Get Mystery Box with random crypto!

'ጋብቻ በአግባቡ ሊኖሩበት ለሚፈቅዱ ሰዎች የንጽሕና ደሴት ነው፤ የአንድ ሰው ተፈጥሮ አውሬያዊ እን | ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

"ጋብቻ በአግባቡ ሊኖሩበት ለሚፈቅዱ ሰዎች የንጽሕና ደሴት ነው፤ የአንድ ሰው ተፈጥሮ አውሬያዊ እንዳይኾንም ይጠብቀዋል፡፡ አንድ ግድብ የሚፈስሰውን ውኃ ገድቦ እንደሚይዘው ኹሉ፥ ጋብቻም ሩካቤ ሕጋዊና ሥርዓት ያለው እንዲኾን ዕድል ይሰጣል፤ በዚህ መንገድ የሩካቤ ወንዝ መሻትን ይቆጣጠራል፡፡ ጸጥተኛ በኾነ ባሕር ውስጥ እንድንኾን ያደርገናል፡፡ ስርግርግ በሚል የዝሙት ማዕበል ውስጥ እንዳንሰጥም ይጠብቀናል፡፡ ይህን ትድግና (ረዳትነት) የማይፈለጉና በባሕሩ ላይ እስከ መጨረሻው ዋኝተው መሔድ የሚሹ አንዳንድ ሰዎች ግን አሉ፡፡ ከዚህ ከጋብቻ ደሴት ይልቅ በፆም፣ በትግሃ ሌሊት፣ መሬት ላይ በመተኛትና የትሕርምት ሕይወትን በመኖር ራሳቸውን መግዛት የሚፈልጉ አሉ፡፡ ለእነዚህ ሰዎች እንዳያገቡ እመክራቸዋለሁ እንጂ የግድ ከጋብቻ አልከለክላቸውም፡፡"

~ በእንተ ድንግልና፥ 9፥1