2022-07-29 18:26:48
ይህ ሀውልት ህያው የሆነ መንፈስን ተሸክሟል። በአቡነ ጴጥሮስ ውስጥ
ጀግንነትን ልበ ሙሉነትን እምነትን እናስተውላለን። ደግሞም አንዳንድ ጊዜ
ይህቺ ሀገር በደም የቆመች መሆናን እናስተውላለን። አንዳንዱ ለትውልድ ብርሃን
አብርቶ ያልፋል ልክ እንደ አቡኑ አንዳንዱ ደግሞ ልክ አቡኑን እንደገደሉት
ባንዶች ብርሃኗን ያጠፋሉ። በቃ ይች ናት ኢትዮጵያ ። ብዙ ጀግኖች ደማቸውን
ያፈሰሱባት ብዙ ባንዳዎች ሀገርን የሸጡባት ምድር ኢትዮጵያ ።
አቡነ ጴጥሮስ ለዘሩ አልነበረም የሞተው። ለአንድ ሀይማኖቱ ለአንድ ሀገሩ
ነበር።
ምናለ አሁን ላይ የሀይማኖት አባቶቻችን የአቡኑን መንፈስ በተቀበሉ!?
ምናለ ትቂት እንኳ እምነትን ለህዝብ መሞትን በተማሩ!?
ምናለ ለእምነት መሞትን ከሱ በወረሱት!?
ሁሌም ከታሪክ የማንማር መሆኑስ አያስተዛዝብምን!?
እያልሁ ሁሌም ጀንበር ወደ ማደሪያዋ ስታሽቆለቁል ከሀውልቱ ስር አንገቴን ደፍቼ
እራሴን እጠይቃለሁ። እንባ በአይኖቼ እንደወረዱ የምሽቷን ጀንበር አንጋጥጬ
እመለከታለሁ።
እውነት የትኛው ነው!? ይህ ህያው ሀውልት ወይንስ ለስጋቸው የሞቱ እነዚያ
የሰሜን ባንዶች!?
እንጃ!!
ታላቁ ገጣሚ በውቀቱ ስዩም እንዳለው :- እውነትና ንጋት እያደረ እንግዳ ይሆን?
ይሄን መልስ አልባ ጥያቄየን እጠይቃለሁ።
ተስፋ እንዲሁም ህልም በውስጤ እያረገዝኩ። እንዲሁም ተስፋ ቢስ እሆናለሁ
ይሄን ድንቅ ሰው በሞት የነጠቀንን አረመኔ እያሰብሁ።
............................ . . . . . ... ... . . .
.
.
.
..
..
..
..
..
..
...
ምላሽ አልባ ጥያቄ?¿
ይነበብ መዝገቡ ነኝ! (Yinuka)
182 viewsYinebeb, 15:26