Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yohansafework — ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yohansafework — ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የሰርጥ አድራሻ: @yohansafework
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.61K
የሰርጥ መግለጫ

ኦርቶዶክሳዊ ጽሑፎች ይቀርቡበታል !

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-12-21 08:46:05
"ኃጢአትን ኃጢአት የሚያደርገው በገቢር መፈጸሙ ብቻ እንደ ኾነ አድርጋችሁ አታሰቡ፡፡ ኃጢአትን ኃጢአት አድርጎ በእኛ ላይ ፍዳ የሚያመጣው ቁርጥ ሕሊናችን ነው፡፡"

~ ኦሪት ዘፍጥረት፥ ድር. 22፥9
3.8K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-18 22:38:45
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሷል፤ ያበሰብሷልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?
4.6K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-16 21:33:38 "አካሔድህን አስተካክል”

“ከአፍቃሪያችን ክርስቶስ ያገኘነው ስጦታ እንዲህ ነው ተብሎ በቃላት መግለጥ የሚቻል አይደለም፡፡ እንዴት ያልን እንደሆነ እኛ በኀጢአት እየተንፏቀቅን ባለንበት ወራት እርሱ በምሕረቱ ጐብኝቶናልና፡፡ ኀጢአት ሸክም በሆነችብን ጊዜ እርሱ በእኛ ቦታ ተገብቶ ተሸክሞልናልና፡፡ በዚህ የማይለካ ፍቅሩ ከዲያብሎስ አገዛዝ ወደ መንግሥቱ አፈለሰን /ቈላ.1፡14/፡፡ እኛው ራሳችን ርቀን እርሱ ራሱ አቀረበን፡፡ እኛ ራሳችን በድለን እርሱ ካሠልን፡፡ ተወዳጆች ሆይ! ይህን ሁልጊዜ ከልቡናችን አናውጣ፡፡ የተሠጠንን ነጻ ሥጦታ አንዘንጋ፡፡ ከምን እንደወጣን አንርሳ፡፡

ሰው ሆይ! የተጠራኸው ወደ ዘለዓለም ሕይወት ነው፡፡
የተጋበዝከው ወደ ልጁ መንግሥት ነው፡፡ ታድያ አንተ
እዚህ ስለምን ታንጠራራለህ? ስለምን እዚህ ትቀመጣለህ? ስለምን እዚህ ትንፏቀቃለህ? ስለ ሥጋህ ድሎት ብዙ ዋጋን ትከፍላለህ፡፡ ታድያ ስለ ነፍስህስ ትንሽ አይገድህምን? ወደ ሕይወት ተጠርተህ ሳለ ስለምን ወደ ሞት ትሮጣለህ? ቢያስፈለግ ይህ ያገኘኸው ስጦታ ላለማቆሸሽ ብዙ መሥዋዕትነትን መክፈል በተገባኽ ነበር፡፡ ብዙ ሰይፍን መታገሥ በተገባህ ነበር፡፡ ወደ እሳት እንኳ ብትጣል ስለ ድኅነተ ነፍስህ መቋቋም ይገባህ ነበር፡፡ ወዳጄ ሆይ! እስኪ ንገረኝ! የመንግሥተ ሰማያት ዜጋ ለመሆን ተጠርተህ ሳለ ራስህን የዚህ ዓለም ዜጋ ማድረግህ ስለምንድነው? እንደምን ያለ ስንፍና እንደያዘህስ ታስተውላለህን? ይህን ዓለም የመውደደህ ምስጢር ምቾትን መሻትህ ያሳያል፡፡ በዚህ ዓለም በምቾት መኖርን የሚሻ ሰው ደግሞ ክርስቲያን መሆን፣ ክርስቲያን ተብሎ መጠራት፣ ክርስቶስን መስሎ መመላለስ ምቾት ሳይሆን እስር ቤት መስሎ ይታየዋል፡፡ ሁላችንም ወደዚሁ ቈጥ ካስገባን ሰነባብተናል፡፡ ከዚህች ዓለም ጋር የተወዳጀ ግን ምንም ክርስቲያን ቢባልም ምንም በአርባና በሰማንያ ቀኑ የሥላሴን ልጅነት ቢያገኝም ክርስቲያን ክርስቲያን መሽተቱ እየጠፋ ይሔዳል፡፡በዚኽ ዓለም ወጥመድ ተቀፍድዶ ይያዛል፡፡

ወዳጄ ሆይ! ይህን አድምጥና ፍርሐትና ረዓድ ይያዝህ!!! ምንም በቤተ መንግሥት ብትኖርም፣ ምንም በተሽቆጠቆጠ መኖርያ ቤት ብትኖርም እንደተመቸህ አድርገህ አትንገረኝ፡፡ አንተ የምትኖርበት ኑሮ ለእኔ ወኅኒ ቤት ነው፤ ያውም ሊፈርስ የተቃረበ ቤት!!! ይኽ ቤትህ ክረምት ሲመጣ ይፈርሳል፡፡ ክረምት (የመጨረሻይቱ ቀን) ስትመጣ ቤትህ ይፈርሳል፡፡ ክረምት ስላልኩህ ደግሞ “ለሁሉም ሰው ክረምት ከሆነበት እኔ ከማን እለያለሁ” ብለህ አታስብ፤ ይህቺ ቀን ለሁሉም ክረምት አትሆንምና፡፡ ዳግመኛም እግዚአብሔር ሌሊትና ቀን ብሎ ጠርቷታልና፡፡ ሌሊት የምትሆንባቸው ለኀጥአን ነው፤ ቀን የምትሆንላቸው ደግሞ ለጻድቃን ነው፡፡ እኔም ክረምት ብዬ መናገሬ ከዚህ አንጻር ነው፡፡ ሁላችንም ክረምት ሲመጣ መብረር እንችል ዘንድ በበጋው ላይ ካላደግን የገዛ እናቶቻችን እንኳ ቢሆኑ ትተዉን ይሔዳሉ እንጂ በዚያ ሰዓት እኛን መሸከም (ማዳን) አይቻላቸውም፡፡ የገዛ እናቶቻችን እንኳ በረሃብ እንሞት ዘንድ ትተዉን ይሔዳሉ፡፡ ቈጡ (ቤቱ) በላያችን ላይ ሲፈርስ እኛን መታደግ አይቻላቸውም፡፡ እግዚአብሔር ቤቱን ሲያፈርሰው፣ አሮጌው እንደ አዲስ ሲያደርገው፣ እያንዳንዱ እንዳልነበረ ሲሆን እኛን መርዳት የሚችል አንድ ስንኳ አይገኝም፡፡ የዚያን ጊዜ ጌታን በአየር ላይ መገናኘት የማይችሉቱ፣ የመንፈስ ክንፍ ተሰጥቶአቸው መብረር የማይችሉቱ ቤቱ በላያቸው ላይ ይፈርስባቸዋል፡፡ ስቃይ የስቃይም ስቃይ ይሆንባቸዋል፡፡ ስቃዩ የስቃይ ስቃይ ነው ማለቴ ከ እስከ የሚባል ስለሌለው ነው፤ ለዘለዓለም ስቃይ ስለሆነ ነው፡፡ ክረምት ብዬ መጥራቴ ስለዚሁ ነው፤ ኧረ እንደውም ከክረምት የባሰ ነው፡፡ እንዴት ያልከኝ እንደሆነ በዚሁ፡ክረምት ላይ የሚዘንበው ውኃ አይደለምና፤ እሳት እንጂ፡፡ በዚሁ ክረምት ዙርያህ ጨለማ የሚሆነው ከደመና ብዛት የተነሣ አይደለምና፤ ጽኑ ጨለማ እንጂ፡፡ የብርሃን ጭላንጭል የሌለው ጨለማ እንጂ፡፡ እዚህ የሚገቡት ሰዎች ተድላ መንግሥትን ማየት አይቻላቸውም፤ ሰማያትን ማየት አይቻላቸውም፡፡ ከመቃብር ውስጥ የባሰ ጨለማ ይውጣቸዋል እንጂ፡፡

ወዳጄ ሆይ! አሁንስ አትርድምን? ወዴት እየሔድክ እንደሆነ አታስተውልምን? ፊትህንስ ወደ ልጁ መንግሥት አታደርግምን?”… አካሔድህን አስተካክል
4.4K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, edited  18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-12 11:33:43 + ለምንድን ነው የምንጾመው? +

እንደ አንድ ክርስቲያን [በግልም በአዋጅም] በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡ ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ! ለምንድን ነው የምንጾመው? በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን? በየቀኑ እግዚአብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታወቀ የተረዳ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ [በመጾማችን - በመራባችን] ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?

በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡ ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያት ነው፡፡

#አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች - ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ - አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡ በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደ ኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡

#ኹለተኛው ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ አጥቶ የመራብ ትርጕሙ ምን ማለት እንደ ኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡ በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድናስብ ያስፈልጋል፡፡
11.2K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-08 21:50:42
"ለወፎች ክንፍ የተሰጣቸው"

ለወፎች ክንፍ የተሰጣቸው በወጥመድ እንዳይያዙ ነው። ሰዎችም የማሰቡ ኃይልን የተሰጣቸው ኃጢአትን እንዲያስወግዱ ነው። እንግዲህ እንዲህ የማሰብ ኃይል ተሰጥቶን ሳለ ይባስ ብለን ከምድር አራዊት በታች የማናስተውል ከኾንን ሊደረግልን የሚችል ምህረት ወይም ይቅርታ እንደምን ያለ ምሕረት እንደምንስ ያለ ይቅርታ ነው?

በወጥመድ ተይዛ የነበረች ወፍ ድንገት ከወጥመዱ ብታመልጥ፤ ወደ ወጥመድ ገብቶ የነበረ አጋዘን ወጥመዱን በጣጥሶ ቢሄድ ከእንግዲህ ወዲህ በተመሳሳይ ወጥመድ እነዚህን መያዝ ከባድ ነው። የሕይወት ተሞክሮ ለሁለቱም ጥንቃቄን አስተምሯቸዋልና። እኛ ግን ምንም እንኳ በተመሳሳይ ወጥመድ ብንያዝም ተመልሰን ወደዚያ ወጥመድ እንወድቃለን፣ ምንም እንኳን በለባዊነት የከበርን ብንኾንም አእምሮ እንደሌላቸው እንሰሳት እንኳን ቀድመን አናስብም፤ አንጠነቀቅም!

ሴትን በማየት እልፍ ጉዳቶችን ተቀብለን ወደ ቤታችን የተመለስነው፤ በዝሙት ተመኝተንም ስናበቃ ለአያሌ ቀናት ያዘንነው ስንቴ ነው? ነገር ግን ከዚያ በኋላም ቢሆን በዚሁ ጉዳይ ላይ ጠንቃቆች አልኾንም፤ አንዱን ቁስል ሳናገግም ወደዚያ ክፉ ጠባይ እንወድቃለን፣ በተመሳሳይ መንገድ እንያዛለን፤ እጅግ ጥቂት ለኾነች የደስታ ሽርፍራፊ ብለንም ረጅምና ተደጋጋሚ ሥቃይን እንቀበላለን።

ዘውትር "በወጥመዶች መካከል እንደምትኼድ በገደልም መካከል እንደምትመላለስ ዕወቅ" የሚለውን ኃይለ ቃል ደጋግመን ለራሳችን ብንነግረው ግን ከእነዚህ ጉዳቶች ኹሉ እንጠበቃለን (ሲራ 9:13)

~ በእንተ ሐውልታት
5.6K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-02 22:31:05
“ጋብቻ ልጆችን ለመውለድ የተሰጠ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ግን ወደ በባሕርያችን ዘልቆ የገባውን ፆር እንገታበት ዘንድ የተሰጠ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ሲመሰክር፡- ‘ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት' ብሏል (1ኛ ቆሮ.7፡2)፡፡ ‘ልጅ ስለ መውለድ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው' አላለም፡፡ እንድናገባ የጠየቀንም የብዙ ልጆች አባት እንድንኾን አይደለም፡፡ ታዲያ? ‘ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ' (1ኛ ቆሮ.7፡5)፡፡ ጥቂት ወረድ ብሎም ‘ብዙ ልጆችን መውለድ ቢፈልጉ' ሳይኾን ‘ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ' አለ (1ኛ ቆሮ.7፡9)፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልሁት፥ መጀመሪያ ላይ ጋብቻ እነዚህ ኹለት ዓላማዎች ነበሩት፡፡ ምድርና ባሕር ዓለምም ኹሉ በሰው ከተሞላች በኋላ ግን የሚቀረው አንድ ዓላማ ብቻ ነው - ሴሰኝነትንና ፈቃደ ሥጋን መግታት!”

ትንሿ ቤተ ክርስቲያን፥ ገ. 131
4.5K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-02 06:57:53
ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ ዐይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው ? ታዲያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘላለም ሲወድቁ እንድምን እጃችን የበለጠ አይዘረጋም ? ወገኖቼ! በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰው ስታዩ " የእኔ ሥራ አይደለም፣ የቀሳውስቱና የመነኮሳት ሥራ እንጂ። " አትበሉ። አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ " ይህ እኔን አይመለከተኝም ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ " ትላላችሁን ? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሱት አይደለምን ? ይህ ወደ ዘላለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ እንዲወድቅ አትደግፉት።

ሰማዕትነት አያምልጣችሁ
ተርጓሚ ገብረእግዚአብሔር ኪደ
4.4K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 08:22:08
“ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥ አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡ አስቀድመህ እንደዚህ ካደረግህም፥ ወደ ትዳር ከገባህ በኋላ ፍቺ አይገጥምህም፡፡ ሚስትህ ሌላ ሰውን አትመኝም፡፡ በሌላ ሴት እንድትቀናም አታደርግህም፡፡ በመካከላችሁ [ለክፉ የሚሰጥ] ጠብና ክርክር አይኖርም፡፡ ከዚህ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና ፍቅር በመካከላችሁ ይሰፍናል፡፡ እነዚህ ካሉ ደግሞ ሌሎች በጎ ምግባራትን፣ ትሩፋትን ለመፈጸም አትቸገሩም፡፡”

ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ፣ ገጽ 33
3.9K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 22:32:25
“አንኳኩቼ አላገኘሁም” አትበል፡፡ ብቻ የለመንከው፣ ደጅ የጠናኸው አንተ የምትወደው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚወድልህ ይሁን፡፡ ወደ እግዚአብሔር የተዘረጋ እጅ ፈጽሞ ባዶውን አይመለስም፡፡ ስለዚህ ራስህን፣ ልመናህን ምን ዓይነት እንደሆነ ፈትሽ እንጂ አንኳኩቼ አላገኘሁም አትበል፡፡ እንኳንስ ንጹሐ ባሕርይ የሆነው እግዚአብሔር ክፋት የሚስማማው ምድራዊ አባትም ለልጁ ጀሮውን አይደፍንም፡፡

አስቀድሞ ሕያዊት ነፍስን “እፍ” ብሎ እንዲሁ የሰጠን ጌታ፣ ኋላም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጁን ሳይራራ ከሰጠን እንደምን በዚህ ይታማል? እንደምንስ አይሰጠንም እንላለን? /ሮሜ.8፥32/፡፡ ልጁን የሰጠው እኮ ጭራሽ “ስጠን” ብለው ላልለመኑ አሕዛብም ጭምር ነው፡፡ ታድያ እንዲህ የምንለምን እኛማ እንዴት አብልጦ አይሰጠንም? የሚበልጠውን ሰጥቶን ሳለስ እንደምን ትንሹን አይሰጠንም እንላለን? ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀውን ሳናደርግ “እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማም” የሚል የሰነፎች አባባል የምንናገር አንሁን፡፡ ጆሮን የፈጠረ ይሰማል!”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ ገጽ 178
3.7K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-29 11:27:54
"ጋብቻ በአግባቡ ሊኖሩበት ለሚፈቅዱ ሰዎች የንጽሕና ደሴት ነው፤ የአንድ ሰው ተፈጥሮ አውሬያዊ እንዳይኾንም ይጠብቀዋል፡፡ አንድ ግድብ የሚፈስሰውን ውኃ ገድቦ እንደሚይዘው ኹሉ፥ ጋብቻም ሩካቤ ሕጋዊና ሥርዓት ያለው እንዲኾን ዕድል ይሰጣል፤ በዚህ መንገድ የሩካቤ ወንዝ መሻትን ይቆጣጠራል፡፡ ጸጥተኛ በኾነ ባሕር ውስጥ እንድንኾን ያደርገናል፡፡ ስርግርግ በሚል የዝሙት ማዕበል ውስጥ እንዳንሰጥም ይጠብቀናል፡፡ ይህን ትድግና (ረዳትነት) የማይፈለጉና በባሕሩ ላይ እስከ መጨረሻው ዋኝተው መሔድ የሚሹ አንዳንድ ሰዎች ግን አሉ፡፡ ከዚህ ከጋብቻ ደሴት ይልቅ በፆም፣ በትግሃ ሌሊት፣ መሬት ላይ በመተኛትና የትሕርምት ሕይወትን በመኖር ራሳቸውን መግዛት የሚፈልጉ አሉ፡፡ ለእነዚህ ሰዎች እንዳያገቡ እመክራቸዋለሁ እንጂ የግድ ከጋብቻ አልከለክላቸውም፡፡"

~ በእንተ ድንግልና፥ 9፥1
3.5K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ