Get Mystery Box with random crypto!

እየቀለድክ መሆን አለበት እንጂ እንዲህ የተቀዳደደ ጫማ አድርገህ ልትጫወት አትመጣም!አለው በስጨት | የ እውቀት ማዕድ

እየቀለድክ መሆን አለበት እንጂ እንዲህ የተቀዳደደ ጫማ አድርገህ ልትጫወት አትመጣም!አለው በስጨት ብሎ
እኔ ምርጥ የምለውን ጫማዬን ነው አድርጌ የመጣሁት ግን በችሎታዬ ስለምተማመን እንደምትመርጡኝ አልጠራጠርም ብሎ መለሰ "እስቲ ግባ እንይህ"ተባለ ገባ ተጫወተ በ15 ደቂቃ ውስጥ ማንነቱን በተቀዳደደው ጫማው ሳይሆን በአይምሮው እና በእግሮቹ ጥበብ አሳየ አሰልጣኙ ጉድ አለ በችሎታው ተመሰጠ አንተንማ ፈረንሳይ ነው የምወስድህ አለው! ፈረንሳይ ደርሷ እንኳን ለእናቱ መደወያ ካርድ አልነበረውም!! ከጓደኘው ስልክ ተውሷ "እማዬ ፈረንሳይ ገብቼለው" ሲል እናት ደነገጡ "የትኛው ፈረንሳይ ነው የምትለው አውሮፓ ያለው? አላመኑም በቃ እንዳሁም ኳስ ስጫወት በቲቪ አይተሽ ታምኛለሽ አላቸው። ይህ ሰው ቢናቅም ከድህነት ቢነሳም አሁን ከአለማችን ምርጥ አጥቂወች መሀል አንዱ ነው ታውቁታላችው የሊቨርፑል ኮከብ፤ የሴኔጋል እንቁ #ሳዲዮ ማኔ
ምንም በሌለህ ሰአት አለባበስህን ሁኔታህን አይተው ሰወች ሊንቁህ ሊሸሹህ ይችላሉ ስትለወጥ ደሞ ዙሪያህን ሊከቡህ ይችላሉ!ወዳጄ እንዳትገረም ዛሬ፤ነገም፤ ከሺህ አመት በፊትም ወደፊትም ሰወች እንደዚህ ናቸው። ወጥረህ ሰርተህ ማንነትህን አሳይ! አለዛ ከፈጣሪ በቀር ማንም እንዲሁ ሊወድህ ሊያከብርህ አይችልም!

@yewuketmaed