Get Mystery Box with random crypto!

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikrclinic — ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikrclinic — ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️
የሰርጥ አድራሻ: @yefikrclinic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.93K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓
❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤
❤ HBD ለማለት፤ 🎂
❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀
❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂
🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን። @yefikrclinic_bot
contact us 👉 @yefikrclinic
ላይ ይላኩሉን

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-01 11:21:39 እስኪ እርግቤ ለዛች ለልቤ ንግስት ለኪያዬ አድርሽልኝ እባክሽን............



............
@yefikrclinic @yefikrclinic
1.3K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 08:46:55 ልጩህበት!

ክፍል- 23

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
ምኑን ከምኑ ነው እምመርጠው?
"ወይ ኤደንን እኔ ሄጄ እንዳናግራት መፍቀድ ካልሆነ ከልጅቷ ጋር ፍቅር ጀምረህ ኤደንን መርሳት!"
ጆሲ አምርሯል ግራ ገባኝ ። ኤዱን እንዲያናግራት በጭራሽ እንደማልፈልግ አውቃለሁ ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ ጡጫ ሆነብኝ ቢሆንም•••
ውስጤ እንደማይሆን እያወቀው ከዳኒ ጭቅጭቅ ለመገላገል ስል •እሺ አልኩት
በቃ እሺ!
"በቃ እሺ ምን በየትኛው ሀሳብ?"
"በቃ ካልካት ልጅ ጋር እንቀራረባለና!"
አዋ ዳንዬ አንዳንዴ እንኳን እንደዚህ እሺ በለኝ እስቲ ዳንዬ ዋናው መቀራረባችሁ ነው ከዛ ቡሀላ ሌላው ይከተላል ኤዱንስ ቢሆን ሳትቀርባት አላፈቀርካት!"
እሺ አልኩህ እኮ በቃ አልኩት። ከዛች ሰአት ጀምሮ ጆሲ ስራውን ጀመረ ።
ልጅቷን እቤት ያመጣትና መጣሁ ብሎ በመውጣት ጥሎን ይጠፋል።
መቀራረብ ብንጀምርም እውነቱን ለመናገር እሷን ለብቻዋ ከማገኛት ይልቅ ኤዱን ከልጁ ጋር ሆና ባገኛት እመርጥ ነበር።
ለሶስት ወር ልጅቷ እና ጆሲ ስራ አደረጉኝ የተቀየረ ስሜት አልነበረም በመሀል ድንገት ለተከታታይ ቀናት ጥፍት አለች።
ለስድስት ቀን ያህል ድምጿንም ስልኳንም አጥፍታ ከተሰወረች ቡሀላ በሰባተኛው ቀን እኔና ጆሲ ሰፈር ውስጥ ቁጭ ባልንበት እራሷ ጆሲ ስልክ ላይ ደወለች።
ስልኩን ለሁለታችንም እንዲሰማ አደረገና •••
" ምን ሆነሽ ነው የጠፋሽው?" የጆሲ ጥያቄ ነበር
" ምን ላድርግ ጋደኛህ ኤደን የምትባል ሰይጣን አጠናፍራዋለች መሰለኝ በተገናኘን ቁጥር ወሬው ሁሉ ከሷ አያልፍም እንዴ እኔ ልጅቷን ሳላውቃት ሁላ እንድጠላት ነው ያደርገኝ በጣም ነው የተጎዳሁት ጆሲ ከቻልክ ጓደኛህን ወይ አሳክመው ወይ ፀበል ውሰደው " ብላው እርፍ አለች ።
ጆሲ ዘወር ብሎ ሲያፈጥምኝ ተነስቼ ካጠገቡ ሄድኩ።
ከዛን ቀን ቡሀላ ከጆሲ ጋር ስለምንም ነገር ሳናወራ የኤዱ ምርቃት ሰባት ቀን( ሳምንት) ቀረው ።
ስድስት ቀን ሲቀረው ደውላ ቤተሰቦቿ ለምርቃቷ ከሁለት ቀን ቡሀላ እንደሚመጡ እና ከምርቃቷ ቡሀላ አብራቸው ወደ አዲስ አበባ እንደምትሄድ ነገረችኝ ።
ይህ ንግግሯ መብረቅ በሉት ለኔ ።ጨነቀኝ ።
ያን ቀን ጠጥቼ ብገባም እንልፍ እንቢ አለኝ እኩለ ለሊት ላይ አንድ ሀሰብ መጣልኝ።
ተነስቼ ለኤዱ ደብዳቤ መፃፍ ጀመርኩ•••
••••• ለኤደን
ኤዱዬ ህይወትን መራራም ጣፋጭም እንድትሆን ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?
እኛ ሰዎች ስላለፈው እና ስለ አሁኑ እንጂ ነገ ምን እንደሚፈጠር እለማወቃችን ነው ።
ነገን አለማወቅ የራሱ የሆነ ብዙ ጥሩም መጥፎም ገፅታዎች አሉት።
ነገ የሚከሰተውን መጥፎ ነገር ቀድመን ስናውቅ እና ነገ የሚከሰተውን ጥሩ ነገር ቀድመን ስናውቅ የሚሰሙን ሁለት ተቃራኒ ስሜቶች ናቸው።
እንዲህ ያልኩሽ አሁን የሆንኩትን ነገር ያኔ በዛ በብርድ እዛ ሆቴል በር ላይ ቆመሽ ባየሁሽ ሰአት ቀድሜ ባውቀው ምን እወስን ነበር ብዬ ሁሌም እራሴን ስለምጠይቀው ነው
"አሁን ምን ሆንክ? ትይ ይሆኖል። ምንም አታውቂምና ጥያቄሽ ልክ ነው የኔ ስስት ያኔ ካሁን ቡሀላ ወንድምሽ ነኝ ስልሽ አንቺም ተቀብለሽ የእውነት ወንድም አድርገሽኛልና ምን ሆንክ ብትይኝ ባንቺ አይፈረድም እኔ ግን ብዙ ሆኛለሁ አንቺን በማፍቀሬ እንኳን አንቺ እኔ እንኳን የማላውቀው ሌላ ዳኒ እንደሆኑኩ አውቃለሁ።
ኤዱዬ አፈቅርሻለሁ!
ይህን ስታነቢ ምን ትይኝ ይሆን?
በቃሌ የማልገኝ እራስ ወዳድ ነኝ አደል ኤዱዬ?
በጣም ይቅርታ።
ከግዜ ቡሀላ ለኔም ባልገባኝ መንገድ ውስጤ ተቀያይሮ ካቅሜ በላይ ሆኖብኝ እንጂ ያኔ ወንድም እሆንሻለሁ ከጎንሽ ነኝ እንደወንድምሽ እይኝ ያልኩሽ ግን ከልቤ ነበር!።
ሁሌም ቃሌን ያጠፍኩ መስሎ ይሰማኛል ላንቺ ስላልነገርኩሽ ምንም ባትይኝም ብታውቅ ምን ትለኛለች እያልኩ ከመሸማቀቅ አልዳንኩም።
ፍቅር የሻቱትን ማግኘት ብቻ አይደለምና የኔ እንደማትሆኚ እያሰብኩም አፈቅርሻለሁ።
ከምንም ነገር በላይ አንቺን በእውኔም በህልሜም ማየት፣ ስላንቺ ማሰብ ፣ ስላንቺ ማውራት ያስደስተኛል ። ካንቺ ውጪ ሁሉ ነገር አልጥምህ ካለኝ ወራቶች ተቆጥረዋል።
"ታድያ በነበረን ግዜ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ከነበርክ እንዴት አልነገርከኝም?
ወይም እንዴት ከፊትህ መረዳት አልቻልኩም? " ትይኝ ይሆናል
በፍቅር ንዳድ ከመለብለብ በላይ በልብ ውስጥ ያለውን የፍቅር እሳት አውጥቶ ላፈቀሩት ሰው ንዳዱን ማሳየት ለብዙ አፍቃሪዎች ከባድ ነው።
እኔን ግን አውጥቶ ከመናገሩም በላይ ከባድ የሆነብኝ ብነግርሽ የሚሰማሽን ስሜት ማሰብ ነው።
ፍቅረኛሽ ሆኜ ቢሆን አሁን ወንድምሽ በመሆኔ የተደሰትሽውን ያክል እምትደሰቺ መስሎ አይታየኝም ።
ካፌ ሻይ ቡና እያልን ፊት ለፊቴ ቁጭ ብለሽ ከናት ካባቴ ባትወለድም አንተን የመሰለ ወንድም በስጦታ ስለሰጠኝ እያልሽ ፈጣሪን ስታመሰግኚ ስሰማ እንኳን ልነግርሽ ማፍቀሬን የምታውቂብኝ እየመሰለኝ ምክንያት ፈጥሬ ካጠገብሽ እሽሻለሁ ።
ጆሲ ጓደኛዬ ምን እንደሚለኝ ታውቂያለሽ ኤዱዬ?
••••" አንተኮ መፍታት ያቃተህ መጀመሪያ ላይ እራስህ አጥብቀህ ያሰርከውን ቋጠሮ ነው አልፈታ ባለህ ቁጥር ደግሞ በንዴት ለመበጠስ እየሞከርክ የበለጠ ታጠብቀዋለህ!" ይለኛል
እውነቱን ነው ትዝ ይልሻል እዱዬ?
ስለመሲ ስናወራ አንድ ሰው ውለታ ውሎልሽ ውለታውን በመንተራስ ከፍላጎትሽ ውጪ የሚጫንሽ ከሆነ ውለታ ሳያስቀድም ተመሳሳይ ጥያቄ ከሚጠይቅሽ ሰው በላይ እርኩስ ነው ብዬሽ ነበር ።
እኔም የፍቅር ጥያቄዬ ካደረኩልሽ ትንሽ ውለታ ጋር እንዳይያያዝብኝ ፈራሁ።
አንቺንም እኔን ወንድም እንጂ ፍቅረኛ የማድረግ ፍላጎት ውስጥሽ ሳይኖር የምጫንሽ ጥያቄዬን ባለመቀበልና እኔን ባለማስከፋት መሀል ሆነሽ የምትጨነቂ መስሎ ታየኝ ።
በዚህ መሀል እናንተ ባታዩኝም ከልጁ ጋር ሆኖችሁ ብዙ ቦታዎች ታጋጥሙኝ ጀመር።
ያኔ በሱም ባንቺም ሳይሆን በራሴ ይበልጥ መናደድ ጀመርኩ ።
ህመምህ መድሀኒት የለውም አትድንም እንደተባለ በሽተኛ የፍቅር ህመሜ ፈውስ የሆንሽውን አንቺን የኔ እንደማላደርግሽ ተረዳሁ ።
ኤዱዬ በመመረቅሽ እንኳን ደስ አለሽ!
በመመረቅሽ የተሰማሽን ደስታ ትንሽ ሳታጣጥሚውና ከድሬ ሳትወጪ አንብበሽው ሌላ ስሜት ውስጥ እንድትገቢ ስላልፈለኩ ነው ይህን ደብዳቤ በእጅሽ ሳልሰጥሽ ከምርቃቷ ቡሀላ ወደ አዲስ አባባ ስሸኛት ሳታየኝ የልብስ ሻንጣዋ ውስጥ አስቀምጥላታለሁ ባየችው ግዜ ትየው ብዬ የወሰንኩት።
በነበረን ስሜት ወንድምሽ ሆኜ ልሸኝሽ ቀናቶች ቀርተዋል ለዛም ተዘጋጅቻለሁ ።
የኔ ኤደን ዛሬም ቢሆን ስላወኩሽ ደስተኛ ነኝ።
የማንም ሁኚ እኔ ግን አፈቅርሻለሁ። መቼም ቢሆን አረሳሽም። ዝምምምም ብዬ ሳፈቅርሽ እኖራለሁ።
ሰላም ሁኚ!
ዳኒ ነኝ።
••••
የመጨረሻው ክፍል 24 በመሆኑም ቻናላችንን ሼር በማድረግ ቀጣዩን ክፍል ያንብቡት

ይቀጥላል....
@yefikrclinic
@yefikrclinic
@yefikrclinic
1.5K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 11:10:23 ልጩህበት!

ክፍል- 22

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
በመሲ ጥሪ በዛ ፍጥነት ሰው ሊደበድቡ መምጣታቸውን ሳስበው ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው የሚኖሩ አሳሞች መስለው ታዩኝ መሲ ማነች ? ምንድን ነች? አያገባቸውም ብቻ ትክፈላቸው እንጂ እንደ እንስሳ ወደፈለገችበት ትነዳቸዋለች ። ገልቱዎች ።
ጥበቃውን ሰው እንዳይወጣ አስጠነቀቁትና
መሀላቸው አድርገዋት ግቢ ውስጥ መዟዟር ጀመሩ ብዙ ሰው የለም ያሉትም ጥንድ ጥንድ ሆነው ነው የተቀመጡት ብቻዬን ቁጭ ያልኩት እኔ ብቻ ነኝ ።
ደረታቸውን ገልብጠው እየተሽከረከሩ የሚዝናኑትን ሰዎች ምን እንደሚሏቸው ባላውቅም አንዳንዶቹን ጠጋ ብለው እያናገሩ ያንዳንዶቹን ሞባይላቸውን ተቀብለው እየመለሱላቸው እኔ ወዳለሁበት ቦታ መጠጋት ጀመሩ።
ሂሳብ ዘጋሁ።
እነዚህን ዱባ ጭንቅላቶች ፈርቼ ሳይሆን የሰው ሆቴል ውስጥ ብጥብጥ ተፈጥሮ ላለመታሰር ስል ተነስቼ ወደ መውጫው በር ስጠጋ•••
" እንዳታስወጣው! ጥበቃ እንዳታስወጣው !"
የሚለው የመሲ ጩኸት ጆሮዬ ላይ አንቃጨለብኝ ዘወር ስል እሷ ከጀርባቸው ቆማ ሶስቱም ወደኔ ሲመጡ እየኋቸው•••
ጥበቃው ወደኔ ተጠግቶ አየት አደረገኝና ጠቀስ አርጎኝ ሳቁ ልገንፍልብህ እንዳለው ሰው በእጁ አፉን ይዞ ወደነሱ ዞረና
" ማንን ዳኒን?" አላቸው በአመልካች ጣቱ ወደኔ እያመላከታቸው •••
" እሱን ነው እንዳይወጣ ያልሽው አንቺ ልጅ? "የቀበጡ ለት•••"
አለ የሀገር ሰው ትሰሚያለሽ እሱን እንኳን እኔ ታንክ አያቆመውም ቅድም ስትፈክሪ የነበረው እሱን ለማስመታት ነው እንዴ ?
ቆይ ዛሬ ነው ድሬ የገባችሁት? እንግዶች ናችሁ እንዴ?
ዳኒኮ በካራቴ ትምህርት ጥቁሩን ቀበቶ እንደ አባቶቹ ዝናር ደጋግሞ ወገቡ ላይ የጠመጠመ የድሬ ዥግና ነው !
ቆይ ቆይ ቆይ በወፈረ መስሎሽ ነው እነኝህን ይዘሽ የመጣሽው ምነው "ለሀምሳ ጋን አንድ አሎሎ ይበቃል " ብለው ቲተርቱ ውልእንኳ ብሎብሽ አያውቅም?
ታይነኩት አይነካም ምላሳችሁንም እግራችሁንም ሰብስባችሁ ሂዱ ዳንዬ በል አንተም ሂድ ምን ይደረግ
አንዳንዱ ተማን ጋር እንደተጣላ የሚገባው ተተወቀጠ ቡሀላ ነው !
ቢያውቁህማ እንኳንስ ለጠብ አስቁመው ሊሉኝ ሰአት ጠይቀው ለማለትም ባልደፈሩ ነበር በል ሂድ መሽቷል!"
ሲለኝ ገለማምጫቸው ሁለት እጄን ኪሴ ውስጥ ከትቼ ብወጣም ከወጣሁ ቡሀላ ካልወጣሁ እያለ ከሚታገልኝ ሳቅ ጋር መታገል ፈተና እንደሆነብኝ ጉንጬን ነፍቼ ትንሽ ራቅ እንዳልኩ ሳቄን ለቀኩት!
ወይ ጥቁር ቀበቶ! ኬት አምጥቶት ነው?
የባጃጇ ነው እንዳልል ባጃጄ ቀበቶ የላትም ።
ከጥበቃው ጋር የምንተዋወቀው በስራ ነው
አልፎ አልፎ ቀን ቀን በብዛት ደሞ ማታ ማታ ሆቴሉ ውስጥ የሚዝናኑ ብሎም እዛው አልጋ ይዘው ድሬ ሰንበትበት ብለው የሚሄዱ ደንበኞቻቸው ታክሲ እንዲጠራላቸው ሲነግሩት ደውሎ ይጠራኛል የተወሰነ ኮምሽን አስብለታለሁ እሄን እማደርገው ከብዙ ሆቴል ጥበቃዎች ጋር ነው አንድ ሁለቴ እዛ ስጠቀም ጋብዤዋለሁ አለቀ ከዚህ ያለፈ ቅርርብ አልነበረንም ።
ባንድ ግዜ የከተማው አክተር አድርጎኝ ቁጭ ሲል እንኳን እነመሲ እኔ እራሴ እራሴን ሳልፈራው አልቀረሁም ወይ የሰው ነገር እራሴን ታዘብኩት እሱ በካበኝ ቁጥር ፍታቸው ሁለት እግሬን ከፈት አድርጌ ፊቴን አጨፍግጌ በመቆም በለለኝ ደረት ስወጣጠር ፈንድቼ ነበርኮ እያልኩ በራሴው ንግግር እኔው እየሳኩ ወደቤት ስገባ ደንግጦ ከንቅልፉ የባነነው ጆሲ ቀና ብሎ አየኝና •••
"ወይኔ ወንድሜን ለየልህ በቃ!?"አለኝ።
ስማ ጆስዬ በዚህ ሰአት ቢለይልኝማ በምን እድሌ እየውልህ ጆስዬ ሁሉንም ነገር ስንፈልግ የምንሆነው ሳንፈልግ የማንሆነው ቢሆን ኤዱን እስክረሳት ብቻ ባብድ ደስ ይለኝ ነበር!
"ከዚህ በላይ! በል ተኛ አሁን ጥዋት እናወራለን" ሲለኝ ተኛሁ።
ረፋድ አራት ሰአት አከባቢ ከንቅልፌ ነቃሁ።
ማታ የዘጋሁትን ስልኬን ስክፍተው መሲ ሶስት መልክቶችን በተከታታይ ስልኬ ላይ ልካልኛለች ።
ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩ•••
የመጀመሪያው መልከት እባክህ ወንድሜ እንደዛ እንዳታረግ ትንሽ አላሳዝንህም ? ቆይ እህት የለህም ?" ይላል
ህለተኛው መልክቷ" ያንን ቪድዬ እንዳልከው እምትለቀው ከሆነ እራሴን እንደማጠፋ እወቅ! ይፀፅትሀል!" ይላል
ሶስተኛው መልክቷ" ጨነቀኝ ኧረ በናትህ መልስ እንኳን ስጠኝ!" ይላል ።
አሳዘነችኝ ልበል ኧረ አልልም !።
መልስ መፃፍ ጀመርኩ•••
አንቺ ክፉ ልታደርጊባቸው ስለቻልሽ ሌሎች ላይ ክፉ ስታደርጊ አንቺ ላይ ክፉ የማረግ አቅም ያለው ሌላ ሰው እንዳለ አትርሺ ቢሆንም ከስተትሽ ተምረሽ ክፋትሽን ካቆምሽ አንቺን በመጉዳቴ ሳይሆን በማስተማሬ ብዙ አተርፋለሁና በጭራሽ አልጎዳሽም!
መልክቱን ልክ እንደላኩት ስራ ሄዷኩ ያለው ጆሲ ተመልሶ መጣ ።
ምነው ጆሲ ስራ የለም እንዴ ለምን መጣህ?
"አንተን ላናግር መነጋገር አለብን ዳኒ!"
ስለምን?
"ስላንተ ነዋ!"
ስለኔ ምን ?
"ቆይ ዳኒ ለምን እኔንስ ታስጨንቀኛለህ እንደወንድሜ እማይህ ጓደኛዬ ነህ ያንተ እንዲህ መሆን የሚያስደስተኝ ይመስልሀል እንዴ?
ምን ሆንኩ?
ምን ያልሆንከው አለ! ስራህን በአግባቡ እየሰራህ
አይደለም ፣ ማታ ማታ አዘውትረህ ትጠጣለህ ከኔ ጋር እንኳን ማውራት አስጠልቶካል የኔስ ችግር የለውም ቤተሰብጋም እኮ ሄደህ አታውቅም እናትህ ሳያዩህ ሲያድሩ ምን ያህል እንደሚጨነቁ ታውቃለህ አንተን ፍለጋ እዚህ ድረስ መምጣት አለባቸው ዳኒ! ቆይ እስከመቼ እውነቱን ልንገርህ እኔ ወስኛለሁ ይቺ ኤደን የምትላትን ልጅ ሄጄ አናግራታለሁ!"
ብሎኝ ከቤት ሲወጣ ተከትዬው ወጥቼ አንገቱን አነኩትና
አታደርገውም ዳኒ አልኩት
"ቆይ ለምን" አለኝ እጄን እያስለቀቀ
ለምን እንደሆነ እነግርሀለሁ።
እሺ ወይ ያቺ የምትወድህን የኔን ሲስተር ጓደኛ ጀምራትና ይቺን ኤደን ተብዬዋን እርሳታ በቃ ዳኒ !"
ካካካካካ ኤዱን ነው በሷ እምረሳት አልኩት ከልቤ ነበር የሳኩበት!
አትሳቅ ዳኒ እንድትስቅብኝ አደለም ስራ አስፈቅጄ የመጣሁት ሁለት አማራጭ አለህ አንዱን ካልመረጥክ ከኔጋም ትጣላለህ!
ምኑን ከምኑ ነው እምመርጠው?
"ወይ ኤደንን እኔ ሄጄ እንዳናግራት መፍቀድ ካልሆነ ከልጅቷ ጋር ፍቅር ጀምረህ ኤደንን መርሳት!"
ጆሲ አምርሯል ግራ ገባኝ ። ኤዱን እንዲያናግራት በጭራሽ እንደማልፈልግ አውቃለሁ ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ ጡጫ ሆነብኝ ቢሆንም•••

ይቀጥላል....
@yefikrclinic
@yefikrclinic
@yefikrclinic
992 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 17:16:46
She took my arm, I don't know how it happened, we took the floor and she said don't you dare look back just keep your eyes on me, she said shut up and dance with me in the rain

@yefikrclinic
@yefikrclinic
@yefikrclinic
915 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 12:41:19 ከተራራህ መውደቅ ትችላለህ፣ ከዛፍም መውደቅ ትችላለህ ... ነገር ግን ከሁሉም የተሻለው ግን በፍቅር መውደቅህ ነው፡፡

#ያድ
@yefikrclinic
@yefikrclinic
@yefikrclinic
196 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, edited  09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 07:14:41 ልጩህበት!

ክፍል- 21

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
ሰውየው መለፍለፉን አላቆመም ወይ እሱ ወይ እኔ ከዛ ቤት ካልወጣን ዝም እንደማይል ስለገባኝ ተነስቼ ወጣሁና ግማሽ ኪሎ ሜትር አከባቢ በግሬ ተጉዤ " ጨለማው ቤት" በመባል ወደ ሚታወቀው ሆቴል ገባሁ።
ብዙ ግዜ ጥንዶች የሚዝናኑበት ሆቴል ቢሆንም እኔ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ስጠጣ ሁለት ቢራ ጨርሼ ሶስተኛውን እንዳገባደድኩ ከፊት ለፊቴ በቅርብ ርቀት ከተቀመጡት ሶስት ሰዎች መካከል ድንገት ቦግ ብሎ በበራው የሞባይል መብራት የመሀለኛዋን እየኋት•••
ያቺን እርኩስ አየኋት እስከዛሬ ሳያት ከሚሰማኝ የንዴት ስሜት በተለየ ሁኔታ ጠላቴ መስላ ታየችኝ የግቢ ሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆን እኔ ሂወት ላይም የተጫወተች መስሎ ተሰማኝ።
አዎ እሳ ነች ለኔ እና ለኤዱ መተዋወቅ ምክንያት ሆና እዚህ የማልወጣው የፍቅር ገደል ውስጥ ወድቄ የመንፈስ ስብራት እንዲያጋጥመኝ የሞራል የደስታ ባጠቃላይ የኑሮ ጣእምና ለዛዋ ሁሉ እንዲጠፋብኝ ቀንደኛዋ ተዋናይ እሷ ነች ብዬ አሰብኩኝ ።
አዋ! እሷ ነች ያን ቀን ኤዱን አታላ ለዛ ፀያፍ ስራዋ አመቻችታ ይዛት ባትወጣ ኖሮ እኔና ኤዱ ባልተዋወቅን ባላየኋት ባላየችኝ እህቴ ብዬ ስቀርባት ዉንድሟ አርጋኝ ባላረፈችው ነበር
እሳ እስከዛሬም እንደወንድሟ እያየችኝ የኔ ግን ምን እንደገለበጠው ባይገባኝም ወደማላውቀውና ለኔ አዲስ ወደሆነ ከባድ የፍቅር ስሜት ተገልብጦ እንዲህ ቀንና ለሊቱ ባልተገለባበጠብኝ ነበር።
አንዳንዴ ኧረ የምን አንዳንዴ ሁሌም ቢሆን በተለይ ከራሴ ጋር የሚያላትመኝ ፍቅር ከያዘኝ ወዲህ ምነው ባላወኳት እላለሁ ።
ደሞ መልሼ በተለይ ከተዋወቅን ጀምሮ በቃሌ መሰረት እንዳትሳቀቅ በማሰብ ያሰፈልገኛል ብላ ጠየቀችኝም አልጠየቀችኝም በየወሩ አቅሜ የፈቀደውን ያህል በባንክ አካውንቷ ሳስገባላት ወድያው ትደውልና•••
"በመጀመሪያ አንተን ሳይሆን ከናት እና አባቴ ባትወለድም አንተን የመሰለ ወንድም በስጦታ የሰጠኝ ፈጣዬን ሁሌም አመሰግናለሁ በመቀጠል ደሞ አንተንም እመሰግናለሁ እሺ ወንድሜ "
የምትለኝ ሁሌም የማይቀየር ንግግሯ
ሀሳቤን ያስቀይረኝና መተዋወቃችንን ሳይሆን ማፍቀሬን በመኮነን ከራሴ ጋር እጣላለሁ
ሆነም ቀረ ከብዙ ግዜ ቡሀላ ያጋጠመችኝን አሁን ከፊቴ ሶስት ደረጃ ከፍ ብላ ከአንድ ክልስ ከሚመስል ሰውና ከሌላ አዲስ እንቡጥ ሴት ጋር ተቀምጣ የምታስካካውን መሲን በጭራሽ እንደማላልፋት ወሰንኩ!
ሞባይሌን አወጣሁ!
በሁለተኛው ሲም ካርድ ስም ቀይሬ በከፈትኩት ቴሌግራም•••
ካሁን ቡሀላ የግቢ ሴቶችን እያወጣሽ እንደእቃ ስትቸረችሪ ቢያጋጥመኝ ወይ ብሰማ እሄን ጉድሽን በሁሉም ማህበራዊ ሚድያ ለቅቄ መደበቂያ እንደማሳጣሽ እወቂ!
አሀንም አብራሽ ያለችውን ልጅ ቶሎ ወደ ግቢ መልሻት ከሚል አጭር ትእዛዝ ጋር ያ ሰውዬ የላከልኝን የራሷን ቪድዮ ወደ ቴሌግራም አካውንቷ ላኩላትና ወድያው ሞባይሌን ኪሴ ከትቼ እምትሆነውን መጠባበቅ ጀመርኩ።
የቴሌግራም ማሳወቂያውን (notification) አጥፍታዋለች መሰለኝ አዲስ መልክት እንዳላት ስላልነገራት ጭራሽ ሞባይሏን ከፍታ ሳታየው ቆየች።
ስልኳ ላይ መልክት መላክ ግድ ሆነብኝ ቴሌግራም አካውንትሽ ላይ መልክት አለሽ ገብተሽ ተመልከችው ብዬ ላኩ።
ወድያው ሞባይሏ ብልጭ ብሎ ድርግም ሲል አየሁት።
ከፍታ እየተመለከተችው ነው
ቪድዮውን አይታው ነው መሰለኝ በርግጋ ከመቀመጫዋ ተነሳች ፀጉሯን እንደመንጨት እያደረጋት ቪድዮውን የላከልሽ ሰው ውጪ በር ላይ ነው ያሏት ይመስል ያደረገችው ተረከዘ ረጅም ጫማ መሆኑን ረስታ እየተውረገረገች በፍጥነት ደረጃውን ለመውረድ ስትሞክር በየር ላይ ተበረጋግዳ መሬት ተሰጣች ።
ፈገግ አልኩ አናቴ ላይ ያለውን ኬፍያ ዝቅ እያደረኩ።
ሁሉም ተደነጋግጦ ወደሷ ሲሮጥ ለቅሶ በተናነቀው ድምፅ
"ምንም አልሆንኩም እንዳትጠጉኝ!" ብላ በእልህ ተነሳችና የተጎዳ እግሯን እየጎተተች እና እስከባቷ የተሰነጠቀውን ሮዝ የራት ልብሷን ለማራገፍ እየሞከረች በደመነፍስ የሆቴሉ የውጪ በር ላይ ደረሳ ወደላይና ወደ ታች እየተገላመጠች የጠረጠረችውን ሰው መፈለግ ጀመረች።
ምንም ማየት ባለመቻሏ ተስፋ ቆረጠች ያኔ ስትወድቅ የተመታችበት ቦታ ህመመ ተሰማት ጎኗ አከባቢ ይዛ እያቃሰተች መቆም ስላቃታት ቁጭ ብላ ማልቀስ ጀመረች።
ሰውየውና አብራት የነበረችው ልጅ አጠገባ እንደደረሱ ልጅቷ በጣም ተጨንቃ ዝቅ ብላ ልታናግራት ልታባብላት በምትሞክርበት ሰአት መሲ ተቀየረችባት•••
"ዞወር በይልኝ ወደዛ ያንቺ ገዳፋ ነው እሄ ሁሉ መጀመሪያም ምንሽም አልጣመኝም ነበር ካሁን ቡሀላ ላይሽ አልፈልግም አሁኑኑ ባጃጅ ያዢና ቀጥ ብለሽ ወደ ግቢ ሂጂ !" በማለት ስታምባርቅባት ልጅቷ ሽምቅቅ ብላ ዘወር አለች ሄደች ወደግቢ ።
"ጎበዝ መሲ ትዛዝ ታከብሪያለሽ ማለት ነው!" ብዬ መልክት ላኩላትና ስልኬን አጥፍቼ ኪሴ ውስጥ ከተትኩ እሄን ግዜ እንደ እብድ አደረጋት መልክቱ እየደረሳት ያለው እዛው ሆቴል ውስጥ እየተዝናና ካለ በቅርብ ርቀት ከሚያያት ሰው መሆኑን እርግጠኛ ሆነች ።
እንደምንም ተነስታ ስልክ መደወል ጀመረች ወደኔ እምትሞክር መስሎኝ ነበር ጎረምሶቿን እየጠራች እንደሆነ የገባኝ ሶስት
ክብደት ገፊ ፣ደረተ ሰፋፊ ፣ ባስተሳሰብ ደሞ ቀፋፊ የሆኑ በጭንቅላታቸው ሳይሆን በተከመረው ጡንቻቸው የሚያስቡ ወጣቶች ከመቅስፈት ደርሰው መሲን በመክበብ ምን እንደፈጠረ ሲጠይቋት እንደተመለከትኩ ነው ።
በመሲ ጥሪ በዛ ፍጥነት ሰው ሊደበድቡ መምጣታቸውን ሳስበው ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው የሚኖሩ አሳሞች መስለው ታዩኝ
መሲ ማነች ? ምንድን ነች? ስራዋ ምንድን ነው ማንን ነው የምታስደበድበን ? ለምን?
አያገባቸውም ብቻ ትክፈላቸው እንጂ እንደ እንስሳ ወደፈለገችበት ትነዳቸዋለች ። ገልቱዎች ።
ዘበኛውን ሰው እንዳይወጣ አስጠነቀቁትና
መሀላቸው አድርገዋት ግቢ ውስጥ መዟዟር ጀመሩ ብዙ ሰው የለም ያሉትም ጥንድ ጥንድ ሆነው ነው የተቀመጡት ብቻዬን ቁጭ ያልኩት እኔ ብቻ ነኝ ።
ደረታቸውን ገልብጠው እየተሽከረከሩ የሚዝናኑትን ሰዎች ምን እንደሚሏቸው ባላውቅም አንዳንዶቹን ጠጋ ብለው እያናገሩ ያንዳንዶቹን ሞባይላቸውን ተቀብለው እየመለሱላቸው እኔ ወዳለሁበት ቦታ መጠጋት ጀመሩ።
ሂሳብ ዘጋሁ።
እነዚህን ዱባ ጭንቅላቶች ፈርቼ ሳይሆን የሰው ሆቴል ውስጥ ብጥብጥ ተፈጥሮ ላለመታሰር ስል ተነስቼ ወደ መውጫው በር ስጠጋ•••
" እንዳታስወጣው! ጥበቃ እንዳታስወጣው !"
የሚለው የመሲ ጩኸት ጆሮዬ ላይ አንቃጨለብኝ ዘወር ስል እሷ ከጀርባቸው ቆማ ሶስቱም ወደኔ ሲመጡ እየኋቸው•••

ይቀጥላል....
@yefikrclinic
@yefikrclinic
612 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 23:56:21 #እመኚኝ
ነይ ግቢ በሞቴ

#እቤት ማንም የለም የለችም እናቴ
እመኚኝ ግድ የለም ምንም አናደርግም
ወደ ውስጥ ገብተሽ በሩን ብንዘጋውም
አንድ ላይ ተቀምጠን አብረን ብናወጋም
ከንፈርሽን ልስም ወዳንቺ ብጠጋም
ብስምሽም እንካን ስጋት እንዳይገባሽ ...ምንም አናደርግም
በፀጉሮችሽ መሀል ጣቴን ባንሸራሽር
ጠረንሽ ቢሸተኝ ገብቼ አንገትሽ ስር
እጄ ሚይዘው አቶ ጡትሽን ቢነካካ እየጨባበጠ መጠኑን ቢለካ
እንዳጠረጥሪኝ ለሌላ እንዳይመስልሽ ውዴ ሙች እመኚኝ
በዚህ ሁሉ መሀል በስሜት ገንፈዬ ልብስሽን ባወልቅም ልብሴን ወድያ ጥዬ
እርቃንሽን ሆነሽ እርቃኔንም ሆኜ
አልጋው ላይ ብጥልሽ በክንዴ ዘግኜ በሚገርም ሁኔታ ፍቅር ብንሰራም እመኚኝ አለሜ ምንም አናደርግም

@yefikrclinic
@yefikrclinic
#ሼር join us
1.0K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 22:25:57 የደስታዬ ምንጭ የህሊና እረፍቴ
የህመሜ ፈዋሽ የልብ ምቴ።

ናፍቆትሽ በዛበኝ ሆድ ባሰኝ
ከአንቺ በላይ ለኔ ማን አለኝ።

@yefikrclinic
@yefikrclinic
501 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 19:54:45 ልጩህበት!


ክፍል- 20

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
በዚህ ሁኔታ ብዙ ታገልኩ ዛሬ ግን አልቻልኩም!
ለሊቱን ሙሉ በህልሜ ሳያት ስላደርኩ ነው መሰለኝ ናፍቆቴ ልኩን አለፈ ባላገኛት እንኳን ወደዛ አጥር ወደለለው ዩንቨርስቲያቸው ሄጄ ከሩቁ አይቻት ልመለስ ሄድኩ።
ደርሼ አምስት ደቂቃ ያክል እንኳን ሳልቆም ከሩቅ ኤዱን አየኋት !
ግን ብቻዋን አልነበረችም ከልጁ ጋር ነች ውስጤ ሲፈነቃቀል ታወቀኝ እዛው በቆምኩበት
ጩህ ጩህ ስሟን ከፍ አድርገህ ጥራት ጥራት አለኝ••
ግን አልጮሆኩም ዝም ብዬ ፈዝዤ ስመለከታቸው ሁለት የማላውቃቸው ሴቶች መጥተው ተቀላቀሏቸው ወድያው ልጁ ሁለቱን እጃቸውን ጨብጦ ትከሻቸውን በመግጨት ኤዱን ግን ጉንጯን በመሳም ተሰናበታቸውና በርምጃ ከግቢው መውጣት ጀመረ ውስጤ በልጁ እና በኤዱ መካከል የሆነ ነገር እንዳለ እርግጠኛ ሆነ መሰለኝ ፍርሀት ፍርሀት ሲለው ታወቀኝ።
የቆመ ባጃጅ ውስጥ ገብቶ ሲሄድ ተከተልኩት።
ከዚራ አከባቢ ሲደርስ ወርዶ የሆነ ካፍቴርያ ውስጥ ገባ ።
ትንሽ ቆየት አልኩና እዛ ካፍቴሪያ ውስጥ ድንገት እንደተከሰተ ሰው መስዬ ገባሁ ።
ልጁና አንዲት የምታምር ሴት ጎን ለጎን ተቀምጠው ጭማቂ በስትሮ እየማጉ ያወራሉ።
ክው አልኩ እሄ ልጅ ኤዱን እያጃጃላት ባልሆነ እቺ ደሞ ማነች እያልኩ በውስጤ ፈንጠር አልኩና ጀርባዬን ሰጥቻቸው ተቀመጥኩ። ስልኬን አውጥቼ ለኤዱ ደወልኩላት•••
"ወዬ የዘጋከኝ ወንድሜ!" አለች እየሳቀኝ እቺ ልጅ ደግሞ እሄ ወንድሜ እምትለውን ነገር አፏ ላይ ነው እንዴ ያተሙባት እያልኩ ለራሴ የት እንደሆነች ጠየኳት ግቢ ከጓደኛቿ ጋር መሆኗን እንደነገረችኝ
ጓደኛሽ ደና ነው? ስላት ደህና መሆኑን ነግሯት ዛሬ እሚገርም ኳስ አለ ብሏት እኛ ሰፈር ወዳለው ድሬ ዳዋ እስታዲየም ኳስ ሊመለከት መሄዱን አከለችበት"
ተሰናብቻት ስልኩን ዘጋሁትና ። ኳስ ሜዳው ካፌ ኳሷ ደሞ ልጅቷ እንዳትሆን ብቻ አልኩና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ወደ ልጅ በመሄድ ድንገት እንዳየሁት ሆኜ ሰላምታ ተለዋውጠን ፍቃደኛ ከሆነ አንድ ግዜ ለ አምስት ደቂቃ ላናግረው እንደምፈልግ ስነግረው ፍቃደኛ ቢሆንም ከኤዱ ጋር ምን አይነት ግኑኝነት እንዳላቸው ስጠይቀው
በጣም በሚያስጠላ ሁኔታ ምን አገባህ የሚል ስሜት ባዘለ መልኩ መልስ ሊሰጠኝ ሲሞክር አቋርጬው ቤተሰቦቿ እንዴት ሆነው እንዳስተማሯት ስለነገረችኝ እንዳትሰናከል በማሰብ እንጂ እሱ እንዳለው እንደማያገባኝና ያንንም ጠንቅቄ እንደማውቅ ነግሬው መልስ ሳይሰጠኝ በቆመበት ጥዬው ሄድኩ።
እንዲሁ እንደተወዛገብኩ ቀን ቀኖችን ቀኖች ሳምንትን ሳምንት ወርን ወሮች አመትን እያስከተሉ ነጎዱ እነኤዱም ሁለት አመት ተምረው የመጨረሻውን አንድ አመት መማር ከጀመሩ አንድ ወር ሆናቸው።
ያሁኖቹን ባላውቃቸውም መጀመርያ ላይ ጓደኛቿ ከነበሩት ትግስት ከመሲ ጋር አብሯ ስታብድ ትምህርቷን በአግባቡ ስላልተከታተለች እስከመጨረሻው ላትመለስ ከትምህርት ቤቱ ተባራ እዚሁ ድሬ ዳዋ ልዩ ስሙ ነምበር ዋን በመባል ወደ ሚታወቀው አከባቢ አንድ ሆቴል ውስጥ በአስተናጋጅነት ስትቀጠር ረድኤት ደሞ ለአንድ አመት ተቀጥታ ወደ ቤተሰቦቿ መሄዷን ነግራኛለች ።
ኤዱ ግን ልትመረቅ ወራቶች ብቻ ቀርተዋታል ልትመረቅ መሆኑን ባሰብኩ ቁጥር ጭንቀቴ ይጨምራል ስጨነቅ እንቅልፍ አጣለሁ ከጭንቀቴ ለመደበቅ እንቅልፍ ለመተኛት ስል ማታ ማታ ቋሚ ጠጪ ከሆንኩ ቆየሁ።
ሁሌም የምጠጣው ለመጀመሪያ ግዜ ኤዱን በሩ ላይ ቆማ ያየኋት ጭፈራ ቤት ውስጥ ነው ።
ወደ ውስጥ ከመግባቴ በፊት የቆመችባትን ቦታ ቆም ብዬ አያለሁ ኤዱ ግን የለችም ጠጥቼ ስወጣ ግን ወደዛ ከተመለከትኩ ቆማ ትታየኛለች እራሴንም እሷንም እየተሳደብኩ ወደ ቤት እንደምገባ ብዙ ግዜ ዳኒ ነግሮኛል ዛሬም እዛው እየጠጣሁ ነው።
በግዜ ስለገባሁ ሙዚቃው በስሱ ነው የተከፈተው ነገር ግን ካኔ በሁለት እርምጃ ርቀት እንደኔው ብቻውን የሚጠጣው ሰው ሰላሜን አሳጣኝ በሱ ምክንያት እራሴን ማዳመጥ አልቻልኩም ሰውየው አስተናጋጇን ያለ ምንም ምክንያት ይሰድባታል።
እሱ በሰደባት ቁጥር እኔ እናደዳለሁ።
የማይሆን ጥያቄ ይጠይቃትና መልስ አልሰጥ ስትለው ይሰድባታል •••
"ቆይ እሄ ቂጥሽ ሀይ ኮፒ ነው ኦርጅናል? ንገሪኝ ሀይ ኮፒ ነው ? ሳላረጋግጥ እማ ወይ ፍንክች "
ይላል እሚፈነክት ይፈንክተውና ምን ማረጋገጥ እንደፈለገ ሳስበው ደሞ ሳቄ ይመጣል ።
ትንሽ ቆይቶ ያጨበጭብና ሌላ ይዛለት እንድትመጣ ያዛል። ልክ እንዳመጣችለት ሊነካት እየሞከረ•••
" እንዴ ንገሪኛ እኛ ሀይኮፒም ዩዝድም ባንድ ላይ ጉዳት ነው ንገሪኛ በናትሽ !"
ሲል ልጅቷ ተበሳጭታ መልስ ስለሰጠችው ብድግ አለ ሊመታት ያኔ የኔም ንዴት ገነፈለና ተንደርድሬ በጥፊ ከመሬቱ ጋር አላትሜ አርፎ እንዲጠጣ አስጠነቅቄው ወደ ቦታዬ ተመለስኩ ።

@yefikrclinic
@yefikrclinic
820 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 21:54:46 የኔ ሙሽራ አፈቅርሻለሁ      @Yefikrclinic
620 viewsHilo, edited  18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ