2022-06-25 16:03:12
...... አንድ ሰው የስሜቱ ባሪያ ሊሆን አይገባም!! ስሜት ባለማወቅ የሚፈጠር ነገር ነውና። ሌላው ደግሞ ተፈጥሮ ሊቀየርና ሊሻር የማይቻል ነገር ነች። አየህ ታላቁ መፅሐፍ ቅዱሳችን ላይ እንኳ አዳም የፍጥረታት ገዥ ነው ይላል!? ይሄ ከምን የመነጨ ይመስልሃል? ከማወቅ ከማሰብ ከሰው ልጅ መመራመር የመጣ ነው። ገና ከገነት ከተባረረ ጀምሮ እፀ በለስን (የእውቀት ዛፍን ) ከቀጠፈ ቀን ጀምሮ የሰው ልጅ ሀዘንንና ደስታን በቅጡ ማወቅ ጀመረ። የሰው ልጅ ከእንስሳ ይለያል የምንለው ለዚህ ነው።
እሽ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ!
ከሰው ልጅ እንስሳም ያለቅሱ ይስቁ ከሆነ ! ማሰብ ማሰላሰል ይችላሉ አለማቸውን ስላላየን ነው ካልክም ። ፍልስፍናቸው የታለ። የሰው ልጅ እንደደረሰ የሚነዳቸው እንደደረሰ የሚገድላቸው ለምን ከዚህ ህይወታቸው ተላቀው የራሳቸውን ነገድ አላቋቋሙም። በአንተ ፍልስፍና ልምጣ ብዬ ነው።
በመጨረሻ አንድ ነገር ልበልህ እና ይብቃኝ
ሁሌም ፍልስፍና የሚመስለን ምዕራባዊያን የተባሉ ፈላስፎች ሲሞነጫጭሩልን የምንደልቅ ከሆነ የገሌ ምርጥ ፈላስፋ ነው። እገሌ እንዳለው ከሆነ እያለን ብቻ የምንንነጉድ ከሆነ ከበቀቀን አልተሻልንም።
አየህ ፍልስፍና ያለ ከማንም አለም ከማንም ህይወት ውስጥ ነው። ታላቁ ጠቢቡ ሰለሞን ምናለ!?
ምናልባት በመንፈሳዊ ብቻ አስረናቸው እንጂ እነገሌን የሚያስንቁ ፈላስፎች አሉን።
ፊደላትን የቀመሩ ማንነታችንን የገለጡ ምርጦች የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያን ናቸው።
ዜማን የፈጠረ ቅዱስ ያሬድ እሱ ምርጥ ፈላስፋ ነው።
የሀገራችን የአለባብስ ሁናቴ የሀገራችን የአነጋግር ስልት የሀገራችን የአመጋግብ ጥበብ። ይሄ ሁሉ እረቂቅ ፍልስፍና ነው።
ከዚያ በዘለለ ስለ እንስሳቶች የተባሉ የተከተቡ ብዙ መዛግብቶች አሉ
ይነበብ መዝገቡ ነኝ (ይኑካ)
132 viewsYinebeb, edited 13:03