Get Mystery Box with random crypto!

❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikrclinic — ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikrclinic — ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️
የሰርጥ አድራሻ: @yefikrclinic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39.06K
የሰርጥ መግለጫ

🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓
❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤
❤ HBD ለማለት፤ 🎂
❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶‍♀
❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦‍♂
🤩 የፈለጉትን የፍቅር ቃል ለኛ ላይ ይላኩልን 📬 በፍጥነት እናደርሳለን። @yefikrclinic_bot
contact us 👉 @yefikrclinic
ላይ ይላኩሉን

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-02-23 22:51:29
Amen
15.9K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-15 10:53:20       
          
              


   በጣም ተጠግተሽ ብታይው አንቺ እንዳለሽበት ታውቂያለሽ??
ታውቂያለሽ .. ትናንትና ማታ ከቤቴ ገባሁና እግዚአብሔር ስለሰጠኝ
መልካም ነገሮች ማሰብ ጀመርኩ። ጊዜ አልፈጀብኝም ወዲያው አንቺ
ትዝ አልሽኝና ፈገግ አልኩ...ፈገግ ፈገግ በረጅሙ
ፈገግግግግግግግ... .
ታውቂያለሽ አይደለ ከምንም ነገሮች በላይ የሚያስደስተኝ ጠዋት
ከእንቅልፌ ተነስቼ አንቺ የኔ እንደሆንሽ ማሰቡ። ኡፍፍፍፍፍ ታድየ
ለእያንዳንዱ ሂወት ወይም የህልውና ቅጠላ ቢያንስ አንድ ነገር
ምክንያት ይሆነዋል። ዝናብ እንዲዘንብ ደመና ይኖራል፣ አበባ
እንዲያብብ ዝናብ ያስፈልጋል፣ አንቺም ልክ እንደዚህ ነሽ። ለኔ መኖር
አንቺ እንደምትፈለጊ ታውቂያለሻ? .
እንዲሁ ትናንትና ማታ በሂወቴ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያላቸውን ሰዎች
ልዘረዝር አጀንዳ አወጣሁና በእርሳስ መጻፍ ጀመርኩ። አንቺ ላይ
ስደርስ ግን በእስኪብርቶ መጻፍ እንዳለብኝ ተሰማኝ ምክንያቱም አንቺ
መቼውንም አትቀየሪምና። ታውቂያለሽ አይደለ ምን ያህል
እንደምተማመንብሽ?
ሁልጊዜ ስምሽን ስጠራው እርበተበታለሁ። አንቺም አልሽ!? "ምን ሆነክ
ነው ግን ስሜን ስትጠራው ልብህ እንዲህ በሃይል የሚመታው?" እኔም
ይሄን አልኩ... ፍቅርሽ በልብ ትቦዎቼ ገብቶ እየሮጠ ነው። ታውቂያለሽ
እውነቴን መሆኑን?
ታውቂያለሽ አይደለ ምንግዜም እንደምወድሽ? ምንግዜም
እንደማፈቅርሽ? ምንግዜም የመጀመሪያየ ምርጫየ እንደሆንሽ?
ታውቂያለሽ አይደለ ልትወድቂ ባልሽብኝ ቁጥር እንደምደግፍሽ?
ብዙ ጊዜ እግዜር ለሰዎች የተለያየ ስጦታ ያዘንብባቸዋል። ግን
እግዜር ለምን ስጦታ በመስጠት ይደክማል። ለምን ልክ እንደ ፍቅሬ
ያለ አንድ ሆኖ እንደ ሺ የሚጠቅም ስጦታ ሰጥቶ አይገላገላቸውም!?
     ብይአስቤለሁ 
  ፍቅር ማለት መቀበልን ብቻ ሳይሆን
መስጠትንም ይፈልጋል
☞መፀሀፍ አብቤ እፎይ ባልኩኝ ሰአት
ምነው ዛፍ በሆንኩኝ እያልኩ እመኛለሁ

ወይ ፍሬ አፈራለሁ
ወይ ጥላ እሆናለሁ

☞ቢያንስ አንድት ወፍ በቀን ወዳኝ
ወይም በውል አምናኝ
ጎጆ ቤቷን ሰርታ ልጆቿን ጥላልኝ
ምግቧን ልትፈልግ ስትበር አያለሁ
በውል ተማምናብኝ
እንደምትመካ እተማመናለሁ
ያኔ በትክክል ለአደራ እበቃለሁ፡፡


✦━━━━━━━━

ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

Join us

@yefikrclinic
25.9K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-11 15:17:20 ​​━━━━━━━━━━━━━━━━


እናትነት


እውነተኛ_ታሪክ

ገነት አራት ልጆች አሏት ሁሉም ወንዶች ናቸው የመጀመርያ ልጇ ቢንያም 24 አመቱ ነው ሁለተኛ ልጇ ሱራፌል 22 አመቱ ሦስተኛ ልጇ ሳሚ16 አመቱ የመጨረሻ ልጇ አሜን ግን ገና 3 አመቱ ነው። ገነት ና ባለቤቷ ኪሮስ የሚያስቀኑ ደስ የሚሉ ባል ና ሚስት ናቸው። ኑሮአቸውን የሚያስተዳድሩት አንድ ሬስቶራት ከፍተው እየተጋገዙ በመስራት ነው ። በሳምንቱ የመጀመርያ ቀን ጥዋት ቤታቸው ተንኳኳ ፖሊሶች ነበሩ ኪሮስን ይዘዋቸው ሔዱ ምክንያቱም እሳቸው ትግሬ ስለሆኑ ሰሞኑን በሚሰራው ወንጀል ፓሊሶች ጥርጣሬ ስላደረባቸው ነው። ገኒ ባለቤቷ ስለታሰረባት ብቻዋን ቤት በማስተደደር ተጠምዳለች ለልጆቿ ሚያስፈልጋቸውን ነገር ካሰናዳችላቸው በኋላ ባለቤቷን እስር ቤት ሔዳ ካየችው በኋላ ወደ ሬስቶራንቱ የሦስት አመት ልጇን አሜንን ይዛ ትሔዳለች አሜንም አጠገቧ መጫወችያ ሰታው በአይኗ እየተቆጣጠረችው ሲያለቅስ እያባበለችው ሲተኛ በጀርባዋ አዝላ ስትሰራ ቆይታ ማምሻዋን ወደ ማደርያዋ ትመለሳለች። በባለቤቷ አለመኖር ብትከፋም ብታዝንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ትሰራለች። ኪሮስ ከታሰረ ሦስት ቀን ሆኖታል ገኒ እደተለመደው ተነስታ ልጇን ይዛ ወደ ስራ ቦታ ሔዳ ለአሜን መጫወቻውን ሰታው በስራ ተጠምዳለች ይሔኔ ነበር አሜን ከ አይኗ የተሰወረው ገኒ ስራዋን ጨርሳ ቀና ስትል ልጇን ታጣዋለች ወዴት እንደሔደ ለማጣራት ተጣራች አሜን አሜን የት ነህ አሜን ግን መልስ የለም ደግማ ተጣራች አባ አባቴ የት ሔድክብኝ አሁንም መልስ የለም ትንሽ ዞር ዞር ብላ ስታጣው ምናልባት ከተስተናጋጅ ጋር ከሆነ ብላ ወደ ፊት ለፊት ሰው ላከች ግን የለም አሁንም ደግማ ተጣራች አሜን አባቴ ግን መልስ የለም። ገነት ደነገጠች ምናልባት ወደ ጓሮ ሔዶ ይሖን ሩጫ ወደ ጓሮ እየተጣራች ገሰገሰች። ጓሮ ቆሻሻውን ለማስመጠጥ ብለም የከፈቱት 5ሜ ያልተከደነ ጉድጓድ አለ ከ ዛሬ ነገ አስከድነዋለው እያሉ ረስተውታል ገነት ሮጣ ከደረሰች በኋላ ወደታች ለማየት ብትሞከርም ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ ሊታያት አልቻለም ባትሪ አስመጥታ ስታይ ልጇ በጭንቅላቱ ተደፍቶ ታየዋለች በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሉታል እንዲ ነው ። ገነት አልቻለችም ጮኸች ኸረ ልጄ ኡኡኡ ልጄን አድኑልኝ ምትይዘው ምትጨብጠው ጠፋት አብረዋት የነበሩ ሰራተኞች ተደናገጡ ሰፈሩ በጩኸት ተናጋ እናት ግን ደቅቃ መጠበቅ አልቻለችም ከመቅስፈት ዘላ ወደ ጉድጓዱ ገባች በሷ መግባትም እንደገና ሌላ ጩኸት ኡኡኡ ድረሱልን ።ገኒ እንደገባች በፍጥነት ልጇን ከተደፋበት አነሳችው ምታደርገውን አታቅም በደመ ነብስ ልጇን አቅፋዋለች በህይወት ነበር ግን ትንፋሹ ይቆራረጣል ልጄን ልጄን አድኑልኝ ብላ ጮኸች ደጋግማ ልጄን አድኑልኝ ትላለች ልጇ አሜን በትንፋሽ ማጠር ና ቆሻሻም በመጠጣቱ በጣም ደክሟል። አብረዋት ልጇን ሲያፋልጓት የነበሩ ሰራተኞች በናት ና ልጅ ቆሻሻ ጉድጓድ ውስጥ መግባት ቢደናገጡም በፍጥነት ተጨማሪ ሰው ጠርተው እንዲሁም ጩኸቹን የሰሙ ሰዎች ተሰብስበው አሶጧቸውና የህክምና አርዳታ እንዲያገኙ ወደ ሆስፒታል ወሰዷቸው። ገነት በወገቧ ና በእጇ ላይ ጉዳት ቢደርስባትም የሷ መጎዳት አልታያትም ለዶክተሮቹ በልቧ ደሞ ፈጣሪን ልጇን እዲያድኑላት ተማፅናቸዋለች እዳሳቧ ፈጣሪም አላሳፈራትም ልጇ ሰላም ሆኖላታ በእግዚአብሔር ቸርነት ልጇ ተርፎላታል አሁን ደስተኛ ናት ።
በአሁን ሰአት እግዚአብሔር ይመስገን አናትም ልጅም በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው።
ምን አይነት መሰዋትነት ነው? ምን አይነት እናት ናት ነብስ እስከመስጠት ልጇን የምትወደው? ፈጣሪ ለናቶች የሰጣቸው ልብ ምን አይነት ነው? ይሔ የኔ ጥያቄ ነው። ድንቅ እናት የምትወደድ ለነብሷ ያልሳሳች እኔ መቼም አረሳትም ፈጣሪ አድሜሽን ያርዝመው።
ክብር ፣እድሜ ና ምስጋና ለእናቶች



━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

Join us  @yefikrclinic
18.8K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-09 22:34:51 ቤተልሔም

የመጨረሻ ክፍል

በ ያድ

ክፍል 18
••••••••••••ወደ ውስጥ ደስ እያት ገባች ።
ናሆም ግን በተቃራኒው ህሊናውን አጥቶ ቤቱን እንኳን ፈርቶት ሆቴል ነበር ያደረው ..........

ከ 1 አመት ቦሀላ...

ህሊና 3ኛ አመቷን አጠናቃ ክረምቱንም አሳልፋ ዛሬ መልሳ ወደ ዩኒቨርሲቲ ልትሄድ ጥቂት  ደቂቃዎች ይቀሯት ነበር በነዛ ደቂቃዎች ቤቲን ቀጥራ አግኝታት አንድ አመት ሙሉ በልቧ የተቀመጠ መልስ ያላገኘውን ጥያቄ ጠየቀቻት
"አምና ስለናሆም ስጠይቅሽ ስለሱ በቀል እንደምታስቢ ነግረሽኝ ነበር አሁንም ለረፍት ስመጣ አላገኘሁትም የት እንደሆነም አልሰማሁም ቤቱም ባንኳኳ ማንም አይከፍትም የት እንዳለ ታውቂያለሽ? "
"አዎ"
"የት ነው?"
"እስርቤት"
"ምን? በምን ወንጀል?"
"ያኔ በቀል ያልኩሽ ያለምክንያት ሳይሆን የወንድሜ አስገዳይ እሱ ስለነበር ነው ያንን ያወኩት............................................እና የዛን ቀን ምሽት ቅውስ ብሎ ወጣልሽ ከዛ ቦሀላ ቤቴ ድርሽ ብሎ አያውቅም በየቀኑ ስለ ፊሊ እያስታወስኩ እያነሳሁ አሰቃየሁት እኔ እንደዛ በመሆኔ ተፀፅቶ ብቻ አይመስለኝም እጁን ለፖሊስ የሰጠው አስታውሳለሁ እውነቱን እንዳወኩ የነገርኩት ቀን የሆነውን መቼም አልረሳውም እሱ ቤት ሆነን.
"ሰርፕራይዝ " አልኩት ድንገት በዝምታችን መሀል
"ምን ተገኘ የኔ ፍቅር"አለኝ
"የወንድሜን ገዳይ አገኘሁት "
"ምን?" እየደነገጠ
"አዎ ምነው ደነገጥክ?"  እቅፋን ከትከሻዬ ላይ አስለቅቄ ተነስቼ ፊትለፊቱ ቆምኩ
"ኧረ አልደነገጥኩም"
"ምነው አንተ ነህ እንዳልልህ ፈራህ እንዴ?"
"ቤቲዬ ቀልዶችሽ እኮ...."
"አልቀለድኩም!" ጮህኩበት
" አልቀለድኩም አዎ ናሆም ሁሉንም እውነት ደርሼበታለሁ ፊሊ የስራ ባልደረባህ ነበር እናም በ አንድ ተራ ገንዘብ ያልታመነ ስለመሰለህ ብቻ አስገደልከው"
"አይደለም እኮ ቤቲ"
"እንዳትጨርስልኝ እሺ ቆይ ከኔ ደግሞ ምን ፈለክ እኔንም ልታስገድለኝ ነው? ... ግደለኝ!    ግደለኝ ይኸው ግደለኝ ከዚህ የተመቻቸ ጊዜ አታገኝም ! .... ግን ያ ሁሉ ለምን ? ለምን?" አቅፎኝ ሳለቅስ ለማባበል ሞከረ የዛን ሰአት ግን የምናገረውን አላውቅም ከልቤ የሚሰማኝን ሁሉ ነበር የምናገረው ...
"ልቀቀኝ ! አታስብ አልከስህም አላሳስርህም ሁለተኛ ግን አይንህን ማየት አልፈልግም አጠገቤ እንዳትደርስ አላውቅህም አታውቀኝም!" ብዬ እየጠራኝ ጥዬው ሄድኩ ከዛ ቀን ጀምሮ አጊንቼው አላውቅም ቤት ሁላ ሳይቀር መጥቶ አንኳኩቶ ነበር በወር ከምናምኑ እንደታሰረ ሰማሁ ሄጄ በደምብ ሳረጋግጥ በ ፊሊሞን እና በሌሎች ሁለት ሰዎች ግድያ ወንጀሉን መስራቱን አምኖ ፍርድ ቤት ቀጠሮው በቅርቡ እንደሆነ ሰማሁ ፍርድቤቱ ብያኔ ቀን ላይ በአካል ተገኘሁ እናም የእድሜልክ ፅኑ እስራት ሲፈረድበት በራሴ ጆሮ ሰማሁ እናም ናሆም እስር ቤት ነው"

"ይገርማል በፍፁም ናሆም እንደዚህ አይነት አውሬ አይመስለኝም ነበር ይገርማል ግን ከህግ ያመለጠውን ነገር ያውም በራስሽ መንገድ ማውጣትሽ ያውም ናሆምን ከሚያክል አደገኛ ሰው ላይ " ህሊና ወደ ጅማ የሚወስዳት ቅጥቅጥ መኪና ውስጥ ገብታ ከፊት አለው ወምበር ላይ ተቀምጣ ቤቲ ደግሞ ከስሯ ዝቅ ብላ ቆማ ነበር የሚያወሩት ሰው እየሞላ ነው
"አዎ ፍቅር ከ ጥላቻና ግብግብ የተሻለ ጉልበት እንዳለው አምናለሁ ለዛም ነው ናሆምን መበቀል የቻልኩት ፍቅር ደግሞ የማንም ሰው ድክመት ነው ማንንም ጥፋተኛ ከህግ በላይ ከሆነ ከህግ በላይ በሆኑ መቅጫ አንቀፅ በሌላቸው ህጎች መቅጣት ልምዴ ነው ደምን በደም የምንበቀልበት ዘመን አልፏል የኔ ቆንጆ እነዚህ  አለንጋቸው የሚያርፈው አካል ሳይሆን አእምሮ እና ልብ ላይ ነው "
"ልክ ነሽ ! ይገርማል..."
"እ ማማ ? ትሄጃለሽ ወይስ?" አላት ረዳቱ በሩን ይዞ ቤቲ በ እጇ ጨብጣ ከተሰናበተቻት ቦሀላ ወረደች "እፎይ አሁን የሰላም ህይወት መኖር እጀምራለሁ አለች በውስጧ በረጅሙ እየተነፈሰች" ህሊናን በመስታወቱ ላይ እጇን  እየተሰናበተቻት ... ህሊናም እጇን እያውለበለበችእያውለበለበች  ሳታስበው በተቆጠበ ድምፅ በሹክሹክታ ከራሷ ጋር ታወራለች መኪናው እየተንቀሳቀሰ ነው..
"በዚህ አለም ላይ  አንቀጽ ያልወጣላቸው ጉዳቶች ፍትሀቸው ምን ይሆን " የህሊና የመጨረሻ ቃል ነበር ! ..............


                       ተ ፈ ፀ መ



፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ፍቅር ለዘላለም ይኑር!!!፧፧፧፧


2015 E.C
•••••••••••••••••••••|  |•••••••••••••••••••••

     ደራሲ = @yaddiii ON @yefikrclinic

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

Join us @yefikrclinic

♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲   
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ
13.5K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-06 19:21:32 ቤተልሔም



ክፍል : 15



••••••••••••••••• እየተሳኩላት ይመስላል ወዲያው ቅርብ ጓደኞቿ ጋር ደውላ ወጥተው እንዲጠብብቋት እና ፈታ እንዲሉ ነገረቻቸው ከነዛ ውስጥ አንዱ ልዑል ነበር
°°°
ናሆም እቤቱ ገብቶ ስለ ቤቲ ማሰብ ጀመረ ቅድም ሲያቅፋት የተሰማው ስሜት ማንንም ሲያቅፍ ተሰምቶት አያውቅም በሆነ በተለየ መንገድ ልቡ ውስጥ እንደገባች ገብቶታል በየቀኑ ሴት ሲያፈራርቅ የነበረው ናሆም ዛሬ ከቤቲ ሌላ የሴት ስልክ ማንሳት አስጠልቶታል ለመጀመሪያ ጊዜ የህሊና ፀፀት ውስጥ ገብቷል ከራሱ እና ከማይደራደርበት ክብሩ የበለጠ ቦታ በህይወቱ ላይ ሲሰጣት ይታወቀዋል በጣም በጣም!......
ሌላኛው ቀን ነጋ የቀኑን መንጋት አስተውሎ ሳይጨርስ ሰአቱን ሲያይ ረፍዷል በፍጥነት ተነስቶ ስራ ቦታ ሄዶ የትላንቱንም ጭምር ስራውን ሲሰራ ዋለ በጣም ቢዚ ስለነበረ ስለሌሎች ነገሮች ማሰላሰያ ጊዜ አልነበረውም ምንም ሳያርፍ መሸ 12:30 ሆነ 1:30 ላይ ቢሮውን ዘግቶ ወጣ ማንንም ሳያገኝ ቤቱ ሄዶ ለማረፍ ቢሞክርም አልተሳካለትም ቤቲን ሳያገኛት ሳያያት መዋሉ ረብሾታል ከቀኑ ውስጥ የሆነ ነገር እንደጎደለ ተሰማው እንደ ትራ ለመቁጠር ቢሞክርም አልተሳካለትም..... መኪናውን አስነስቶ ቤቲ ጋር መሄድ ጀመረ
°°°
ቤቲ ቤት ከገባች ቆይታለች ራቷን በልታ ወደ መኝታ እየሄደች ነበር ድንገት ከውጪ ክላክስ ሰማች ወዲያው በ ፎቁ መስታወት ስታይ የናሆም መኪና ነበር ሁኔታው ቢያስፈራም አማራጭ ስለሌለ መክፈት ነበረባት ወዲያው የውጭው በር በእጅ መንኳኳት ሲጀምር ወጥታ ከፈተች ከኋላዋ ሽጉጧን ይዛ ነበር ልክ ስትከፍት ሰላም እንኳን ሳይል አቀፋት በሁኔታው ብትደናገጥም ምንም እንዳልተፈጠረ ሲያቅፋት አቀፈችው። ረጅም ሰአት ቆይተው ተላቀቁ .....
"ምን ሆነህ ነው በዚህ ሰአት?"
"ና... ናፈቅሺኝ " ቁና ቁና እየተነፈሰ
"ምን?" እየሳቀች
"አዎዋ ዛሬ እኮ አልተገናኘንም"
"ታዲያ ሳንገናኝ ብዙ አመታትን ኖረን የለ እንዴ ? "
"ላልውቅሽ አዎ"
"እሺ አሁን አገኘኸኝ ይኸው "
" እሺ......................ልሂድ?"
"አዎዋ መሽቷል እኮ"
"ህህህ ታዲያ ሲመሽ እኮ ግባ መሽቶልሀል እደር ነው የሚባለው
"እንዴ ገና ነው እኮ ብላ የእጅ ሰአቷን አየችው••••••••••


ይ..
ቀ......
ጥ.........
ላ.................
ል........,,............



ሙሉ ታሪኩን ለመጨረስ @yefikrclinic
12.6K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, edited  16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 22:55:53
.....ለወደድካት እንስት
ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጅ
ልብህን አትስጣት..
12.7K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 07:36:30 ዳግም ትንሳኤ
እንኳን ለዳግም ትንሳኤ
በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
3.5K viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 20:02:54 Live stream finished (2 minutes)
17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 19:59:55 Live stream started
16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 15:05:31 ​​ #ከላይ #የቀጠለ
​የሚያስችል ቁመና፣ መልክና ተክለሰውነት ያላት ግሩም ሙሉ ሴት እንደሆነች በድፍረት መመስከር እችላለው..እርግጠኛ ነኝ እኔ ከጎኖ ባልኖር ኖሮ እስከዛሬ ብቻዋን ያለባል የምትኖር አይነት ሴት አልነበረችም…እና ቢያንስ ዘና ለማለት አሁን ሰውዬው ጋር ወጣ ብትል ብዬ አሰብኩ…ግን አንዴት እንደዛ ላስብ ቻልኩ…..?.እንዴት የእናቴ ብቸኝነት እሰከዛሬ ሳያሳስበኝ ዛሬ ሊያሳስበኝ ቻለ…...?ሁለት ምክንያት ነው ያለኝ፡፡አንደኛው እናቴ ዘና ለማለት ወጣ ብትል…እኔም እዚህ ከትርሲት ጋር የጀመርኩትን ፍቅር እቀጥላለው በሚል እሳቤ….ሁለተኛው ግን እናቴ ለዘመናት ምን እንዳጣች በደንብ ያወቅኩት ሰሞኑን በተለይም ዛሬ ስለሆነ ነው..ከሚወዱት ሰው ከንፈር ላይ ከንፈርን ማጣበቅ ምን አይነት ደስታ እንደሚያጎናጽፍ አሁን ነው የተረዳውት…በሚያፈቅሩት ሰው መታቀፍ..በሚወዱት ሰው መዳሰስ….እነዚህ ነገሮች አንድ በህይወት ላለ ጤነኛ ሰው ለመኖር ከሚያስፈልገው አየር እኩል ዋጋ ያላቸው መሰረታዊ የደስታው መፍለቂያ ሪሞቶች መሆናቸውን መረዳቴ ነው….እናቴ ይሄንን ነው የሰዋችው..ለእኔ ለልጇ ስትል..፡፡ለአንድ ቀን አይደለም..ለግማሽ ዕድሜዋ..፡፡እኔ ግን ለሽርፍራፊ ሰከንድ ከነበርኩበት የደስታ መንደር ስላወጣችኝ ቅሬታ ተሰማኝ..አይገርምም..? …
‹‹እቴቴ…አረ እዚህ ብተኛ ይሻለኛል››
‹‹እንዴት ይሻለኛል..?››
‹‹ማለቴ....?ምን መሰለሽ..?›…››ምትናገረው ጠፋባትና በንዴት ጉንጮቾ ቀሉ..እናቴ ፈገግ አለች
ትርሲት‹‹በቃ እሺ እንዳልሽ…››ብላ ወደ እዛኛው ክፍል መራመድ ጀመረች
‹‹አረ ቀስ በይ….ስቀልድ ነው…ቅድም ገዝቼልሽ ሳልሰጥሽ ስለረሳው ይሄንን ልሰጥሽ ነው የመጣውት….››ብላ በቀኝ እጇ ይዛው ነበረውን ፔስታል አቀበለቻት
‹‹ምንድነው..?››
‹‹ስጦታ ነው… ይሄ ደግሞ ያንተ ነው››ብላ በግራ እጆ የነበረውን ፔስታል አልጋው ላይ ከጎኔ ወርወር አድረገችው..
ትርሲት እናቴን‹‹አመሰግናለው..››ብላ ተንጠራርታ ጉንጮን ሳመቻት
እኔም ተጨማዶ የቆየውን ፊቴን በፈገግታ ተረከኩት ….እንዲህ ሰላሳ ሁለት ጥርሶቼ የተሰጡት እናቴ ለሰጠችን ስጦታ ሳይሆን ትረሲት ከእኔ ጋር የማደሯ ጉዳይ አሁንም ባለመሰረዙ ነው….አናቴ ጎንበስ ብላ ግንበሬን ሳመችኝና…. እሷንም ጉንጮን ስማ‹‹..በሉ ደህና እደሩልኝ….በጣም እወዳችሆለው…››ብላ ወደ በራፉ እርምጃ ጀመረች
‹‹እኛም እንወድሻለን››አለች ረትርሲት እኔንም ወክላ…እናቴ ሄደች ትሪሲት በራፍን ቀርቅራ እየፈነጠዘች መጣች….
‹‹ይህቺ እቴቴ ግን ተንኮለኛ ነች….ካንተ ልትለየኝ መስሎች ከፍቶኝ ነበር….›› አለቺኝ…እኔም ተመሳሳይ ስሜት ተሰምቶኝ እንደነበር በምልክት ነገርኳት
እስቲ ስጦታው ምን ይሆን.? ልየው ብላ ፔስታሉን ከፈተች እና እጇን ወደ ፔስታሉ ሰዳ አወጣችው …ስስ ሮዝ ከለር ያለው የሚያምር ስስ የለሊት ልብስና የሚያማምሩ ሶስት ፓንቶችን ናቸው…‹‹ወይኔ ሲያምሩ .?ቆይ ያንተስ ምንድ ነው.?››ብላ ወደ አልጋው ጎንበስ አለችና ለእኔ የመጣውን ስጦታ ከፔስታሉ አወጣችው…‹‹ሚያምር ጋዎን ፒጃማ እና ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ፓንቶች ናቸው
‹‹አይ እቴቴ….አለች ትርሲት እየተፍለቀለቀች…ቆይ እንደውም ልለካው..››አለችና የለበሰችውን ቀሚስ አወለቀች…ብስል ቀይ ገላዋ ለእይታ ተጋለጠ …ቀይ ቀለም ያለው ጡት መያዣዋ ጡቶቾን በግልጽ እናዳላይ ከልለውኛል…ግን መቀሰራቸውን ማየት ብቻ ልብን ያርዳል እና ተመሳሳይ ቀይ ቀለም ያለው ፓንቷ ይታየኛል፡፡
ከፓንቶቹ መካከል አንዱን አነሳች…‹‹እንዴ ምን ነካኝ .?እንዴት አድርጌ ልለካው›››ግራ በመጋባት አፍጥጣ እያየችኝ ጠየቀችን
‹‹አንተን እኮ ነው..ፊትህን ወደ እዛ አዙርልኝ ..››
ይበልጥ አይኖቼን በልጥጬ አፈጠጥኩባት
‹‹‹ምን አይነት ፈጣጣነው በእግዚያብሄር…‹‹ብላ ፊቷን ከእኔ በተቃራኒው አዞረችና የለበሰችውን ፓንት ወደ ታች ሳበችው..ጎንበስ ብላ ከእግሮቾ አሾልካ ለማውለቅ ጎንበስ ስትል ችምችም ባለ ቁጥቋጦ ደን የተሸፈነውን ስንጥቅ ስምጥ ሸለቆዋን በከፊል ሾፍኩት…….በእሷ ቤት ስለዞረች አይታይም አሉ…. ከዛ አዲሱን ፓንት አደረገችና ‹‹..አያምርም…እየው እስቲ ..››ልክ በተለያ የፈረንጅ ቻናሎች እንደማያቸው ሞዴሎቹ እየተምነቀነቀች እና እየተውረገረገች በመሽከርከር አስጎበኘችኝ ..ከዛ ቢጃማዋን አነሳችና ለበሰችው…ስስ ከመሆኑ የተነሳ መላ ሰውነቷን ወለል አድርጎ ያሳያል..ቢሆንም ግን ያምራል…ያምራል ብቻ ሳይሆን ያማልላል..ያማለለኝ ግን ቢጃማው አይመስለኝም በቢጃማው የተጠቀለለው ውቡ ገላ እንጂ…
በል እንግዲህ የእኔን ስጦታ በደንብ ጎብኝተሀል አሁን ተራው ያንተ ነው በማለት ቅድም አልብሰኝ የነበረውን አልጋ ልብስ ከሰውነቴ ላይ ገፈፈች..ከዛ የሱሪዬን ቁልፍ ፈታች..ከዛ ዚፑን ወደ ታች አንሸራተተችው….ከዛ ሱሪያን እየጎተተች ከእግሮቼ ላይ ሞሽልቃ አወለቀችውና ኮመዲኖ ላይ ወረወረችው….ከዛ ከውስጥ የለበስኩትን ሰፋ ያለ ፓንት በተመሳሳይ ሁኔታ አወለቀችውና ሱሪውን ያስቀመጠችበት ቦታ አስቀመጠች…፡፡ከወገቤ በታች እርቃኔን ቀረው.‹‹.ቆይ ቆይ ከላይ ያለውም መውለቅ አለበት›› አለችና የለበስኩትን ቲሸርት ከነ ውስጥ ካኔቴራው ወደ ላይ ጠቅልላ አወለቀችው…ሙሉ በሙሉ እርቃኔን ቀረው..‹‹አሁን ያንተን ፓንት እንሞክረው ከዛ ጋዎንህን ታደርግና ተቃቅፈን ለጥ ነው..››ብላ ወደ ፓንቱ ልትዞር ስትል እጆን ቀጨም አድርጌ ያዝኮት…
‹‹እንዴ ምነው.?››
ጎተትኮት
‹‹ቆይ መጀመሪያ ላልብሰህ››አልሰማዋትም…በአንድ እጄም ቢሆን መጎተቴን ገፋውበት … እርቃን ገላዬ ላይ ስቤ አጣበቅኮት..‹‹አንተ ልጅ ይሄ እጅህ በጣም እየጠነከረ እና እያንገላታኝ ነው››ብላ ወቀሳ በሚመስል ግን በደስታ በተወጠ ሰሜት እንድትለጠፍልኝ ከፈለግኩት በላይ ተለጠፈችብኝ…እንድታቅፈኝ ከፈለኩት በላይ ጨመቀቺኝ…እንድትስመኝ ከፈለኩት በላይ መጠጠቺኝ..ይህቺ ልጅ መቼስ እግዜር ነው ላሳለፍኩት የሠለፈ ደባሪ ህይወቴ ማካካሻ የሸለመኝ… እንጂማ አሁን እኔ ለፍቅር የምመረጥ ሰው ነኝ..አሁን እኔ በፍቅር የምሳም በፍቅር የምላስ ሰው ነኝ…እንዲሁ ፈርዶባት እንጂ …፡፡ስታሳዝን

ይቀጥላል

VOTE ማድረግ እንዳይረሳ
@yefikrclinic
@yefikrclinic
@yefikrclinic
236 viewsY⃨A⃨D⃨I⃨, 12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ