Get Mystery Box with random crypto!

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikrclinic — ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikrclinic — ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️
የሰርጥ አድራሻ: @yefikrclinic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.93K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓
❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤
❤ HBD ለማለት፤ 🎂
❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀
❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂
🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን። @yefikrclinic_bot
contact us 👉 @yefikrclinic
ላይ ይላኩሉን

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-03-21 21:49:07
One day....
Join here
@yefikrclinic
664 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 18:21:45 ልጩህበት!

ክፍል- 19

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
ደርሰን እሱ ከፊት እኔ ከጀርባው ተከታትለን እንደገባን
"ያቿትና"
አለኝ ፊት ለፊት ካንድ ሰው ጋር የተቀመጠች ቆንጂዬ ሴት ተመለከትኩ ።
ወደሱ ስዞር አራት ጣቶቹን ከንፈሩ ላይ ጭኖ እንዳፈጠጠባቸው ትንሽ ቆየና
"ውይ ውርዴት !
አቤት ቅሌት !
እሄ እኮ ውጪ ሀገር የነበረ ያክስቷ ልጅ ነው የሰርጋችሁን ግማሽ ወጪ እኔ እችላችሃምሀለሁ ብሎ ቃል ገብቴልናል! በቅርብ ነው የመጣው።
ጓደኛዬም ያላወቀው ለዛ ነው!
እነደመጣ አዲስ አበባ ነበር ያረፈው ሰሞኑን ወደ ድሬ ይመጣል ስትለኝ ነበር እንደዛ ሲፎክር የነበረው ሰው ጭራሽ "ደብቀኝ እንዳታየኝ ! "
እያለ እኔን ጎትቶ ከጀርባዬ ተደበቀና
"ዝም ብለህ ወደ ኋላ ና እንውጣ!" አለኝ።
እየተጓተትን ወጣን።
እሺ አሁን ወዴት እንሂድ? ስለው•••
"ዛሬ በቃ ካንተ ጋር የመረጥከው ቦታ ስጠጣ አድሬ ጥዋት በዛው ወደሀረር መመለስ ነው
እምፈልገው ግን ፍቃደኛ ከሆንክ ነው ?"
አለኝ እኔም በኤዱ ተከፍቼ ስለነበር መጠጣት ፈለኩ በሀሳቡ ተስማማሁና ተያይዘን ሄድን እየጠጣን ስለራሱ ብዙ እያወራልኝ ቆየና ድንገት በመሀል •••
"ቅድም ከልጁ ጋር ያየሀት ልጅ ግን እውነት ያክስትህ ልጅ ነች እንዳትዎሸኝ በናትህ እ ያክስትህ ልጅ ነች?"
ለምን ጠየከኝ ? አልኩት
"እኔ እንጃ የሆነ የፍቅር ስሜት አይንህ ውስጥ ያነበብኩ መስሎኝ ነው እ ተሳሳትኩ?!"
ኧረ በጭራሽ የፍቅር ስሜት እኔ ላይ ልታነብማ አትችልም ግን ያክስቴ ልጅ አይደለችም ብዬ ስለኤዱ በስሱ ነገርኩት ጎህ ሲቀድ ትዝ ይለኛል ግን ብዙ ከመጠጣቴ የተነሳ መች? እና እንዴት? እሱ ወደ ሀረር እኔም ወደ ቤት እንደገባሁ ትዝ አይለኝም።
በነጋታው ስድስት ሰአት አከባቢ ተነሳሁና ገላዬን ተጣጥቤ ወደ ስራ ወጣሁ።
በአከባቢያችን ባለ አንድ ምግብ ቤት ገብቼ ምሳ አዘዝኩና ከመምጣቱ በፊት ኤደንጋ ደወልኩ።
አነሳችችው ድምፁዋ ስትጨፍር ማደሯን ይመሰክራል ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ•••
የት ነሽ?
"ዶርም ነኝ ጋደም ብዬ !
ትናንት ታክሲ አገኛችሁ?
አዎ ዳንዬ ካንተ ጋር እንደወጣን ወድያው ነው ያገኘነው;"
በግዜ ገባችሁ?
አዎ ምነው?
አይ ምንም ከአንደበትሽ ልስማው ብዬ ነው!
ምኑን ዳኒ?
በቃ ተይው!
ምን ሆነሀል ዳኒ!?
ምን ሆንኩ?!
"አይ ምን እንደጠየከኝ እንኳን ሳይገባኝ በቃ ተይው ስትለኝ ግራ ገብቶኝ ነው"
በቃ እንደውም እንኳን ያልገባሽ ወሬ እንቀይር••
እሺ ካልክ!
እሺ!
"እሺ ምን!"
እሺ ምንም!
እንዴ ዳኒ ግራ አጋባከኝ እኮ ወሬ እንቀይር አላልክም እሺ ስለ ምን እናውራ?"
ምን አዲስ ነገር አለ?
"ምንም ዳኒዬ ምን አዲስ ነገር ይኖራል ብለህ ነው"
በቃ እሺ
በቃ እሺ ምን?
በቃ እሺ ቻዋ አዲስ ነገር ከሌለ!
"እሺ ቻው ግን•••" እያለች ስልኩን ዘጋሁት።
ስራው አስጠላኝ ባጃጄን ላጣቢ ሰጥቼ ገብቼ ተኛሁ።
ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ጆሲ እና ያ ጅምር እብድ ጓደኛው በርጫቸውን ይዘው እየተሳሳቁ ሲገቡ በሆዴ ተደፍቼ በመተኛት የተኛ ሰው መሰልኩ።
ጆሲ••••" እንዴ ዳኒ ስራ ወጥተህ አልነበር እንዴ በል ተነስ አትደብረን •••" ምናምን እያለ ሊቀሰቅሰኝ ቢሞክርም አውቆ የተኛን እንዲሉ ዝም አልኩ።
ከቆይታ ቡሀላ ከነመኖሬም ረስተውኝ ጆሲ እና ጓደኛው በራሳቸው አለም ውስጥ ገብተው የባጥ የቋጡን መዘባረቅ ጀመሩ።
የተኛሁ መስዬ ብተኛም ወሬያቸው እረፍት ነሳኝ ከአንዱ ርእስ ወደ ሌላ ለመሄድ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ አይጠብቁም ወሬያቸውን ይጀምሩታል እንጂ አያልቅም።
ብስጭትጭት ብዬ በመነሳት ቤቱን ጥየላቸው ስወጣ ጆሲ•••
"ና እንጂ ዳንዬ! ወዴት ልትሄድ ነው? ረበሽንህ እንዴ! ማታ ሰክረህ ምን ስትል እንደነበር ልንገርህ ክክክክ !"
መልስ ሳልሰጠው ወጥቼ ሄድኩ።
ከዛን ቀን ቡሀላ ህይወቴ እራሱ የሰከረ ሆኖ ታየኝ ከኤዱ ጋር እንኳን ልንገናኝ ስልክ ተደዋውለን ሰላም ሰላም ከመባባል ውጪ የረባ ነገር ሳናወራ ወራቶች ተቆጠሩ የሷን ባላውቅም እኔ ግን ከራሴ ጋር ስለሷ ሳላወራ አድሬ አላውቅም ።
ጥፋተኛዋ እሷ ሆና ሳለ ስለመገናኘት አንስታብኝ ስለማታውቅ እልህ ያዘኝ ።አንድም ቀን ላግኝሽ ሳልላት አልፎ አልፎ በስልክ ድምጿን ብቻ እየሰማሁ ብቆይም ጤነኛ አለነበርኩም።
ለካ ከፍቅር ጋር እንደመጣላት ከባድ በሽታ የለም ቆይ በአለም ላይ ከፍቅር ጋር ተጣልቶ ያሸነፈ ጀግና አለመኖሩን እያወቁ ፀብ መግጠም ምን ይሉታል እኔ ማነኝ እናነው እንኳን ተራው እኔ ክርስቶስም የተረታው ለፍቅር አይደል እንዴ?! ምን እሚሉት ነው እሄ ትንቅንቅ ! እውነታውን ብረዳም ብቻየን መታመም ብቻ ሆነ ስራዬ ያለሁበትን ሁኔታ እንኳን ለሷ ለጓደኛዬ ለጆሲም አልነገርኩትም ።
ሁኔታዬን ተረድቶ ሲጠይቀኝም መልሴ ቀና አልነበረም በብስጭት እጬህበታለሁ።
"ማፍቀር እኮ መታደል ነው ዳንዬ አፍቅረሀታል በቃ ለምን አታምንም?!" ሲለኝ
ቁስሉን እንደነኩበት አንበሳ ቁጣዬ ገንፍሎ እጮሀለሁ እሱም ድርቅ ያለ ደረቅ አደል ይስቅና •••
"ጩኸትህ መሸነፍህን በደንብ በፍቅሯ መንበርከክህን ያረጋግጥልኛል እንጂ ሀሳቤን አያስቀይረኝም ይልቅ ብናወራ ይሻላል በጩኸት ዝም ልታስብለኝ አትሞክር!
ጓደኛዬ አንተኮ መፍታት ያቃተህ እራስህ ያሰርከውን ገመድ ነው አውቃለሁ እራስህ ያሰርከውን ገመድ መፍታት አለመቻል እጅግ ያበሳጫል ነገር ግን እየተበሳጨህ አልፈታ ያለህን ቋጠሮ ጎትተህ ልትበጥሰው በሞከርክ ቁጥር ጭራሽ እያጠበከው እንደምትሄድ እወቀው!!
በቃ ልትበጥሰው ልታስቀረው አለመቻልህን እመን ያኔ ቢያንስ ላትበጥሰው እየጎተትክ ከማጥበቅ ትቆጠብ ይሆናል!
ለማንም ሳትናገር ብቻህን በተብሰከሰክ ቁጥር መጨረሻህ ማበድ ይሆናል እሺ እሄን እወቀው ብሎኝ ካጠገቤ ይሄዳል!
ቤቱን ብቻውን አገኘዋለሀ!
ያኔ "" ኤዱን በናትሽ አንዴ ብቻ ልጩህ!?" ያላት ሰካራም ፊቴ ድቅን ይላል በሩን እዘጋና ልክ እንደሱ እጬሀለሁ !
በዚህ ሁኔታ ብዙ ታገልኩ ዛሬ ግን አልቻልኩም!
ለሊቱን ሙሉ በህልሜ ሳያት ስላደርኩ ነው መሰለኝ ናፍቆቴ ልኩን አለፈ ባላገኛት እንኳን ወደዛ አጥር ወደለለው ዩንቨርስቲያቸው ሄጄ ከሩቁ አይቻት ልመለስ ሄድኩ።
ደርሼ አምስት ደቂቃ ያክል እንኳን ሳልቆም ከሩቅ ኤዱን አየኋት !
ግን ብቻዋን አልነበረችም ከልጁ ጋር ነች ውስጤ ሲፈነቃቀል ታወቀኝ እዛው በቆምኩበት
ጩህ ጩህ ስሟን ከፍ አድርገህ ጥራት ጥራት አለኝ•••

ይቀጥላል....
@yefikrclinic
@Yefikrclinic
1.0K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 18:09:08 የኔ ሙሽራ አፈቅርሻለሁ
    
@Yefikrclinic
1.9K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, edited  15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 20:48:14 ልጩህበት!

ክፍል- 18

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
ስላቆየንባቹ በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን
.
.
ኧረ በናትህ ተወኝና ዝም ብለህ ንዳ አንተ ደሞ
ነው ወይስ አብሯት ያለው ሰውዬ አጎትህ ነው ብዙ ተከራከርክላት እኮ !"
ሲለኝ እውነትም ዝም ብዬ ብነዳስ አልኩና ዝም አልኩ ።
እንደደረስን ምንም ሳይለኝ ወርዶ ወደ ሆቴሉ ሲገባ ተከትየው ገባሁ።
በር ላይ ቆም ሲል ቆምኩ።
ወደውስጥ ገልመጥ ገልመጥ አደረገና ካጠገቤ ድንገት ተፈናጥሮ በመሄድ ቀዝቀዝ ባለው ዘፈን ጥንድ ጥንድ ሆነው ተጣብቀው ከሚወዘወዙት መሀል•••
በስተግራዋ እስከ ባቷ መገባደጃ የተቀደደ ትከሻውን በዞሩ ሁለት ቀጫጭን ገመዶች ተንጠልጥሎ ከደረቷ ጀምሮ ቁልቁል ገላዋ ላይ ቀዳዋ እስኪመስል የተጣበቀ እሮዝ ቀለም ያለው የራት ልብስ ለብሷ አብሯት እሚደንሰው ሰው አንገት ውስጥ በፍቅር መርከብ እየተንሳፈፈች የምትደንሰውን ሴት ክንዷን ይዞ በመጎተት ከሰውየው እቅፍ ውስጥ መንጭቆ አወጣት!
እሷ ምን መጣ ብላ በድንጋጤ ስትዞር፤ እሱ ፊቷን አይቶ የሱ ፍቅር አለመሆኗን ሲረዳና አብሯት ያለው ሰው ይቅርታ የምትለውን ቃል ከፉ አውጥቶ እስኪጨርሳት እንኳን ግዜ ሳይሰጠው ተደፈርኩ በሚል ስሜት እንደነብር ተወርውሮ አንገቱን ሲያንቀው ዘልዬ መሀላቸው ገባሁ!
ይቅርታ አርግለት ባባ በስተት ነው በስተት ነው ስለው መጀመሪያውኑ ፊቷን እንዳየ ሲደነግጥ አስተውሎት ነበር መሰለኝ ከማነቅ ውጪ ቦክስ እንኳን ሳይሰነዝር•••
"እብድህን ወደዛ ይዘህልን ውጣ ባክህ ! ብሎ እሱን ገፈተረውና ሽምቅቅ ብላ ወደቆመችው ፍቅሩ ዞሮ •••
" አስደነገጠሽ አይደል የኔ ማር?!" አላት። እኛም በፍጥነት ተያይዘን ውልቅ አልን።
ባጃጅ ውስጥ ገብተን ወደሶስተኛው ቤት ጉዞ እንደጀመርን ድንጋጤው ለቀቀው መሰለኝ•••
"አይገርምም የሰይጣን ስራ ቁመቷ፣ ከለሯ፣ ፀጉራ ከነ አያያዟ እራሷን ቁጭ እኮ ነች በዛላይ የለበሰችው ልብስ ተውሳት ነው እንዴ እውነቴን ነው ሀሉንም ነገር ከፍቅረኛዬ የተዋሰችው እኮ ነው እምትመስለው ቢያንስ እንኳን በውፍረት መለያየት የለባቸውም ደባዋ እራሱ ቁጭ የኔዋን!" ሲል
ሳቄን በጭራሽ መቆጣጠር አልቻልኩም ኪኪኪኪኪ•••
"ሳቅ አንተ ምን አለብህ!"
እና በዛች ሰከንድ ውስጥ እሄን ሁሉ ደባዋን (ቂጧን ) ሳይቀር ማየትህ ቢያስቀኝ በኔ ይፈረዳል?
"ኧረ አይፈረድም"
እሄኔ ልጅቷ ከፍቅረኛህ ጋር በብዙ ነገሯ ትለያይ ይሆናል አንዳንዴ ውስጣችን የሚፈልገውን ነው አይናችን የሚያየው ለዛ ይሆናል።
አልኩትና በሆዴ ዛሬማ የከተሟዋ ሴቶች ሁሉ እሷን መስለው ነው እሚታዩህ ብዬ አከልኩበት።
ሶስተኛው ቤት ገባን እዛም አልነበረችም።
አሁን የቀረን አንድ ቦታ ብቻ ነው ወደዛው መብረር ጀመርን።
ልንደርስ ትንሽ ሲቀረን መንገድ ላይ ወዳለ ወደ አንድ ከፍንዳታዎችና ከዩንቨርስቲ ተማሪዎች ውጪ ሌላ ሰው ወደማይገባበት ቀውጢ ጭፈራ ቤት እየተገላመጥኩ መቸስ እዚህ አትኖርም አደል ስለው•••
ድንገት በሩ ላይ ኤዱን አየኋት ሊያውም ከዛ ልጅ ጋር!
በፍጥነት እየነዳ ድንገት ሰው እንደገባበት ሹፌር ልቤ ስንጥቅ ሲል ፍሬኑን ጭምቅ አደረኩት ባጃጇ ሲጢጢጢጢጢጢ ብላ ቀጥ ስትል ሰውየው ተፈናጥሮ ወደ ትከሻዬ መጣና ሳይመለስ •••
"ምነው! ሰው ገባብህ? ውሻ ገባብህ?" እያለ ወደ ፊት በማንጋጠጥ ምን እንደገባብኝ ለማየት ሲሞክር •••
ሰው አይቼ ነው።አልኩት።
"ማንን? አየሀት? እሷን ነው? የቱጋ? የታለች?" ሲል •••
ማነች እሷ አልኩት ግራ ተጋብቼ
" የኔዋ ነቻ! የኔዋ ጉድ ሌላ ማንን ታያለህ!"
ወይ ጉድ••••
"የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ብለው ከሚተርቱ የጨነቀው የሚናገረውን አያውቀው ቢሉ ኖሮ ሳይሻል አይቀርም እስቲ አሁን የሱን ፍቅረኛ የት አውቂያት ነው የማያት ?
እንኳን ለኔ ለራሱም ሳትጠፋበት አትቀርም እያልኩ ውስጥ ጫጫታው ስላልተመቻቸው ሳይሆን አይቀርም ስልክ ለማናገር ወጥተው አንድ ስልክ እየተቀባበሉ በጋራ ከሚያውቁት ከሌላ ሰው ጋር እያወሩና እርስ በርስ እየተያዩ ወደ ሚሳሳቁት ወደ እነ ኤደን ከርቀት እንዳፈጠጥኩ •••
ወርደህ ቀጥ ብለህ ሂድላት ከዛ ኤዱ ቅድም ከቤት ስትወጡ ወደ ግቢ ነው እምንሄደው ብለሽ መዋሸቱ ለምን አስፈለገ እኔን ዋሽኝ ችግር የለውም ግን በዚህ ሰአት ሊያውም እዚህ በየቀኑ ፀብ በማያጣው ጭፈራ ቤት ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ በላት በላት የሚል ስሜት ተሰማኝ።
ዘወር ብዬ ሰውየውን ሳየው እሱም ግራ ተጋብቶ እኔን ተከትሎ እነ ኤዱ ላይ አፍጥጧል።
መለስ አለና " ማነች? ታውቃታለህ? " አለኝ
ማነች ልበለው? አዎ ያክስቴ ልጅ ነች፤ የዩንቨርስቲ ተማሪ ነች በዚህ ሰአት ከወንድ ጋር ጭፈራ ቤት••••
አላስጨረሰኝም •••
"ታድያ ምን ችግር አለው አለው አብረው ተዝናንተው የሚለያዩ ንፁህ ጋደኛሞች ሊሆኑ ይችላሉ ። አለኝ በስላቅ ።
በንዴት •••
አዎ ችግር የለውም ይዝናኑ እኛም እንሂድ አልኩና ባጃጇን አስነስቼ ወደ መጨረሻው ቤት ጋለብኳት።
ደርሰን እሱ ከፊት እኔ ከጀርባው ተከታትለን እንደገባን
"ያቿትና"
አለኝ ፊት ለፊት ካንድ ሰው ጋር የተቀመጠች ቆንጂዬ ሴት ተመለከትኩ ።
ወደሱ ስዞር አራት ጣቶቹን ከንፈሩ ላይ ጭኖ እንዳፈጠጠባቸው ትንሽ ቆየና
"ውይ ውርዴት !
አቤት ቅሌት !
እሄ እኮ ውጪ ሀገር የነበረ ያክስቷ ልጅ ነው የሰርጋችሁን ግማሽ ወጪ እኔ እችላችሃምሀለሁ ብሎ ቃል ገብቴልናል! በቅርብ ነው የመጣው።
ጓደኛዬም ያላወቀው ለዛ ነው!
እነደመጣ አዲስ አበባ ነበር ያረፈው ሰሞኑን ወደ ድሬ ይመጣል ስትለኝ ነበር እንደዛ ሲፎክር የነበረው ሰው ጭራሽ "ደብቀኝ እንዳታየኝ ! "
እያለ እኔን ጎትቶ ከጀርባዬ ተደበቀና
"ዝም ብለህ ወደ ኋላ ና እንውጣ!" አለኝ።
•••

ይቀጥላል...
@yefikrclinic
@yefikrclinic
2.4K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 11:27:34 ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ እንኳንም በግዜ አወኩሽ መልካሙን ሁሉ እመኝልሻለህ!" ብለህ ብቻ ብትለያት
"ምንምንምምን !? "ያልተነካ ግልግል ያውቃል" አሉ ደሞ መች በግዜ አወኳት ከዛ በፊት ያንከራተተችኝን ተወው እሺ ብላኝ አብረን ከሆንን እንኳን አንድ አመት ከስድስ ወር ሆኖናል እኮ!"
ቢሆንም ገና አልተጋባችሁም ብዬ ነዋ!
"እና ባንጋባስ?!"
ማለቴ እንደምታገባት እርግጠኛ ካልሆነች•••
አልኩና መናደዱን ከድምፁ በመረዳቴ ያሰብኩትን ሳልጨርሰው ዝም አልኩ•••
"ካልሁነች ምን?! ጨርሰዋ !
ኧረ በናትህ ተወኝና ዝም ብለህ ንዳ አንተ ደሞ
ነው ወይስ አብሯት ያለው ሰውዬ አጎትህ ነው ብዙ ተከራከርክላት እኮ !"
ሲለኝ እውነትም ዝም ብዬ ብነዳስ አልኩና ዝም አልኩ ።
እንደደረስን ምንም ሳይለኝ ወርዶ ወደ ሆቴሉ ሲገባ ተከትየው ገባሁ።
በር ላይ ቆም ሲል ቆምኩ።
ወደውስጥ ገልመጥ ገልመጥ አደረገና ካጠገቤ ድንገት ተፈናጥሮ በመሄድ ቀዝቀዝ ባለው ዘፈን, ጥንድ ጥንድ ሆነው ተጣብቀው ከሚወዘወዙት መሀል•••
•••

ይቀጥላል....

@yefikrclinic
@yefikrclinic
@yefikrclinic
782 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 11:27:34 ልጩህበት!

ክፍል- 17

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
ምን ሊፈጠር እንደሚችል ሳስበው ጨነቀኝ ።
ከሰው ጋር ታየች የተባለበት ሆቴል በር ላይ እንደደረስን በፍጥነት በመውረድ እጁን እያወናጨፈ ወደ ሆቴሉ ቅጥር ግቢ ሲግሰግስ ወርጄ ተከተልኩት•••
ወደ ውስጥ ስንዘልቅ ያን ያህልም ሰው ስላልነበረ አየት አየት አድርጎ እየወጣን•••
"የለችም ባክህ••• እዚህ መጥታ ጭር ሲል ደብሯት ቦታ እንቀይር ብላው ይሆናል አውቃታለሁ እኮ ልትዝናና ስትወጣ ግርግር ትወዳለች ሰው ከማን ጋር እንደሆነች እንዳያስተውላት ነው መሰለኝ ከኔም ጋር ስትዝናና ቦታው በሰዎች ጢም ካላለ አይመቻትም!
ወይኔ ደጉ ያኔ መች ገባኝ !
አሁን አሁን እኮ ነው ቀስ እያለ ነገረ ስራዋ በሙሉ የሚገለጥልኝ •••
የባጥ የቋጡን እየለፈለፈ ተመልሰን ባጃጇ ውስጥ እንደገባን •••
"ንዳው! ንዳው! አለኝ።
ወዴት ልንዳው? ስለው•••
"ከሶስቱ ውጪ አትሆንም!" አለና •••
ትኖራለች ብሎ የሚጠረጥርባቸውን ሶስት ጭፈራ እና ሆቴል ቤቶች ነግሮኝ•••
"ከሚቀርብህ ጀምር" አለኝ።
በቅርብ ወዳለው አዙሬ መንዳት እንደጀመርኩ ፍቅረኛውን ከሌላ ሰው ጋር ስትቀብጥ ያያት ጓደኛው ሲደውልለት ከምሽቱ ሁለት ሰአት ተኩል አልፎ እንደነበርና በብስጭት ከሀረር ብቻውን አንድ ሚኒባስ በመያዝ የሙሉ ሰው ከፍሎ እንደመጣ ነገረኝ።
አሳዘነኝ።
ምናልባት የእውነት ሆኖ ከሆነ የሆነው ሆነ የኔ ስጋት ግን በሷ መከዳቱ ሳያንስ በብስጭት ያልሆነ ፀብ ውስጥ ገብቶ መታሰር የሚሉት ሌላ ጣጣ ውስጥ እንዳይገባ ነው።
ቢረጋጋ ጥሩ ነበር ምን ብዬ ላረጋጋው ? ትንሽ አሰብ አደረኩና•••
ቆይ ብታገኛት••• ማለቴ እንደተባለው ከሰው ጋር ሆና ብታገኛት ምን ልታደርግ ነው?
"እኔ እንጃ ብቻ ላግኛት ያኔ የሚሆነው ይሆናል በናትህ ራቅ ስለሚል ፍጠን!
በበኩሌ ከወንድ ልጅ ጋር ተዝናናች ማለት ወሰለተች ማለት ነው ብዬ አላምንም!
ተዝናንታ ክብሯን ጠብቃ ወደ ቤቷ ልትመለስ አስባ ሊሆን እንደሚችልም ማሰቡ ጥሩ ነው ያንን ካሰብክ ቡሀላ የሚፀፅትህን ነገር ከማድረግ ትቆጠብና ቅድሚያ ቢያንስ እርግጠኛ ለመሆን ትሞክራለህ አይመስልህም ስለው•••
አይመስለኝም በጭራሽ አይመስለኝም እኔ የፍቅር ሂወቴን በመሰለኝ ሳይሆን ልቤ በሚለኝ በራሴ እምነት ነው የምመራው
በኔ እምነት ሴት ልጅ አንሶላ የተጋፈፈች ቀን ሳይሆን ወንዶችን ቀለል ብላ የመቅረብ ባህሪ ያላት መሆኑን ያወኩ ቀን ነው እምነቷንና እምነቴን የምታጎድለው!"
ማለት?•••
ቀለል ብላ የመቅረብ ስትል ጭራሽ የወንድ ዘር መቅረብ የለባትም እያልከኝ እንዳይሆን?! ስለው•••
"አንድ ነገር ልጠይቅህ ?" አለ ።
ጠይቀኝ•••
"ለግዜው የማይፈልገው ገንዘብ እንዳለው ማበደር እንደሚችል እያወክ 300 ብር አበድረኝ ስትለው የለኝም ብሎ የከለከለህን ሰው በሌላ ግዜ አንድ ሺ ብር አበድረኝ ብለህ ትጠይቀዋለህ?
ካላበድኩ በስተቀር እንኳን ሺ አንድ ብርም አልጠይቀውም ግን እሄ ከፍቅር ወይም ካነሳነው ጉዳይ ጋር ምን አገናኘው?
"ሌላ ጥያቄ ልድገምህ ያኔ በምን መልኩ እንደሚገናኝ ሳልነግርህ እራስህ ትረዳዋለህ"
እሺ ቀጥል•••
"ታክሲ ውስጥ ባጋጣሚ አጠገብህ የተቀመጠችውን ሴት ልታዋራት ልታጫውታት ስትሞክር ፊቷን እንዳኮማተረች ወደ አንተ አንድም ግዜ እንኳን ዞራ ሳታይ ልክ እንደሹፌሩ ፊት ለፊቷን ብቻ እየተመለከተች ጫወታህን ባጭር ባጭሩ ዝግት የሚያደርግ መልስ እየመለሰች ብታከሽፍብህ ከመለያየታችሁ በፊት ስልክ ቁጥሯን ለመጠየቅ ትደፍራለህ?"
ሰውየው ነገሮችን ቤት በኩል እያገናኛቸው እንደሆነ እያሰላሰልኩ መልስ ሳልሰጠው ስለ ዘገየሁ•••
"መልስልኛ! ትጠይቃታለህ?!
እንዴ ፊቷን አጨማዳው እንዴት ልጠይቃት እችላለሁ አልጠይቃትም መጀመሪያ ልግባባት ስሞክር ፊት ከነሳችኝ ከታክሲው እስክወርድ ዞሬም ሳላያት እንደምሄድ እርግጠኛ ነኝ።
" አየህ መጀመሪያ ቀለል ብላ አንተ የባጥ የቆጡን ስትቀባጥር ከገለፈጠችልህ ግን ስልክ ለመጠየቅ ቀለለህ ማለት ነው!
ስልክ ስጠይቅ በቀላሉ ከተሰጠህ ደግሞ ደውሎ እንገናኝ ልጋብዝሽ ለማለት ቀለለህ••
ግብዣህን በቀላሉ ከተቀበለች ወደ ቀጣዩ ጉዳይህ ለመግባት አልጋ ባልጋ ሆነልህ ማለት ነው ስለዚህ እቺ ሴት የኔዋ ብትሆን እምነቷን የሸረሸረችው መቼ ነው? ብዬ እራሴን ብጠይቅ
በኔ እምነት አልጋ ውስጥ ሳይሆን ታክሲ ውስጥ የተገናኛችሁ ቀን ነው ያን ቀን እኔ ባጋጣሚ እሷ ሳታየኝ ከጀርባችሁ ቁጭ ብዬ ቢሆን መጨረሻችሁን አልጠብቅም እንደከዳችኝ የምቆጥረው ያኔውኑ ነው!"
ሲለኝ የእውነት ነበርና አመለካከቱ ያስደነገጠኝ•••
በዚህ ሀሳብህ በፍፁም አልስማማም እስቲ አንተንም አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ አንዳንድ ሴቶች
ፍቅረኛም ባልም ሳይኖራቸው ፣ ያሉበት ሁኔታ ፍቅር ለመጀመር ፈቅዶላቸው፣ ውስጣቸውም ፍቅር ለመጀመር ፍላጎት እያለው
በዛ ላይ ሽቅርቅር ብለው እየወጡ በተለያየ አጋጣሚ ከወንዶች ጋር በተገናኙ ቁጥር ወንዶቹ ሊቀርቧቸው ሲሞክሩ ኮሶ የጋቷቸው ይመስል
ፊታቸውን ከስክሰው የወንዶችን ቆሌ የሚገፉት በምን ምክንያት ነው?ስለው•••
"አይነጥላ ነው አዎ አይነ ጥላ ያለባት ሴት ካልሆነች በስተቀር በዚህ ሁኔታ ላይ ሆና በጤናዋ እንደዚህ የምትሆን ሴት ብዙ የምትኖር አይመስለኝም! ብሎኝ አረፈው። ሳይታወቀኝ እየጮህኩ•••
አትሳሳት ይልቅ •••
የተግባባች ፣ የሳቀች፣ ወንዶችን በቀላሉ የቀረበች ሴት ሁሉ ሌላ ፍላጎት አላት የተኮሳተረች ሴት ሁሉ ደግሞ ፍላጎት ስለለላት ነው ብለህ መደምደም ትልቅ ስተት መሆኑንን ብታምን የተሻለ ይመስለኛል!
አንተ ምናልባት ከፍቅረኛህ ውጪ ልክ እንደወንዶች ጓደኛችህ በጓደኝነት የምትቀርባቸው ሴቶች ከለሉ አላቅም!
እኔም ወንድሜቼም ጋደኞቼም በዚህ መልኩ የምንቀርባቸው ሴቶች አሉ አንዳንድ ሴቶች እንደውም ሁሉም ወይም አብዛኛቹ የቅርብ ጋደኛቻቸው ወንዶች እንዲሆኑ እንደሚፈልጉና እንደሆኑም የሚናገሩ አሉ ።
በጋደኝነት ህይወታቸው ወጣ ብሎ ከመዝናናት አንስቶ ብዙ ነገሪችን በጋራ ያሳልፋሉ ያ ማለት በተገኘው አጋጣሚ በሙሉ ሌላ ጉዳይ ውስጥ ይገባሉ ማለት አይደለም!።
"እሱማ ፍቅረኛ ወይም ባል ሳይኖራቸው ሊሆን ይችላል"
ኧረ እያላችው ! እሄውልህ ማናችንም ብንሆን የምንፈልገውን ነገር ለማድረግ የሚከለክለን የፍቅር ጓደኛ መኖር ወይም አለመኖሩ ሳይሆን የውስጣችን ስብእናና የልባችን ትርታ ብቻ ነው
ምንም ነገር ለማድረግ መቀራረብ ሳይሆን መተዋወቅ በማያስፈልግበት በዚህ ዘመን ፍቅረኛህን ታሟኝ የምታደርገው ወንድ አትቅረቢ እያልክ በመጮህ ሳይሆን እራስህን ልቧ ውስጥ ማስቀመጥ ከቻልክ ብቻ ነው ያለበለዚያ ፍቅረኛ ሳይሆን እረኛ ሆነህ ትቀራለህ"! አንተን ለማለት ፈልጌ አይደለም ይቅርታ አመለካከቴን ነው ያወራሁት አልኩትና በዛው ቀጠል አድርጌ•••
ወደ ሆቴሉ እየደረስን ነው ይልቅ አሁን ወደ ጉዳያችን እንመለስና እንደታናሽ ወንድም እምመክርህ ምናልባት ከሰው ጋር ሆና ብታገኛት በኔ በኩል ኩሩና በሳል ወንድ ሆነህ ብታሳያት ደስ ይለኛል!
"ማለት?!"
የተባለው እውነት ሆኖ ከተገኘ በቃ አለ አይደል ምንም ሳትናደድ
820 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 08:42:33 ትንሽ ቆየና •••
"የገዛ ጓደኛዬ አይቷት አይቷት እኮ ነው የደወለልኝ በአይነ ብረቱ ነው ያያት ወይኔ ደጉ ደግነቴን የዋህነቴን አይታ ነው የተጫወተችብኝ እነሱ እኮ ደግ ወንድ አይወዱም ዛሬ እጅ ከፍንጅ ስይዛት ምን እንደሚውጣት አያለሁ አጠገባ ያለውን ሰውዬ ትውጠው እንደሆነ እንተያያለን !"አለ።
ሁሉም ነገር ገባኝ። ፍቅረኛውን ከሰው ጋር ያያት ጋደኛው ደውሎለት እንደመጣ ተረዳሁ። በዚህ ሁኔታው ቢያገኛት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ሳስበው ጨነቀኝ ።
ከሰው ጋር ታየች የተባለበት ሆቴል በር ላይ እንደደረስን በፍጥነት በመውረድ እጁን እያወናጨፈ ወደ ሆቴሉ ቅጥር ግቢ ሲግሰግስ ወርጄ ተከተልኩት
•••••••••••••••••

ይቀጥላል....
@yefikrclinic
@yefikrclinic
318 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 08:42:33 ልጩህበት!

ክፍል- 16

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
ስላቆየንባቹ በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን
.
.
መናደድ ጀመርኩ። ልጁ እኔ ብቻ ላውራ አድምጡኝ በማለት የሚከተለውን ሙድና የኔን ንዴት በመጠኑም ቡሆን የተረዳችው ኤዱ ጀርባዋን ለሱ ሰጥታ እኔን ለማዋራት ሞከረች።
ከቆይታ በኋላ ካርድ ልግዛ በሚል ሰበብ ወጣ ብሎ ሲመለስ በፊት የነበረበትን ቦታ ትቶ እኔና ኤዱ መሀል ገብቶ ሲቀመጥ ንዴቴን መመጠንም መቆጣጠርም አቅቶኝ ጠፍቶ ድንገት ሀይል ጨምሮ እንደመጣ መብራት ሁለመናዬ ቦግ
••••
ቦግ አለ። ነደድኩ!፤ ፊቴ ተቀያየረ!፤ ደምስሬ ተወጣጠረ!
ልጁ ግን አየት አደረገኝና ከቁብም ሳይቆጥረኝ •••
"ኤድሻ ፌስ ቡክ ላይ የሆነ ፈን ነገር አይቼ እኮ ነው ቆይ ላሳይሽ እይውሟ እሄንን፤ እሄን አየሽው"እያለ ከሞባይሉ ላይ አይኗ እንዳይነቀል ስላደረጋት እሷም ሳታየኝ ተንጨርጭሬ እንደቀዘቀዝኩ ሆን ብሎ እኔን ለማናደድ እንደዛ እንደሚያደርግ በደንብ ያስታውቃል ብድግ አልኩና•••
እቤቴ ባትመጣ በዚህ አመት ከተጣላኋቸው ሰዎች አንዱ ትሆን ነበር ግን ምን ያረጋል
እቤቱ የመጣን ሰው ካልነከስኩ የሚለው ውሻ ብቻ ነው ውሻ ነገር ነህ አቦ! ገገማ! እያልኩ በውስጤ እየተሳደብኩ ተነስቼ ወጣሁና ግቢ ውስጥ ፊቴን መታጠብ ጀመርኩ።
ተመልሼ ስገባ እራሱ እያወራ እነሱ ሳይስቁ እራሱ ይስቃል ። የነበረን ቆይታ በልጁ ምክንያት ምኑም ሳይጥመኝ በሱ ውትወታ " በቃ እንሂድ" ብለው ተነሱ አላግደረደርካቸውም።
ከቤት እንደወጣን ግቢ ላድርሰችሁ ? አልኳቸው።
ከልቤ ነበር ከኛ ሰፈር ግቢ ድረስ ኮንትራት ካልያዙ በስተቀር ቀጥታ የሚወስዳቸው ታክሲ የለምና እንዳይቸገሩ ብዬ በማሰብ
"ስራ ትወጣለህ እንዴ ከዚህ ቡሀላ? አለችኝ ኤዱ
ስራ እንደማልወጣና እነሱን ብቻ አድርሻቸው ወደ ቤት እንደምመለስ ስነግራት•••
" አይሆንም በቃ ለኛ ብለህማ እዛ ድረስ መድከም የለብህም በትራንስፖርት እንሄዳለን!" ብላ ድርቅ አለች!
ተሰነባብተን ወደ ቤት ተመለስኩ።
አመሻሹ ላይ ጆሲ ድንገት በሩን ብርግድ አድርጎ ሲገባ ደንብሬ ተነሳሁ•••
"በለው በለው በቅዳሜ ቀን መጋደም ! ምን ሆነሀል አንተ ? እኔኮ የዳኒ እንግዳ ሄደች እንዴ ብዬ ሚሚ ባለሱቋን ስጠይቃት " ቆዩኮ ከወጡ!" ስትለኝ ገርሞኛል ቆይ ቆይ•••
በማህበር ተደራጅተው ነው እንዴ የመጡት?
እኔ እሷን ብቻ የቀጠርካት መስሎኝ አደል እንዴ የተቀየስኩት እዚሁ ደቅ ብዬ የቅዳሜ በርጫየን እንዳላጣጥም መሄድ እማልፈልግበት ቦታ ሄጄ ተጦልቤ ነው የመጣሁት ሰራህልኝ አቦ ቀጥሪያታለሁ ትመጣለች ከምትለኝ ይመጣሉ አትለኝም ወይ ምናለ ከመጡ ቡሀላስ ብትደውል መጥቼ ጀማውን እቀላቀል አልነበር እንዴ ! ግን እንዴት ነበር ውሎ?"
ኧረ ብትኖርልኝ ይሻለኝ ነበር ጆስዬ እኔም የመጨረሻ ተደውኬ ነው የዋልኩት !።
"እንዴ ለምን?" አለኝ ከበር ላይ ወደ ውስጥ ገብቶ አጠገቤ እየተቀመጠ
አላ! አብሯት የመጣው ልጅ ደዋኪ ነገር ነው ባክህ
"ማነው ልጁ ዝም ብሎ ጀለሳቸው ነው ወይስ•••?
አቦ ! ያ ነዎ! ባለፈው መሲ ልታስበላት ስትል ከጀለሶቹ ጋር ቀመር ቀምረው አስመለጣት ብዬ የነገርኩሁ የክፍሏ ልጅ
የፈራሁት ደረሰ ወይኔ ወንድሜን አንተ በህትነት ምናምን ነው እምንከባከባት እያልክ እራስህንም እኔንም ስትሸውድ በፍቅር የሚንከባከባትን አምጥታ አስተዋወቀችህ? ፍቅረኛዬ ነው ተዋወቀው ብላህ እጅ አፈችው አደል ?"
ውይይይይ ጆሲ ደግሞ እስቲ አሁን ማን እንደዛ አለ ? እንደዛ አለችኝ አልኩህ? ወጣኝ!?
"ታድያ እንደዛ ካልሆነ ምን አናደደህ? ብዬ ነዋ!"
አሃ! እኔ እምናደደው እሱ ስለጠበሳት ብቻ ነው ማለት ነው?
"ታድያ ፍላጎቱ እንደዛ መሆኑን ወይ አብሯት መሆኑን ብታውቅ እንጂ በምን ትናደዳለህ በዚ የማትናደድ ከሆነማ በምንም ልትናደድ አትችልም!"
ማለት?
"በዚህ ካልተናደድክ ሌላው ምክንያት እንዳለ ከዚህ በታች ነው ብዬ ነዋ!"
ይሆናል ብሎ ከመደምደም በምን ተናደድክ ብሎ መጠየቅ አይሻልም?
"እሺ በምን ተናደድክ?"
በቃ ልጁ እኔን ብቻ አድምጡኝ ከኔጋ ብቻ አውሩ ሙድ የሚያራምድ ነገር ነው ማለት•••አልኩና ከመጡ ጀምሮ የነበረውን ሁኔታ ነግሬው ሳበቃ••••
"ካካካካካ•••!" ሳቁን ለቀቀው!።
ምን ያስቅሀል?! አልኩት ተናድጄ!
" አይ ዳንዬ በዚህ ያልተሳቀ በምን ይሳቃል የፍቅርን አመል ስለማውቀው ነው አንድ ፈላስፋ ምን እንደሚል ታውቃለህ••••"
አላውቅምም ደሞም እንዳታወራልኝ ! ኤጭ አሁንስ አንተና ያ ጓደኛህ ወሬያችሁ ጅማሮውን በሙሉ
" አንድ ፈላስፋ ምን እንዳለ ታውቃለህ?
"እገሌ የተባለው መፅሀፍ ላይ ምን እንደሚል ታውቃለህ?
አንድ ምሁር ሰው ምን እንዳለ ልንገርህ?
በሚል እያሟሻችሁ የራሳችሁን ሀሳብ በቀላሉ ሰው እንዲቀበለው ለማድረግ የምትሄዱበት መንገድና
አለም ላይ ምን ተፈጠረ ብዬ ዜና ለማዳመጥ በተቀመጥኩ ቁጥር የሀገራችን የቲቪና ራድዬ ሚድያዎች
"ምሁራን ተናገሩ!
የህግ ባለሞያዎች ገለፁ!።
ነዎሪዎች እንዲህ አሉ !/
እገሌ እንዲህ አለ
እገሊት እንዲህ አለች" እያሉ የግልን አስተያየት ምልከታ አንድ ሰአት በሙሉ ዜና ብለው የሚያደርቁን ነገር እንዴት እንደሰለቸኝ •••
"በናትህ ይጠቅምሀል እቺን ብቻ አድምጠኝ ፈላስፋው እውቅ የግሪክ ፈላስፋ ነው ምን አለ መሰለህ ••••" ብሎ ሊቀጥል ሲል•••
በናትህ ተወኝ አልኩትና በንዴት ተነስቼ ክፍሉን ለቅቄለት ወጣሁ ። ስራ አልወጣም ያልኩት ሰውዬ ባጃጄን አስነስቼ ወደ ከተማ ከነፍኩ።
ንዴቴን በስራ ለመርሳት ተፍ ተፍ ስል አምሽቼ ልክ ከምሽቱ አራት ሰአት አከባቢ ከገንደቆሬ ወደ ሼል እየመጣሁ ብሎሰም ሆቴል ክርባው ጋር እንደደረስኩ አንድ እድሜው በአርባዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚሆነው ፈርጠም ያለ ጎልማሳ ሰው ሁለት እጁን በየተራ እያርገበገበ•••
"ባጃጅ ኮንትራት ኮንትራት " አለኝ ። አቆምኩና
የት? አልኩት ፉቱ ላይ እንደእሳት የሚንቀለቀለውን ንዴቱን እያስተዋልኩ
"የት እንደሆነች አላውቅም !
የገባችበት ጉድጓድ ውስጥ ገብቼ እስካገኛት ከኔ ጋር ነህ!
ያልከኝን እከፍላለሁ !"
አለኝና መጀመሪያ የምንሄድበትን ሆቴል ነገረኝ።
እየሄዱን በየመሀሉ •••
" እኔ ላይ! ለኔ እሄ ይገባኛል!" እያለ የአንዱ እጁን መዳፍ በሌላኛው እጁ ቡጢ ያጎነዋል።
ተናድጄ ብወጣ ከኔ የባሰ በንዴት የተከነ ሰው አጋጠመኝና የራሴን ንዴት ረሳሁት። ምን ሆኖ ይሆን እንዲህ ግብግብ ያለው? አልኩ ለራሴ።
ምን ሆነህ ነው ዘመዴ? አልኩት ፈራ ተባ እያልኩ•••
"ወይይይ ሴት ! አይይይ ሴት ገና ለገና ለሳምንት ያህል ለስልጠና ሀረር ሄጃለሁ ስላልኳት በከተማው የለም ብላ እግሬ ከመውጣቱ ቱ የማትረባ !
እሄማ መጀመሪያ የተቀባበለ እንጂ ሄጄ ገና ሶስት ቀን እንኳን ሳይሞላኝ ኬት ይመጣል እስካሁንም እየተጫወትሽብኝ ነበር ማለት ነው እኔ አንቺ ለማግባት ስሰናዳ በግዜ ጉድሽን ያሰማኝ!
ዛሬ ምን እንደሚውጥሽ አያለሁ "! አለ ።
ከንግግሩ ለኔ ጥያቄ መልስ እየሰጠኝ ይሁን ብሶቱን እየተነፈሰ መረዳት ተሳነኝና ግራ ተገብቼ ዝምታን መረጥኩ ።
340 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 20:34:20
Touch her not just with your hands and lips touch her with your mind your heart and your words
@yefikrclinic
1.1K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 15:14:14 ልጩህበት!

ክፍል- 15

አዘጋጅ፦
የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
ቴሌግራምህን ክፈት ሶስት መልእክቶች አሉህ በድምፅ! በፅሁፍና; በምስል! ቻው !!"ብቻ ብሎኝ ስልኩን ዘጋው•••
በፍጥነት ቴሌግራም አካውንቴን ስበረግደው ቀድሞ የታየኝ የመሲ ልብስ አልባ ገላ የሚያሳየው ቪድዮ ነበር ከስር የመሲን ስልክ ቁጥር አስቀምጦ
"አቢቲ በዚህ ቁጥሯ የተከፈተ ቴሌግራም አካውንቷ ላይ ቪድዮዋን ልከህ ካሁን ቡኋላ በሴት ተማሪዎች ህይወት መነገዷን እንድታቆም ያለ በለዚያ ግን ቪድዮዋን እንደምትለቀው ነግረህ አስጠንቅቃት!" ይላል በርግጌ ከፍራሼ ላይ ተነሳሁ።
ቪድዮውን ስከፍተው •••
የሶስት ደቂቃ እድሜ ሲኖረው በዚች ሶስት ደቂቃ ውስጥ መሲ ያልተቀረፀ የሰውነት እካሏ አልነበረም ስካሯ ከመጠን ያለፈ ነበርና ያላትን በሙሉ እያደረገች ትስቃለች ። የሚገርመው የሰውየው አንዲት ጣት እንኳን በትይንቱ ውስጥ አለመኖሯ ነው።
ተጫወተባት እናቴ ትሙት በደንብ አርጎ ነው የተጫወተባት አልኩኝ ጮክ ብዬ መጮሄ ሳይታወቀኝ።
ለኔ በአለም ደስ የሚሉ ግን ያልተፃፉ ህግ አስከባሪም ፍርድቤትም ዳኛም ሳያስፈልጋቸው ከሚተገበሩ ተፈጥሮአዊ ህጎች አንዱ
"ሁሉም የእጁን ያገኛል "የሚለው የውስጤ እምነት ነው ማንም ቢሆን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የዘራውን ማጨዱ የማይቀር ነው
ይዘግይም ይፍጠን፡ ይነስም ይብዛ ቅጣቱን መቀበሉ የማይቀር ነው
ስንቶቹን በክፋቷ አሳልፋ እንዳልሰጠቻቸው እሷን ከክፉ የሚጠብቃት ከሷ በብዙ ክንድ ራቀና አጋለጣት በክፋታችን ያራቅነውን የላይኛውን ጠባቂ የትኛውም የምድር ሀይል ሊተካው አይችልምና አብሯት የነበረው የሰፈራችን ሰውዬም አስረክቧት ፈረጠጠ።
ቪድዮውን ዘጋሁትና የድምፅ ቅጂ መልእክትን ከፈትኩት።
የድምፅ ቅጂው በሁለት ሰዎች መካከል የተደረገን ምልልስ ይዟል ።
የት እንደገባ እስካሁን ያልተመለሰልኝን ያንን ሽንት ቤት ድረስ ሄጄ የፈለኩት ሰውዬ ተከትሎት ሄዶ ሲያናግረው ይጀምራል•••
በቅጂው የመጀመሪያ አስር ሰከንዶች የኮቴ እና በጭፈራ ቤቱ በዛች ቅፅበት ሲዘፍን የነበረው የ ቦብ ማርሊ ዘፈን በስሱ ይሰማል ።
ልክ አስራ አንደኛው ሰከንድ ላይ •••
"ጤና ይስጥልኝ ?
ጤና ይስጥልኝ ምን ነበር እንተዋወቃለን ወንድም?
እኔ እንጃ እንተዋወቃለን መሰለኝ እንካ እስቲ እሄን ተመልከት!
ምንድን ነው እሱ ?
አይታይህም እንዴ መታወቂያ ነዋ !
ያ የሰፈራችን ሰው መታወቂያውን ካየ በኋላ መሰለኝ ድምፅ ተቀየረ።
ታድያ ም-ም-ም-ም-ም-ምን ልታዘዝ ጌታዬ? በርግጥ አላወኮትም ወይ ያጠፋሁት ነገር ይኖር ይሆን ?
ያጠፋሁት ነገር ይኖር ይሆን ትላለህ እንዴ ደሞ?
ለነገሩ ላንተም ለብዙዎቹም ለህግም ጥፋት መስሎ የማይታይ ጥፋት ስለሆነ አይታወቅህም
ማለት? እንዴት? መቼ? ምን አድርጌ ? የኔ ጌታ እስቲ ና አረፍ በልና ልጋብዝህ እየጠጣን እናውራ!
ህሊናቸውን በብራቸው ቁልል አፍነው የትውልድን አእምሮ የሚያቀንጭር ስራ ላይ ከተሰማሩ ከብቶች መሀል አንዱ ነህና ሰውን ሁሉ በብር በግብዣ ከመግዛት የሚሻገር አስተሳሰብ የለህም እንኳን እኔን ልትጋብዘኝ ከዚች ሰከንድ ጀምሮ አብረሀት ያለችውን አንድ ፍሬ ልጅ ደግመህ ሳታያት እዚሁ ቆሜ እያየሁህ በጓሮ በር ሹልክ ብለህ ጥፋ! ያለበለዚያ •••
ኧረ እሺ እሺ ጌታዬ እሄዳለሁ ግን የጓሮ በር ያለው አይመስለኝም ቤቱ!
በዛጋ ወደ ሽንት ቤቱ መጊቢያ በስተቀኝ በኩል ባለችው ቀጭን መንገድ ወደ ውስጥ ትንሽ ሄደህ ደረጃውን ቁልቁል ስትወርድ በር ታገኛለህ
እሺ ጌታዬ እሄው ያለብኝ ሂሳብ ነው!
ፍጠን!
እሺ እሄው ሄድኩኮ!"
ሰውየውን በዚህ መልኩ ቆሌውን ገፎ ማባረሩን ሳዳምጥ ከተሰማኝን ደስታ ጋር ግን እሄ ሰውዬ ማን ነው? ለምንድን ነው መታወቂያውን ሲያሳየው እንደዛ ምላሱን የዋጣት ይመስል ንግግሩ ሁሉ የተቆላለፈበት ?የሚለው ጥያቄ ገዝፎ አንቃጨለብኝ!።
ሰውየውን ለግዜው እንቆቅልሽ እንደሆነብኝ ተውኩትና ጆሲን ቀስቅሼ ከማታ ጀምሮ የተፈጠረውን ነገር ነገርኩት።
"ለማንኛውም ቪድዮውን ለመሲ ከመላክህ በፊት አስብበት ማለቴ አረጋጋው !" አለኝ።
ቅዳሜን በጣም እወዳታለሁ በዛ ላይ ዛሬ ከኤዱ ጋር ቀጠሮ አለን።
ከቀኑ ልክ 7:30 ላይ ኤዱ ደወለችና ሰፈር መድረሷንና ያለችበትን ቦታ ነገረችኝ ።
ስትነሺ ደውይልኝ መጥቼ እወስድሻለሁ ብያት ስለነበር ለምን ቀድማ እንዳልደወለችልኝ እየጠየኳት ከቤት ወጣሁና ብር ላይ, ያቆምኳትን ባጃጄን! አስነስቼ ከነፍኩ ።
እነሱ ሳያዩኝ ገና ከሩቁ እንዳየሁዋቸው ደነገጥኩ ግን ምን አስደነገጠኝ ? እኔ እንጃ!
ኤዱ ብቻዋን አልነበረም የመጣችው ሶስት ናቸው ከረድኤት አንድ ባለባበሱ ፍንድትድት ያለ ወጣት ወንድ አብሮአቸው አለ።
ማንም አብሮአቸው ቢኖር ግን ምን አገባኝ ?
ግን ለምን ሶስት ሆነው እንደሚመጡ ቀድማ አልነገረችኝም ?
ግን ማን ነው? እያልኩ መልስ በለላቸው ጥያቄዎቼ እራሴንም ባጃጇንም እያጣደፍኩ አጠገባቸው ደረስኩ።
ከሷ እና ከረድኤት ጋር በመተቃቀፍ ሞቅ ያለ የቅርብ ሰው ሰላምታ ከተለዋወጥን ብሀላ ፈንጠር ብሎ ሞባይሉን የሚነካካውን ልጅ እያመለከተችኝ ዳንዬ ተዋወቀው ባለፈው ከመሲ አስመለጠኝ ያልኩህ የክፍሌ ልጅ ፣ ጓደኛዬ እሱ ነው አለችና ደሞ እሱን
ቴዲዬ ተዋወቁ ምርጥ ወንድሜን " አለችው
ልጥጥ እንዳለ እጁን ዘርፕጋልኝ ጨበጥኩትና ግቡ እንሂድ አልኳቸው።
ባጃጅ ውስጥ ገብተው ወደቤት እየሄድን በመካከላችን ወሬ ጠፋ!።
በኔ በኩል የልጁ ሁኔታ ይሁን ሌላ ባይገባኝም የሆነ ደስ የማይል አዲስ ስሜት ውስጤ ሲላወስ እያዳመጥኩት ነበርና ዝም ማለቴንም አላስተዋልኩትም ነበር ።
እቤት እንደደረስን የውስጤ ስሜት ፊቴ ላይ እንዳይታይ እየታገልኩ ላጫውታቸው ብሞክርም ልጁ እኔ ከረድኤትም ይሁን ከኤዱ አልያም ከሁለቱን ጋር ወሬ ስጀምር እየጠበቀ በማክሸፍ ነበርና የራሱን የሚተኩሰው ሊያስወራኝ አልቻለም።
መናደድ ጀመርኩ። ልጁ እኔ ብቻ ላውራ አድምጡኝ በማለት የሚከተለውን ሙድና የኔን ንዴት በመጠኑም ቡሆን የተረዳችው ኤዱ ጀርባዋን ለሱ ሰጥታ እኔን ለማዋራት ሞከረች።
ከቆይታ በኋላ ካርድ ልግዛ በሚል ሰበብ ወጣ ብሎ ሲመለስ በፊት የነበረበትን ቦታ ትቶ እኔና ኤዱ መሀል ገብቶ ሲቀመጥ ንዴቴን መመጠንም መቆጣጠርም አቅቶኝ ጠፍቶ ድንገት ሀይል ጨምሮ እንደመጣ መብራት ሁለመናዬ ቦግ ••••••••••••••••••••
@yefikrclinic
@yefikrclinic
1.4K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, edited  12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ