Get Mystery Box with random crypto!

ልጩህበት! ክፍል- 23 አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ . . . ምኑን ከምኑ ነው እምመርጠው? | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

ልጩህበት!

ክፍል- 23

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ
.
.
.
ምኑን ከምኑ ነው እምመርጠው?
"ወይ ኤደንን እኔ ሄጄ እንዳናግራት መፍቀድ ካልሆነ ከልጅቷ ጋር ፍቅር ጀምረህ ኤደንን መርሳት!"
ጆሲ አምርሯል ግራ ገባኝ ። ኤዱን እንዲያናግራት በጭራሽ እንደማልፈልግ አውቃለሁ ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ ጡጫ ሆነብኝ ቢሆንም•••
ውስጤ እንደማይሆን እያወቀው ከዳኒ ጭቅጭቅ ለመገላገል ስል •እሺ አልኩት
በቃ እሺ!
"በቃ እሺ ምን በየትኛው ሀሳብ?"
"በቃ ካልካት ልጅ ጋር እንቀራረባለና!"
አዋ ዳንዬ አንዳንዴ እንኳን እንደዚህ እሺ በለኝ እስቲ ዳንዬ ዋናው መቀራረባችሁ ነው ከዛ ቡሀላ ሌላው ይከተላል ኤዱንስ ቢሆን ሳትቀርባት አላፈቀርካት!"
እሺ አልኩህ እኮ በቃ አልኩት። ከዛች ሰአት ጀምሮ ጆሲ ስራውን ጀመረ ።
ልጅቷን እቤት ያመጣትና መጣሁ ብሎ በመውጣት ጥሎን ይጠፋል።
መቀራረብ ብንጀምርም እውነቱን ለመናገር እሷን ለብቻዋ ከማገኛት ይልቅ ኤዱን ከልጁ ጋር ሆና ባገኛት እመርጥ ነበር።
ለሶስት ወር ልጅቷ እና ጆሲ ስራ አደረጉኝ የተቀየረ ስሜት አልነበረም በመሀል ድንገት ለተከታታይ ቀናት ጥፍት አለች።
ለስድስት ቀን ያህል ድምጿንም ስልኳንም አጥፍታ ከተሰወረች ቡሀላ በሰባተኛው ቀን እኔና ጆሲ ሰፈር ውስጥ ቁጭ ባልንበት እራሷ ጆሲ ስልክ ላይ ደወለች።
ስልኩን ለሁለታችንም እንዲሰማ አደረገና •••
" ምን ሆነሽ ነው የጠፋሽው?" የጆሲ ጥያቄ ነበር
" ምን ላድርግ ጋደኛህ ኤደን የምትባል ሰይጣን አጠናፍራዋለች መሰለኝ በተገናኘን ቁጥር ወሬው ሁሉ ከሷ አያልፍም እንዴ እኔ ልጅቷን ሳላውቃት ሁላ እንድጠላት ነው ያደርገኝ በጣም ነው የተጎዳሁት ጆሲ ከቻልክ ጓደኛህን ወይ አሳክመው ወይ ፀበል ውሰደው " ብላው እርፍ አለች ።
ጆሲ ዘወር ብሎ ሲያፈጥምኝ ተነስቼ ካጠገቡ ሄድኩ።
ከዛን ቀን ቡሀላ ከጆሲ ጋር ስለምንም ነገር ሳናወራ የኤዱ ምርቃት ሰባት ቀን( ሳምንት) ቀረው ።
ስድስት ቀን ሲቀረው ደውላ ቤተሰቦቿ ለምርቃቷ ከሁለት ቀን ቡሀላ እንደሚመጡ እና ከምርቃቷ ቡሀላ አብራቸው ወደ አዲስ አበባ እንደምትሄድ ነገረችኝ ።
ይህ ንግግሯ መብረቅ በሉት ለኔ ።ጨነቀኝ ።
ያን ቀን ጠጥቼ ብገባም እንልፍ እንቢ አለኝ እኩለ ለሊት ላይ አንድ ሀሰብ መጣልኝ።
ተነስቼ ለኤዱ ደብዳቤ መፃፍ ጀመርኩ•••
••••• ለኤደን
ኤዱዬ ህይወትን መራራም ጣፋጭም እንድትሆን ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?
እኛ ሰዎች ስላለፈው እና ስለ አሁኑ እንጂ ነገ ምን እንደሚፈጠር እለማወቃችን ነው ።
ነገን አለማወቅ የራሱ የሆነ ብዙ ጥሩም መጥፎም ገፅታዎች አሉት።
ነገ የሚከሰተውን መጥፎ ነገር ቀድመን ስናውቅ እና ነገ የሚከሰተውን ጥሩ ነገር ቀድመን ስናውቅ የሚሰሙን ሁለት ተቃራኒ ስሜቶች ናቸው።
እንዲህ ያልኩሽ አሁን የሆንኩትን ነገር ያኔ በዛ በብርድ እዛ ሆቴል በር ላይ ቆመሽ ባየሁሽ ሰአት ቀድሜ ባውቀው ምን እወስን ነበር ብዬ ሁሌም እራሴን ስለምጠይቀው ነው
"አሁን ምን ሆንክ? ትይ ይሆኖል። ምንም አታውቂምና ጥያቄሽ ልክ ነው የኔ ስስት ያኔ ካሁን ቡሀላ ወንድምሽ ነኝ ስልሽ አንቺም ተቀብለሽ የእውነት ወንድም አድርገሽኛልና ምን ሆንክ ብትይኝ ባንቺ አይፈረድም እኔ ግን ብዙ ሆኛለሁ አንቺን በማፍቀሬ እንኳን አንቺ እኔ እንኳን የማላውቀው ሌላ ዳኒ እንደሆኑኩ አውቃለሁ።
ኤዱዬ አፈቅርሻለሁ!
ይህን ስታነቢ ምን ትይኝ ይሆን?
በቃሌ የማልገኝ እራስ ወዳድ ነኝ አደል ኤዱዬ?
በጣም ይቅርታ።
ከግዜ ቡሀላ ለኔም ባልገባኝ መንገድ ውስጤ ተቀያይሮ ካቅሜ በላይ ሆኖብኝ እንጂ ያኔ ወንድም እሆንሻለሁ ከጎንሽ ነኝ እንደወንድምሽ እይኝ ያልኩሽ ግን ከልቤ ነበር!።
ሁሌም ቃሌን ያጠፍኩ መስሎ ይሰማኛል ላንቺ ስላልነገርኩሽ ምንም ባትይኝም ብታውቅ ምን ትለኛለች እያልኩ ከመሸማቀቅ አልዳንኩም።
ፍቅር የሻቱትን ማግኘት ብቻ አይደለምና የኔ እንደማትሆኚ እያሰብኩም አፈቅርሻለሁ።
ከምንም ነገር በላይ አንቺን በእውኔም በህልሜም ማየት፣ ስላንቺ ማሰብ ፣ ስላንቺ ማውራት ያስደስተኛል ። ካንቺ ውጪ ሁሉ ነገር አልጥምህ ካለኝ ወራቶች ተቆጥረዋል።
"ታድያ በነበረን ግዜ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ከነበርክ እንዴት አልነገርከኝም?
ወይም እንዴት ከፊትህ መረዳት አልቻልኩም? " ትይኝ ይሆናል
በፍቅር ንዳድ ከመለብለብ በላይ በልብ ውስጥ ያለውን የፍቅር እሳት አውጥቶ ላፈቀሩት ሰው ንዳዱን ማሳየት ለብዙ አፍቃሪዎች ከባድ ነው።
እኔን ግን አውጥቶ ከመናገሩም በላይ ከባድ የሆነብኝ ብነግርሽ የሚሰማሽን ስሜት ማሰብ ነው።
ፍቅረኛሽ ሆኜ ቢሆን አሁን ወንድምሽ በመሆኔ የተደሰትሽውን ያክል እምትደሰቺ መስሎ አይታየኝም ።
ካፌ ሻይ ቡና እያልን ፊት ለፊቴ ቁጭ ብለሽ ከናት ካባቴ ባትወለድም አንተን የመሰለ ወንድም በስጦታ ስለሰጠኝ እያልሽ ፈጣሪን ስታመሰግኚ ስሰማ እንኳን ልነግርሽ ማፍቀሬን የምታውቂብኝ እየመሰለኝ ምክንያት ፈጥሬ ካጠገብሽ እሽሻለሁ ።
ጆሲ ጓደኛዬ ምን እንደሚለኝ ታውቂያለሽ ኤዱዬ?
••••" አንተኮ መፍታት ያቃተህ መጀመሪያ ላይ እራስህ አጥብቀህ ያሰርከውን ቋጠሮ ነው አልፈታ ባለህ ቁጥር ደግሞ በንዴት ለመበጠስ እየሞከርክ የበለጠ ታጠብቀዋለህ!" ይለኛል
እውነቱን ነው ትዝ ይልሻል እዱዬ?
ስለመሲ ስናወራ አንድ ሰው ውለታ ውሎልሽ ውለታውን በመንተራስ ከፍላጎትሽ ውጪ የሚጫንሽ ከሆነ ውለታ ሳያስቀድም ተመሳሳይ ጥያቄ ከሚጠይቅሽ ሰው በላይ እርኩስ ነው ብዬሽ ነበር ።
እኔም የፍቅር ጥያቄዬ ካደረኩልሽ ትንሽ ውለታ ጋር እንዳይያያዝብኝ ፈራሁ።
አንቺንም እኔን ወንድም እንጂ ፍቅረኛ የማድረግ ፍላጎት ውስጥሽ ሳይኖር የምጫንሽ ጥያቄዬን ባለመቀበልና እኔን ባለማስከፋት መሀል ሆነሽ የምትጨነቂ መስሎ ታየኝ ።
በዚህ መሀል እናንተ ባታዩኝም ከልጁ ጋር ሆኖችሁ ብዙ ቦታዎች ታጋጥሙኝ ጀመር።
ያኔ በሱም ባንቺም ሳይሆን በራሴ ይበልጥ መናደድ ጀመርኩ ።
ህመምህ መድሀኒት የለውም አትድንም እንደተባለ በሽተኛ የፍቅር ህመሜ ፈውስ የሆንሽውን አንቺን የኔ እንደማላደርግሽ ተረዳሁ ።
ኤዱዬ በመመረቅሽ እንኳን ደስ አለሽ!
በመመረቅሽ የተሰማሽን ደስታ ትንሽ ሳታጣጥሚውና ከድሬ ሳትወጪ አንብበሽው ሌላ ስሜት ውስጥ እንድትገቢ ስላልፈለኩ ነው ይህን ደብዳቤ በእጅሽ ሳልሰጥሽ ከምርቃቷ ቡሀላ ወደ አዲስ አባባ ስሸኛት ሳታየኝ የልብስ ሻንጣዋ ውስጥ አስቀምጥላታለሁ ባየችው ግዜ ትየው ብዬ የወሰንኩት።
በነበረን ስሜት ወንድምሽ ሆኜ ልሸኝሽ ቀናቶች ቀርተዋል ለዛም ተዘጋጅቻለሁ ።
የኔ ኤደን ዛሬም ቢሆን ስላወኩሽ ደስተኛ ነኝ።
የማንም ሁኚ እኔ ግን አፈቅርሻለሁ። መቼም ቢሆን አረሳሽም። ዝምምምም ብዬ ሳፈቅርሽ እኖራለሁ።
ሰላም ሁኚ!
ዳኒ ነኝ።
••••
የመጨረሻው ክፍል 24 በመሆኑም ቻናላችንን ሼር በማድረግ ቀጣዩን ክፍል ያንብቡት

ይቀጥላል....
@yefikrclinic
@yefikrclinic
@yefikrclinic