Get Mystery Box with random crypto!

​​ #ከላይኛዉ #የቀጠለ ​በልጆቾ የምትጨክን….ከዛ ቡኃላ አባቴ እኔን መራገም ጀመረ… የበለጠ | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

​​ #ከላይኛዉ #የቀጠለ
​በልጆቾ የምትጨክን….ከዛ ቡኃላ አባቴ እኔን መራገም ጀመረ… የበለጠ ጠላኝ….….ከእናቴ ጋር እልክ ተጋባ..‹‹ልጇን ትቻል..ልጆቼን ችላለው››በማለት ፎከረ ‹‹ላም ቀንዶ አይከብዳትም››አለ..በማግስቱ በሰው በሰው አፈላልጎ ለቤቱ ሰራተኛ ቀጠረ…ከእናቴ ጋር አንድ ትምህርት ቤት ስለሚስተምሩ በእየእለቱ ቢገናኙም አይነጋገሩም ነበር.. አንድ ወር አለፈ… የወዳጅ ዘመድ ጉትጎታ እና አማላጅነትም ፍሬ ስለላፈራ በሁለተኛዋ ወር ፍቼ ፈጻሙ….በተጋቡ በስምንት ዓመታቸው ማለት ነው ….ሰማኒያቸው ተቀዳደደ… በቃ.
…..በሶስተኛው ወሩ ለእናቴ ከአባቴ ደብዳቤ ደረሳት……
ሁሉ ነገር ህልም ነው የሆነብኝ..እንዴት ገነት ውስጥ እንዲህ በድንገት ሲኦል ሊመሰረት ይችላል...?እንዴት ያ ሁሉ በመካከላችን የነበረው ሳቅና ፈንጠዝያ ወደ ሀዘንና መሳቀቅ ሊቀየር ቻለ….?ምን አይነት መቅሰፍት ነው በትዳራችን ላይ የዘነበው….?ምን አይነት የእዮብን አይነት ፈተና ነው ለቤተሰባችን የተላከው….?የእዬብን አይነት ፈተና እኮ በድል ለመወጣት ከእዬብን አይነት ትዕግስት ጋር አብሮ መፈጠርን ይጠይቃል፡፡ታውቂያለሽ እኔ ደግሞ እንደዛ አይነት ሰው አይደለውም..ያ ላንቺ የተሰጠ ስጦታ ነው..መቼስ ይገባሻል ማንም ሰው የገዛ ልጁን አይጠየፍም..እኔ ግን አልቻልኩም ፡፡
እሱን እያየው መሳቀቁ ካቅሜ በላይ ነበር….፡፡እና ልገላገላው እንደምችል ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ላንቺ እንደዛ አይነት ምርጫ ሳቀርብልሽ ብታንገራግሪም የምትቀበይኝ መስሎኝ ነበር..ግን የጽናትሽን መጠን አላውቀውም ኖሮል…እንኳንም ጥለሺኝ ወጣሽ…እንኳንም ፈታሺኝ..እኔ ለአንቺ የምገባ ሰው አይደለውም..ለአንቺ ባልነትም የሚመጥን ስብዕናና ያለኝ ግለሰብ አይደለውም…፡፡ለልጆቼ አባት… ለተማሪዎቼ አስተማሪ ….ለአንቺም ባል.. ሆኜ ለመቀጠል ሞራሉ የሌለኝ ከንቱ ሰው ነኝ….፡፡የገዛ ልጁን የተጠየፈ ሰው እንዴት የሰውን ልጅ ተከታትሎ እና ተንከባክቦ በማስተማር የሀገርን አደራ ተቀብሎ መልካምና ውጤታማ ዜጋ ሊያፈራ ይችላል…በፍፅም..ጥሩ አባት መሆን ያልቻለ ሰው ጥሩ መምህር ነኝ ቢል ምፀት ነው… ስለዚህ ከአሁን ቡኃላ ለፀጋ ብቻ ሳይሆን እኔጋ ላሉ ሶስቱ ልጆቻችንም ከእኔ ይልቅ አንቺ ነሽ ምታስፈልጊያቸው…አንቺ እቤቱን ለቀሽ ከወጣሽ ቡኃላ አንድ ቅጽበት እንኳን በፊታቸው ላይ ሳቅ ልፈጥር አልተቻለኝም…..፡፡
ቤቱ ሬሳ የወጣበት የሙት መንፈሶች ጉባኡ የተቀመጡበት መቃብር ቤት ይመስላል….ስለዚህ ስራዬን ትቼ ልጆቼን ትቼ… ሀገሩን ለቅቄ ሄጄያለው..ወዴት ብለሽ እንዳትጠይቂኝ…ልታፈላልጊኝም እንዳትሞክሪ .. ለጊዜው መሄዴን ብቻ እንጂ ወዴት እንደምሄድ እኔም እራሴ አላውቀውም…..ብቻ በመጨረሻ አንድ ነገር ላስቸግርሽ..እውነት እንደምታምኚው የልጅሽ አዕምሮ በትክክል ጤነኛና የሚያገናዝብ ከሆነ እኔ አባቱ ያደረኩበትን ነገር ነግረሽ ግን ደግሞ ከቻለ ይቅር እንዲለኝም ጠይቂልኝ….››
በይ ቻው ያንቺው አፍቃሪ….
እናቴ ደብዳቤውን በእንባ እየታጠበች ነው ያነበበችው..ውስጥ ድረስ በጠሊቅ የሚጠዘጥዝ እና አጥንት የሚያሳሳ ሀዘን ነበር ያጋጠማት …እርግጥ እቤቱን ጥላ የወጣች ቀን ከፍቷት ነበር …ግን በዚህ መጠን አልነበረም ..፡፡ሰማኒያቸውን ፍርድ ቤት ቀርበው የቀደዱ ቀንም ከፍቷት ነበር ግን እንደዚህ ቅስሞ አልተሰበረም ነበር
በስተመጨረሻ እናቴ ምርጫ አልነበራትምና …መኪና ፈልጋ እቃዎቾን ጭና እናም እኔንም ተሸክማ ወደ ቤቷ ተመልሳ ገባች… ከልጆቾ ተቀላቀለች…፡፡
ይሄው እቤቱም አሁን ያለንበት ነው … ልጆቹም እኔንም ጨምረው ጓረምሰው እዚሁ ቤት አሉ …አባቴ ግን…. አባቴ በአሁኑ ጊዜ የት እንዳለ ሌላ ጊዜ እነግራችሆለው..፡፡እናቴ ግን በአስተማሪ ደሞዞ እኛን አራት ልጆቾን አንቀባራ በስርአት አስድጋናለች ፡፡ደረጃው ይለያይ እንጂ ሁላችንንም አስተምራናለች.. ይሄው እስከአሁንም ከእሷ ትከሻ ላይ ሁላችንም ሙሉ በሙሉ አልተላቀቅንም..ታዲያ ሀርሜ-ኮ ጀግና አይደለች….ታዲያ የልቤ የክብር ሊሻን አይገባትም ትላላችሁ....እናቴ ለእኔ ገነቴ ነች፡፡
በነገራችን ላይ እናት ብቻ ሳትሆን ሀገርም እንዲሁ ነች፡፡ሀገር በጦርነት ወይም በአመፅ ስትታመስ የምትጨነቀውና በተራሮቾ ላይ ሸሽጋ፤ በዋሻዎቾ ውስጥ ሸጉጣ ፤በጫካዎቾ ውስጥ ሰውራ ህይወታቸውን ማተረፍና የተሸለ ቀን እስኪመጣ ለማቆየት የምትጥረው ባላገሮች የሆኑትን ጎስቆላዎችን እና ሚስኪን ዜጎቾን ነው፡፡ሀብታሞቹና የነቁት ምሁራኖችማ እራሳቸውን ለማዳን ሁሌ ዝግጁ ናቸው፡፡ገና የመጀመሪያውን የጥይት ተኩስ ሲሰሙ ብራቸውን ሰብስበው፤ ሻንጣቸውን ሸክፈው ፓስፖርታቸውን ይዘው በቦሌ በኩል እብስ ነው፡፡ከዛ አነስ ያለውም በሞያሌና በመተማ ቀሪው በጅብቲ በኩል ይነጉድና ከእሳቱ እርቆ ከመከራው ተጠብቆ የተሸለ ቀን እስኪመጣ እራሱን በምቾት ያቆያል፡፡እና ሀገር በመከራ ጊዜ የምትጨነቀው በፍፅምነትም የምታስፈልገው ወደየትም ጥጋት መሸሻ ሀሳቡም እድሉም ለሌላቸው ሚስኪን ዜጎቾ ነው…ልክ እንደ እናት፡፡

ይቀጥላል
@yefikrclinic
@yefikrclinic
ይህን የእናትነትን ፅኑ ፍቅር ውስጡ የገባ አንብባችሁ ስትጨርሱ እያረጋችሁ እለፉ አብሮነታችሁንም በዛው እናያለን