Get Mystery Box with random crypto!

“ጋብቻ ልጆችን ለመውለድ የተሰጠ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ግን ወደ በባሕርያችን ዘልቆ የገባውን ፆር እ | ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

“ጋብቻ ልጆችን ለመውለድ የተሰጠ ነው፡፡ ከዚህ በላይ ግን ወደ በባሕርያችን ዘልቆ የገባውን ፆር እንገታበት ዘንድ የተሰጠ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ሲመሰክር፡- ‘ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት' ብሏል (1ኛ ቆሮ.7፡2)፡፡ ‘ልጅ ስለ መውለድ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው' አላለም፡፡ እንድናገባ የጠየቀንም የብዙ ልጆች አባት እንድንኾን አይደለም፡፡ ታዲያ? ‘ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ' (1ኛ ቆሮ.7፡5)፡፡ ጥቂት ወረድ ብሎም ‘ብዙ ልጆችን መውለድ ቢፈልጉ' ሳይኾን ‘ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ' አለ (1ኛ ቆሮ.7፡9)፡፡ ቀደም ብዬ እንዳልሁት፥ መጀመሪያ ላይ ጋብቻ እነዚህ ኹለት ዓላማዎች ነበሩት፡፡ ምድርና ባሕር ዓለምም ኹሉ በሰው ከተሞላች በኋላ ግን የሚቀረው አንድ ዓላማ ብቻ ነው - ሴሰኝነትንና ፈቃደ ሥጋን መግታት!”

ትንሿ ቤተ ክርስቲያን፥ ገ. 131