Get Mystery Box with random crypto!

የ እውቀት ማዕድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yewuketmaed — የ እውቀት ማዕድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yewuketmaed — የ እውቀት ማዕድ
የሰርጥ አድራሻ: @yewuketmaed
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.20K
የሰርጥ መግለጫ

ቻነሉ የተለያዪ አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞችን እንዲሁም አዳዲስ መረጃወችን አለም አቀፍ ግኝቶችን በተለያዩ ዘርፍ እውቀት የምትቀስሙበትን አማራጭ ያቀርባል።
ማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ ካላችሁ @teppi10_Bot ላይ አስፍሩልኝ!
የመወያያ Group—https://t.me/yewuketmaed8

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-27 17:31:43 አንድ ጊዜ አባት ከቢሮ ድክም ብሎት ቤት ሲገባ ልጁ ሁለት ፖም ይዞ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ አባት ፈገግ አለና ልጁን አንዱን ፖም እንዲሰጠዉ ጠየቀዉ፡፡ ይህን የሰማዉ ልጅ ሁለቱንም ፖሞች አንድ አንዴ ገመጥ ገመጥ አደረጋቸዉ፡፡

#በዚህ_ጊዜ አባት ተቆጣ... “አንተ ሆዳም! እንደዚህ ይደረጋል! አንዱ አይበቃህምና ነዉ ሁለቱንም ለመብላት የምትጣደፈዉ...!” እያለ የንዴት መትረየሱን አርከፈከፈዉ፡፡

ልጅ አዝኖ እንዲህ አለ “አባዬ እኔኮ ሁለቱንም የገመጥኩት ከሁለቱ የትኛዉ በጣም እንደሚጣፍጥ ለማወቅ ነዉ ... ይሄ በጣም ይጣፍጣል... ስለዚህ እንካ ላንተ! እኔ የቀረዉን ልብላ' ብሎት ለአባቱ የሚጣፍጠዉን ፖም ሰጠዉ:: አባት እንባዉን መቆጣጠር አልቻለም፡፡

#አንዳንዴ_ነገሮች ምንም ሳይገቡን መጮህ፣ መናደድና መቆጣት እንፈልጋለን፡፡ አንድን ነገር ዉጤቱን ገምተን ከምንጀምር ቀረብ ብለን ከመሰረቱ ብንረዳ የበለጠ መልካም ነዉ፡፡

@yewuketmaed
957 viewsedited  14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 21:52:56 ተው በሉት!

ሀይ ባይ ከልካይ ዳኛ
ሰሚ የጠፋ እለት
ፖለቲካ አይደለም
አትግደሉን ማለት።
690 viewsedited  18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 17:56:11 ለምንድነው_መኖር_የደከመህ??
.
ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ? ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ? አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ አንተ አላስፈልግም ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ

☞ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡
☞ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡
☞ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡
☞ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡

የቻልከውን ያህል ሞክር አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡

፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ህይወትህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ነው፡፡ "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ወይም መሸነፍ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::"
በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት አትቸኩል ይሄ ማለት ሳትፅፍ ለማጥፋት መሞክር ማለት ነው፡፡

@yewuketmaed
1.2K views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 14:20:31 ​​ሁሉንም ነገር ያጣቹ ከመሰላቹ ይህን አስታውሱ ዛፎች በየአመቱ ቅጠላቸውን ቢያጡም የተሻለ ቀን እንደሚመጣ በመጠበቅ ጠንክረው ይቆማሉ፡፡

ሁሉም ነገር ለበጎ ነው አንድ ቀን ነገሮች ይስተካከላሉ ከእኛ የሚጠበቀው ትግስት ነው ።

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
3.3K views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 23:04:28 ከዕለታት አንድ ቀን አንበሶች ለምንድነው ሁሌ እያደንን ምንበላው ለምን ቁጭ ብለን አንበላም አሉና መላ ዘየዱ!!
መላውም ምንድነው፦ ሁሉንም የጫካ እንስሳት በመጥራት ተራበተራ እየወጡ ቀልድ እንዲያቀርቡ ይደረጉ እና ቀልዱ ካላሳቀ ወይም ሁሉም ስቀው አንዱ እንስሳ እንኳን ካልሳቀ ይበላል አሉ!!

የመጀመሪያው ቀልድ አቅራቢ ቀበሮ ሆነና ቀልዱን ማቅረብ ጀመረ ፤ ቀልዱን አቅርቦ ሲጨርስ ሁሉም ሳቁ ፥ አህያዋ ግን አልሳቀችም ነበር!!
በዚህ ምክንያት ቀበሮዋ በአንበሶች ተበላች!!

ቀጣይ ተረኛ ጅብ ነበር እና ፥ ጅቡም በተመሳሳይ ቀልዶ አህያዋ ስትቀር ሁሉም እንስሶች ሳቁ። ጅቡም እንደቀበሮው ተበላ።

ሶስተኛ ቀልድ አቅራቢ ጦጢት ሆነች እና ጦጢቷ ቀልዷን ልታቀርብ ስትል አህያዋ ከት ብላ ሳቀች!!

ገና ቀልዱ ሳይጀመር ምንድነው ሚያስቅሽ ስትባል
ቀበሮው ያቀረበው ቀልድ አስቆኝ ነው አለች አሉ!!
2.4K viewsedited  20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-03 15:44:04 አስር አመት ያልሞላው ህጻን ልጅ ኪሱ ላይ ጥቂት
ሳንቲሞችን ይዞ አንድ አነስተኛ ካፌ ጎራ አለ ።ሰው ጥቅጥቅ
ብሏል።
ህጻን ከመሆኑ የተነሳ ማንም ትኩረት አልሰጠውም አይኖቹን
ከርተት አድርጎ
አንድ ክፍት ወንበር አገኘና ሄዶ ቁጭ አለ።
አስተናጋጇ መጣችና በቁጣ ምን ፈለክ ስትል አስደነገጠችው

ልጅ፦ በተሰበረ ልብ ድምፁን ዝግ አድርጎ አይስክሬም አለ??
አስተናጋጇ፦ብር ይዘሀል?.....
ህጻኑም ስንት ነው???
አስተናጋጃ፦አንድ ብር ከ ስሙኒ ነው ስትለው ወድያው ኪሶቹ
ውስጥ ያለውን
ሳንቲሞች አውጥቶ መቁጠር
ጀመረ።
አንድ ብር ከ ሀያ አምስት ሳንቲም ነው ልጁ የያዘው
ቶሎ በል ባክህ ሌላ ስንት ምታዘዘው ሰው
አለ አንተ፦ ሳንቲም ትቆጥራለህ ብላ
አመናጨቀችው።
ህጻኑም ሳንቲሞቹን ቆጥሮ፦ እሺ ኬክ ስንት
ነው ??..
አሁንም በቁጣ አንድ ብር አለችው
ኬክ አምጪልኝ ብሎ ከቆጠረው ሳንቱም ሀያ አምስቱን
ሳንቲም አስቀርቶ
ሳንቲሞቹን
ሰጣት ስትቆጥረው አንድ ብር ነው።
ኬኩን ውርውር አድርጋለት ሄደች ህጻኑም
በልቶ ጨርሶ ወጣ
አስተናጋጅዋም የበላበትን እቃ ለማንሳት
እቃውን ስታነሳ ከ ሳህኑ ስር ሀያ አምስት
ሳንቲም አስቀምጦላት ነበር።
ይህን ጊዜ ደነገጠች ወድያው ፊቷ በእንባ ረጠበ
ስቅስቅ ብላ አለቀሰች የሚወደውን እና
የሚፈልገውን አይስክሬም ብር ከ ሀያ አምስት
ከፍሎ ከበላ ለአስተናጋጁዋ
የሚሰጣት ነገር ስላልነበረው ያልፈለገውን ኬክ
በአንድ ብር በልቶ ስሙኒውን ለሷ ቲፕ
አስቀምጦላት ሄደ።
ትንሹ ልጅ ትንሹዋን ስጋውን አሸንፎ ክብርንና ርህራሄ
መስጠትን በትህትና ላላስተናገደችው
አስተናጋጅ ትህትና አስተማራት።

@yewuketmaed
2.2K viewsedited  12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 21:32:45 እየቀለድክ መሆን አለበት እንጂ እንዲህ የተቀዳደደ ጫማ አድርገህ ልትጫወት አትመጣም!አለው በስጨት ብሎ
እኔ ምርጥ የምለውን ጫማዬን ነው አድርጌ የመጣሁት ግን በችሎታዬ ስለምተማመን እንደምትመርጡኝ አልጠራጠርም ብሎ መለሰ "እስቲ ግባ እንይህ"ተባለ ገባ ተጫወተ በ15 ደቂቃ ውስጥ ማንነቱን በተቀዳደደው ጫማው ሳይሆን በአይምሮው እና በእግሮቹ ጥበብ አሳየ አሰልጣኙ ጉድ አለ በችሎታው ተመሰጠ አንተንማ ፈረንሳይ ነው የምወስድህ አለው! ፈረንሳይ ደርሷ እንኳን ለእናቱ መደወያ ካርድ አልነበረውም!! ከጓደኘው ስልክ ተውሷ "እማዬ ፈረንሳይ ገብቼለው" ሲል እናት ደነገጡ "የትኛው ፈረንሳይ ነው የምትለው አውሮፓ ያለው? አላመኑም በቃ እንዳሁም ኳስ ስጫወት በቲቪ አይተሽ ታምኛለሽ አላቸው። ይህ ሰው ቢናቅም ከድህነት ቢነሳም አሁን ከአለማችን ምርጥ አጥቂወች መሀል አንዱ ነው ታውቁታላችው የሊቨርፑል ኮከብ፤ የሴኔጋል እንቁ #ሳዲዮ ማኔ
ምንም በሌለህ ሰአት አለባበስህን ሁኔታህን አይተው ሰወች ሊንቁህ ሊሸሹህ ይችላሉ ስትለወጥ ደሞ ዙሪያህን ሊከቡህ ይችላሉ!ወዳጄ እንዳትገረም ዛሬ፤ነገም፤ ከሺህ አመት በፊትም ወደፊትም ሰወች እንደዚህ ናቸው። ወጥረህ ሰርተህ ማንነትህን አሳይ! አለዛ ከፈጣሪ በቀር ማንም እንዲሁ ሊወድህ ሊያከብርህ አይችልም!

@yewuketmaed
1.8K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 20:48:45 አዎን ህይወት ታስጠላለች ለዛውም ባልጠበካቸው የኔ ብለህ በምትመካባቸው ሰዎች ስትጎዳ፣ አዎን ህይወት ታስጠላለች ብዙ ታግሰህ ከዛሬ ነገ ይሳካልኛል ብለህ ጥረህ ጥረህ ደጋግሞ ሲመክንብህ፣ አዎን ህይወት ታስጠላለች ሃዘንህን፣ ደስታህን፣ ችግርህን፣ መከራህን ብቻህን ሆነህ ስትታገል፣ አዎን ህይወት ታስጠላለች ባላሰብከው መንገድ እራስህን ሌላ ውስብስብ በሆነ አለም ውስጥ ስታገኘው፤ አዎን የህይወት ገጿ ብዙ ነው፤ እኛ ከምናስበው፣ ከምንመኘው፣ መሆን ከምንፈልገው የተለየ ገጽ አላት። #ወዳጄ በሁሉም ነገር ውስጥ እኛ የማናውቀው መልካም ነገር አለ #ታገስ ሁሉም በጊዜው መልስ ያገኛል። #ትዕግስትህም እንዲሁ ባክኖ አይቀርም።

@yewuketmaed
1.7K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 12:36:24 ህይወት የሚደምቀው በፍቅር እንጂ በብር
አይደለም.....ገንዘብ በማንኛውም ሰዓት ከሰራሽ ልታገኚው
ትችያለሽ ፍቅር ግን ከፈጣሪ ነውና የሚገኘው አብዝተሽ
ፈጣሪሽን ለምኚ ወንድ ልጅ ከወደደሽ ራሱን ይሰጥሻል ይህ
ማለት ደሞ አንቺ እንደፈለክሽ አንገት ሆነሽ ታዞሪዋለሽ ....
ብዙ ሀብት ኖሮት ምንም ስብእና ወይም ላንቺ ክብር
ከጎደለው ሰው ጋር አይደለም ትዳር ለአንድ ቀን አድሮ መለየት
አትመኚ በማስመሰል እራሱን ደብቆ የሚመጣ አስመሳይ
ወንድ ወጥመድ እንዳትገቢ ጥንቃቄ ይኑርሽ ....
ብዙ ወንድ በማስመሰል የሚፈልገውን እስኪያገኝ
የማይፈልገውን ያደርጋልና .... እንዲ አይነቱ ወንድ በኑሮ
ህይወት እንደ እስስት ሲቀያየር ትመለከችዋለሽ .....
በውሳኔው የማይፀና አቋም የሌለው ሰው ላይ ብትወድቂ
እድሜሽን በሙሉ ስትንከራተተቺ ትኖርያለሽና እንደዚ አይነቱን
ወንድ ለማስተካከል ካልቻልሽ በትዳር እንዳትታሰሪ ጠንቃቃ
ሁኚ......
ደስታ የሚገኘው የውስጥ ፍላጎት በነፃነት መግለፆ ሲቻል
ነውና ነፃነትሽን የሚነፍግ ፍላጎትሽን የማይጠብቅ ወንድ ገና
ሲጀመር አትቅረቢው እንደዚ አይነት ወንድ ምን ጊዜም እራሱ
የሚያወራውን እንጂ አንቺ የምታወሪውን አይሰማም ቢሰማም
ቦታ ይሰጠውም እሱ የወደደው እንጂ አንቺ በመረጥሽው
መንገድ አይጓዝም ና........
አንቺ ለምትናገሪው ለምታደርጊው ነገር ስህተት ቢመስለው
እንኳን በቀስታ እንጂ ጮሆ ለሚናገር ወዳጅ አታበጂ ዛሬ
ከጮኸብሽ ነገ ሊመታሽ እንጂ የሚያነሳው ምንም ምክንያት
የለውምና........
ከሀብት ከቁሳቁስ ንጹህ ልብ ንጹህ ፍቅርን የሚሰጥሽ ወንድ
ተመኚ ....
የወንድን ያለውን ሀብት ወይም ኪሱን ሳይሆን ይዞ የመጣውን
ንጹህ ፍቅር ተመልከቺ እንደዚ አይነት ወንድ ትልቅ ዛፍ ሆኖ
ሊጠልልሽ ፍሬ ሊሰጥሽ ይችላልና ምክንያቱም የሁሉ መሰረት
ፍቅር ነውና ደስታ የሆነ ህይወት ከፈለክሽ ግን እህቴ ሁል
ጊዜም አስተውይ ብር ሳይሆን ፈጣሪን የሚፈራ ላንቺ ክብር ያለው ወንድን
አግቢ !!!፡፡

@yewuketmaed
1.6K views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 22:02:12 ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር
አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር
ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ
የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ
የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ። ሁሉን ልያዝ ማለትም
ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።

ቂም አፍን የሚያመር ፣ ልብን የሚያነቅዝ ፣ ተግባርን
የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ ሰው ቅያሜህን ግለጥለት ፤
ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ ።

ከህሊናህና ከመንፈሳዊ አማካሪህ ሳትመክር ምንም ነገር
አትወስን ፤ አጥርተህ ሳትሰማ ቃል አትግባ ። መከራ ካልደረሰ
በቀር ባል በሌለበት ቤት ውስጥ ከሚስቲቱ ጋር ብቻህን
አትቀመጥ ።
:
የሚበልጥህ ልኩራብህ እንዳይልህ ፣ ያነሰህ ልድረስብህ
ብሎ እንዳያጠፋህ የሀብትህን ልክ እንዳታወራ ፤ በገዛ አፍህ
ባንዱ ትከብራለህ ባንዱ ትቀላለህና።

በጣም በማክበርህ እንዳታመልከው ፤ በጣም በመናቅህ
እንዳታዋርደው ሠው እንዳንተ መሆኑን እወቀው ።

የእኔ መናገር ምን ይለውጣል? ብለህም ስህተትን አትለፍ
፤ የእኔ አስተዋፅኦ ምን ይጠቅማል ? ብለህም ስጦታህን
አትጠፍ ።

መልካም ቃል ከስጦታ ይበልጣልና መልካም ቃል ተናገር
፤ ማንኛውም ስጦታ ከልመና ወንበር አያስነሣም ። የተስፋ
ቃል ግን እንደሚያስነሣ አውቀህ ለሰዎች የተስፋ ቃል
ስጣቸው ።

ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን
አይጨርስም ። ዕውቀትህን የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን
ያሳይሃል ። አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት ፣ ሰውነትህን
ለመግዛት ትዕግስት ፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት
ያስፈልግሃል ። ለህሊናህ እረፍት ግን እምነት ያሻሃል ።
ተከታይ ለማበጀት ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ
ይልሃል ።

አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል
አትበል ። ዘመን እኔና አንተ ነን ፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን
የለም።

መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል ።
ትክክለኛም ውሳኔ ከመልካም ምክር ነውና..!!

@yewuketmaed
1.5K viewsedited  19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ