Get Mystery Box with random crypto!

አስር አመት ያልሞላው ህጻን ልጅ ኪሱ ላይ ጥቂት ሳንቲሞችን ይዞ አንድ አነስተኛ ካፌ ጎራ አለ ።ሰ | የ እውቀት ማዕድ

አስር አመት ያልሞላው ህጻን ልጅ ኪሱ ላይ ጥቂት
ሳንቲሞችን ይዞ አንድ አነስተኛ ካፌ ጎራ አለ ።ሰው ጥቅጥቅ
ብሏል።
ህጻን ከመሆኑ የተነሳ ማንም ትኩረት አልሰጠውም አይኖቹን
ከርተት አድርጎ
አንድ ክፍት ወንበር አገኘና ሄዶ ቁጭ አለ።
አስተናጋጇ መጣችና በቁጣ ምን ፈለክ ስትል አስደነገጠችው

ልጅ፦ በተሰበረ ልብ ድምፁን ዝግ አድርጎ አይስክሬም አለ??
አስተናጋጇ፦ብር ይዘሀል?.....
ህጻኑም ስንት ነው???
አስተናጋጃ፦አንድ ብር ከ ስሙኒ ነው ስትለው ወድያው ኪሶቹ
ውስጥ ያለውን
ሳንቲሞች አውጥቶ መቁጠር
ጀመረ።
አንድ ብር ከ ሀያ አምስት ሳንቲም ነው ልጁ የያዘው
ቶሎ በል ባክህ ሌላ ስንት ምታዘዘው ሰው
አለ አንተ፦ ሳንቲም ትቆጥራለህ ብላ
አመናጨቀችው።
ህጻኑም ሳንቲሞቹን ቆጥሮ፦ እሺ ኬክ ስንት
ነው ??..
አሁንም በቁጣ አንድ ብር አለችው
ኬክ አምጪልኝ ብሎ ከቆጠረው ሳንቱም ሀያ አምስቱን
ሳንቲም አስቀርቶ
ሳንቲሞቹን
ሰጣት ስትቆጥረው አንድ ብር ነው።
ኬኩን ውርውር አድርጋለት ሄደች ህጻኑም
በልቶ ጨርሶ ወጣ
አስተናጋጅዋም የበላበትን እቃ ለማንሳት
እቃውን ስታነሳ ከ ሳህኑ ስር ሀያ አምስት
ሳንቲም አስቀምጦላት ነበር።
ይህን ጊዜ ደነገጠች ወድያው ፊቷ በእንባ ረጠበ
ስቅስቅ ብላ አለቀሰች የሚወደውን እና
የሚፈልገውን አይስክሬም ብር ከ ሀያ አምስት
ከፍሎ ከበላ ለአስተናጋጁዋ
የሚሰጣት ነገር ስላልነበረው ያልፈለገውን ኬክ
በአንድ ብር በልቶ ስሙኒውን ለሷ ቲፕ
አስቀምጦላት ሄደ።
ትንሹ ልጅ ትንሹዋን ስጋውን አሸንፎ ክብርንና ርህራሄ
መስጠትን በትህትና ላላስተናገደችው
አስተናጋጅ ትህትና አስተማራት።

@yewuketmaed