Get Mystery Box with random crypto!

#ሀርሜ_ኮ : ክፍል-3 : ....‹‹ያን የመሰለ ደስተኛ ኑሮችን እንዲህ ምስቅልቅሉ የወጣው… | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

#ሀርሜ_ኮ
:
ክፍል-3

:


....‹‹ያን የመሰለ ደስተኛ ኑሮችን እንዲህ ምስቅልቅሉ የወጣው…ይሄ ልጅ ከተወለደ ቡኃላ ነው››
‹‹አረ ተው ጡር አትናገር….ምንም ቢሆን ልጃችን አይደል››አለችው ኮስተር እና ቆፍጠን ብላ..
‹‹አይ ይሄ ልጃችን አይደለም….ይሄ ሳቃችንን የነጠቀን እና ፈገግታችንን የሰረቀን ለቤታችን የተላከ መቅሰፍት ነው››
‹‹ልጄንማ እንዲህ እንድትለው አልፈቅድልህም…..››
ቁጣዋን ችላ ብሎ ሌላ ጥያቄ ጠየቃት ‹‹ታፈቅሪኛለሽ አይደል.?››
‹‹ምን የሚሉት ጥያቄ ነው ….?በደንብ አፈቅርሀለው››መለሰችለት፡፡
‹‹እንደዱሮችን በሳቅ በተሞላ ኑሮ በደስታ እየቧረቅን ልጆቻችንን አብረን እንድናሳድግ ትፈልጊያለሽ አይደል.?››
‹‹አዎ እፈልጋለው..በጣም እፈልጋለው››የተቋጠረ ፊቷን አላቀ የተከደነ ጥርሷን ከፈት አድርጋ በተስፋ መለሰችለት
‹‹እንግዲያው ለእሱም ለእኛም ስንል..ይሄንን ልጅ ለእርዳታ ድርጅት እናስረክበው..እዛ የተሸለ ህክምና ያገኛል..ከእኛ በተሻለ…..››የእናቴ ተስፋ መልሶ ጨለመ...እሱ ለተናገረው እሷ ተሳቀቀች
‹‹እንዳትጨርሰው….ልጄን በህይወት እያለው ለማንም አልሰጥም..እንኳን ለእርዳታ ድርጅት ለገዛ እናቴም አልሰጥ..እንደው አቅም አንሶኝ ለማሳደግ ብቸገር እንኳን ሌሎቹን ልጆቼን አሳዳጊ ልሰጥ እችል ይሆናል እንጂ እሱን አላደርገውም፡፡ምክንያቱም ማንም እንደእኔ ሊረዳው አይችልም..፡፡ ማንም እንደእኔ ሊንከባከበው አይችልም..፡፡ለእኔ ከእግዜር የተሰጠኝ የህይወት ዘመን ፀጋዬ ነው፡፡አንድም ቀን መከራዬ ሆኖ ተሰምቶኝ አያውቅም..ለዛም ነው ፀጋዬ ብዬ የምጠራው››
‹‹እኔ ግን አልችልም..አካሉም አዕምሮውም በድን የሆነ ልጅ ጥዋት ማታ እያየውና እየተሳቀቅኩ ቀሪ ዘመኔን መቀጠል አልችልም…..ያቅማችንን ሞክረናል..ያለንን ገንዘብ ጌጣችንን እና ንብረታችንን ሁሉ እሱን ደህና ለማድረግ ስንል በትነናል…. ከዛም አልፎ እዳ ውስጥ ገብተናል..እንደዛም ሆኖ ግን ምንም ጠብ ያለ ነገር የለም…አዕምሮው የተበላሸ ልጅ ምንም ልናደርገው አንችልም……››
‹‹የእኔ ልጅ አካሉ የማይንቀሳቀስ ሊሆን ይችላል…አዕምሮው ግን ጤነኛ ከሆኑት ልጆችህ በተሸለ ያስባል…. ይሰራል››
‹‹እሱ የእናትነት ልብሽ የሚያስበው ነው…ምኞት፡፡አዕምሮውም ልክ እንደመላ አካሉ አንድ ቦታ ረግቶ የተቀመጠ መስራት ያቆመ..በቃ ምን ልበልሽ… የነከሰ ሞተር ማለት ነው፡፡››
‹‹ተሳስተሀል››እየተንዘረዘረች፡፡
‹‹አልተሳሳትኩም…ያልኩሽን እንድርጊና የቀድሞ ህይወታችንን እንኑር ..አንቺም ወደስራሽ ተመለሺ..የቻልነውን ሞክረናል..እግዜሩም ሰውም በዚህ ውሳኔችን ይደግፉናል እንጂ የሚያዝንብን የለም››
‹‹አልችልም ..በህይወት እያለው.ከልጄ መነጠል አልችልም››
‹‹እንግዲያው የሶስት ቀን ማሰቢያ ጊዜ ሰጥሻለው …እሱ ባለበት እንዲህ በሀዘን የተጨመላለቀ አሳቃቂ ኑሮ ውስጥ መኖር አልችልንም›› ብሎ ፈታኝ ጥያቄ ላይ ጥሏት ወደ ስራ ይሄዳል
እናቴ ለአንድ ቀን ሙሉ በነገሩ ላይ አሰበችበት..አወጣች አወረደች ይሻላል ያለችውን በሁለተኛው ቀን ወሰነች…ወደትምህርት ሚኒስቴር ሄደችና ወደስራዋ አንዲመልሳት ማመልከቻዋን አስገባች..ልጄን ቢያምብኝ ብላ ለክፉ ቀን ያስቀመጠቻትን ሽርፍራፊ ገንዘብ አውጥታ ቤት ተከራየች..በሶስተኛው ቀን አባቴ ስራ ሲሄድ ጠብቃ….አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ የእኔን እና የእሷን እቃዎች..መተኛ አልጋችንን..ማብሰያ ዕቃዎችን የመሳሰሉትን አዲስ ወደ ተከራየችው ቤት አጋዘች..ተክሲ ተኮናትራ እኔን ይዛ እቤቱንም ልጆቾንም ጥላ ወጣች….
አንደተለመደው አባቴ አምሽቶ እና ወሳስዶ እቤት ሲመጣ ሶስቱ ልጆች በግራ በመጋባት እና በፍራቻ ውስጥ ሆነው ጎን ለጎን ተኮልኩለው ነበር ያገኛቸው፡፡
‹‹ምን ሆናችሁ.?››
‹‹እማዬ››ከመንታዎቹ አንዷ
‹‹እማዬ ምን.?››
‹‹ሄደች››
‹‹ሄደች ማለት.?››
‹‹ሄደች …ጥላን ፀግሽን በታክሲ ይዛው ሔደች››ግራ ተጋባ
‹‹አመመው እንዴ...?ሀኪም ቤት ነው የወሰደችው.?››
‹‹አይ አይደለም… ይሄን ስጡት ብላለች››ብለው ወረቀቱን አቀበሉት… ገለበጠው፡፡ ለእሱ የተጻፈ ደብዳቤ ነበር፡፡በቆመበት በሚንቀጠቀጥ እጅ ጨምድዶ ይዞ በሚርገበገቡ አይኖቹ ማነበቡን ቀጠለ፡፡
……..ይህቺ ቀን ትመጣለች ብዬ መቼም አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ካየውህና ካወቅኩህ ቀን ጀምሮ አፈቅርህ ነበር ..እርግጥ አሁንም አፈቅርሀለው ….. የመጀመሪያ ፍቅሬ ነህ..ሴት ያደረግከኝ አንተ ነህ…ልቤ ካንተ ውጭ ሌላ ሰው ለሽርፍራፊ ሰከንዶች ቢሆን እንኳን ጎራ ብሎበት አያውቅም..ሳገባህ ገነት የገባው አይነት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር…አብሬህ ስኖር በሙሉ ልቤና ነፍሴም ጭምር ነበር..፡፡እመነኝ ከአንተ ጋር ህይወቴን ሙሉ ለመኖር ህይወቴንም ቢሆን በክፍያ ለማቅረብ ዝግጁ ነኝ… ልጅን ግን አላደርገውም፡፡ለወደፊትህም አንድ ምክር ልስጥህ አንድን እናት በምንም አይነት ከልጅሽ አስበልጪኝ የሚል ፈታኝ ምርጫ አታቅርብላት ከዛ ይልቅ ሙቺልኝ ብትላት የተሻለ ትክክለኛ እና ፍትሀዊ ጥያቄ ይሆናል…ካፈቀረችህ ያለማቅማማት ልትሞትልህ ትችላለች ..ልጆን ግን…..በፍፅም፡፡
እርግጥ ይገባኛል..ለአንተም ልጅህ እንደመሆኑ መጠን ጫናው ከብዶህ እንጂ ጠልተሀው እንዳልሆነ አውቃለው..እኔ ግን እናት ነኝ መቼም መቼም ቢሆን በልጄ ተስፋ ልቆርጥ አልችልም…ይሄንን ስሜቴን ምን አልባት እመብርሀንም ልጅ ስለነበራት ትረዳኝ ይሆናል..ለእናንተ ስል ልጄን ከምተው ..ለልጄ ስል ሁላችሁንም ባሌንም… ልጆቼንም…ቤቴን ብተው እመርጣለው….እዚህ ላይ ንፅፅር እንዳታደርግ ..ጥለሻቸውስ የሄድሽው ልጆችሽ አይደሉም ወይ ብለህ እንዳትጠይቀኝ..፡፡ከሶስት ጤነኛ ልጆች እንዴት አንድ መላ አካሉን ማዘዝ የማይችል ልጅ ልትመርጪ ቻልሽ እንዳትለኝ...? የዚህን መልስ ለመመለስ ለእኔ ቀላል አይደለም…ግን ቢያንስ እነሱን ማንም ተቀብሎ ሊያሳድጋቸው ይችላል…..የፈለጉትን መጠየቅ የተበደሉትን መናገር ይችላሉ፡፡እቤት ከአንዱ ክፍል እሳት ቢነሳ በጎሮ በር ወይም በመስኮት ዘለው ለማምለጥ ለእነሱ ቀላል ነው፡፡ቢርባቸው እንኳን ማድቤት ገብተው ምግብ ፈልገው ለመጉረስ አይሰንፉም፡፡ሽንታቸውን ቢወጥራቸው ወደ ሽንት ቤት ሄደው ለመሽናት ውሃ ቢጠማቸው ወደ ፍሪጅ ሄደው አልያም ከቧንቧ ቀድተው ደቅነው ለመጠጣት ለእነሱ በጣም ቀላል ነው….አየህ የእኔ ሚስኪን ልጅ ግን ይሄን ሁኑ ማድረግ አይችልም…ምን እንደፈለገ እንኳን መናገር ስለማይችል ከእኔ ከእናቱ ውጭ ማንም ሊረዳው አይችልም…ግን ደግሞ እሱም እንደእነሱ በህይወት አለ..እሱም እንደነሱ ይራባል…፤እሱም እንደነሱ መጸዳዳት አለበት.ያን ሁሉ ማድረግ የሚችለው ግን በእኔ በእናቱ እርዳታ ነው እናም እኔ ለእናንተ ከማስፈልገው በላይ በብዙ ሺ እጥፍ ለእሱ አስፈልገዋለው ስለዚህ አንተንም ላለመረበሽ ስል ቤቱን ለቅቄ ልጄን ይዤ ወጥቼያለው፡፡አይዞህ እንዴት ይኖራሉ ብለህ አታስብ ወደ ስራዬ ለመመለስ ስለወሰንኩ ማመልከቻ አስገብቼያለው አንተም ልጆችህን ጥሩ አባት ሆነህ እንደምታሳድግ ምራጫውን ለአንተ ትቼዋለው ከፈለግክ ሰራተኛ ቅጠር …ከፈለክም ማግባት ትችላልህ፡፡ በዚህ ምንም ቅሬታ አይሰማኝም…..ፍቺያችንንም ዝግጁ ስትሆን ንገረኝና በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲያልቅ አደርጋለው፡፡ብቻ አደራ ምልህ እቅፍ ውስጥ ላሉት ሶስት ጤነኛ ልጆቸች ጥሩ አባት ሁናቸው፡፡ያንተው አክባሪህ
ፈጽሞ ያልጠበቀው ዱብ እዳ ነው ያጋጠመው..መቼም እንዲህ አይት ውሳኔ ላይ ትደርሳለች ቡሎ ገምቶም ጠርጥሮም አያውቅ ነበር .፡፡በእሱ የምትጨክን