርሰናል፡፡
#1ኛ_እጣ ባለ 3 መኝታ ከነሙሉ እቃው፡፡
#2ኛ_እጣ ባለ 2 መኝታ ከነሙሉ እቃው፡፡
#3ኛ_እጣ ባለ 1 መኝታ ከነሙሉ እቃው፡፡
ቀጥሎ ላሉ 100 እድለኞች የ6000 ብር ሽልማት ይኖረዋል፡፡ ይህ እጣ የሚቆየው እስከ ንሀሴ 30 ሲሆን በኮምፒዩተር እጣ አወጣጥ ዘዴ በመታገዝ እድለኞችን ንሀሴ 30 በዚ ቻናል ላይ ይፋ የምናደርግ ይሆናል፡፡
ከእናንተ ሚጠበቀው ቻናላችንን እና ቦታችንን መቀላቀል እንዲሁም ደግሞ ለዘመድ አዝማድዎ ለወዳጅቾ #በቦቱን እድላቸውን እንዲሞክሩ ቢያንስ ለ40 ሰዎች ሼር በማረግ እንዲቀላቀሉ መጋበዝ ብቻ ነው፡፡ #ከ_40_ሰው በላይ መጋበዝ እድልዎን ያሰፋል፡፡

#ቦቱ @Ahadu_bank_bot

መልካም እድል ከ አሀዱ ባንክ፡፡

https://t.me/bank_ahadu
https://t.me/bank_ahadu
830 views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 09:27:51
የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብር ኃይል ለአትሌቲክስ ቡድናችን አቀባበል ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ

በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ደማቅ ውጤት ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የልዑካን ቡድን አባላት አቀባበል ሲባል ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብር ኃይል ይፋ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ የሚገባ ሲሆን÷ ለቡድኑ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

በአቀባበሉ ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚደረጉ ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ግብረ ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ለአትሌቲክስ ቡድኑ አባላት ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ደማቅ አቀባበል የሚደረግ ሲሆን የአትሌቲክስ ቡድኑ ካረፈበት ስካይላይት ሆቴል ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በአጀብ በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ስለሚጓዝ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ግብረ ኃይሉ ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

@Adisnews
1.1K views06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 17:57:43
በአዲስአበባ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሸከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ ነው

በመዲናዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ነገ እለተ ማክሰኞ ከቀኑ 8፡30 ላይ ለሚዲያ ተቋማት ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

የታሪፍ ማሻሻያው ከሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን አፈፃፀሙ በተገቢው እንዲከወን የህግ አስከባሪ አካላት ሚና የጎላ በመሆኑ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል፡፡ህብረተሰቡም የሚወጣውን ትክክለኛ ታሪፍ አውቆ በመክፈልና ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማጋለጥ በኩል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ቢሮው መልዕክት አስተላልፏል፡፡

@Adisnews
@Adisnews
769 views14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 15:00:27
በመዲናዋ ከዛሬ ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት ይሰጣል

በአዲስ አበባ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ ይሰጣል፡፡

የክትባት ዘመቻው ከዛሬ ሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2014 የሚቆይ ሲሆን፤ ቤት ለቤት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ወላጀች ወይም አሳዳጊዎች ህጻናትን በማስከትብ ከሚደርስባችው የአካል ጉዳትና የጤና ችግር በመታደግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መጠየቁን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@Adisnews
@Adisnews
@Adisnews
1.4K views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 15:00:24 የተለያዩ መረጃ እና ዜናዎች እናቀርባለን።
@Adosnews
@Adisnews
@Adisnews
1.2K views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-12 12:31:44
ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ እንዲያሟሉ ተጨማሪ የሁለት ወር ጊዜ ተሰጣቸው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፋይናንስ ውስጥ ያለውን ውንብድና ለመቆጣጠር ለባንኮች አዲስ የደንበኛ ማንነት እንዲያዘጋጁ ያስቀመጠውን የግዜ ገደብ ማራዘሙን ተገልጿል። ምንጩ ያልታወቀና የህገወጥ ገንዘብ ለመከታተል ወይም በተጭበረበሩ ሰነዶች የሚገላበጠውን የገንዘብ ዝውውር ለማስቀረት ሁሉም ባንኮች ደንበኞቻቸው እነማን እንደሆኑ እንዲያጣሩ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ማውጣቱ ይታወሳል።

የተሰጠው ቀን ገደብ በመጠናቀቂያው ሰዓት ጥድፊያና ግርግር ታይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት የብሔራዊ ባንክ ባንኮች የደንበኛቸውን መረጃ እንዲሰንዱ ተጨማሪ የሁለት ወር ግዜ መስጠቱን ገልጿል።

@Adisnews
@Adisnews
@Adisnews
2.1K views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 13:17:02
ከ1500 በላይ የሸኔ አባላት ተደምስሰዋል፣ ከ7500 በላይ የአሸባሪው ሸኔ እና ህወሀት አባላት በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል

የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከህዝብ ጋር በመተባበር የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው የተቀናጀ ዘመቻ ከ1500 በላይ የሸኔ የሽብር ቡድን አባላት ተደምሰዋል ብለዋል።

በከተሞች ውስጥ የተደራጁ የአሸባሪው ሸኔና ህወሓት የሎጂስቲክ እንዲሁም የመረጃ ስራ የሚሰሩ ከ7500 በላይ አባላቶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ስለመሆኑም በመግለጫው ተገልፆል። ሸኔን እስከ መጨረሻው በመደምሰስ የኦሮሚያ ክልልና የኢትዮጵያን ሰላም የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

@Adisnews
3.0K views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ