Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yohansafework — ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yohansafework — ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የሰርጥ አድራሻ: @yohansafework
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.61K
የሰርጥ መግለጫ

ኦርቶዶክሳዊ ጽሑፎች ይቀርቡበታል !

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-09 00:05:07
+++ እግዚአብሔር ሲቀጣን ... +++

"[አንድ] ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡

"እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገ. 36
https://t.me/Bakosbookstore
3.1K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, edited  21:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 16:31:08 በጥንቱ ዘመን ሰማዕትነት ከዓላውያን ነገሥታት ጋር ነበር። ዓላውያን ነገሥታት ክርስቲያኖችን ያሳድዷቸዋል። ክርስቲያኖቹም ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ይሰደዳሉ። ስለ ሀብት ንብረታቸው፣ ስለ ምድራዊ ክብራቸው፣ ስለ ሚስቶቻቸው፣ ስለ ልጆቻቸው፣ ስለ ምድራዊት ኑሯቸው አይጨነቁም። ዋናው ጭንቀታቸው ነፍሳቸው ከአምላኳ፣ ከወዳጇ፣ ከሞተላት አፍቃሪዋ ርቃ እንዳትሰደድ ነበር። ታዲያ ለዚህ ብለው የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ግማሾቻቸው ዱር ለዱር፣ ግማሾቻቸው ተራራ ለተራራ፣ ግማሾቻቸው ዋሻ ለዋሻ ፣ ግማሾቻቸው ፍርክታ ለፍርክታ ተቅበዘበዙ። ብዙ የብዙም ብዙ መከራ ተቀበሉ። ነፍሳቸውን ለማትረፍ ብለው ራሳቸውን በየመቃብሩ፣ በየበረሃው ይደብቁ ነበር። በጣም የሚያስደንቀኝ ግን ይህን ያደረጉ በጣም ብዙ እናቶች መኖራቸው ነው።

ልጆቼ! የእኛ ሰማዕትነት ግን እንዲህ አይደለም። የእኛ ሰማዕትነትና ውጊያ በላያችን ላይ ካሉ ነገሥታት ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት ከምኞቶቻችን ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት ከስግብግብነት፣ ከእንቅልፍ፣ ከዋዛ ፈዛዛ፣ ከስንፍና፣ ከውሸት፣ ከሐሜት ጋር ነው። የእኛ ሰማዕትነት በጠዋት ተነሥቶ ኳስ ለመጫወት ሳይኾን ለጸሎት፣ ለስግደት ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ነው። የእኛ ሰማዕትነት ወንበራችን እስኪጎደጉድ ድረስ ፊልም ማየት ሳይኾን ቃለ እግዚአብሔር ማንበብ፣ መመልከት ነው።

ስለዚህ ልጆቼ! ከምኞታችን ጋር ተጋድሎ እንግጠም። ነፍሳችንን ከአምላኳ ጋር ከሚያጣሉ ደግሞም ለጊዜው ሳይኾን ለዘለዓለም ከሚለይዋት ፍላጎቶቻችን ጋር እንጋደል። ስለ ምድራዊ ሀብት፣ ስለ ምድራዊ ዝና፣ ስለ ጊዜአዊ ደስታ ብለን ነፍሳችንን ለዓላውያን ነገሥታት (ለምኞቶቻችን) ትንበረከክ ዘንድ አሳልፈን አንስጣት። ነፍሳችንን ከእነዚህ ነገሥታት መከራ እናድናት። እነዚህን ነገሥታት ድል አድርገን ከአምላኳ ጋር እናገናኛት። ከእንቅልፍ ጋር ተዋግተን ድልም አድርገን ጧት ለስግደት፣ ለጸሎት እናበርታት። የእኛ ዘመን ሰማዕትነት ይኼ ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ምንጭ፦ "ሰማዕትነት አያምልጣችሁ"
ትርጉም፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
2.7K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-07 09:17:07
ከዚህ በፊት እንደ ነገርኋችሁ ልጆቻቸውን በምግባር በሃይማኖት እንዲያድጉ የማያደርጉ ወላጆች የልጆቻቸው ገዳዮች ናቸው፡፡ እስኪ ንገሩኝ! ለዔሊ ልጆች መሞት ተጠያቂው ማን ነው? እርሱ ራሱ አይደለምን? እርግጥ ነው የጠላት ጦር ልጆቹን ወግቶ ገድሏቸዋል፡፡ የአባታቸው የዔሊ ደንታቢስነት ግን ጦሩ ልጆቹን አነጣጥሮ እንዲወጋቸው አድርጎታል፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር ስለ ራቃቸው በፍልስጥኤማውያን ጦር ፊት እንዲቆሙ አደረጋቸው፡፡ በዚህም አባታቸው ራሱንም ልጆቹንም ገደለ፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ይህንን ዕለት ዕለት በዓይናችን ፊት እያየነው ነው፡፡ የማይታዘዙትንና ሥርዐት የለሽ ልጆቻቸውን በአግባቡ መቅጣት የማይፈልጉ ወላጆች ስፍር ቊጥር የላቸውም! ልጆቻቸውን ጠንከር አድርገው መገሠጽን ይፈራሉ፡፡ የወላጆቹ እንደዚህ መኾንስ የሚያመጣው ውጤት ምንድን ነው? የልጆቹ ሥርዐት አልበኝነት ይጨምራል፡፡ አለመቀጣታቸው ወደ ዓመፃ ወንጀል ያመራቸዋል፡፡ ወደ ወኅኒ ይወሰዳሉ፡፡ ከዚህ እጅግ ከከፋም በሞት ይቀጣሉ፡፡ ወዮ! የራሳቸውንና የተፈቀደላቸውን የመቅጣት መብት ችላ በማለታቸው፥ ልጆቻቸውን ለከፋ ቅጣት አሳልፈው ይሰጣሉ፤ ሕዝባዊ ሕጉም ለራሱ የተፈቀደለትን ቅጣት ይቀጣቸዋል፡፡ እነርሱ (ወላጆቹ) እያዩአቸው በቀላል ቅጣት ሊያስተካክሏቸው ሲገባቸው፥ ይኸው ማንም አጠገባቸው በሌለበት አሰቃቂ ቅጣት ይፈጸምባቸዋል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ፣ ገጽ 162
7.2K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 19:49:16 ምን ብዬ ልንገራችሁ? እንዴት ብዬስ ልግለፅላችሁ? የወለደች ድንግል እመለከታለሁ፤ የተወለደ ሕፃንም አያለሁ፡፡ እንዴት እንደ ተፀነሰ [እንደተወለደም] ግን አላውቅም፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ ድካም መጣ፤ ፍጥረትም ከድካሙ ዐረፈ፡፡ ሊነገር የማይችል ጸጋ !
6.3K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-31 21:03:06
“አንተ ራስህን መሥዋዕት አድርገህ ብታቀርብ ከአንተ ጋር አንድ አካል ለኾነችው [ለሚስትህ] ነው፡፡ ክርስቶስ ግን የገዛ ነፍሱን አሳልፎ የሰጠው ጀርባዋን ላዞረችበትና እርሱን ለጠላችው [ለቤተክርስቲያን] ነው፡፡”

~ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ፥ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው፥ ገጽ 43
6.9K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-29 09:31:57
"ተስፋ አትቁረጪ፡፡ ኦሎምፒያስ ሆይ! እውነተኛውና እጅግ ክፉው ነገር አንድ ብቻ ነው፤ እውነተኛ ፈተና አንድና አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ኃጢአት ነው፡፡ እንዲህ ብዬ አሰምቼ መንገሬንም መቼም መች አላቋርጥም፡፡ ሌሎች ነገሮች ግን - ለምሳሌ ሴራዎች፣ ጥላቻዎች፣ ማጭበርበሮች፣ ሐሜቶች፣ ስድቦች፣ ወቀሳዎች፣ የራስ ያልኾነን ነገር የእኔ ነው ብሎ መያዝ፣ ስደት፣ ስል የኾነ የጠላት ጎራዴ፣ የጉድጓድ ውስጥ የኾኑ አደጋዎች፣ ከዓለም ኹሉ የሚመጣ ውጊያ፣ እንዲሁም አንቺ ልትጠሪው የምትችዪ ሌላም ኹሉ ነገር - እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም፡፡ የእነዚህ ነገሮች ክብደታቸው ምንም ይኹን ምን ሐላፊያን ናቸው፤ የሚጠፉ ናቸው፤ ሟች ሰውነታችንን ሊጎዱ ቢችሉም እንኳን መንፈሳዊው ማንንታችንን ግን ምንም ሊያደርጉ የማይችሉ ናቸው፡፡ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስም ከዚህ ዓለም ሕይወት ጋር ተያይዘው የሚገኙ ደስታዎችም ኾኑ ኀዘኖች ምናምንቴነትን ሊናገር ወድዶ እውነቱን በአንዲት አረፍተ ነገር ገልጦታል፤ እንዲህ ሲል፡-“የሚታዩ ነገሮች ጊዜያዊ ናቸውና” /2ኛ ቆሮ.4፥18/፡፡ ታዲያ እንደ ፈሳሽ ውኃ የሚያልፉ ጊዜያዊ ነገሮችን የምትፈሪው ስለ ምንድን ነው?

@ ወደ ኦሎምፒያስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
6.1K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 09:20:35 ፊልጵ.4፡1፣ 1ኛ ቆሮ.10፡33)፡፡ እነርሱ ራሳቸው ግን ሞትን እንደ ናቁት ወደ እቶኑ እሳትም ኾነ ወደ አንበሳ ጕድጓድ ሲጣሉ ምንም ምን ባለመፍራታቸው ግልፅ ኾኖአል፡፡ ኹልጊዜ ግን ድል መንሣት ይፈልጉ የነበረው በረድኤተ እግዚአብሔር ነበር፡፡ ቀጥለውም እግዚአብሔር ይህን እንዲያደርግላቸው ሲለምኑት፥ እነርሱ ራሳቸው እርሱን ለመለመን የተገቡ እንዳልኾኑ በማሰብ ይጸልዩ የነበረው “ስለ ባለሟልህ ስለ ይስሐቅና ስለ ወዳጅህ ስለ አብርሃም ስላከበርኸውም ስለ ያዕቆብ” በማለት ለአባቶቻቸው የገባውን ቃል ኪዳን በማሳሰብ ነበር (መዝ.ሠለ.ደቂ. ቊ.11)፡፡ እነርሱ ራሳቸው ለእግዚአብሔር ያቀርቡት የነበረው ግን አንድ ነገር ብቻ ነበር - “የተሰበረ መንፈስ” (ቊ.16) !

እንግዲያውስ እነዚህን ወጣቶች አብነት እናድርጋቸው፡፡ ዛሬም በፊታችን የቆመ የወርቅ ምስል፥ እንዲያውም ከዚህም የከፋ የገንዘብ ሐውልት አለና፡፡ ነገር ግን በዙሪያ ኾኖ የሚሰ’ማውን የከበሮውንና የእምቢልታውን፣ የበገናውን ወይም የገንዘብ ሐውልትን በዓል አድማቂዎችን ድምፅ አንስማ፡፡ አዎን፥ ወደ “ድኽነት እቶን” ውስጥ ብንገባም እንኳን ለዚህ ጣዖት ላለመስገድ እንቁረጥ፤ ያን ጊዜም “የእሳቱ ነበልባል እንደ ቀዘቀዘ ነፋስ” ይኾንልናል (ቊ.25)፡፡ ስለዚህ ስለ “ድኽነት እቶን” በሰማን ጊዜ አንራድ፤ አንንቀጥቀጥም፡፡ በባቢሎኑ እቶን እሳት አማካኝነት ክብርን የተጎናጸፉት እነዚያ ወደ እቶኑ የተጣሉት ሠለስቱ ደቂቅ ናቸው፡፡ ወላፈኑ ያቃጠላቸው ከእቶኑ እሳት ውጭ የነበሩትና ለወርቅ ምስሉ የሰገዱት ናቸውና፡፡ ለገንዘብ ሐውልት ለሚሰግዱ ሰዎች የእሳቱ ወላፈን የሚያገኛቸው አንዳንዶቹን በዚህ ዓለም ነው፤ ሌሎቹን በወዲያኛው ዓለም ነው፤ አንዳንዶቹን ደግሞ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ነው፡፡ ለገንዘብ ሐውልት ከሚሰግዱ ይልቅ የድኽነትን እቶን የመረጡ ግን በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይሾማሉ፤ ይሸለማሉና፡፡ በዚህ ዓለም አለአግባብ ባለጠጋ የኾኑትም በወዲያኛው ዓለም ፍጹም ፍዳ ያገኛቸዋልና፡፡
አልዓዛር ከዚህ ከ “ድኽነት እቶን” ውስጥ ገብቶ ሠለስቱ ደቂቅ ካገኙት ክብር ይልቅ ይበልጥ ክብርን አግኝቶአል፡፡ ባለጠጋው [ነዌ] ግን ለወርቅ ምስሉ እንደ ሰገዱትና በወላፈኑም እንደ ጠፉት ሰዎች፥ እሳተ ገሃነም አገኘው (ሉቃ.16፡23)፡፡ የሠለስቱ ደቂቅና በወላፈኑ እሳት የሞቱት ሰዎች ምሳሌነታቸው ለዚህ ነበርና፡፡ ስለዚህ ሠለስቱ ደቂቅ ወደ እቶኑ እሳት በተጣሉ ጊዜ የእሳቱ ነበልባል ምንም እንዳልነካቸውና ይልቁንም ጽኑዓን እንደ ኾኑ ኹሉ፥ ለገንዘብ ጣዖት ላለመስገድ ወደ “ድኽነት እቶን” ውስጥ የሚጣሉትም ዕጣ ፈንታቸው ጽዋ ተርታቸው በወዲያኛው ዓለም በመንግሥተ ሰማያት ጽኑዓን ኾነው መኖር ነው፡፡ በፈለገ እሳት (በእሳት ጅረት) የሚኼዱ ቅዱሳን ሕማም እንደማያገኛቸውና ይልቁንም ደስ እንደሚሰኙ ኹሉ፥ ለዚህ ምስል የሰገዱ ግን የእሳቱ ወላፈን ከየትኛውም አርዌ ምድር በላይ በላያቸው ላይ ሲከመር፥ ወደ ራሱም ጎትቶ ሲያቃጥላቸው ያዩታል፡፡ ስለዚህ እሳተ ገሃነም መኖሩን የሚጠራጠር ሰው እርሱ አሁን የሚደረጉትን ተመልክቶ ሊመጣ ያለውን ከማመን አይዘግይ፡፡ ከ “ድኽነት እሳት” በላይም የኃጢአትን እሳት ይፍራ፤ ይንቀጥቀጥም፡፡ በእውነት ያለ ሐሰት እሳትም ሥቃይም የኃጢአት እሳት ነውና፤ የድኽነት እሳት ግን ጠልና ዕረፍት ነውና፡፡ ከኃጢአት እቶን ጋር ያለው ዲያብሎስ ነውና፤ በድኽነት እሳት ውስጥ ግን ያሉት ነበልባሉን የሚያጠፉ ቅዱሳን መላእክት ናቸውና፡፡

@የማቴዎስ ወንጌል፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ድር.4፥18-19
4.6K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 09:20:35 +++ ዛሬም በፊታችን የቆመ የወርቅ ምስል አለ +++

እውነተኛ ክብርን ማግኘት ትፈልጋለህን? ክብርን ናቅ፤ ያን ጊዜም ትከብራለህ፡፡ ለምን እንደ ናቡከደነፆር ታስባለህ? እርሱ ክብርን መጨመር በፈለገ ጊዜ ከዕንጨትና ከድንጋይ የራሱን ምስል ሐውልት አቁሞአልና፤ ሕይወት በሌለው በዚህ ግዑዝ ነገር ሕይወት ላለው ለእርሱ ክብር የሚጨምርለት መስሎት ነበርና፡፡ [ነገር ግን ክብር ሳይኾን ውርደት አገኘው፡፡] እንግዲህ የስንፍናውን መጠን አለፍነት ታያለህን? እከብርበታለሁ ብሎ ባቆመው ነገር እንዴት የገዛ ራሱን እንደ ዘለፈበት ትመለከታለህን? በራሱና በገዛ ነፍሱ ንጽህና ሳይኾን ሕይወት በሌለው ነገር ላይ መደገፉ፣ በዚያ ረዳትነትም ክብርን ማግኘት ፈልጎ ሐውልቱን ማቆሙ፥ ከዚህ በላይ ምን ሞኝነት አለ? ራሱን ለማክበር ብሎ የገዛ ሕይወቱን እንደ ማስተካከል፥ በዕንጨት ላይ ዕንጨት እንደ መጨመር ያለ ምን ሞኝነት አለ? ይህ ማለት “አንድ ሰው ፈሊጥ ያውቃል የሚባለው ሰው በመኾኑ ሳይኾን የቤቱ ምንጣፍ ያማረ ስለ ኾነ፣ የቤቱ ደረጃም የተወደደ ስለ ኾነ ነው” እንደ ማለት ይቈጠራል፡፡ በእኛ ዘንድ በእኛ ዘመን ናቡከደነፆርን የሚመስሉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እርሱ ሐውልት እንዳቆመ አንዳንዶችም ስለ ለበሱት ልብስ፣ ስለ ገነቡት ቤት፣ ስላላቸው ፈረስ፣ ገንዘብ ስላደረጉት ሠረገላ፣ ወይም ስለ ቤታቸው አሠራር ክብር የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡ ከሰውነት አፍአ ወጥተው ይህን በመሰለ መጠን አለፍ ዕብደት ይያዛሉ፡፡ የራሳቸውን ሕይወት እንደ ማስተካከል ቁሳዊ ነገርን በመሰብሰብ ክብርን ይፈልጋሉ፡፡

ቅዱሳንና የእግዚአብሔር አገልጋዮች የኾኑት [ሠለስቱ ደቂቅ] ግን ክብርን ያገኙት እነርሱ ራሳቸው ኖረው ባሳዩት ሕይወት ነው እንጂ [ናቡከደነፆር ክብር አገኝባቸዋለሁ ባላቸው] በእነዚህ ነገሮች አይደለም፡፡ ለራሳቸው ብቻ ሳይኾን ለሌሎችም ብርሃን ኾነው እውነተኛ ክብርን ያገኙት በዚህ መንገድ ነበር፡፡ ምርኮኞች፣ ባሪያዎች፣ ወጣቶች፣ ከሀገራቸው ርቀው የሚኖሩ ለሀገሩ ባዕዳንና ሀብታቸውን ኹሉ የተቀሙ የነበሩ ቢኾኑም ከማረካቸው፣ ከጌታቸው፣ በሀገሩም ይኖር ከነበረው ከናቡከደነፆር ይልቅ ንዑዳን ክቡራን የኾኑት እነርሱ ነበሩና፡፡ ናቡከደነፆር ከሐውልቱም፣ ከንግሥናውም፣ ከአለቆች ብዛትም፣ ከሠራዊቱ ብዛትም፣ ከወርቁ ብዛትም፣ ወይም ከሌላው ነገር ጓጉቶለት የነበረውን ክብር ማግኘትም ኾነ ከእነዚህ የተነሣ ታላቅ መኾን አልተቻለውም፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ እነዚህ ኹሉ ያልነበሩአቸው ሦስቱ ወጣቶች ራሳቸውን በመግዛታቸው ብቻ ይህን ኹሉ ክብር አገኙ፡፡ በራሱ ላይ የደፋው ዘውድ፣ የተጎናጸፈውም ሐምራዊ መጎናጸፍያ፥ ይህን የመሰለ ምንም ከሌላቸው ይልቅ እርሱ ራሱ እጅግ ሕሱር እንደ ኾነ ለናቡከደነፆር አሳዩት፡፡ ፀሐይ ከዕንቊ ይልቅ ደምቃ አሸብርቃ እንደምትታይ፥ እነርሱም ንጉሡ ካገኘው ክብር ይልቅ እነርሱ ያገኙት ክብር እጅግ እንዲሻል አስረዱት፡፡

“እንዴት አሳዩት?” ብለህ የጠየቅኸኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- አስቀድሜ እንደ ተናገርሁት እነዚህ ወጣቶች፣ ምርኮኞችና ባሪያዎች ዓለም ኹሉ ተሰብስቦ የንጉሡን በዓል ወደሚያደርግበት ሥፍራ ተከስሰው ተወሰዱ፡፡ ያን ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተቈጣ፤ የፊቱም መልክ ተለወጠ፡፡ መኳንንትና ሹማምንት፣ የዲያብሎስ ትርኢትም ኹሉ በዙሪያቸው ቆሙ፡፡ መለከትና እምቢልታ በኹሉም አቅጣጫ ተነፋ፤ የዘፈኑ ድምፅም እስከ ሰማያት ድረስ ተሰማ፡፡ የእቶኑ እሳት ያለ ልክ ወደ ላይ ተንበለበለ፤ እስከ ደመናትም ደረሰ፡፡ ያን ጊዜ ኹሉም ፈራ፤ ተንቀጠቀጠም፡፡ ሦስቱ ወጣቶች ግን ምንም ምን ፍርሐት አይታይባቸውም ነበር፤ እነዚያ እነርሱን እንደ ናቁአቸው እነዚህም እሳቱን ንቀዉታልና፡፡ እሳቱን መናቅ ብቻም አይደለም፤ ጥብዓትንም አሳዩ እንጂ፡፡ ቅድም ሲነፉአቸው ከነበሩት መለከቶችና እንቢልቶች በላይ ጽሩይ ኾኖ የሚሰማ ድምፅም አሰሙ፡፡ “ንጉሥ ሆይ! ይህን ዕወቅ” አሉ (ዳን.3፡18)፡፡ እንዲህ ማለታቸው ንጉሡን መስደብ ሽተው አልነበረም፡፡ ሌላ ቃልም ሊናገሩት ፈልገው አልነበረም፤ ሃይማኖታቸውን ብቻ ሊያሳውቁት ነው እንጂ፡፡ ስለዚህም ምክንያት ንግግራቸውን አላስረዘሙም፤ በአጭር አነጋገር፡- “የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል” አሉት እንጂ (ዳን.3፡17)፡፡ “ይህን ኹሉ ሰው ሰብስበህ የምታሳየን ለምንድን ነው? የእቶኑን እሳት የምታቀጣጥለውስ ለምንድን ነው? እኮ፥ ሰይፍህን የምትስለው ለምንድን ነው? ከሠራዊትህ ውስጥ ኃያላኑን መርጠህ የምታዘውስ ለምንድን ነው? ይህን ዕወቅ፡- አምላካችን እግዚአብሔር ከእነዚህ ኹሉ በላይና ኃይለኛ ነው፡፡”

እግዚአብሔር በእሳቱ እቶን ተቃጥለው እንዲሞቱ ሊፈቅድ እንደሚችል ባሰቡ ጊዜም፥ የተናገሩት ነገር ሐሰት እንደ ኾነ አስቦ ንጉሡ እንዳይሳለቅባቸው ጨምረው፡- “ንጉሥ ሆይ ! እርሱ ባያድነን እንኳን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ምስል እንዳንሰግድለት ዕወቅ” አሉት (ዳን.3፡18)፡፡ “ባያድነን እንኳን ከእኛ ኃጢአት የተነሣ ነው” ብለዉት ቢኾን ኖሮ ንጉሡ ባላመናቸው ነበር፡፡ በእሳቱ እቶን ውስጥ ኾነው ግን “ባመጣህብን መከራ ኹሉ አንተ ጻድቅ ነህ፤ በእውነተኛ ፍርድህ ስለ ኃጢአታችን ይህን ኹሉ መከራ አምጥተህብናልና” እያሉ ስለ ኃጢአታቸው ወደ እግዚአብሔር ደጋግመው ይጸልዩ ነበር (መዝ.ሠለ.ደቂ. ቊ.4)፡፡ በንጉሡ ፊት ግን ስለ ኃጢአታቸው ከመናገር ዝም አሉ፡፡ ዝም ማለታቸው ብቻም ሳይኾን ቢሞቱም እንኳን ሃይማኖታቸውንም እንደማይለውጡ ቁርጥ ውሳኔያቸውን ነገሩት፡፡
ያደረጉትን ኹሉ ሲያደርጉም “ከእሳቱ እቶን ያድነናል፤ ከፍልሰታችን ወደ ሀገራችን ይመልሰናል፤ ከባርነታችን አርነት ያወጣናል፤ የቀደመ ባለጠግነታችንም ይሰጠናል” ብለው ሳይኾን እንዲሁ ለአምላካቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ብቻ ነበርና፡፡ አዎን ! ሀገራቸውን፣ ነጻነታቸውንና ሀብታቸውን አጥተዋል፡፡ በቤተ መንግሥት ስለ ነበራቸው ክብር አትንገረኝ፡፡ ቅዱሳንና ጻድቃን ስለ ነበሩ በባዕድ ሀገር እልፍ ጊዜ ይህ ኹሉ ከሚኖራቸው ይልቅ በሀገራቸው ኾነው ነዳያን መኾንንና የቤተ መቅደሱን በረከት መቀበልን ይመርጣሉና ምንም አልነበራቸውም፡፡ “ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ” ይላልና (መዝ. 83፡10)፡፡ ስለዚህ በባቢሎን ነገሥታት ከሚኾኑ ይልቅ በሀገራቸው የተጣሉ የተናቁ ሰዎች ይኾኑ ዘንድ እልፍ ጊዜ እንደሚመርጡ በዚህ የታወቀ የተረዳ ነው፡፡ “ስለ ኃጢአታችን በሀገሩ ኹሉ ዛሬ የጐሰቆልን ኾን” በማለታቸውም ይታወቃል (መዝ.ሠለ.ደቂ. ቊ.13)፡፡ እነርሱ ራሳቸው ታላቅ የኾነ ክብርን አግኝተው የነበሩ ቢኾኑም እንኳን፥ የሌላውን ሰው መከራ እያዩ ግን እጅግ ያዝኑ ነበርና፡፡ የቅዱሳን ሰዎች ልዩ ጠባያቸው እንደዚህ ነውና፡- ከወንድማቸው ደኅንነት በላይ ለእነርሱ ክብርም ቢኾን፣ ሹመትም ቢኾን፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላም ቢኾን ኢምንት ነውና፡፡ ለምሳሌ በእሳቱ እቶን ውስጥ ኾነው እንኳን ለወገናቸው እንደ ምን ያለ ምልጃ ያቀርቡ እንደ ነበሩ ተመልከት፡፡ እኛ ግን በደኅናውም ጊዜ እንኳን ስለ ወንድማችን አናስብም፡፡ የከለዳውያን ጠንቋዮች ንጉሡ ስላለመው ሕልም ጠይቆአቸው መመለስ ባለመቻላቸው ሊገድላቸው ትእዛዝ አውጥቶ ነበር፡፡ እነዚህ ወጣቶች ግን “የባልንጀራቸውን እንጂ የራሳቸውን ጥቅም ሳይመለከቱ” የባቢሎን ጠቢባን እንዳይሞቱ በማሰብ ስለ ሕልሙ ይነግራቸው ዘንድ ከሰማይ አምላክ ምሕረት ይለምኑ ነበር (ዳን.2፡17-18፣
4.3K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-27 06:57:41 +++ አብዝተን እናጭድ ዘንድ አብዝተን እንዝራ +++

ወንድሞቼ ሆይ! ወደ ቤተ ክርስቲያን ውድ ስጦታዎችን ይዛችሁ ስትመጡ አያለሁ፡፡ መልካም አድርጋችኋል፡፡ ነገር ግን ስትመለሱ ደግሞ መበለቶችን፣ ደሀ አደጎችንና ሕጻናትን ስትበድሉ አያችኋለሁ፡፡ ታድያ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ምሥዋዕና ጽዋዕ ብታቅረቡ ምን ይጠቅማችኋል? ለምንስ መሥዋዕቱን ማክበር ስትፈልጉ አስቀድማችሁ ልባችሁን መባ አድርጋችሁ አታቀርቡም? ልባችሁ በጭቃ ተጨማልቆ ምሥዋዑ እንኳን ወርቅ ፕላቲንየምስ ቢሆን ምን ይረባችኋል? ምንስ ይጠቅማችኋል?

ተወዳጆች ሆይ! አመጣጣችን በወርቅ የተለበጠ መሠዊያ ለማቅረብ ሳይሆን ይኸን ከልብ በመነጨ ለማቅረብ ይሁን፡፡ ከልባችን የምናቀርበው ነገር ሁሉ ከወርቅ የበለጠ መባ ነው፡፡ ልብ በሉ! ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ እግዚአብሔር እኮ ሥጦታችንን የሚቀበለው ደሀ ሆኖ ሳይሆን ስለ ነፍሳችን ብሎ ነው፡፡

ክርስቶስን ማክበር ትወዳላችሁን? እንግዲያስ ዕራቆቱን ስታዩት ችላ አትበሉት፡፡ እናንተ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመጡ እጅግ ውድ በሆኑ ልብሶች አጊጣችሁ ስትመጡ እርሱ በብርድና በመራቆት ሊሞት ነውና ብያንስ ትንሽ እንኳን እዘኑለት፡፡ ቤተ መቅደስ ረግጣችሁ ቤተ መቅደስ አትምጡ፡፡ በቃሉ “ይህ ሥጋዬ ነው” ያለው ጌታ በተመሳሳይ ቃሉ “ተርቤ ስታዩኝ አላበላችሁኝም፤… ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም” ይለናል /ማቴ.25፡42፣45/፡፡ በእውነት ይህ ምሥዋዕ ልብሳችሁን ሳይሆን ልባችሁን ነው የሚፈልገው፤ እነዚህ የተራቡት ግን ልብስም ምግብም ያስፈልጋቸዋል፡፡
ስለዚህ በሕይወታችን ክርስቶስ እርሱ እንደሚወደው ማክበርን እንማር፡፡ እከብር አይል ክቡር የሆነው እርሱ ደስ የሚያሰኘው ክብር እኛ ውድ ነው ብለን የምናቀርበው ሳይሆን እርሱ ሊቀበለው የወደደውን ስናቀርብለት ነው፡፡ ጴጥሮስ ጌታን ያከበረ መስሎት እግሩን መታጠብ እምቢ አለ፤ ይህ ግን በጌታ ዐይን ማክበር ሳይሆን ተቃራኒው ነበር፡፡
ስለዚህ ጌታን ማክበር ስትፈልጉ ገንዘባችሁን አስቀድማችሁ በድሆች ላይ አውሉት፡፡ ምክንያቱም እርሱ የሚፈልገው ወርቃማ ምሥዋዕን ሳይሆን ወርቃማ ነፍሳትን ነው፡፡ ይህን ሁሉ የምላችሁ ግን መባ እንዳትሰጡ እየከለከልኳችሁ አይደለም፤ ይልቁንም ከዚሁ ጐን ለጐን እንደውም አስቀድማችሁ መመጽወትን እንድትለማመዱ ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር ለምሥዋዑ ያመጣችሁትን መባ ይቀበላል፤ ለድሆች የምትሰጡትን ደግሞ ከዚሁ በበለጠ ይቀበላችኋል፡፡ ለምሥዋዕ የሚሆን ወርቅ ብታመጡ ተጠቃሚዎች እናንተ ብቻ ናችሁ፤ ለድሆች ስትሰጡ ግን ድሀውም እናንተም ትጠቀማላችሁ፡፡ ለምሥዋዕ የሚሆን ወርቅ ስትሰጡ ውዳሴ ከንቱ ሊያመጣባችሁ ይችላል፤ ለድሆች ስትሰጡ ግን ርኅራኄንና ሰው ወዳድነትን ያመጣላችኋል፡፡

ጌታ ተርቦ ሳለ ምሥዋዑ በወርቅ ቢንቆጠቆጥ ምን ጥቅም አለው? ከሁሉም በፊት ጌታ ተርቦ ስታገኙት አብሉትና ከዚያም ምሥዋዑን አስጊጡት፡፡ ነገር ግን እርሱ አንድ ኩባያ ውኃ እንኳን ሳያገኝ እናንተ ጽዋውን የወርቅ ጽዋ ታደርጉታላችሁን? እርሱ ገላውን የሚሸፍንባት ቁራጭ ጨርቅ እንኳን አጥቶ እናንተ ምሥዋዑን በወርቅ ልብስ ታስጌጡታላችሁን? ከዚሁ የምታገኙት መልካም ነገርስ ምንድነው? እስኪ ንገሩኝ! እርሱ የሚበላውን ዳቦ አጥቶ እናንተም ረሀቡን ሳታስታግሱለት ወደ ቤተ መቅደሱ መጥታችሁ ምሥዋዑን በብር ስታስጌጡት የሚያመሰግናችሁ ይመስላችኋልን? ንገሩኝ እንጂ? የማይቆጣችሁስ ይመስላችኋልን? እንደገና አንድ ሰው ቁራጭ ጨርቅ ለብሶ ብርድ ሲያቆራምደው እየተመለከታችሁ ምንም ልብስ ሳትሰጡት በቤተመቅደስ መጥታችሁ “ይህ ሥጦታ ለጌታዬ ክብር ነው” ብላችሁ ምሥዋዑን በወርቅ ብታስጌጡት ጌታ፡- “ፌዘኞች!” ብሎ እንደሰደባችሁት የማይቈጥረው ይመስላችኋልን?

እርሱ መጠለያ ፈልጐ እንግዳና መንገደኛ ሆኖ ሲዞር እናንተ ግን ባለ ብዙ ክፍል ቤት እያላችሁ ችላ ብላችሁታል፡፡ ቤታችሁ በተለያዩ የመብራት ዓይነት አጊጦ ሳለ ክርስቶስ ግን በእስር ቤት ነው፤ ልታዩት እንኳን አልወደዳችሁም፡፡ ወንድማችሁ በጣም ተቸግሮ እያያችሁት እናንተ ግን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ለማስጌጥ ትሮጣላችሁ፤ ነገር ግን አማናዊው ቤተ መቅደስ ከሕንጻው የበለጠ ወንድማችሁ ነበር፡፡

ወንድሞቼ! ልንገራችሁና እናንተም አድምጡኝ! ለሕንጻው ቤተ መቅደስ የምታመጧቸው ጌጣጌጦች አንድ ኢአማኒ ንጉሥ፣ ወይም ጨካኝ መሪ፣ ወይም ሌባ ሊዘርፋቸው ይችላል፡፡ ወንድማችሁ ሲራብ፣ እንግዳ ሆኖ ሲመጣ እና ሲታረዝ የምታደርጉለትን ማንኛውም ነገር ግን እንኳንስ ጨካኝ መሪ፣ እንኳንስ ጨካኝ ሌባ የጨካኞች አባት የሆነው ዲያብሎስም መውሰድ ይቅርና ሊያይባችሁም አይችልም፡፡ ገንዘባችሁ ሁሉ በአስተማማኝ ቦታ ይከማቻል፡፡

ምጽዋት የመንግሥተ ሰማያትን ደጅ ትከፍታለች፡፡ “ጸሎትህ እና ምጽዋትህ ለመታሰብያ እንዲሆን ዐረገ” እንዲል /ሐዋ.10፡4/፡፡ ምጽዋት ከመሥዋዕት ሁሉ የበለጠች መሥዋዕት ናት፡፡ “ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፣ ከሚቃጠለውም መሥዋዕት ይልቅ እግዚአብሔርን ማውቅ እወዳለሁ” እንዲል /ሆሴ.6፡6/፡፡ ምጽዋት ኃጢአትን ታነጻለች፡፡ “የሚወደድ ነገርስ ለምጽዋት ስጡ፤ ሁሉም ንጹሕ ይሆንላችኋል” እንዲል /ሉቃ.11፡41/፡፡ እንግዲያስ አብዝተን እናጭድ ዘንድ አብዝተን እንዝራ፡፡ ...
3.8K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 11:51:20
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ

ከባኮስ መደብር!

አድራሻችን አምስት ኪሎ ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አጠገብ፥ ከማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ ፊት ለፊት

ስ.ቁ. 0912074575/ 0911571530
4.1K viewsገብረእግዚአብሔር ኪደ, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ