Get Mystery Box with random crypto!

አዎን ህይወት ታስጠላለች ለዛውም ባልጠበካቸው የኔ ብለህ በምትመካባቸው ሰዎች ስትጎዳ፣ አዎን ህይወ | የ እውቀት ማዕድ

አዎን ህይወት ታስጠላለች ለዛውም ባልጠበካቸው የኔ ብለህ በምትመካባቸው ሰዎች ስትጎዳ፣ አዎን ህይወት ታስጠላለች ብዙ ታግሰህ ከዛሬ ነገ ይሳካልኛል ብለህ ጥረህ ጥረህ ደጋግሞ ሲመክንብህ፣ አዎን ህይወት ታስጠላለች ሃዘንህን፣ ደስታህን፣ ችግርህን፣ መከራህን ብቻህን ሆነህ ስትታገል፣ አዎን ህይወት ታስጠላለች ባላሰብከው መንገድ እራስህን ሌላ ውስብስብ በሆነ አለም ውስጥ ስታገኘው፤ አዎን የህይወት ገጿ ብዙ ነው፤ እኛ ከምናስበው፣ ከምንመኘው፣ መሆን ከምንፈልገው የተለየ ገጽ አላት። #ወዳጄ በሁሉም ነገር ውስጥ እኛ የማናውቀው መልካም ነገር አለ #ታገስ ሁሉም በጊዜው መልስ ያገኛል። #ትዕግስትህም እንዲሁ ባክኖ አይቀርም።

@yewuketmaed