2022-05-05 08:07:32
.ላንቺ ማንሆነው የለ መቸም.....
#ሰምተሻል . This is for u
ባዶ ቤት በክረምት
አንቺ የሌለሽበት እህህ.
፦.፦
የሚለውን ዘፈን እያንጓራጎረ~እጁን በደረቱ ታቅፎ ቆዝሟል
ብርዱ አንዘፍዝፎት እትት... እያለ ሲያዩት ያሳዝናል
ከምር!..በትመጫለሽ ተስፋ ደጅ ደጁን እያየ ልቡ እየቋመጠ
"ነይልኝ"ን ሊፅፍ ስንት ቃል አላምጦ ስንት ሆሄና ግስን ስንት ሀረግ አማጠ
ነይለት እንዲሉት ስንቴ ተጠበበ ስንት ድርሳን ገለጠ?
ደሞ ይገርምሻል~~ተዘግቷል ብለሽ እንዳትመለሺ በራፉን ከፋፍቶ አንቺን በጠበቀ
ስንት ቆነጃጅት በራፉን ሲያንኳኩ ካ'ላንቺ አይሆን ብሎ 'እምነት' አጠበቀ!
.. #እምነት_ስል_አንቺዬ ....
በዚህ በኛ ዘመን ከሀዲ በርክቶ ሀቅ በጠፋበት
በጠረረ ፀሀይ የህዝብ፣የሀገር ሀብት በሚዘረፍበት
በዚህ በኛ ሀገር ፍትህ በሌለበት
ሀቅ እውነትን ያለ በሚሰቃይበት..
አዎ በኛ ሀገር..!
ታማኝ ታታሪ ሕዝቦቹን አገልጋይ መሳይ ለእይታ
ኮተቱ እንዳይታይ በአዋጅ አለባባሽ ገፅታ ግንባታ
ነፃነትን ነፍጎ በሚያስመርር መንግስት!
ከላይ ከላይ ኗሪ አስመሳይ ባለበት
ለብልጭልጭ አለም አይደለም ገላውን ሀገር የሚክዱ ሺዎች በሞሉበት
..ይህ ሰው ግን ስላንቺ ታምኖ እንደታመነ
ከስጋው ፍላጎት ከቶ እንደመነነ
በቀዘቀዘ ቤት ፅልመት በወረሰው እትት እያለ
ይሄው ዛሬም አለ ትመጫለሽ ተስፋን በልቡ እንዳዘለ
እናም እታለሜ.
ለዚህ ሰው ነይለት ፅኑ እምነቱን አይተሽ'
ብቻ ሚከብደውን ክረምቱን አስበሽ!!.
For any comments:- @fear121
@kalina1924
JOIN US
@Philosophyworld1
@Philosophyworld1
Join our group:- @philosophyworldd
@philosophyworldd
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
1.3K viewsMr. x, 05:07