Get Mystery Box with random crypto!

የፍልስፍና አለም

የቴሌግራም ቻናል አርማ philosophyworld1 — የፍልስፍና አለም
የቴሌግራም ቻናል አርማ philosophyworld1 — የፍልስፍና አለም
የሰርጥ አድራሻ: @philosophyworld1
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.29K
የሰርጥ መግለጫ

“የማያነብ ሰው እና ማንበብ የማይችል ሰው ልዩነት የላቸውም” ይህ ቻናል ማንኛውም ፍልስፍና ተኮር የሆኑ ጽሑፎች የሚቀርቡበት ነው ። ፍልስፍናን እንደነብሴ እወዳለሁ ያለ ሁሉ ይቀላቀለንና አብሮን ፍልስፍናን ይኮምኩም... @Philosophyworld1

ግሩፓችንን መቀላቀል ለምትፈልጉ @Philosophyworldd
ለአስታየት እና ለCross @fear121

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 20:50:32
የማንለብሰውን ጃኬት ሁላችንም ዉጭ ለሚተኙ ጎዳና ተዳዳሪዎች ለመስጠት እንዝመት

ከብርድ ቀድመን እንድረስላቸዉ!!


@philosophyworld1
@philosophyworld1
▬▬▬▬▬▬▬▬
261 viewsAb, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 16:46:51 ዋ ዘንድሮ እኔንጃ

ባይገርምሽ
የማያቁት ሀገር ~ የሄድኩኝ መሰለኝ
ኢትዮጵያ ናት ብሎ ~ ለማመን ቸገረኝ
የወንዞች ሁሉ ራስ ~ አባይ በደም ራሰ
ክቡሩ የሰው ልጅ ~ ከእንስሳ እንኳ አነሰ

ሌቦ ፈረስ ጋልቦ ~ ቼ በለው እያለ
አርማሽ አስጠልቶት ~ በሌላ እየማለ
ሰንበር ነው ሚታየው ~ በእውነተኞች ገላ
ማ ዘንድ ይደር ሳያቅ ~ ህዝባዳም ተቀላ

የደም መሬት ሆነ ~ የወይኑ ስፍራ
ካሳለፍነው ይልቅ ~ ይሄኛው ግፍ ሰራ
ኬር ይሁን ብሎ ጮኀ ~ አራዳ ለአራዳ
ለጥያቄው ምላሽ ~ ልምጭ ተሰናዳ

አቦጊዳ ብሎ ~ ፊደል ያልቆጠረ
ከመምህር በላይ ~ ቆዳውን ወጠረ
ለማን ልማሽ አንቺን ~ የትውልድ መንደሬ
እጠኚ እንጂ አጥፊን ~ ዘቅዝቀሽ በርበሬ

ያስነጥሰውና ~ ይውጣለት በሽታው
ወይ ተነስቶ ይሂድ ~ እንጃለት ወዳሻው
ይህን ካላደረገሽ ~ ትዝብት ነው ትርፉ
መልስ ስጪው ገርፈሽ ~ ክፉዉን በክፉ

የአቤልና ቃየል ~ ስም ተቀያየረ
ካባ ሲጣልለት ~ ሀቅ ክዶ አደረ
ስለ ፍቅር አውሪ ~ ተናቀ ተጠላ
ፍርድ ተገምድሎ ~ ለጊዜ አደላ

አላን ይዞ ተጓዥ ~ ስሙ ነው ሞኛሞኝ
አተናል ጓደኛ ~ ሁሉ ሻጭ ነው ስሞን
ባልተገራ ፈረስ ~ ጭኖን ባልደራሱ
ወርዶ ገሰገሰ ~ ጥሎን ለንፋሱ

ሰለሜ ሰለሜ ~ ጭፈራው አንድ ቤት
የሌሎቹን ታዛ ~ ወርሶት ክፉ ንዴት
"አናኛቱ" እንበል፤
በአምፖል እሳቤ ~ ይዞ ላንባዲና
እሱ ይምራን ለሚል ~ ናፍቆ ብልፅግና

አባታችን ስማ ~ ልጥራህ ተንበርክኬ
ቀብተህ ላክልን ~ ስሙ "ሰው በልኬ"
አበባ አየህ ወይ ስንል ~ ምላሽ በሚሰጠን
በተስፋ ምልክት ~ በአደይ አሽቆጥቁጠን።


For any comments:- @fear121
@kalina1924
JOIN US
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1


Join our group:- @philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ

KIDUS TADESSE (ኪዳ የገጠር ልጅ_ቅዱስ
1.3K viewsAb, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:11:59 እውነተኛ ታሪክ ≅

!! በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ መምህሯ ክፍል ገብታ
ስታስተምር ከተማሪወቹ አንዱ ይነሳና" መምህር እቃ
ተሰርቂያለሁ" ይላል። መምህሯ የተሰረቀው እቃ ምን እንደሆነ
ካጣራች በሀላ ተማሪወች ለፍተሻ እንዲዘጋጁ አደረገችና
ፍተሻዋን ቀጠለች።

!! በፍተሻው ሰአት ታዲያ አንዲት እድሜዋ 10 አመት
የማይሞላ ተማሪ ተራዋ ደርሶ ቦርሰዋን እንድትከፍት ስትጠየቅ
አሻፈረኝ ትላለች። መምህሯም በአንዲት ጦፋ አንች ሌባ አንች
ነሽ የሰረቅሽው ፖሊስ ነው ምጠራልሽ እያለች ስትጮህ የሰሙት
ዳይሬክተሯ ከተፍ ይላሉ።

!! ይህን ጊዜ ልጅቷ የባሰ ድንጋጤና ፍርሀት እያተንቀጠቀጣች
እባክሽን የቅር በይኝ እኔ ሌባ አይደለሁም ከፈለግሽ እንኪ
ፈትሽኝ ግን እዚህ ከተማሪወች ፊት አይደለም እያለች መምህሯ
እግር ስር ወድቃ ልመናዋን ቀጠለች። መምህሯ ገን እየደነፋች
ነው።

!! በዚህ ጊዜ በእድሜ ጠና ያሉት ሴት ዳይሬክተር ቆይ እስኪ
መምህር ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ ብለው ዳይሪክተሯ ወደ ቢሮ
ወሰዷቸው። ከዛም ልጅቷን በተረጋጋ ሁኔታ እድትቀመጥ
ቢያደርጉም መምህሯ ግን እስካሁን መረጋጋት አልቻለችም።
ዳይሬክተሯ መምህሯን አገላመጡና ዝም እድትል ካደረጉ በሀላ
ልጅቷን እረጋ ብለው "ቦርሳው ውስጥ ምንድን ነው ያለው"
ብለው ጠየቋት።

!! ልጅቷም "ቦርሳው ውስጥ ያለው ተማሪወች በልተው
የጣሉት ትርፍራፊ ነው" አለች በህፍረት እየተሸማቀቀች።
ሴትየዋም በመገረምና ባለማመን ስሜት "እንዴት እዲህ ይሆናል"
ሲሉ ጠየቋት።

!! እሷም "ለወንድሞቸ ልወሰድላቸው ብየ ነው"አለች አንገቷን
ደፍታ በሚያሳዝን ሁኔታ ቅስሟ ተሰብሮ። ይህን ጊዜ ዳይሬክተሯ
ከመቀመጫቸው ተነስተው ተጠጓትና ፀጉሯን እየዳበሱ "አይዞሽ
የኔ ልጅ ተረጋግተሽ ስለ አባትሽና ስለ እናትሽ ንገሪኝ አሏት።

!! ይች አንዲት ፍሬ ልጅ እንበዋ እየወረደ እንዲህ አለች"
አባቴ በሹፍርና ነበር የሚያስተዳድረን በሀላ ግን በአዳጋ
ተለይቶናል። እናቴም ብትሆን ምንም ገቢ ያልነበርት ስትሆን
የአባቴን ሞት ስትሰማ እራሷን ስታ ሆስፒታል ገባች። በዛው የተነሳ
ሽባ ሆና ቀረች። ታዲያ ሁለት ጨቅላ ወንድሞች አሉኝ ቤት ነው
ጥያቸው የመጣሁት ዘመድ ስለሌለን ዘወር ብሎ የሚያየን
የለም።

!! እሚላስ እሚቀመስ የለንም።ታዲያ ይችን ፍርፋሪ ወስጀ
ህይወታቸውን ብታደግ ብየ ነው። እባካቹ ለተማሪወች
እዳትናገሩብኝ።ትምህርቴንም ቢሆን አቋርጣለሁ። ብቻ
አትናገሩብኝ እያለች አንጀት በሚያላውስ ሁኔታ ችግሯን ስትናገር
ዳይሬክተሯ ልጅቷን አቅፈው አነባ። ስለዚህ ከመፀፀት ይልቅ
የሰወችን ሁኔታ በእርጋታ ለመረዳት መሞከር ታላቅነት ነው።

መልካም ምሽት ምርጦቼ


https://t.me/philosophyworld1
1.4K viewskalina, edited  20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 10:48:19 ዛሬ ደሞ እስኪ ትንሽ ፈገግ እንበል

እኔና ሚስቴ ልጆች ስላልወለድን ለልጅ ስም ሰጥቶ የሚገኘውን ደስታ ማጣጣም አልቻልኩም ነበር። እና ያንን ለማካካስ ለሰውነት ክፍሎቼ ስም እሰጣቸዋለው። . .. ለምሳሌ አይኔን 'ቦጋለ' ብየዋለሁ። እጄን 'ለገሰ' ብየዋለው። ደረቴን 'ወሰን የለህ ብየዋለዉ። አፌን 'አመንሲሳ' ብየዋለሁ። በኦሮምኛ አመንሲሳ ማለት አሳምነው ማለት ነው። መላ ሰውነቴን ደግሞ 'ባይፈርስ' ብዬ ሰይሜዋለው።

በመጨረሻ ሚስቴን "ቤብዬ እስቲ ለዚህ ስም አውጭለት፣ .." አልኳት ወደ ሱሪዬ መጋጠሚያ እየጠቆምኳት። "ለአጅሬ አንቺ ስም አውጭለት" አልኳት ደግሜ

የሚገርማችሁ ነገር የጠበኩት አናጋው' ትለዋለች ብዬ ነበር። … ይሄ እንኳን ቢቀር "ሃጎሴ" ምናምን ትለዋለች ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር ... እሷ ግን ምንም ሳታመነታ "ቢያድግልኝ ብየዋለው..."


ከፍልስፍና ዓለም

For any comments:-
@kalina1924
@fear121






@Philosophyworld1
@Philosophyworld1


Join our group:- @philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
580 viewsአቢግያ, edited  07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 19:45:23
660 viewsAb, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 21:11:56
ለፈገግታ ያህል

በጣም የተማሩ አባትና ልጅ ለሽርሽር ከከተማው ወጣ ብለው ለመዝናናት አሰቡና ወተው እዛው መሸባቸው።
.
አዳራቸውን እዛው ሜዳ ላይ አጫጭር ድንኳናቸውን ዘርግተው ከተኙ በኃላ.
.
ልክ እኩለ ሌሊት ሲሆን አባት ልጁን ቀስቅሶ...
.
አባት:- አሁን ምን ይታይሃል?

ልጅ:- ጨረቃ ና ብዙ ክዋክብት ይታዩኛል፣
.
አባት:- ታድያ ከዚህ ምን ተረዳህ?.
.
ልጅ ፡- ባስትሮኖሚ ቋንቋ ብዙ ፕላኔቶች በራሳቸው ምህዋር በህዋ ውስጥ እንዳሉና የክዋክብቶች ክምችት ብሎ ከጋላክሲ አፈጣጠ...
.
አባትዬው:- ልጁን በጥፊ ዝም ካሰኘው በኃላ...

አትቀባጥርብኝ!!! አንተ ዶማ!!! ድንኳን ተሰርቀናል!!


ከፍልስፍና ዓለም

For any comments:- @fear121
@kalina1924
JOIN US
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1


Join our group:- @philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
959 viewsAb, edited  18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 23:35:22 በዚህ ምድር ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ (ያለምንም Qualification) ጥሩ የሆነው ነገር ምንድ ነው ?” ሲል ይጠይቃል ኢማኑኤል ካንት የሞራል ፍልስፍናውን ሲጀምር ። ለዚህ ጥያቄ ካንት እራሱ መልሱን እንዲ ሲል ይሰጠናል ፡፡ |
#ገንዘብ! ? አይደለም ፤ ገንዘብ ጥሩ የሚሆነው ለጥሩ ነገር ስናውለው እንጂ ገንዘብ በራሱ በተፈጥሮ ባህሪው ጥሩነት የለውም ::
# ዕውቀት!? ዕውቀት አይደለም ፤ እውቀት ጥሩ የሚሆነው መልካም ሰው ሲያገኝ ነው
#ጉብዝና(Courage)!? እሱም አይደለም ፤ ጉብዝና ጥሩ የሚሆነው ለጥሩ ዓላማ ሲሆን ነው ። ለምሳሌ ሂትለር ጎበዝ (Couragous) ነው :: ሆኖም ግን ፣ የእሱ ጉብዝና መጥፎ #ጉብዝና ነው እና ታዲያ ምንድ ነው? ለካንት መልሱ አንድ ነው»በዚህ ዓለም ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በራሱ መልካም የሆነው ነገር አንድ ብቻ ነው ፤ እሱም " በጎነት ወይም ቅንነት /Good Will" ነው፡፡ (Kant 1987፡ 7) ዕውቀት ፣ በጎነትና ጉብዝና ቅንነት ላይ ካላረፉ አደገኛ ይሆናል ።


ከፍልስፍና ዓለም

For any comments:- @fear121
@kalina1924
JOIN US
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1


Join our group:- @philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
825 viewsአቢግያ, edited  20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 09:20:07 ተሸካሚ በሌለበት ሸክም የለም...!!

፨፨፨

<< አንድ ነገር የሚታየው በሌላ አካል ለመታየት ስለሚችል ሳይሆን ነገር ግን ሌላ አካል ስላየው ነገሩ ሊታይ ቻለ፤ ወይም አንድ ነገር ተመሪ የሚሆነው መሪ ስላለው እንጂ ነገሩ ተመሪ ስለሆነ አይደለም። አንድ ነገር ሸክም የሆነው ተሸካሚ ስላለው እንጂ ነገሩ በራሱ ሸክም ሆኖ አይደለም። ይኽ ማለት አንድ ውጤት በራሱ ልቆ የወጣበት አካል ውጤቱ የራሱ ሳይሆን ምክንያት ስላለው ነው። ውጤት የሆነ ነገር በራሱ ውጤት አያመጣምና። ቅድስናም እንዲሁ ቅዱስ የሚሆነው አማልክት ስለሚወዱት እንጂ በራሱ ቅዱስ ስለሆነ አይደለም። >>

/ ሶቅራጥስ /

ከፍልስፍና ዓለም

For any comments:- @fear121
@kalina1924
JOIN US
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1


Join our group:- @philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.1K viewsAb, 06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 14:51:32 Take time!!

by DEMIS SEIFU 

“Give me six hours to chop down a tree and I will spend the first four sharpening the axe.” ― Abraham Lincoln

እየሄዱ መቆም የመሄድን አቅም መጨመር ነው… መዘግየት አይደለም… እያረፉ መጓዝ የብልህነት ከፍታ ነው … ስንፍና አይደለም… ‘በየመሃሉ’ ማለት መታደስ ነው… ኋላ መቅረት አይደለም… ለረጅም ሰዓት ያሽከረከረ ሹፌር ጥጉን ይዞ ‘እረፍት’ የሚወስደው የበለጠ መጓዝ እንዲችል ነው… የጋለው ሞተር ቀዝቅዞ አቅም መግዛት አለበት… የዛለ ክንዱም በርትቶ መሪ ማዞር አለበት… በየሰከንዱ በምንስበው አየር የመታደስ ያህል ነው – ‘በየመሃሉ’ ማለት… አንዴ በሳቡት አየር ዕድሜ ልክ ልኑር አይባልምና…

ሰውየው በአንድ ድርጅት ውስጥ በእንጨት ቆራጭነት ስራ አምስት ዓመት ያህል ቢያገለግልም ሁሌም የደመወዝ እድገት እንደናፈቀው ነው… ከእርሱ በኋላ የተቀጠሩ ሰራተኞች ዓመት ሳይደፍናቸው የክፍያ መሻሻል አይተዋል… እናም ሰውየው ዘወትር ‘ለምን?’ ይላል… የድርጅቱ ኃላፊ ‘እንደምታውቀው ድርጅታችን ውጤት ተኮር ነው… ብዙ የሰራ ብዙ ያገኛል… አንተን እንደማይህ የዛሬ አምስት ዓመት ትቆርጥ የነበረውን እንጨት ነው ዛሬም የምትቆርጠው… ይሄ ደግሞ ላንተ ለውጥም ሆነ ለድርጅቱ እድገት አንዳች አይፈይድም’ ብሎታል… እናም ይለፋል… ይጥራል… ይግራል… ጠብ የሚል ነገር የለም…

በድጋሚ አለቃውን አግኝቶ ጠየቀ… ‘እስኪ ካንተ በኋላ የተቀጠሩትን ቆራጮች ተመልከታቸው… በየጊዜው መሻሻል እያሳዩ ነው… ለምን እነርሱን አታማክራቸውም… ለምሳሌ እከሌን ማናገር ትችላለህ… ምናልባት እኔና አንተ የማናውቀውን ምስጢር ይጠቁምህ ይሆናል’… ሲል መለሰለት…

ሰውየው የተጠቆመው ሰው ዘንድ ሄዶ ችግሩን አስረዳው… ባለሙያውም ሁኔታውን በደንብ ካጤነ በኋላ ‘ለመሆኑ መጥረቢያህን ከሳልከው ስንት ጊዜ ሆነህ?’ ሲል ጠየቀው… እንጨት ቆራጩ እንደ ማሰላሰል አለ… በጣም ቆይቶ ነበር… በጣም… ባለሙያው አከለለት… ‘ይኸውልህ.. እኔ በየጊዜው የተወሰኑ የእንጨት ክምሮችን ከቆረጥኩ በኋላ መጥረቢያዬን እሞርዳለሁ… በዚህም ምክንያት ብዙ እንጨት መቁረጥ ችያለሁ’ አለው… ሰውየው ለረጅም ጊዜ የተደበቀበት የስኬት ምስጢር ለካ ‘በየመሃሉ’ ማለት ነው…

ብዙዎቹ መጥረቢያዎቻችን ደንዘዋል… ችግሩ ዛሬም በትናንት አቅማቸው እንዲያገለግሉን እየጠበቅን ነው… ነጋ ጠባ በሚቆርጡት እንጨት ጥርሶቻቸው ተሸራርፎ አልቋል… ችርችፍ ብሏል… ዶልዱሟል…

ላሞችህ ወተት እንዲሰጡህ የምትጠብቀው መመገብ እንዳለብህ ዘንግተህ ከሆነ ችግር አለ… የገባው ነው የሚወጣው .. መልኩን ከመቀየሩ ውጪ… የአገልግሎት ማሻሻያ ሳያደርግ ከፍተኛ ገቢ የሚጠብቅ ድርጅት… ሳያነብ ልጨኛ ጽሑፍ መፃፍ የሚፈልግ ‘ደራሲ’… በአግባቡ ሳያስተምር ጎበዝ ተማሪዎችን ማየት የሚናፍቅ መምህር… የድርሻውን ሳይወጣ ያደገች ሃገር ማየት የሚሻ ሕዝብ… የሚጠበቅበትን ሳያደርግ የሚጠበቅብህን የሚጠይቅ መንግስት… ለአርዓያነት ሳይበቃ ‘የተመረቀ ልጅ’ የሚጠብቅ ቤተሰብ… ሁሉም የደነዘ መጥረቢያቸውን አስተውለውት አያውቁም… የአንዳንዶቹ እንዲያውም ዝገት ጀምሮታል…

ከድግሪህ በኋላ ማንበብ ካቆምክ ድግሪህ እርባን የለውም… ዶክትሬትም ቢሆን… ከሽልማት በኋላ መስራት ካቆምክ መሸለምህ ከንቱ ነው… ቅዱስም ብትሆን… ዜኖች እንዲህ ይላሉ… “Before enlightenment, chop wood, carry water. After enlightenment, chop wood, carry water.”

መጥረቢያህን ሳል… በመቁረጥ ላይ ብቻ እንደተመሰጥክ ያስታውቃል… ስትሞርድ ስለት ብቻ አይደለም የምትጨምረው… የሆነ የምታራግፈው ቆሻሻም አለ… ውጋጅ ነገር… አሮጌ አስተሳሰብ… ጠማማ ገጽታ… የተንሸዋረረ እይታ… ግድግዳ ኩራት…

ለመሞረድ የምታጠፋው ጊዜ የባከነ አይደለም… ነዳጅ እንደመጨመር ነው… የሆነ ጊዜ ድንገት ቀጥ ትላለህ… ምናልባት ያኔ ለመሞረድ ሁነኛ ጊዜህ አይሆን ይሆናል… እናም መቆሚያህ እንዳያጥር መቋቋሚያህን አጽና…

A woodsman once asked “what would you do if you had just five minutes to chop down a tree?’… He answered, ‘I would spend the first two & a half minutes sharpening my axe.”…

MORAL OF THE STORY
Let us take a few minutes to sharpen our perspective.

ባላችሁበት ሰላም!!

ምርጫችሁ ስለሆንን ስናመሰግኖት ከልብ ነው !!! @Philosophyworld1 @Philosophyworld1

ለማንኛውም ሀሳብ ወይም
አስተያየት በዚህ አግኙን @fear121
@kalina1924
1.2K viewsAb, 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 14:48:26 ተሸካሚ በሌለበት ሸክም የለም...!!

፨፨፨

<< አንድ ነገር የሚታየው በሌላ አካል ለመታየት ስለሚችል ሳይሆን ነገር ግን ሌላ አካል ስላየው ነገሩ ሊታይ ቻለ፤ ወይም አንድ ነገር ተመሪ የሚሆነው መሪ ስላለው እንጂ ነገሩ ተመሪ ስለሆነ አይደለም። አንድ ነገር ሸክም የሆነው ተሸካሚ ስላለው እንጂ ነገሩ በራሱ ሸክም ሆኖ አይደለም። ይኽ ማለት አንድ ውጤት በራሱ ልቆ የወጣበት አካል ውጤቱ የራሱ ሳይሆን ምክንያት ስላለው ነው። ውጤት የሆነ ነገር በራሱ ውጤት አያመጣምና። ቅድስናም እንዲሁ ቅዱስ የሚሆነው አማልክት ስለሚወዱት እንጂ በራሱ ቅዱስ ስለሆነ አይደለም። >>

/ ሶቅራጥስ /

ከፍልስፍና ዓለም

For any comments:- @fear121
@kalina1924
JOIN US
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1


Join our group:- @philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.2K viewsMr. x, 11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ