Get Mystery Box with random crypto!

ከዕለታት አንድ ቀን አንበሶች ለምንድነው ሁሌ እያደንን ምንበላው ለምን ቁጭ ብለን አንበላም አሉና | የ እውቀት ማዕድ

ከዕለታት አንድ ቀን አንበሶች ለምንድነው ሁሌ እያደንን ምንበላው ለምን ቁጭ ብለን አንበላም አሉና መላ ዘየዱ!!
መላውም ምንድነው፦ ሁሉንም የጫካ እንስሳት በመጥራት ተራበተራ እየወጡ ቀልድ እንዲያቀርቡ ይደረጉ እና ቀልዱ ካላሳቀ ወይም ሁሉም ስቀው አንዱ እንስሳ እንኳን ካልሳቀ ይበላል አሉ!!

የመጀመሪያው ቀልድ አቅራቢ ቀበሮ ሆነና ቀልዱን ማቅረብ ጀመረ ፤ ቀልዱን አቅርቦ ሲጨርስ ሁሉም ሳቁ ፥ አህያዋ ግን አልሳቀችም ነበር!!
በዚህ ምክንያት ቀበሮዋ በአንበሶች ተበላች!!

ቀጣይ ተረኛ ጅብ ነበር እና ፥ ጅቡም በተመሳሳይ ቀልዶ አህያዋ ስትቀር ሁሉም እንስሶች ሳቁ። ጅቡም እንደቀበሮው ተበላ።

ሶስተኛ ቀልድ አቅራቢ ጦጢት ሆነች እና ጦጢቷ ቀልዷን ልታቀርብ ስትል አህያዋ ከት ብላ ሳቀች!!

ገና ቀልዱ ሳይጀመር ምንድነው ሚያስቅሽ ስትባል
ቀበሮው ያቀረበው ቀልድ አስቆኝ ነው አለች አሉ!!