Get Mystery Box with random crypto!

ጊዜው ነው ያስከፋን ጊዜው ነው ያስደፋን አንገት አሰብሮ ዝቅ አርጎ ያስቀረን ጊዜው ነው ሰዓቱ የጅ | ከኢትኤል ብዕር ነጠብጣቦች......✍️

ጊዜው ነው ያስከፋን
ጊዜው ነው ያስደፋን
አንገት አሰብሮ ዝቅ አርጎ ያስቀረን
ጊዜው ነው ሰዓቱ
የጅል ወቅት ሁኖብን
ጅል የፈነጨብን!
በዬ አመታቱ!!
ተምሮስ ነበረን
እሳቤስ ነበረን
በደናቁርት ምሃል ነደን ግን አለቀን!!
አውቃለሁ!
እራስን ሰቅሎ የሌሎችን ማውረድ
እውቀት እንዳልሆነ
አውቃለሁ
ሌሎችን ተሳድቦ
እራስን ላይ ክቦ
መመልከት መራር ነው።
ግና አንዳንድ ጊዜ
እውነታን መንገርም
ታላቅ ጥበብም ነው።
ጊዜው ነው የሰበረን
ጊዜው ነው የደፋን
የጊዜ ውላጆች
እኒያ ደናቁርቶች
እነሱ ያነፁት
እነሱ ያበጁት
የደናቁርት ቅፅር
አለምን ያጠረ የጊዜዎች ሚስጥር
መሪው ደናቁርት ነው
ተመሪውም ያው ነው!!
ከነዚያ ሰዎች ውስጥ
እኛም ተፈጥረን
አቦ ተሰቃየን።
ብንናገር እብዶች
ዝም ስንል ሞኞች
እንዲህ አየተሰጠን
ጊዜው ሰባበረን!!
አቦ ተሰቃየን