Get Mystery Box with random crypto!

ከኢትኤል ብዕር ነጠብጣቦች......✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ yinuca — ከኢትኤል ብዕር ነጠብጣቦች......✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ yinuca — ከኢትኤል ብዕር ነጠብጣቦች......✍️
የሰርጥ አድራሻ: @yinuca
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 881
የሰርጥ መግለጫ

አንባቢያንን እናበረታታለን። ደራሲያንን እንገነባለን!! የተሻለች ሀገር ለመፍጠር እንተጋለን! እኛ ጋር ነዎት!?
👉የዩቲዩብ ቻናላችን ሊንክ
👇👇👇👇
https://youtube.com/@yinuka_777
አስተያይት አለዎ
👇👇👇
https://t.me/ethelmezgebu

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-06-22 17:33:57 ሙዚቃ
የሰው ልጅ ፍልስፍናን አተኩረህ ብትመለከት እጅግ እረቂቅና ውበት የተላበሰ ሁኖ ታገኘዋለህ። ያለምክንያት የተፈጠረ ባህል የለም። ሁሉም በማሰብ ደረጃ የተፈጠሩ ናቸው። ደስታቸውን በሙዚቃ ሀዘናቸውን በሀዘን ሙሾ ሲያወርዱት ትመለከታለህ። ይሄን ሁሉ በትኩረት ከተመለከትክ እንደእውነቱ አንተ ምርጥ ፈላስፋ ነህ። ፍልስፍና ግኝት ፈጠራ ነውና። ብዙ ጠቢባን ነን ባዮችን ተመለከትሁ። የፍልስፍና ጣሪያን የሚለኩት አንድ ሰው ፈላስፋ ስለተባለው ሰው ህይወት መተንተን እና ማወቅ ይመስላቸዋል። ፍልስፍና ጥያቄ ብቻ የሚመስላቸው እንከፎችንም ተመልክቻለሁ። አየህ ወዳጄ ፍልስፍና ግን የአንድ ነገር ችግር መቅረፊያ የአንድ ነገር ግኝት ውጤት ፍልስፍና ይባላል። የሰው ልጅ ጥበብን በአተኩሮት ተመልከት። እምነታቸውን ሀይማኖታቸውን። እንደእየእምነቱ ፈጣሪያቸውም ይለያያል። ለምን ይሄ ሁሉ አጥር ተፈጠረ ብለህ ማጤን ከጀመርህ ግን የሰው ልጅ የማሰብ ውጤቱ ያበጀው መስመር እንደሆነ ይገባሃል። ሀዘን እየበዛበት በሄደ ቁጥር ሙዚቃን ለመንፈሱ ሰላም ፈጠረ። ታዲያ በየነገዱ ሁሉ የሙዚቃ ስልታቸውም ይለያያ። ለምን ይሄ ሆነ ብለህ ጠይቅ። አየህ ያኔ ከእራስህ ጋር ትገናኛለህ።
የሰው ልጅ በሁለት ስሜቶች የሚነጉድ ብቸኛ ፍጡር ነው። በሀዘን እና በደስታ መሀከል የሚዋዥቅ ። ለዚያም ነው የሰው ልጅ ከእንስሳት ይለያል ይሚባለው። እንስሳቶች እነዚህ ስሜቶች የሏቸውም። ሀዘንንም ደስታንም አያቁም። የትኛውንም እንስሳ ሲስቅ አይተኸው አታቅም። የትኛውንም እንስሳ ሲያለቅስ አላየህም። ከነሱ ጋርም ማሰብም ሆነ ፍልስፍና የለም። የሰው ልጅ ግን ከሀዘኑ ለመሸሽ ዳንኪራ ይረግጣል ። ህይወትን ከመንፈሱ ጋር ለማገናኘት ሙዚቃን ፈጠረ። የተለያዩ መዝናኛ ነገሮችን እየፈጠረ ይኖራል። ሀዘን እንደመከራ ሲጫነው እራሱ በፈጠረው ፍልስፍና ውስጥ ሀዘኑን ይገልጣል። ይሄ ሁሉ የአለም ትርምስ! ይሄሁሉ የአለም ስልጣኔ ከመለኮታዊ ሀይል ጋር የተገናኘ ነው።
ወዳጄ አውቃለሁ ብለህ ደረትህን አትኮፍስ። የቱንም ያህል ብታውቅ አለም የምትጨበጥ የምትዳሰስ ድንቡልቡል ደንጋይ አትምሰልህ። አለም በብዙ ውህደት የቆመች እረቂቅ ውብ ነገር ናት። ያወቅኸውን ለማሳደግ ግን ወደፊት ተራመድ። ምክንያቱም አንተ ሰው ነህና ። የሰው የማሰብ ሀቅሙ ውስጥህ ላይ አለና። ፍልስፍናህን ፍጠር!!
አዲስ ግኚት አበርክት!
ከማውራት በዘለለ የተግባር ሰው ሁን።
ደስታህን በሙዚቃ ! መንፈስህን በማሰብ አስደስታቸው።
ደህና ሁን ወዳጄ

Yinuka_ይኑካ ሚዲያ
የተለያዩ የግጥም የፍልስፍና እንዲሁም መዝናኛ ፁሑፍና ቪዲዮ የምንለቅበት ቻናል!!!
የዩቲዩብ ቻናላችን ሊንክ


https://m.youtube.com/channel/UCGADom47rRykQk6dRg0cxAg


ለአስተያይቶ
https://t.me/Yinebebmez
https://t.me/yinuca
144 viewsYinebeb, 14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 10:38:35 ....ምናልባትም በአንተ ሚዛን ስትለካኝ ደደብ ወይንም ምጡቅ የምባል ሰው ልሆን እችላለሁ። ነገር ግን እሱ አደለም ዋና ችግሩ። እንደምታውቀኝ በሙሉ አትናገር። የሰው ልጅ ሊታወቅ የማይቻል እረቂቅ ፍጡር ነውና። በሰዎች ህይወት ገብተህ አትፈትፍት ወዳጄ ። መጀመሪያውኑ እራስህን ጠይቅ። እኔ ማነኝ ? ምንትስ ነኝ? ምናምን በል እያልሁ አላዝግህም። ነገር ግን በሰዎች ከመበሳጨትህ በፊት ከጀርባ ያለውን አጢን።
ስማኝ አንተ ፈላስፋ ነኝ ባይ። የፍልስፍና ጣሪያ እንዳንተ ላርራቀቅ እችላለሁ። ይሄን ስላላወቅሁ ግን የማልጠቅም ሰው ነኝ ማለት አደለም። አንተን በዚህ ሚዛን ስላልበለጥሁ ደደብ ነኝ ማለት ነው?
ስማኝ አንተ የቃላት ሀብታሙ ባለቅኔ ቅኔ ባልቀኝም ሚስጥራትን ባላመሳጥርም እኔ ውስጥ እኔ እስካለሁ ድረስ ባንተ ሚዛን ተለክቼ ብወድቅ ደደብ ግን አደለሁም። ሌላም ህይወት አለና። ስማኝ ሙዚቀኛው ድምፅህ ለአለም ልጆች ሁሉ ቢያስተጋባ አለም ሰፍ ብሎ የሚሰማው ለዛ ያለህ ሰው ብትሆንም ድምፄ ካንተ ስላልተስተካከለ እኔ የማልጠቅም ሰው ከመሰለህ ተሳስተሃል።
140 viewsYinebeb, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 09:04:25 ብቻዬን አይቸው በማላውቀው የአለም ትርምስ እናውዛለሁ። የደስታና ሀዘናቸውን ባህል አላውቅም ። አዎ ለእነዚያ ሰዎች እንግዳ ነበርሁ። በባይተዋርነት ብቻየን እየተንከላወስኩ ሁሉንም ነገሮች በትኩረት ማጤን ጀመርሁ። በረሃውን አቋርጨ የንዳድ ዶፉን ተቋቁሜ ከዚህኛውም አለም የመጣሁት እንግዳ ለመሆን አልነበረም። የዚያ ሀገር ሰዎች ግን በነገዳቸው ተሰባስበው የሚጨፍት ጭፈራ የሚዘፍኑት ዘፈን የሚያወርዱት ዳንኪራ ለኔ አዲስ ነው። አንዳንዴ እስቃለሁ። አንዳንዴም አለቅሳለሁ። ያላየሁትን እያሳዩኝ የማይሆነውን ይሆናል ብለው ሲያምኑ ሳይ ፈገግ እያልሁ አስተውላለሁ። ብቻየን ፈንጠር ብየ ባዩኝ ጊዜ ደግሞ እብድ ነው ብለው ተሳለቁብኝ። በእርግጥም ልክ ነበሩ። በእነሱ አለም በነሱ ጎዳና መራመድን አልሞከርኩምና።
በእርግጥም ልክ ነበሩ ሀዘናቸው ላይና እና ዳንኪራቸው ላይ አልቀላቀልም ነበርና። ለሁሉም እንግዳ ነበርሁ። ግን ለምን ብዬ አልጠይቅም እራሴን። ምክንያቱም እኔም ለእኔ እብዶች ነበሩ እና እነሱ።
መንፈሳቸውን በትኩረት ብመለከት የሀዘን ጥላሸት ከቦታል ገፃቸው።
መረጋጋት የለውም ኑሯቸው። እንደሮጡ እንደባከኑ ህይወትን በቅጡ ሳያውቁ ይሰናበቷታል። በእርግጥ እነሱ ህይወትን ከእነ ጭራሹ ይወዷታል እንጂ አያውቋትም። ስለታም ፊታቸው ብልጣብልጥ ኑሯቸው ለእንደኔ አይነቱ ሰው እቤድ ነው ስያሜው።
ሴልጣኔ አለ ብለው ያወራሉ። ነገር ግን ስልጣኔ የሚሉት ሁሉ የክፋት መርዝን ያረገዘ መርዘኛ ሀሳብ ነው ። ለነሱ ስልጣኔ ያመናቸውን መክዳት የሚወዳቸውን መጉዳት አንዱን ለመብለጥ አንዱን መርገጥ : ሁሌም እሽቅድድሞሽ መስመርን መዘርጋት ነው።
ከመንጋው ተነጥዬ ባህላቸውን እምነታቸውን አስተዋልሁ። ሁሉም አስመሳዮች ሁሉም ሸንጋዮች ነበሩ። አምላክ አለን ብለው እንኳ የሚያወሩት አምላክ እንደነሱ ሸንጋይ አስመሳይ ተንኮለኛ አድርገው ቀርፀውታል። ይሄንንም አስተዋልሁ። እንግዳነቴን እየታዘብሁ ከእነሱ ጋር ተዛምጄ እኖራለሁ። ግን አንድ ነገር ስናገር መንፈሴን ለትቂት ቀናት ሽጨላቸው ወደውኝ ነበር። ሳፈነግጥ እራሴን ስሆን ግን እብድ ብለውኛል።እውነት ነው እብድ ነኝ። የነሱ የጤንነት ልኬት ግንህዝቡ ባመነበት መንገድ መንጎድ ብቻ ነው።

እንደ እውነቱ ለእነዚህ ሰዎች እንግዳ ነኝ!!!

ይነበብ መዝገቡ ነኝ!

https://t.me/yinuca
147 viewsYinebeb, 06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ