Get Mystery Box with random crypto!

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikrclinic — ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikrclinic — ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️
የሰርጥ አድራሻ: @yefikrclinic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.93K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓
❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤
❤ HBD ለማለት፤ 🎂
❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀
❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂
🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን። @yefikrclinic_bot
contact us 👉 @yefikrclinic
ላይ ይላኩሉን

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-11 15:27:41 @Yefikrclinic
@Yefikrclinic
@Yefikrclinic
339 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 12:48:31 ​​ #ከላይኛዉ #የቀጠለ
​በልጆቾ የምትጨክን….ከዛ ቡኃላ አባቴ እኔን መራገም ጀመረ… የበለጠ ጠላኝ….….ከእናቴ ጋር እልክ ተጋባ..‹‹ልጇን ትቻል..ልጆቼን ችላለው››በማለት ፎከረ ‹‹ላም ቀንዶ አይከብዳትም››አለ..በማግስቱ በሰው በሰው አፈላልጎ ለቤቱ ሰራተኛ ቀጠረ…ከእናቴ ጋር አንድ ትምህርት ቤት ስለሚስተምሩ በእየእለቱ ቢገናኙም አይነጋገሩም ነበር.. አንድ ወር አለፈ… የወዳጅ ዘመድ ጉትጎታ እና አማላጅነትም ፍሬ ስለላፈራ በሁለተኛዋ ወር ፍቼ ፈጻሙ….በተጋቡ በስምንት ዓመታቸው ማለት ነው ….ሰማኒያቸው ተቀዳደደ… በቃ.
…..በሶስተኛው ወሩ ለእናቴ ከአባቴ ደብዳቤ ደረሳት……
ሁሉ ነገር ህልም ነው የሆነብኝ..እንዴት ገነት ውስጥ እንዲህ በድንገት ሲኦል ሊመሰረት ይችላል...?እንዴት ያ ሁሉ በመካከላችን የነበረው ሳቅና ፈንጠዝያ ወደ ሀዘንና መሳቀቅ ሊቀየር ቻለ….?ምን አይነት መቅሰፍት ነው በትዳራችን ላይ የዘነበው….?ምን አይነት የእዮብን አይነት ፈተና ነው ለቤተሰባችን የተላከው….?የእዬብን አይነት ፈተና እኮ በድል ለመወጣት ከእዬብን አይነት ትዕግስት ጋር አብሮ መፈጠርን ይጠይቃል፡፡ታውቂያለሽ እኔ ደግሞ እንደዛ አይነት ሰው አይደለውም..ያ ላንቺ የተሰጠ ስጦታ ነው..መቼስ ይገባሻል ማንም ሰው የገዛ ልጁን አይጠየፍም..እኔ ግን አልቻልኩም ፡፡
እሱን እያየው መሳቀቁ ካቅሜ በላይ ነበር….፡፡እና ልገላገላው እንደምችል ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ላንቺ እንደዛ አይነት ምርጫ ሳቀርብልሽ ብታንገራግሪም የምትቀበይኝ መስሎኝ ነበር..ግን የጽናትሽን መጠን አላውቀውም ኖሮል…እንኳንም ጥለሺኝ ወጣሽ…እንኳንም ፈታሺኝ..እኔ ለአንቺ የምገባ ሰው አይደለውም..ለአንቺ ባልነትም የሚመጥን ስብዕናና ያለኝ ግለሰብ አይደለውም…፡፡ለልጆቼ አባት… ለተማሪዎቼ አስተማሪ ….ለአንቺም ባል.. ሆኜ ለመቀጠል ሞራሉ የሌለኝ ከንቱ ሰው ነኝ….፡፡የገዛ ልጁን የተጠየፈ ሰው እንዴት የሰውን ልጅ ተከታትሎ እና ተንከባክቦ በማስተማር የሀገርን አደራ ተቀብሎ መልካምና ውጤታማ ዜጋ ሊያፈራ ይችላል…በፍፅም..ጥሩ አባት መሆን ያልቻለ ሰው ጥሩ መምህር ነኝ ቢል ምፀት ነው… ስለዚህ ከአሁን ቡኃላ ለፀጋ ብቻ ሳይሆን እኔጋ ላሉ ሶስቱ ልጆቻችንም ከእኔ ይልቅ አንቺ ነሽ ምታስፈልጊያቸው…አንቺ እቤቱን ለቀሽ ከወጣሽ ቡኃላ አንድ ቅጽበት እንኳን በፊታቸው ላይ ሳቅ ልፈጥር አልተቻለኝም…..፡፡
ቤቱ ሬሳ የወጣበት የሙት መንፈሶች ጉባኡ የተቀመጡበት መቃብር ቤት ይመስላል….ስለዚህ ስራዬን ትቼ ልጆቼን ትቼ… ሀገሩን ለቅቄ ሄጄያለው..ወዴት ብለሽ እንዳትጠይቂኝ…ልታፈላልጊኝም እንዳትሞክሪ .. ለጊዜው መሄዴን ብቻ እንጂ ወዴት እንደምሄድ እኔም እራሴ አላውቀውም…..ብቻ በመጨረሻ አንድ ነገር ላስቸግርሽ..እውነት እንደምታምኚው የልጅሽ አዕምሮ በትክክል ጤነኛና የሚያገናዝብ ከሆነ እኔ አባቱ ያደረኩበትን ነገር ነግረሽ ግን ደግሞ ከቻለ ይቅር እንዲለኝም ጠይቂልኝ….››
በይ ቻው ያንቺው አፍቃሪ….
እናቴ ደብዳቤውን በእንባ እየታጠበች ነው ያነበበችው..ውስጥ ድረስ በጠሊቅ የሚጠዘጥዝ እና አጥንት የሚያሳሳ ሀዘን ነበር ያጋጠማት …እርግጥ እቤቱን ጥላ የወጣች ቀን ከፍቷት ነበር …ግን በዚህ መጠን አልነበረም ..፡፡ሰማኒያቸውን ፍርድ ቤት ቀርበው የቀደዱ ቀንም ከፍቷት ነበር ግን እንደዚህ ቅስሞ አልተሰበረም ነበር
በስተመጨረሻ እናቴ ምርጫ አልነበራትምና …መኪና ፈልጋ እቃዎቾን ጭና እናም እኔንም ተሸክማ ወደ ቤቷ ተመልሳ ገባች… ከልጆቾ ተቀላቀለች…፡፡
ይሄው እቤቱም አሁን ያለንበት ነው … ልጆቹም እኔንም ጨምረው ጓረምሰው እዚሁ ቤት አሉ …አባቴ ግን…. አባቴ በአሁኑ ጊዜ የት እንዳለ ሌላ ጊዜ እነግራችሆለው..፡፡እናቴ ግን በአስተማሪ ደሞዞ እኛን አራት ልጆቾን አንቀባራ በስርአት አስድጋናለች ፡፡ደረጃው ይለያይ እንጂ ሁላችንንም አስተምራናለች.. ይሄው እስከአሁንም ከእሷ ትከሻ ላይ ሁላችንም ሙሉ በሙሉ አልተላቀቅንም..ታዲያ ሀርሜ-ኮ ጀግና አይደለች….ታዲያ የልቤ የክብር ሊሻን አይገባትም ትላላችሁ....እናቴ ለእኔ ገነቴ ነች፡፡
በነገራችን ላይ እናት ብቻ ሳትሆን ሀገርም እንዲሁ ነች፡፡ሀገር በጦርነት ወይም በአመፅ ስትታመስ የምትጨነቀውና በተራሮቾ ላይ ሸሽጋ፤ በዋሻዎቾ ውስጥ ሸጉጣ ፤በጫካዎቾ ውስጥ ሰውራ ህይወታቸውን ማተረፍና የተሸለ ቀን እስኪመጣ ለማቆየት የምትጥረው ባላገሮች የሆኑትን ጎስቆላዎችን እና ሚስኪን ዜጎቾን ነው፡፡ሀብታሞቹና የነቁት ምሁራኖችማ እራሳቸውን ለማዳን ሁሌ ዝግጁ ናቸው፡፡ገና የመጀመሪያውን የጥይት ተኩስ ሲሰሙ ብራቸውን ሰብስበው፤ ሻንጣቸውን ሸክፈው ፓስፖርታቸውን ይዘው በቦሌ በኩል እብስ ነው፡፡ከዛ አነስ ያለውም በሞያሌና በመተማ ቀሪው በጅብቲ በኩል ይነጉድና ከእሳቱ እርቆ ከመከራው ተጠብቆ የተሸለ ቀን እስኪመጣ እራሱን በምቾት ያቆያል፡፡እና ሀገር በመከራ ጊዜ የምትጨነቀው በፍፅምነትም የምታስፈልገው ወደየትም ጥጋት መሸሻ ሀሳቡም እድሉም ለሌላቸው ሚስኪን ዜጎቾ ነው…ልክ እንደ እናት፡፡

ይቀጥላል
@yefikrclinic
@yefikrclinic
ይህን የእናትነትን ፅኑ ፍቅር ውስጡ የገባ አንብባችሁ ስትጨርሱ እያረጋችሁ እለፉ አብሮነታችሁንም በዛው እናያለን
532 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 12:46:39 #ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-3

:


....‹‹ያን የመሰለ ደስተኛ ኑሮችን እንዲህ ምስቅልቅሉ የወጣው…ይሄ ልጅ ከተወለደ ቡኃላ ነው››
‹‹አረ ተው ጡር አትናገር….ምንም ቢሆን ልጃችን አይደል››አለችው ኮስተር እና ቆፍጠን ብላ..
‹‹አይ ይሄ ልጃችን አይደለም….ይሄ ሳቃችንን የነጠቀን እና ፈገግታችንን የሰረቀን ለቤታችን የተላከ መቅሰፍት ነው››
‹‹ልጄንማ እንዲህ እንድትለው አልፈቅድልህም…..››
ቁጣዋን ችላ ብሎ ሌላ ጥያቄ ጠየቃት ‹‹ታፈቅሪኛለሽ አይደል.?››
‹‹ምን የሚሉት ጥያቄ ነው ….?በደንብ አፈቅርሀለው››መለሰችለት፡፡
‹‹እንደዱሮችን በሳቅ በተሞላ ኑሮ በደስታ እየቧረቅን ልጆቻችንን አብረን እንድናሳድግ ትፈልጊያለሽ አይደል.?››
‹‹አዎ እፈልጋለው..በጣም እፈልጋለው››የተቋጠረ ፊቷን አላቀ የተከደነ ጥርሷን ከፈት አድርጋ በተስፋ መለሰችለት
‹‹እንግዲያው ለእሱም ለእኛም ስንል..ይሄንን ልጅ ለእርዳታ ድርጅት እናስረክበው..እዛ የተሸለ ህክምና ያገኛል..ከእኛ በተሻለ…..››የእናቴ ተስፋ መልሶ ጨለመ...እሱ ለተናገረው እሷ ተሳቀቀች
‹‹እንዳትጨርሰው….ልጄን በህይወት እያለው ለማንም አልሰጥም..እንኳን ለእርዳታ ድርጅት ለገዛ እናቴም አልሰጥ..እንደው አቅም አንሶኝ ለማሳደግ ብቸገር እንኳን ሌሎቹን ልጆቼን አሳዳጊ ልሰጥ እችል ይሆናል እንጂ እሱን አላደርገውም፡፡ምክንያቱም ማንም እንደእኔ ሊረዳው አይችልም..፡፡ ማንም እንደእኔ ሊንከባከበው አይችልም..፡፡ለእኔ ከእግዜር የተሰጠኝ የህይወት ዘመን ፀጋዬ ነው፡፡አንድም ቀን መከራዬ ሆኖ ተሰምቶኝ አያውቅም..ለዛም ነው ፀጋዬ ብዬ የምጠራው››
‹‹እኔ ግን አልችልም..አካሉም አዕምሮውም በድን የሆነ ልጅ ጥዋት ማታ እያየውና እየተሳቀቅኩ ቀሪ ዘመኔን መቀጠል አልችልም…..ያቅማችንን ሞክረናል..ያለንን ገንዘብ ጌጣችንን እና ንብረታችንን ሁሉ እሱን ደህና ለማድረግ ስንል በትነናል…. ከዛም አልፎ እዳ ውስጥ ገብተናል..እንደዛም ሆኖ ግን ምንም ጠብ ያለ ነገር የለም…አዕምሮው የተበላሸ ልጅ ምንም ልናደርገው አንችልም……››
‹‹የእኔ ልጅ አካሉ የማይንቀሳቀስ ሊሆን ይችላል…አዕምሮው ግን ጤነኛ ከሆኑት ልጆችህ በተሸለ ያስባል…. ይሰራል››
‹‹እሱ የእናትነት ልብሽ የሚያስበው ነው…ምኞት፡፡አዕምሮውም ልክ እንደመላ አካሉ አንድ ቦታ ረግቶ የተቀመጠ መስራት ያቆመ..በቃ ምን ልበልሽ… የነከሰ ሞተር ማለት ነው፡፡››
‹‹ተሳስተሀል››እየተንዘረዘረች፡፡
‹‹አልተሳሳትኩም…ያልኩሽን እንድርጊና የቀድሞ ህይወታችንን እንኑር ..አንቺም ወደስራሽ ተመለሺ..የቻልነውን ሞክረናል..እግዜሩም ሰውም በዚህ ውሳኔችን ይደግፉናል እንጂ የሚያዝንብን የለም››
‹‹አልችልም ..በህይወት እያለው.ከልጄ መነጠል አልችልም››
‹‹እንግዲያው የሶስት ቀን ማሰቢያ ጊዜ ሰጥሻለው …እሱ ባለበት እንዲህ በሀዘን የተጨመላለቀ አሳቃቂ ኑሮ ውስጥ መኖር አልችልንም›› ብሎ ፈታኝ ጥያቄ ላይ ጥሏት ወደ ስራ ይሄዳል
እናቴ ለአንድ ቀን ሙሉ በነገሩ ላይ አሰበችበት..አወጣች አወረደች ይሻላል ያለችውን በሁለተኛው ቀን ወሰነች…ወደትምህርት ሚኒስቴር ሄደችና ወደስራዋ አንዲመልሳት ማመልከቻዋን አስገባች..ልጄን ቢያምብኝ ብላ ለክፉ ቀን ያስቀመጠቻትን ሽርፍራፊ ገንዘብ አውጥታ ቤት ተከራየች..በሶስተኛው ቀን አባቴ ስራ ሲሄድ ጠብቃ….አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ የእኔን እና የእሷን እቃዎች..መተኛ አልጋችንን..ማብሰያ ዕቃዎችን የመሳሰሉትን አዲስ ወደ ተከራየችው ቤት አጋዘች..ተክሲ ተኮናትራ እኔን ይዛ እቤቱንም ልጆቾንም ጥላ ወጣች….
አንደተለመደው አባቴ አምሽቶ እና ወሳስዶ እቤት ሲመጣ ሶስቱ ልጆች በግራ በመጋባት እና በፍራቻ ውስጥ ሆነው ጎን ለጎን ተኮልኩለው ነበር ያገኛቸው፡፡
‹‹ምን ሆናችሁ.?››
‹‹እማዬ››ከመንታዎቹ አንዷ
‹‹እማዬ ምን.?››
‹‹ሄደች››
‹‹ሄደች ማለት.?››
‹‹ሄደች …ጥላን ፀግሽን በታክሲ ይዛው ሔደች››ግራ ተጋባ
‹‹አመመው እንዴ...?ሀኪም ቤት ነው የወሰደችው.?››
‹‹አይ አይደለም… ይሄን ስጡት ብላለች››ብለው ወረቀቱን አቀበሉት… ገለበጠው፡፡ ለእሱ የተጻፈ ደብዳቤ ነበር፡፡በቆመበት በሚንቀጠቀጥ እጅ ጨምድዶ ይዞ በሚርገበገቡ አይኖቹ ማነበቡን ቀጠለ፡፡
……..ይህቺ ቀን ትመጣለች ብዬ መቼም አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ካየውህና ካወቅኩህ ቀን ጀምሮ አፈቅርህ ነበር ..እርግጥ አሁንም አፈቅርሀለው ….. የመጀመሪያ ፍቅሬ ነህ..ሴት ያደረግከኝ አንተ ነህ…ልቤ ካንተ ውጭ ሌላ ሰው ለሽርፍራፊ ሰከንዶች ቢሆን እንኳን ጎራ ብሎበት አያውቅም..ሳገባህ ገነት የገባው አይነት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር…አብሬህ ስኖር በሙሉ ልቤና ነፍሴም ጭምር ነበር..፡፡እመነኝ ከአንተ ጋር ህይወቴን ሙሉ ለመኖር ህይወቴንም ቢሆን በክፍያ ለማቅረብ ዝግጁ ነኝ… ልጅን ግን አላደርገውም፡፡ለወደፊትህም አንድ ምክር ልስጥህ አንድን እናት በምንም አይነት ከልጅሽ አስበልጪኝ የሚል ፈታኝ ምርጫ አታቅርብላት ከዛ ይልቅ ሙቺልኝ ብትላት የተሻለ ትክክለኛ እና ፍትሀዊ ጥያቄ ይሆናል…ካፈቀረችህ ያለማቅማማት ልትሞትልህ ትችላለች ..ልጆን ግን…..በፍፅም፡፡
እርግጥ ይገባኛል..ለአንተም ልጅህ እንደመሆኑ መጠን ጫናው ከብዶህ እንጂ ጠልተሀው እንዳልሆነ አውቃለው..እኔ ግን እናት ነኝ መቼም መቼም ቢሆን በልጄ ተስፋ ልቆርጥ አልችልም…ይሄንን ስሜቴን ምን አልባት እመብርሀንም ልጅ ስለነበራት ትረዳኝ ይሆናል..ለእናንተ ስል ልጄን ከምተው ..ለልጄ ስል ሁላችሁንም ባሌንም… ልጆቼንም…ቤቴን ብተው እመርጣለው….እዚህ ላይ ንፅፅር እንዳታደርግ ..ጥለሻቸውስ የሄድሽው ልጆችሽ አይደሉም ወይ ብለህ እንዳትጠይቀኝ..፡፡ከሶስት ጤነኛ ልጆች እንዴት አንድ መላ አካሉን ማዘዝ የማይችል ልጅ ልትመርጪ ቻልሽ እንዳትለኝ...? የዚህን መልስ ለመመለስ ለእኔ ቀላል አይደለም…ግን ቢያንስ እነሱን ማንም ተቀብሎ ሊያሳድጋቸው ይችላል…..የፈለጉትን መጠየቅ የተበደሉትን መናገር ይችላሉ፡፡እቤት ከአንዱ ክፍል እሳት ቢነሳ በጎሮ በር ወይም በመስኮት ዘለው ለማምለጥ ለእነሱ ቀላል ነው፡፡ቢርባቸው እንኳን ማድቤት ገብተው ምግብ ፈልገው ለመጉረስ አይሰንፉም፡፡ሽንታቸውን ቢወጥራቸው ወደ ሽንት ቤት ሄደው ለመሽናት ውሃ ቢጠማቸው ወደ ፍሪጅ ሄደው አልያም ከቧንቧ ቀድተው ደቅነው ለመጠጣት ለእነሱ በጣም ቀላል ነው….አየህ የእኔ ሚስኪን ልጅ ግን ይሄን ሁኑ ማድረግ አይችልም…ምን እንደፈለገ እንኳን መናገር ስለማይችል ከእኔ ከእናቱ ውጭ ማንም ሊረዳው አይችልም…ግን ደግሞ እሱም እንደእነሱ በህይወት አለ..እሱም እንደነሱ ይራባል…፤እሱም እንደነሱ መጸዳዳት አለበት.ያን ሁሉ ማድረግ የሚችለው ግን በእኔ በእናቱ እርዳታ ነው እናም እኔ ለእናንተ ከማስፈልገው በላይ በብዙ ሺ እጥፍ ለእሱ አስፈልገዋለው ስለዚህ አንተንም ላለመረበሽ ስል ቤቱን ለቅቄ ልጄን ይዤ ወጥቼያለው፡፡አይዞህ እንዴት ይኖራሉ ብለህ አታስብ ወደ ስራዬ ለመመለስ ስለወሰንኩ ማመልከቻ አስገብቼያለው አንተም ልጆችህን ጥሩ አባት ሆነህ እንደምታሳድግ ምራጫውን ለአንተ ትቼዋለው ከፈለግክ ሰራተኛ ቅጠር …ከፈለክም ማግባት ትችላልህ፡፡ በዚህ ምንም ቅሬታ አይሰማኝም…..ፍቺያችንንም ዝግጁ ስትሆን ንገረኝና በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲያልቅ አደርጋለው፡፡ብቻ አደራ ምልህ እቅፍ ውስጥ ላሉት ሶስት ጤነኛ ልጆቸች ጥሩ አባት ሁናቸው፡፡ያንተው አክባሪህ
ፈጽሞ ያልጠበቀው ዱብ እዳ ነው ያጋጠመው..መቼም እንዲህ አይት ውሳኔ ላይ ትደርሳለች ቡሎ ገምቶም ጠርጥሮም አያውቅ ነበር .፡፡በእሱ የምትጨክን
538 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 21:05:21      #ቀናሽ_አሉ

በቆምሽበት ሌላ ሳቆም
ማዶ ሆነሽ አየሽ አሉ
ስሜን ጠራሽ ጮሽም አሉ
አውለበለበሽ በጅሽ ሁሉ
በእንባ ጠፋ የአይንሽ ኩሉ

ግን ስህተቱ አንቺ ጋ ነው
አጉል ቅናት መለየት ነው
ሺ ቢመጣ ሚወደድ ሰው
ንግስቴ አንቺ
 ፍቅሬ እኮ ላንቺ ነው



,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,
        •═••• •••═•
  
    
@Yefikrclinic  
@yefikrclinic
560 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 10:37:38 ​​​በጣም ነበር ያሰደመማት..ምናልባት ለአሁን ጊዜ ዬኒቨረስቲ ተማሪ ሻራተን እና ኮንትኔታል መጋበዝም ቢሆን ብርቅ ላይሆን ይችላል…አለፍም ካላም ባህር ተሸግሮ ድንበር አቋርጦ አየር ሰንጥቆ ዱባይና ኢስታንቡል ቅዳሜና እሁድን ማሳለፍ እንደው ትንሽ ጉራ ለመንዛት ይጠቅም ይሆን እንጂ ያን ያህል አፍ የሚያስከፍት አይደለም..የዛን ጊዜ ግን ለአንድ ሴት ሻይ ቤት ወንበር ላይ ለዛውም ከጎረምሳ ጋር ቁጭ ብሎ ቀይ ሻይ መጠጣት በአሁን ጊዜ በአደባባይ ሀሽሽ እንደማጬስ ያህል ነውር ነበር…ለሁለቱም እንደዛ አይነት ቦታ ሲገቡ የመጀመሪያ ቀናቸው ነበር…በዛፎች በተከበበውና አረንጎዴ በለበሰው ግቢ ውስጥ አንድ ነጠል ያለ ቦታ ፊት ለፊት ቁጭ ብለው ሚርንዳቸውን እየጠጡ ማውራት ቀጠሉ
‹‹እንዴት ይሄን ቦታ አወቅከው.?››
‹‹ሰው አሳይቶኝ››
‹‹ከዚህ በፊት መጥተህ ነበር››
‹‹አልገባውም…ከውጭ ነው ያየውት››
‹‹እንዴት እዚህ ደርሰህ ሳትገባ ተመለስክ ››
‹‹ካንቺ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ማየት ስለፈለግኩ..ቀድሞ መግባት አላሻኝም፡፡››
‹‹አመሰግናለው…አንተእኮ ምርጥ ጓደኛዬ ነህ››
‹‹ጓደኛዬ ስትይ?››
‹‹ጓደኛዬ ነዋ…ጓደኛ አታውቅም››
‹‹እናም ጓደኛሽ ብቻ ነኝ…››
‹‹አይ አባቴም ነህ››ሀሳቡን ብትጠረጥርም ያልገባት መስላ ቀለደችበት
‹‹እኔ ቀልድም አይደልም ማወራው..ስላንቺ ሳስብ ልቤ ፍርፍር ነው ምትልነብኝ፤ውስጤ እርብሽብሽ ይላል፤እኔ ወዳጄ እንድትሆኚ ነው የምፈልገው››
‹‹ወዳጂ..ምን ማለት ነው?››
‹‹የወደፊት ሙሽራዬ እንድትሆጎኚ እፈልጋለው…እኔ ካንቺ ተለይቼ መኖር አይሆንልኝም…እምቢ ብትይኝ እንኳን ሞጭልፌም ቢሆን የራሴ አደርግሻለው››
እናቴ በገረሜታ‹‹ሞጭልፌ ስትል?››
‹‹ምኖ ነሽ ባክሽ ..አይገባሽም፡፡እጠልፍሻለው እያልኩሽ ነው….››
ከብዙ ማብራሪያና ልመና ቡኃላ ‹‹ላስብበት›› አለችው ፡፡በዛን ጊዜ ላስብበት ማለት ያው ግማሽ እሺታን ይወክል ነበር..አባቴ ፈነጠዘ…ለሚቀርቡት ሁሉ አዋጅ አስነገረ…የመጨራሻው መልስም እንደገመተው እሺ ሆነ …መቼስ በሴት ፍቅር የተማረከ የወንድ ልብ ነፍሱንም ጭምር አሳልፎ ቢሰጥ የሚገርም አይሆንም እና ሁለቱም እንደተመረቁ አዲስ አባባ ነበር ስራ መፈለግ የጀመሩት ያው የትምህርት ውጤታቸው ሁለቱም አሪፍ የሚባል ስለነበረ ወዲያው ነበር በአስተማሪነት አንድ ትምህር ቤት የተቀጠሩት….
ከሁለት ወር ቡኃላ ነበር የተጋቡት….ይሄ አሁን ያለንበትን ቤት አያቴ ነው ማለቴ የእናቴ አባት የሰርግ ስጦታ ገዝቶ ያበረከተላቸው…ይሄ ሲሆን ደግሞ ከዛ እናቴ እንደነገረችኝ ሁሉ ነገር ፍጽማዊ ይመስል ነበር፡፡..ሲጋቡ፤ ሲዋሀዱ፤አንድ መሶብ ቆርሰው አንድ አልጋ ላይ ለሊቱን ሲያሳልፉ በአለም ላይ ያለው ደስታ ሁሉ ተጠራርጎ እቤታቸው ገብቶ ነበር፡፡..እናቴ በስድስት ወሯ አረገዘች፡፡ይሄ ደግሞ ሌላ ደስታ፤ሌላ ፈንጠዝያ በቤታቸው እንዲዘንብ ተጨማሪ ምክንያት ሆነ..፡፡ቀኑ ደርሶ እናቴ ስትወልድ ሁለት መላአክ የመሰሉ መንትያ ሴቶች፡፡…እናቴ አንዷን ፌናን ብላ ስታወጣላት ሌላኛዋን ደግሞ አባቴ ሮዛ ብሎ ሰየማት፡፡መነጋገሪያና ደስታኛ ቤተሰብ ሆነ፡፡እህቶቼ ሁለት አመት ሞልቶቸው ድክ ድክ ማለት ሲጀምሩ እኔ ተረገዝኩ፡፡ አሁንም ሌላ ደስታ ፡፡ሁሌ ሳቅ የሞላበት ቤት፤ሁሌ ጫወታ የደራበት ቤት፤ሁሌ ፈገግታ ማይነጥፍበት ቤት…፡፡ከዛ በሶስተኛ አመት የጋብቻ በአላቸው አካባቢ እኔ ተወለድኩ..ወንድ ልጄ ከነቃጭሉ …፡፡አቤት እግዜር ሲመርቅ ተባለ፡፡ተደገሰ፤ተጨፈረ፡፡…ግን ቀናቶች እየገፉ ሲመጡ ሁኔታዬ ግራ እያጋባ መጣ፡፡እንደ መወራጨት እና መነጫነጭ የመሳሰሉት የልጅ ባህሪዎች ከእኔ ዘንድ ሊታዬ አልቻሉም፡፡ሀኪም ቤት ወሰዱኝ፡፡….አስመረመሩኝ
፤ለውጥ የለም፡፡..ለውጥ ብቻ ሳይሆን ይሄ ነው በሽታው የሚል በእርግጠኝነት የሚናገር ሀኪም ጠፋ፡፡አንድ የነርብ ችግር ነው ይላል፤ሌላው አዕምሮው መልዕክት ሰለማይቀበል ነው ይላል፤ቀስ በቀስ ደስታ ያረበበበት የነበረው ቤተሰብ ሀዘን ይጎበኘው ሲጀምር በፈገግታ ብቻ ተውጦ የኖረው ቤተሰብ የተጨማደደ ፊት ማሳየት ጀመረ፡፡
….ቢሆንም ከአመት ከስምንት ወር ቡኃላ ሌላ ልጅ ተወለደ.. ማሀሪ ፡፡ይሄ በመጠኑ መደበታቸውን ጋብ ቢያደርገውም ብዙም አልዘለቀ…በእኔ ላይ ምንም ለውጥ ባለመታየቱ ጭቅጭቁ እንደአዲስ ተጀመረ፡፡መላ አካሌ በድን ነበር..ብቸኛ መንቀሳቀስ ሚችሉት አይኖቼን ብቻ ነበሩ፡፡ከዛ ወዳጅ ዘመድ ነን ባይ ጭራሽ ለወላጆቼ እዚህ ውሰዱት እዚህ ወሰዱት እያለ ድንግርግራቸውን ያወጧቸው ጀመር፡፡…ጠበል ውሰዱት፣አዋቂ ቤት ውስዱት፤እከሌ ሚባል ሀኪም ቤት ውሰዱት….በመጠየቅ ሰበብ እቤታችን ጓራ ያለውን አስተያየት ይሰጥ ነበር፡፡ ወላጆቼም ከእምነታቸውም እየተጋጪ የእኔን መዳን ብቻ ተስፋ በማድረግ ብዙ ነገር ሞከሩ፡፡…ጉልበታቸውን፤ ጊዜያቸውንም፤ ገንዘባቸውንም በተኑ ፡፡ እኔ እንደሆነ ቅንጣት የተባለች ለውጥ እንኳን ማምጣት አልቻልኩም..እኔን ለማስታመም እና ለመንከባከብ ስትል እናቴ ስራዋን ለቀቀችና በአባቴ ገቢ ብቻ መተዳደር ጀመርን፡፡..ሰውነቴ በድን በሆንኩበት እያደገ እና እየተመዘዘ መጣ፡፡ከእኔ ኃላ የተወለደው ወንድሜ መሀሪ ቀድሞኝ መራመድና መናገር ጀመረ፡፡ አራት አመት ሞላኝ፡፡ምንም ለውጥ የለም..የምፈልገውን መጠየቅ አልችል፤ምጸዳዳው በራሴ ላይ፤ምግብ የምበላው በእናቴ እጅ፤ለዛውም በጣም የራሰ እና ለፈሳሽነት የቀረበ ምግብ ሆኖ በግድ በአንድ እጆ አፌን እየፈለቀቀች በእንድ እጇ ምግቡን ወደአፌ በመሰግሰግ፡፡
…ውሀም ሆነ ወተት..ቀና አድርጋ አንገቴን ደረቷ ላይ አስደግፋ አንድ እጇን እንደኩሬ አጎድጉዳ ከታችኛው ከንፈሬ ላይ በመደቀን ወተቱን ወይም ውሀውን እዛ መዳፌ ላይ በማንጮረር በመጋት ነበር ምትመግበኝ…፡፡
አምስተኛ አመት ላይ ስደርስ ግን አባቴ ተስፋ ቆረጠብኝ፤መነጫነጩ ጫፍ ደረሰ፡፡…ከእናቴ ጋር ንትርክ፤ጠጥቶ መግባት፤በአሽሙር መሳደብ ጀመረ…፡፡እናቴም ሰምቶ እንዳልሰማ ማሰለፍ፤ ሲብስባት ማልቀስ የእየእለት ድርጊቷ ነበር ፡፡ቡኃላ ግን ነገሮች በመሻሻል ፋንታ እየባሱ መጡ…የአባቴ ፀባይ እየከፋበት ሄደ፤ውጭ ማድርና ለእናቴ የሚሰጣት የወር ወጪም እየቀነሰ መጣ..በስተመጨረሻ ለእናቴ አስደንጋጭ ምርጫ አቀረበላት‹‹…ከእኔ ወይ ከልጅሽ አንዳችንን ምረጪ››.......

ይቀጥላል

#ክፍል ሶስት ከ200 ቡኃላ ይቀጥላል
#ሼር እና ቮት እንዳትረሱ
@yefikrclinic
@yefikrclinic

​​​​​​​​​​​​​​​
​​​​​​​​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥ ሀርሜኮ ̶̥✽̶┄┄
​​​​​​​​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥ ሀርሜኮ ̶̥✽̶┄┄
1.2K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 10:36:03 #ሀርሜ_ኮ
:
#ክፍል-2

...ይሄ ታሪክ እናቴ እና አባቴ እንዴት እንደተዋወቁ የሚያትት ነው፡፡ታሪኩን የነገረችኝ እናቴ ነች፡፡እርግጥ ታሪኩን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በስድስት ወር እና በዓመት ልዩነት አቀራረብን ለወጥ እያደረገች የተወሰነውን እየቀነሰች እና በፊት ነግራኝ ከነበረው ውስጥ ያልተካተተ አዲስ ታሪክ እየጨመረችበት ነግራኛለች፡፡እናቴ ስለአባቴ የምታወራኝ ብሶት ሲሰማት ነው..ውስጧን ሀዘን ሲቦረቡረው ነው…ልቧ ውስጥ ያለ ጥልቅ ባዶ ሽንቁር ሲረብሻት ነው፡፡የዛን ጊዜ ትናንቷን ታስታውሳለች፤የድሮ ፍቅሯ ትዝ ይላታል፡፡የዛን ጊዜ አባቴን ታስታውሳለች፤የዛን ጊዜ የሚያዳምጣትን ሰው ትፈልጋለች፤ለማዳመጥ ደግሞ በዚህ አለም ላይ ከእኔ ከልጇ በላይ ችሎታ ያለው ሰው የለም..ድንቅ የተባልኩ አድማጭ ነኝ የማንንም ንግግር አላቋርጥም ደግሞም ሚስጥር ጠባቂ ነኝ ..ማንም የፈለገውን ነገር ለእኔ ቢነግረኝ በቃ ለአምላኩ በሽኩሽኩታ እንደነገረው መቁጠር አለበት.ስለዚህ የቤታችን አባል መተንፈስ እና እፎይ ማለት ሲያስፈልጋቸው ወደ እኔ ነው የሚሮጡት..ይህ እናቴንም ያጠቃልላል፡፡
እና ይሄንን ከአባቴ ጋር የነበራትን የፍቅር ታሪክ ደጋግማ ስለነገረችኝ ልክ በእያንዳንዷ ግንኙነታቸው ወቅት አብሬያቸው የነበርኩ መስሎ ነው ሚሰማኝ …ሁሉ ነገር ልክ አሪፍ ደራሲ እንደደረሰው መሳጭ የፍቅር ድርሰት ፍንትው ብሎ ይታወሰኛል፡፡
የተገናኙት ሁለቱም የአዲስ አበባ የአንደኛ አመት ተማሪ እያሉ ነው፡፡እሱ የኬሚስትሪ እሷ የባይሎጂ ዲፓርትመንት ተማሪ ነበሩ …ያው ፍረሽ ማን ላይ ሁለቱም የሚወስዱት ተመሳሳይ አይነት ኮርስ ነበረ እና የገና ማዕበል ለማምለጥ ሁሉም ተማሪ በፍራቻ ተውጦ፤በስጋት እየተናጠ አንገቱን አቀርቅሮ በየዩኒቨርሲቲው ጥጋ ጥግ እና በላይብረሪው ከወረቀት ጋር እራሱን አጣብቆ ፍዳውን በሚያበት ወቅት ነበር..በተለይ መምህሩ አንብቡ ብሎ የጠቆማቸውን መጽሀፍና፤ሲኒየር ሚባሉት ተማሪዎች ለፈተና ያንን መጽሀፍ አንብቡት ብለው የጠቆሙትን መጽሀፍ ለማግኘት ላይብረሪ ውስጥ ያለው መራኮት እና መሻማት ያስቃልም .ያስተዛዝባልም፡፡ በተለይ የፈተናው ወቅት እየተቃረበ በመጣ ቁጥር ውጥረቶቹ በዛው ልክ እየከረሩ ይሄድ ነበር፡፡
በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ ሞጋስ ባሴ የተባለው ከጎንደር አርማጭኦ አካባቢ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ የመጣው ወጣት በዚህ መራኮት ውስጥ በመደነጋገርም ቢሆን መፋለም ጀምሮ የነበረው..ግን ሁሌ ተሸናፊ ነበር…፡፡ካደገበት ማህበረሰብ የወረሰው ይሉኝታ ለተሸናፊ እንዲዳረግ አመቻችቶታል፤ከመናጠቅ ይልቅ መካፈልን ነበር የሚያውቀው ጓደኛን ወደ ኃላ ስቦ በማስቀረት ወደ ፊት ከመሸምጠጥ ይልቅ አንተ ቅደም ወንድሜ ብሎ ከመንገድ ገለል ብሎ ሌላውን የማሰቀደም ስነ ልቦና ነበር የነበረው፡፡ንጽህ የዋህነት፤የጠራ ሰባዊነት የግል ንብረቶቹ ነበሩ…፡፡ግን አዲስ አበባ ሌላ ነው፡፡እርግጥ ከእሱ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ብዙ የክፍለሀገር ልጆች ነበሩ..ግን በተለይ በመጀመሪያው አመት የሚደምቁትና ፈካ ብለው የሚታዩት የትላልቅ ከተማ ውልዶቹ ናቸው፡፡አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ..በምዕራባዊውና በምሰራቃዊው ፍልስፍና መካከል የሚዋልል ከተሜን በውስጧ የያዘች መንጠቅ እንደብልጠት፣መቅደም እንደአራዳነት የሚታይባት የተለየች ቦታ ..እና አንድ መጽሀፍ ለማግኘት ለ5 ቀን የላይብረሪውን ደጅ ፀንቶ ነበር..አልቀናውም እንጂ..፡፡
‹‹አረ ወዲያ….›› እያለ ላይብረሪውን ለቆ በቅሬታ ሲወጣ ..ያንን የሰሙ ሌሎች እኩዬቹ ሲገለፍጡበት ለሶስት ቀን የታዘበችው እናቴ ታዝባ ቅር ብሎት ነበር…በአራተኛው ቀን ግን ከተቀመጠችበት ወንበር ላይ ሳትንቀሳቀስ በምልክት ጠራችው..እሷ ወደ ተቀመጠችበት መቀመጫ ግራ በተጋባ እይታ ተገትሮ ሲያማትር መልሳ በእጇ ምልክት ጠራችው…፡፡በንዴቱ ውስጥ ቢሆንም…ወደ እሷ ተጠጋ..ስሯ ደረሰ….
‹‹ተቀመጥ አለችው…››በሹክሹክታ
‹‹ምን ይሁነኝ ብዬ….?.››መለሰላት ከእሷ ትንሽ ከፍ ባለ ድምጽ ሌሎችን የላይብረሪ ተጠቃሚዎችን እንዳይረብሹ በመስጋት ግራና ቀኝ በመሳቀቅ ተመለከተችና‹‹ ቁጭ በል›› ብላ ልክ ከዚህ በፊት በደንብ እንደምታውቀው የቅርብ ጓደኛዋ እጁን በመያዝ ስባ አስቀመጠችውና‹‹ይሄን አይደል የፈለከው …እንካ አንብብ››ብላ ስታነበው የነበረውን መጻሀፍ ወደ እሱ ፊት አስጠጋችለት ….ማመን አልቻለም..አንዴ መፅሀፉን ..አንዴ ልጅቷን እያፈራረቀ ማየት ጀመረ
‹‹አጥና እንጂ… ለዚህ መጽሀፍ አይደል ሳምንቱን ሙሉ ስትበሰጭ የሰነበትከው…..?እኔ በቂ ቀን አግኝቼ ማየት ያለብኝን ያህል አይቼዋለው ዛሬ ደብተሬን ነው የማነበው…››
‹‹ታዲያ እማታነቢው ከሆነ ለምን ታቀፍሺው.? ››በብስጭት
‹‹ለአንተ ብዬ.››
‹‹አረገኝ…..?.›.›
‹‹ባክህ ታጠና እንደሆነ አጥና …ካልፈለግክ መጽሀፍን አምጣው..››ለራሷም ባልታወቃት ስሜትም በቁጣ መለሰችለት፡፡…. እንግዲህ የመጀመሪያ ትውውቃቸው እንዲህ ነበር የጀመረው፡፡
እርግጥ ሁለቱም ኢትዬጵያዊ ይሁኑ እንጂ በተለያየ አካባቢ እና ባህል ውስጥ ነው ያደጉት ፡፡ ቢሆንም ይሄ ልዩነታቸው ለግንኙነታቸው እንቅፋት አልሆነባቸውም..እናቴ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት በምትገኘው አዲስ አለም ከተማ ተወልዳ ያደገችና ሀይስኩል ስትደርስ ወደአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ገብታ ተምህርቷን የጨረሰች በመሆኗ ከተሜነት ሲያጠቃት አባቴ ግን ከአነስተኛ የገጠር ከተማ በመውጣቱ በተቃራኒ ስሜት ውስጥ ያለ ነበር..
ከዛን ቀን ወዲህ ለሁለተኛ ጌዜ የተገናኙት አንደኛ ሴሚስተር ፈተና ተጠናቆ የፈተና ውጤቱ ታውቆ ውጤቱም ቦርድ ላይ ተለጥፎ ተማሪ እየተተረማመሰ በሚያበት ጊዜ ሁለቱም ከትርምሱ ውስጥ የየራሳቸውን አይተው ሲወጡ እርስ በርስ በመላተማቸው ነበር…ዞር ብላ ስታየው ማንነቱ ትዝ ስላላት ‹‹…አንተ››አለቸ
‹‹አንቺው…አለሽ ኖሮል.? ››
‹‹ምነው ፈልገሀኝ ነበር እንዴ.?››ይሄንን የሚያወሩት ከተማሪዎቹ አጀቡ ተገንጥለው በመውጣት ብቻቸውን ጎን ለጎን እየተራመዱ ነበር
‹‹እሱማ አልፈለግኩሽም…በሀሳቤ ተሰንቅረሺብኝ እንጂ››
‹‹ምን ተሰንቅረሽብኝ..ማ.. እኔ .?››እናቴ በመገረም
‹‹እንደእሱም ማለቴ እማየደል.?››
‹‹እና እንዴት ማለት ነው.?››
‹‹በቃ ተይው…ለመሆኑ ፈተናይቱን እንዴት ሆንሽ…..?››
‹‹አሪፍ ነው...አንተስ….?››
‹‹እኔማ ጥሩ ነው.. እንዲሁ ባልፈራ ኖሮ የተሸለ አመጣ ነበር…ወይኔ ወንድ በሀገሬ መውዜር እና ምንሽር ቢደቀንብኝ ማልበረግግ ዠግና እዚ በወረቀት ተለቅልቆ ለሚመለስ የፈረንጄ ወሬ ልንቦቅቦቅ…...?››
ከዚህ ቡኃላ ግንኙነታቸው በጓደኝነት ይቀጥላል …ሁለተኛ አመት ግምሽ ድረስ ተመሳሳይ ይሆናል…አብረው ያጠናሉ…አብረው ከተማውን ይዞራሉ…ሚስጥር ይጋራሉ፡፡
ነገሮች የተቀየሩበት ቅጽበት አባቴ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሁለት አመት ሲማር ከዕውቀቱ ይልቅ አራዳነቱ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷ ነበር .ከንግግሩ ቀልጠፍ፤ከአለባበሱ ዘነጥ፤ካረማመዱ ጀነን ማለቱ ለሌላ ሰው አይደለም ለሱ ለራሱ ይታወቀው ነበር…አሁን ከየዋህነት ይልቅ ብልጠትን፤ከመበለጥ ይልቅ መሸወድን፤ከመግደርደር ይልቅ አይን አውጣነትን፤ተጎትቶ ከመቅረት ይልቅ ጎትቶ ማለፍን እለት ከእለት ከመደበኛ ትምህር እኩል እንደውም ከእዛም በላይ እየተለማመዳቸው የህይወቱ አንድ ክፍል አድርጎቸው አድርጓቸው ነበር የእኛ ስልጣኔ እንዲህ አይደል?እና እናቴንም በተመለከተ ሳይቀደም ሊቀድም ወሰነ በአንድ እለተ እሁድ የረፍት ቀን በወቅቱ ዝነኛ ወደ ነበረው እና ዘፋኞች ሁሉ የቪዲዬ ክሊፓቸወንን ወደሚያስቀሩጽበት ብሄረ-ጽጌ መናፈሻ ሳታስብ ወሰዳት
1.2K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 15:58:27 ♡ህይወትን የሚያስውቡ ውብ ሰዎች አሉ።
ሳትፅፍ ያነቡሀል።
ሳትናገር ይረዱሀል።
ውለታን ሳይሹ መልካም ይውሉልሀል።
በእነዚህ ሰዎች ውስጥ መኖር ህይወትህን ውብ ያደርገዋል።

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
#Share
@yefikrclinic
@Yefikrclinic
1.7K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 09:17:11 ​​ #ከላይ #የቀጠለ
እህቶቼን በተመለከተ በጣም የሚማርከኝ ነገር ቢኖር ጫወታቸው ነው፡፡እነሱ እቤት ውሥጥ ካሉ በቃ የእኛ ቤት ኮመዲያን የተሰባሰቡበት ኮንሰርት ነው የሚመስላችሁ…. ..እርስ በርስ ጫወታቸው፤መተራረባቸው፤ከእናቴ ጋር የሚያወሩት ወሬ….ሁለ ነገራቸው ድምቀት አለው፡፡እኚህ እህቶቼ ለማንኛውም ሰው እንደመልካቸው ሁሉ ፀባያቸውም አንድ ይመስለዋል ..ግን በጥልቀት ሲመረመር በጣም ይለያያሉ፡፡
ለምሳሌ ሮማን..እቤት ውስጥ ሮሚ ነው የሚሏት… ትምህርት በጣም ስትወድ ፌናን ደግሞ ቶሎ ብላ በዚህም በዛም ብላ ሀብታም መሆን ነው ፍላጎቷ… ሀብታም ለመሆን የመጀመሪያዋ ምርጫዋ ነጋዴ መሆን ነው....አሁን ጀመራዋለች ፡፡ያ ካልተሳካላት
........... ክፍል ሁለት (2) ይቀጥላል
@yefikrclinic
@yefikrclinic
707 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 09:15:58 ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥ ሀርሜኮ ̶̥✽̶┄┄
#አሳዛኝና_አስተማሪ
#ክፍል 1
​​​​​​​​​​​​​​​​​┄┄✽̶»̶̥ # ሀርሜኮ ̶̥✽̶┄┄
̶̥✽̶┄┄

አንድ ሰው በጣም እድለኛ ከሆነ እስከ ህይወቱ ፍፃሜ ሁለት ነገሮች ይኖሩታል፡፡እናት እና ሀገር፡፡በከፋን ቀን በእናት ጉያ መሸጎጥ ደስ ባለን ቀን በራስ ሀገር ሰማይ ስር መቦረቅ በብር ልንገዛው የማንችል ከመታደል የሚገኝ በረከት ነው፡፡ለዚህ ነው ለእናት ጤንነት እና ለሀግር ሰላም ሁሉም የሚጨነቀው፡፡እናትና ሀገርን ማጣት ማለት እኛነታችንን ማጣት ስለሆነ የእኛ ማንነት እና ሙሉ ታሪክ እናትና ሀገራችን ጉያ ውስጥ ስለሚገኝ….እኛ አስኳል ብንሆን እናትና ሀገራችን አስኳሉን ሸፍነውና ከልለው ከአደጋ የሚጠብቁት እና በህይወት የሚያቆዩት ከመንፈሳዊ ብልፅግና እና ከጥልቅ ፍቅር የተሰሩ ቅርፊቶቹ ናቸው..(ከለላዎች)፡፡ቅርፊቱ ከተሸነቆረ አስኳሉም የለ….አዎ እናት ስትሞት እና ሀገር ስትፈርስ በእቅፋቸው ውስጥ የነበረው ህይወት አብሮ ይከስማል፡፡ህልወና ያከትማል።
……. ቤታችን ሶስት መኝታ ክፍል ከአንድ ሳሎን ጋር ኩሽናንና መታጠቢያ ቤትን አጠቃሎ የያዘ መለሰተኛ ቢላ ቤት ነው፡፡እዚህ ውስጥ መኖር ከጀመርን 25 ዓመታትን አስቆጥረናል …. የቤቱ ኑዋሪዎች የመጀመሪያው መኝታ ቤት ሁለት እህቶቼ እና አንድ የእህቴ ልጅ ሌላው ክፍል ወንድሜ ለብቻው ሶስተኛው መኝታ ክፍል እኔ እና እናቴ እንተኛበታለን..በነገራችን ላይ ከእኔ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ማደር የሚችል አንድ ብቸኛ ሰው ብትኖር እናቴ ብቻ ነች..ምክንያቱም ያው እዛው አልጋዬ መሀከል ላይ ተቀዶ በተሰራልኝ ልዩ መፀዳጃ ስለምፀዳዳ፡፡ ምንም እንኳን እናቴ ተከታትላ ሳትሰለች በየቀበኑ ብታፀዳውም….ሰንደሉንም እጣኑንም ብታጫጭስበትም ጠረን ማምጣቱ አይቀርም…ስለዚህ ማንም እዛ ክፍል ከደቂቃዎች በላይ መቆየት አይችልም..ወንድሜና እህቶቼ እንኳን ስሬ ቁጭ ብለው የሚያወሩኝ እና የሚያጫውቱኝ ተፀዳድቼ መኝታ ቤቴን ለቅቄ ሳሎን በዊልቸሬ ላይ ወይም ሶፋ ላይ ተዘርሬ ሲያገኙኝ ብቻ ነው የሚያዩኝ..እናቴ ግን ይሄው 22 ዓመት ከጎኔ ተለይታኝ ተኝታ አታውቅም…ግን እንዴት አይሰለቻትም..?ለመሆኑ የእናትነት ፀጋ ማለት ከምን አይነት ጽናት ጋር ይሆን ሚሰጠው…?እኔ እንጃ… ይሄ ከእኔ የማሰብ አቅም በላይ ነው፡፡
ይቅርታ አንድ ተጨማሪ ሰው ዘንግቼያለው ባለፍት 5 ዓመታት አብራን የምትኖር ትርሲት የምትባል ሰራተኛ አለች፡፡
እስቲ ሰለቤተሰባችን አባል ዘርዘር ያለ መረጃ ልስጣችሁ… ..ከማን ልጀምር ከእናቴ ጀመርኩ…..?እናቴ ዕድሜዋ 49 ዓመት አካባቢ ይሆናል፡፡በ23 ዓመቷ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ድግሪ በባይሎጂ ተመርቃ ሃይስኩል ውስጥ ማስተማር ከጀመረች 26 ዓመት አልፎታል ፡፡ያው ከእኔ ዕድሜ 4 ዓመት በፊት ጀምሮ ማለት ነው ፡፡ብዙ ሙሁሮችንም ብዙ ብኩኖችንም ለዚህች ሀገር አበርክታለች፡፡
ይሄ እናቴ የምታስተምርበት ሀይስኩል ከቤታችን ከተንቀራፈፉ 5 ደቂቃ ከፈጠኑ ሁለት ደቂቃ ነው የሚርቀው፡፡ያ ማለት … እናቴ መኖሪያዋ እና የስራ ቦታዋ አንድ ቦታ እንደሆነ ማሰብ ትችላላችሁ፡፡እናቴ ይሄን ሁሉ አመት እንዴት አንድ ትምህርት ቤት አንድ አይነት ትምህርት ስታስተምር ኖረች..? እንዴት ትምህርቷን ሳትቀጥል..? እንዴት ስራ ሳትቀይር..?እንዴት ሳታገባ…? የእነዚህ ሁሉ መልስ ከእኔ ማንነት ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡
እናቴ አስተማሪ ሆና ትምህርት ቤቷ ውስጥ እና እናት ሆና ቤት ውስጥ ሁለት የተለያየች ሴት እንደሆነች ነው ሚሰማኝ….እናቴ ውብ ምትባል አይነት ሴት ነች፡፡ወደ ቀይነት ያደላ የሰውነት ቀለም ፤ ደርበብ እና ሞላ ያለ ሰውነት፤ ባለ ስልካካ አፍንጫ እና ቦግ ቦግ ያሉ አይኖች ያሏት ሜትር ከ79 የምትረዝም ዘለግ ያለች ሴት ነች፡፡
ስለፀባይዋ ልንገራችሁ… ልስልስ አመል ያላት ምትገርም ሴት ነች…ለማንም ሰው ቢሆን ሊጣሏት የምታስቸግር አይነት ሰው ነች፡የጋለውን ማብረድ፤የሞቀውን ማቀዝቀዝ፤የተወጠረውን ማስተንፈስ ትችልበታለች፡፡ነገሮችን በተረጋጋ እና ባልተዋከበ እርጋታ መከወን የተካነችበት ስጦታዋ ነው፡፡ያው የዚህ ታሪክ ዋና ምሰሶ እሷ ስለሆነች በየክፍሉ ስለእሷ ምነግራችሁ ብዙ ነገሮች ስለሚኖሩ ይበልጥ እያወቃችኃት እና እየወደዳችኃት ትመጣላችሁ፡፡ …ለአሁኑ ግን ወደሌሎቹ ልሂድ….፡፡ቆይ ስሟን አልነገራኮችሁም ለካ…መገርቱ ትባላለች፡፡
መሀሪ ታናሽ ወንድሜ ነው፡፡የዓለም ቁጥር አንድ ዝርክርክ እና ግድ የለሽ ሰው እሱ ይመስለኛል…ተራሮች ወደ ሸለቆነት ቢቀየሩ ፤ምድር እንደኖህ ዘመን በጥፋት ውሀ ብትጥለቀለቅ፤ፀሀይ በጠለቀችበት በዛው ቀርታ ይህቺ ምድር በጨለማ ብትዋጥ ለእሱ ደንታው አይደለም…፡፡ለዚህ ወንድሜ በህይወት ለመኖር ሶስት ነገሮች በቂው ናቸው… የሚያነበው መጽሀፍ ፤የሚቅመው ጫት እና የሚጎነጨው አረቄ…በቃ ፡፡ከዛ የተረፈው የዓለም ትርምስ ሁሉ ለእሱ ትርፍ ነው፡፡እቤት ሲገባና ሲወጣ እራሱ ማን አለ… ማን የለም.? ዞር ብሎም አያይም…፡፡ደህና ዋሉ ሳይል ይወጣል… ደህና ቆያችሁ ሳይል ይቀላቀላል…፡፡
ከእህቶቹ ጋር ቃላት እንኳን የሚለዋወጠው በወር ወይም በሁለት ወር አንድ ቀን ሊሆን ይችላል..ከእናቴ ጋር ግን የተሻለ ያወራል..ቢያንስ ማውራት ቢያስጠላው እንኳን ግንባሯን ስሞ ገብቶ ግንባሯን ስሞ መውጣቱ የማይዛነፍ ተግባሩ ነው፡፡ከእኔ ጋ ያለው ግንኙነት ግን የተለየ ነው፡፡እኔ ለወንድሜ ሚስጥረኛው ነኝ፡፡ሰው ሁሉ ከቤት ተጠራርጎ ወጥቶ ብቻችንን በምንሆንበት ሰአት የማያወራኝ ነገር የለም… ከግል ሚስጥሩ አንስቶ ስለጠቅላላ ሀገር አቀፍ ሆነ አለም አቀገፍ ወቅታዊ እወነቶች፡ ስላነበባቸው መጽሀፎች፡ ስለሰማቸው ዜናዎች.. ከኢንተርኔት ላይ ስላገኛቸውና ስላስደነቁት ተአምሮች ያለመሰልቸት ያወራኛል፡፡ በጽሞና አደምጠዋለው..፡፡
አንዳንዴም በእኔ ላይ ያለውን ቅሬታ...የህይወቱን አቅጣጫ እንዲህ ዝብርቅርቅ ያደረግኩት እኔ መሆኔን…በዚህም ምክንያት እንደሚበሳጭብኝ በምሬት ይነግረኛል..እኔም እሰማዋለው›..ምክንያቱም ወቀሳው እውነትነት እንዳለው እኔም አምናለው…፡፡
እንዲያም ሆኖ ግን ወንድሜ መሀሪ ባለሞያ ነው.. ጎበዝ የኮምፒተር ባለሞያ…በኮምፒተር ሳይንስ ዲፕሎማ አለው…ግን ከዛ በላይ የተፈጥሮ ስጦታው ይበልጣል…ተለምኖ፤ በስልክ ተጨቅጭቆ ነው የሚሰራው፡፡በቀን ውስጥ በጣም ሰራ ከተባለ ለሁለት ወይም ለሶስት ሰዓት ነው..ግን እንደዛም ሆኖ ተጠቅሞ ከሚጨርሰው ብር የበለጠ ገቢ ያገኛል ….
ቀጥሎ ወደእህቶቼ ልሂድላችሁ …እኚ እህቶቼ መንትዬች ናቸው…ለእኔ ታላቆቼ ናቸው፡፡ፌናን እና ሮማን ይባላሉ ፡፡ስማቸውን ለአንደኛዋ አባቴ ለሌለኛዋ ደግሞ እናቴ ነች ያወጣችላት፡፡አንደኛዋን ከአንደኛዋ በመልክ ለመለየት ለማንም ሰው ከባድ ፈተና ነው..እኔና እናቴ ግን በቀላሉ እንለያቸዋለን፡፡ሁለቱም ቀይ ቀጭን መካከለኛ ቁመት ከግብዴ መቀመጫ ጋር ያላቸው ቆንጆ እና ጎረምሳው ሁሉ ለሀጩን የሚያዝረከርክባቸው ቀሽት ሚባሉ ጉብሎች ናቸው፡፡
731 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 20:38:50
​​ሰላም ሰላም ስለጠፋሁ ሰሞኑን በጣም ይቅርታ ከዚህ ቡሀላ አለሁ ብዙ አስተማሪ ታሪኮች አዘጋጅተናል ​​​​​​​​​​​​​​​​​​እንሆ የእናንተን የማንበብ ፍላጎት እንዲጨምርለማድረግ እየሰራ የሚገኘው #የፍቅር ክሊኒክ እናንተን ያስተምራል ብለን ያዘጋጀነውን የልቤ #ሀርሜኮ የተሰኘውን ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ለማቅረብ ዝግጅታችንን የጨረስን መሆኑን እንገልፃለን። ከእናንተ የሚጠበቀው VOTE ማድረግ ብቻ ነው ይጀምራል።
@yefikrclinic
@yefikrclinic
@yefikrclinic
1.3K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ