Get Mystery Box with random crypto!

ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ ዐይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ | ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ ዐይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው ? ታዲያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘላለም ሲወድቁ እንድምን እጃችን የበለጠ አይዘረጋም ? ወገኖቼ! በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰው ስታዩ " የእኔ ሥራ አይደለም፣ የቀሳውስቱና የመነኮሳት ሥራ እንጂ። " አትበሉ። አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ " ይህ እኔን አይመለከተኝም ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ " ትላላችሁን ? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሱት አይደለምን ? ይህ ወደ ዘላለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ እንዲወድቅ አትደግፉት።

ሰማዕትነት አያምልጣችሁ
ተርጓሚ ገብረእግዚአብሔር ኪደ