Get Mystery Box with random crypto!

Yalelet Wondye

የቴሌግራም ቻናል አርማ yaleletwondy — Yalelet Wondye Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ yaleletwondy — Yalelet Wondye
የሰርጥ አድራሻ: @yaleletwondy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.44K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-12-12 21:27:20
2.2K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 21:27:16 ማቅለጫ ምድጃዎች፣ ቅርፅ ማውጫዎቹ ሁሉ ወደ ፍርስራሽ ኮረብታነት ተለወጠ። የተጀመሩት የመንገድ ሥራዎች ባሉበት ቆሙ። ተሠርተው አግልግሎት መስጠት ጀምረው የነበሩት ጋሪዎች በተረተሩ ወድቀው ቀሩ። በጣና ሐይቅ ላይ የሚንሳፈፉ ጀልባዎችን ለማሠራት የነበራቸው ምኞትም ሰምጦ ቀረ። በጥቅሉ የቴዎድሮስ የተሃድሶ ሥራዎቻቸው ተቋረጡ። ፈጠራዎቻቸውም ያለ ጥቅም ቀሩ።

ምናልባት ቴዎድሮስ ህዝቡም፣ ቀሳውስቱና ሽፍታው እንቅፋት ባይሆንባቸው ኖሮ ለዐማራ ብሔርተኝነት ማበብ ጀምረውት የነበረውን የዐማራ ግዛቶችን በመንገድ፣ በአስተዳደርና በኢኮኖሚ የማስተሳሰር ሂደት ጠንካራ የዐማራ ክልላዊ ብሔራዊ አንድነት መፍጠር ይቻል ነበር። ነገርግን ህልማቸውንም ትልማቸውንም የተረዳችው ባለመኖሩ ያነን ተከትሎ በወሰዱት እርምጃ ደጋፊ ከማሳጣቱ በላይ ከእንግሊዞች ጋር የገቡት ውዝግብ የራዕያቸው መቋጫ የሕይወታቸው መጨረሻ ሆነ። ጀምረውት የነበረው የዐማራ ብሔርተኝነት መጠናከር የዐማራ ብሔር ምሥረታም በአጭር ተቀጨ። ምናልባት የዎድሮስ ትልም ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ የዐማራው ብሔርተኝነት መግለጫ አሁን ካለበት የተለየ መልክ ይዞ በቆየን ነበር።
2.2K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 21:27:16 ያለፈው የዐማራ ትውልድ የፈጸመው ስሕተትና የተጠለፈበት ሴራ ባግባቡ ተመርምሮ ለአሁኑ ትውልድ ባለመተላለፉ ይኸም ትውልድ እንዳለፈው ትውልድ ሁሉ በተመሳሳይ ሤራ እየተጠለፈ ካሰበበት እንዳይደርስ ሆኗል። ያለፈው ትውልድ ከሰራቸው ስህተት መካከል ማርክሲዝም ሌኒኒዝም አምጦ የወለዳቸው ተማሪዎች ተፈረካክሰው ከተበታተኑ በኋላ በየፊናቸው የራሳቸውን ነገድና ጎሣ ነጻ ለማውጣት የነጻነት ግምባር ንቅናቄዎችን ሲያቋቁሙ የዐማራ ተማሪዎች በዐማራነት መሰባሰብ አልቻሉም ነበር። የትግሬው ወያኔ፣ የኤርትራው ሻዕቢያ፣ የምዕራብ ሱማሌ ነፃነት ግምባር፣ የሲዳማ ነፃነት ግምባር፣ በኦሮሞ ስም የተቧደኑት ኦነግ፣ ኦብነግ፣ የኦሮሚያ እስላማዊ ነፃነት ግምባር፣ የኦሮሞ ነፃነት አድነት ድርጅት (ቶኪቹማ)፣ የኦሮሞ አቦ ድርጅት፣ እና ሌሎችም በነጻ አውጭነት ሲቧደኑ በዐማራ ስም የተደራጀ አልነበረም።

ዐማራው በ1966 ዓ.ም. እንደ ሕወሓት፣ ኦብነግ፣ ኦነግ፣...ነጻ አውጭ ግንባር ቢኖረው ኖሮ ዐማራው በጨቋኝነት አይከሰስም ነበር። ይህ ባለመሆኑ ምክንያት ኢትዮጵያ ዐማራው በአምሳሉ የፈጠራትና ብሔሮችን የጨቆነባት ሀገር ናት የሚለውን አፍራሽ ታሪክ እንዲጸና አድርጓል። በወቅቱ ኢትዮጵያ በኮሚኒዝም ርእዮተ ዓለም ስትናጥ፣ የዚህ አዲስ ርዕዮት ተቀጥላ የሆኑ ዐማራን ኢላማ ያደረጉ የብሄር አስተሳሰቦች በኢትዮጵያ አየር እንደ ጆፌ አሞራ ሲያንዣብቡ፣ ዐማራው መኢሶን፣ ኢሕአፓ፣ ኢዲዩ፣ ወዝ ሊግ፣ ማሌሪድ፣ ሰደድ (ኢሠፓአኮ እና ኢሠፓ) ወዘተ በሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ተከፋፍሎ፣ ልክ እንደ እንደ ዘመነ መሣፍንቱ፣ እንደ ዳግማዊ ቴዎድሮስና ተክለጊዮርጊስ ዘመን ርስበራሱ ይባላ ነበር።

ሁለተኛው ችግር ዐማራ ለውጥን መምራት እንጂ ለለውጥ ትግል የማድረግ ችግር የለበትም። ዐማራ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እስከ ኢሕአዴግ ትግል በመጀመር ቀዳሚ ነው። ነገርግን የታገለለት ዓላማ በአንድም በሌላም መንገድ እየተጨናገፈ ግቡን ሳይመታ ቀርቷል። የ1953ቱ የመንፈቅለ መንግሥት ሙከራ ያደረጉት መንግሥቱ ነዋይ፣ ገርማሜ ነዋይና ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ ዐማሮች ናቸው። የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ዘውድ ያነቃነቀው የጎጃም ገበሬዎች አመፅ ነው። በተማሪዎች የለውጥ እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና የነበራቸውን ዐማሮች ነበሩ ነገርግን ዘውዱን ታግሎ ደርግን ወለደ፣ ደርግን አሸንፎ መንበረ ሥልጣኑን ለሕወሓት አስረከበ፣ ወያኔን ታግሎ ብልፅግናን አነገሠ። እነዚህን ሁለት ተከታታይ ሥርዓቶች ደርግና ወያኔን በዐማራ ውድ ልጆች ከፍተኛ መስዋዕትነትና በሌሎችም ሕዝቦች ተጋድሎ ቢገረሰሱም ቀጥሎ በመጣው የብልጽግና ሥርዓት ዐማራ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተሳዳጅና የትም የሚገደል ሆነ።

አሁን ደግሞ ሌላ ምናልባትም እረጅም ዓመት የሚወስድ ትግል ይደረጋል፣ አሁንም ለውጥ አምጥቶ ይቀማል።ስለዚህ ዐማራው የመታገል ሳይሆን ታግሎ ያመጣውን ለውጥ የማስቀጠል ችግር ነው ያለበት።

ሦስተኛው ችግር ለውጡን አምጥቶ፣ ለለውጡ አስፈላጊ ለሆኑ ሰዎች ግዜ ሰጥቶ አብሮ ከመሥራት ይልቅ መቃወምና ማደናቀፍ ሌላኛው ችግር ነው። ለምሳሌ፣ ዐማሮች የቴዎድሮስን መምጣት ይናፍቁ ነበር። በዘመነ-መሳፍንት እንደ ክረምት ዝናብ በማያባራ የእርስበርስ ጦርነት የተማረረው ዐማራ በፍካሬ ኢየሱስ ውስጥ፣ "ኢትዮጵያን ከወደቀችበት የሚያነሳ፣ ጠላቶቿን ከምድረ-ገጽ የሚያጠፋ ንጉሥ ይነግሣል። በዚህ ንጉሥ የስልጣን ዘመን በመላው ሀገሪቱ ሰላም ይሰፍናል። ይህም ንጉሥ ስሙ ቴዎድሮስ ይባላል።" የሚለውን ቃል እያሰበ፣ ያንን ዘመን እየናፈቀ የመከራውን ዘመን ሲገፋ ኑሯል።

ተናፊቂው ቴዎድሮስ መጣ፣ አዳዲስ እርምጃዎች መውሰድ ጀመረ። ቴዎድሮስ አገሪቱ በመሠረተ ልማት ለማስተሳሰር እቅድ ነበረው። በእቅዱ መሠረት ደብረታቦር፣ ጎንደር፣ መቅደላ፣ ደቡብ ጎጃም በመንገድ ተሳስረው ለጉዞ ምቹ እንዲሆኑ ይፈልጉ ስለነበር በጀርመናውያን ሚሲዮናውያን አማካኝነት የመንገድ ሥራ ንድፍ ወጥቶ አሰቸጋሪ ቋጥኞችን በድማሚት የመናድ ሥራ ተጀምሮ ነበር። ራሱ ቴዎድሮስ ቋጥኝ እየናደና አለት እየፈነቀለ መንገድ ለመሥራት ሞክሯል። ለዚህም ከጋፋት እስከ መቅደላ ድረስ ለሴባስቶፖል መድፍ መጓጓዣ እንዲውል ማድረጋቸው ይታወቃል። (ፊሊፕ ማርስዲን፣ 61)

ቴዎድሮስ በእርስ በርስ ሽኩቻና ጦርነት የወደመ ኋላቀር ሀገርን እቀይራለሁ ብሎ ሲነሳ ባለመታደል ይሁን፣ ወይም በእርግማን ወይም በሌሎች በማናውቃቸው ምክንያቶች ከዘመነ መሳፍንት ግፍና ፍዳ ነፃ ካወጡት ህዝብ የገጠማቸው ተቃውሞ ነበር። በዘመነ መሳፍንት ፍዳ የቴዎድሮስን መምጣት ይናፍቅ የነበረ ሕዝብ ቴዎድሮስ ሲመጣ መልሶ ቴዎድሮስን እየረገመ ሌላ ንጉሥ የሚናፍቅ ሆነ።

ቴዎድሮስ በአካባቢ ባለቤቶች ተከፋፍሎ ሕዝቡ የመከራ ሕይዎት የሚገፋባትን አገር፣ ወደ ጥንቱ አንደነቱ መልሶ የበለፀገ፣ የታፈረና የተከበረ አንድ ዐማራንና አንዲት ኢትዮጵያን የማየት ራዕይ ሰንቆ ነበር የተነሳው። የዐማራን አንድነት ትንሣኤ ለማብሰር ከ38 ጊዜ በላይ ጦርነት አካሂደዋል። ጦርነቱ የቴዎድሮስን አመራር አምኖ በተከተለ ዐማራ እና በሌላ በኩል ከእርሳቸው ዓላማ ተፃራሪ ሆነው በቆሙ ዐማሮች መካከል የተካሄደ ትግልና መስዋዕትነት ነው።

ነገርግን ለግል ጥቅሙ እንጂ ለሀገሩ እድገት፣ ለሀገሩ አንድነትና ልማት ለመሥራት የቆረጠ የዐማራ መሳፍንት አልነበረም። ተባባሪ ህዝብ አልነበረም፣ ህዝቡ መሻሻልና መለወጥን ሳይሆን የፈለገው በነበረው የዘልማድ ህይወት መቀጠሉን ነው የመረጠው። ህዝቡ ከቴዎድሮስ ምኞትና አሠራር ጋር የሚጣጣም አልነበረም፡፡ ይህንንም ቴዎድሮስ ለራሳም እንዲህ ነበር ያሉት፣

"በሰላም እንዲኖሩ ሞከርኩ፤ እንደሠለጠነው አለም ወደሥልጣኔ እንዲሄዱ ታገልኩ፤ በሥርአት እንዲኖሩ፣ ልጆቻቸው ተስፋ እንዲኖራቸው ሞከርኩ፡፡ ነገር ግን ክፉ ናቸው" (መቅደላ የቴዎድሮስ ዕጣ፣ 45)

ቴዎድሮስ ህዝብ ሥርዓት እንዲገባ ወታደር በዲሲፕሊን የታነፀ እንዲሆን ሲመኙት የኖሩት ግን አልሳካ ያላቸውን ጉዳይ ነበር። ለናፒየር የጻፉትን ደብዳቤም እንዲህ የሚል ይገኝበታል፣

"...ያገሬን ሰው ግብር ስራት ግባ ብዬ ብለው እምቢ ብሎ ተጣላኝ። እናንተ ግን በስራት በተገዛ ሰው አቸነፋችሁኝ።...
የአገሬ ሰው የፈረንጅ ኃይማኖት ይዟል፣ አሰልሟል እያለ አስሩን ምክንያት ይሰጠኝ ነበር። እኔ ከከፋሁበት እግዚአብሔር መልካም ይስጠው። እንደወደደው ይሁን።"
(ፈሊፕ ማርስዲን፣ 484)

በመጨረሻም ጀግናው ተዋጊና የጦር አዛዥ፣ ሀገራቸው ከዘመነ-መሳፍንት መዳፍ ፈልቅቀው ለማትረፍ የተዋጉት፣ የራሳቸው የዐማራ ሕዝብ እንኳን ዓላማቸውና ራዕያቸውን ያልተረዳላቸው ቴዎድሮስ መቅደላ በእንግሊዞች እጅ መውደቁን ሲያዩ ሽጉጣቸውን ከወገባቸው ቀበቶ ላይ ላጥ አድርገው አፈሙዙን አፋቸው ውስጥ አስገብተው ምላጩን ሳቡት። ከምንም በላይ የሕይዎት፣ የአጥንት፣ የደም፣ የገንዘብ፣ የንብረት፣ የጊዜና ጉልበት ዋጋ የተከፈለበት የዐማራ አንድነት ከመቅደላ መውደቅ ጋር ተቀበረ።

ቴዎድሮስ እንደ ሩሲያዊው ንጉሥ ኒኮሊያ፣ እንደ ፈረንሳዩ ንጉሥ ናፖሊዮን ቦኖፓርቲ በልቡ ያሰበውን ዕቅድ ሳያሳካ የሞተው ጠመጃና መድፍ ስላልነበረው፣ ሥልጣኔን እንደኃጢያት በሚቆጥር ሕዝብ መካከል በመገኘቱ ጋፋት ላይ የተሰራው 16,000 ፓውንድ የሚክደው ሴባስቶፓል መድፍ የተዘጋጀለት ኢላማ ሳይመታ መንገድ ላይ እንደቀረው ሁሉ ህልማቸውም ከሸፎ ቀረ። የመሣሪያ ፋብሪካ እና መማሪያ ትምህርት ቤት የተከፈተባት ጋፋት ወድማ ወደጥንቱ ድንጋያማነት ተመለሰች። በጋፋት የተሰሩ ቤቶቹ ፈረሱ፣ የብረት
2.1K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 22:02:37 የ3ቱን ክልሎች ክልላዊ የህዝብ መዝሙሮች - የአማርኛ ትርጓሜ አንብቡና - ፍርዱን ለህሊናችሁ ስጡት!

1. የትግራይ ክልል መዝሙር /የአማርኛ ትርጉም /

የማንወጣው ተራራ
የማንሻገረው ወንዝ የለም ፤
ፍፁም ወደኋላ የለም
መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም!

በፀሀይ ሀሩር እና በቁር
ነፍሳችን ውሀ ይጥማት
አለት ይሁን ትራሳችን
ዋሻ ይሁን ቤታችን
ሌትም ቀንም ጉዞ ይድከመንም ይራበንም

ሆኖም መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በጭራሽ አንሸነፍም፤

በጅቦች እንከበብ መሬት ይክበበን
የጠላቶቻችን ጥርስ ስጋችን ውስጥ ይቀርቀር!
ስጋችን ላሞራ ደማችን እንደ ጎርፍ ይፍሰስ፤
አጥንታችን ይድቀቅ ዱቄት ሆኖ ይበተን

መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን
በፍፁም አንሸነፍም፤

የጦር መሳሪያ መርዝ ፋሽስታዊ ንዳድ
ሚሊየን ጠላቶቻችን ፊታችን ላይ ይጉረፉ
መስዋዕትነት መቁሰል እና ኪሳራም እንከፍላለን፤
የከፋ መከራም ቢመጣ ወደን እንከፍላለን

መስመር ነው ኃይላችን
ህዝብ ነው ኃይላችን፤
በዚህ ሁሉ ጉዞ ግን አሸናፊዎች እኛ ነን።

☞ በማለት የትግራይ ክልል መንግስት በትግራይ ባሉ ትምህርት ቤቶች ላለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እስካሁን ድረስ ይዘምራል ።

2. የኦሮሚያ ክልል መዝሙር / የአማርኛ ትርጉም /

ኦሮሚያ //2// የትልቅ ህዝብ ታሪክ እናት
የኦሮሞዎች እምብርት ፥ የገዳ ስርአት አዳራሽ
የህግና ስርአት መሬት ፥ የጨፌ ኦዳ እናት
የብልጽግና ልምላሜ ፥ ሁሉን አብቃይ እናት
የመቶ አመት እድፍ ፥ በደማችን አጠብንልሽ
በብዙ እልፍ እልቂት ፥ ባንዲራሽን ከፍ አደረግን
ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ ፥ ስልጣንን መልሰን አገኘን
ሰላምና ዴሞክራሲ ፥ የሰብአዊነት መብት
አስተማማኝ ልማት ፥ ዘላቂ ልማት
ከህዝቦች ጋር ሰላምና ፍቅር
ለመኖር ዋስትና ትልቅ አላማ አድርገን
ኃይላችንን አሰባስበን ፥ ተነስተናል ተማመኚብን
ኦሮሚያ አብቢ ፥ ለምልሚና ኑሪ!

☞ በማለት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እንካሁን ድረስ በኦሮሚያ ክልል ይዘመራል ። አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ካልተዘመረ እየተባለ በተደጋጋሚ እየተነሳ ነው ።

3. የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መዝሙር

የታታሪ ህዝቦች የታሪክ ማህደር
የአኩሪ ባህል አምባ የድንግል ሀብት አፈር
የህዝቦችሽ ተስፋ ለሟ ክልላችን
በሰላም በፍቅር በልማት ጉዟችችን
ተባብረን በስራ እንገነባሻለን

የአማራነት ክብር ደማቅ አርማ ይዘን ፥
ከሌሎች ህዝቦች ጋር እኩል ተከባብረን
በፍቅር በአንድነት አብረን እንዘልቃለን ።

☞ በማለት የአማራ ክልል ህዝብ መዝሙር ይቋጫል ፡፡ ይህ መዝሙርም ላለፉት 30 አመታትን ጨምሮ እስከአሁን ድረስ በክልሉ ይዘመራል ።

ለትውልዱ የጥላቻና የክፋት መርዝ እየጋተ ፥ ሀገርን የሚያፈርሰው ማን እንደሆነ ፥ የህዝብ ህሊና ፍርዱን ይስጥ!
#ሼር
═══════❁✿❁ ═══════
2.8K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 21:48:09 ከጎጃም አዲስ አበባ መስመር በኦነግ የሚታገቱ አማራዎች እስከ አንድ ሚሊዬን ብር ድረስ እየከፈሉ ነው እየተለቀቁ ያሉት። ገንዘቡ የሚከፈለው በኦሮሚያ ባንክ ነው። አስባችሁታል መንግስት እራሱ ማፊያ ሆኖ አብሯቸው እንደሚሰራ? እንጂማ ብሩ በባንክ ሲገባ ሳያውቀው ቀርቶ ነው?
3.1K views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 20:51:50 እነ ሾርት ሚሞሪዎች የንፁሃንን የዕለት ተዕለት ሞት በአንድ ጀንበር እረስተውት በኳስ አብደዋል።
3.0K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 20:13:41 ከጎጃም- ጎንደር-አዲስ አበባ ያለው መሥመር የሀገሪቷን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እና የንግድ ፍሰት ግማሽ ፐርሰንቱም የሚሸፍን መሥመር ነው። የደብረ ማርቆስን ከተማ እና የአካባቢውን ማኅበረስብ ብቻ የሚመለከት ጉዳይ አይደለም።

ጉዳዩ፤ መላው የአማራን ሕዝብ እና የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚመለከት ጉዳይ ነው። በየትኛውም አግባብ መንግስታዊ ድጋፍ ላለው አሸባሪ እና ሽፍታ አንድ ሚሊዮን ብር እየከፈልን፣ ካልከፈልን መሞትን ምርጫችን አድርገን በሥጋት መኖርን ልንቀበል አይገባም በሚል ነው። ግብር እና የአገልግሎት ክፍያ የምንከፍለው መንግሥት አለ እስከተባለ ድረስ ሰላም እና ደኅንነታችንን በማስጠበቅ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል በሚል ነው።

ደብረ ማርቆስ፤ እየጮኽች እና ፍትሕ እየጠየቀች ያለችው ወለጋም፣ ጎንደርም፣ ደሴም፣ ደብረብርሃንም...የትም ለሚኖር አማራ ነው!

@ Tigist Endalamaw
3.1K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 21:41:46 አስቸኳይ መረጃ
****
#ሼር አድርጉት

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ ጃርደጋ ከተማ እና በአካባቢዋ የሚኖሩ ኣማሮች በኦ/ሮ ልዩ ሀይል ፣ሽኔ እና የኦሮሞ ሚልሻ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በተከፈተበት ተኩስ ከ50 በላይ የአማራ ሚልሾች እና ንፁሃን ተጨፍጭፈዋል። ጦርነቱ አሁንም ቀጥሏል። ዛሬ ቀኑ ጨልሞብናል። መንገድ ዝግ ነዉ። መከላከያ ካልገባ አይናችን እያየ መታረዳችን ነዉ። ምን ይሻላል?
6.8K views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 16:41:48 መረጃ ወለጋ
****
ዛሬ ህዳር 29/2015 በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በሶንቦ ፣ለጋፋርሶ እና ጃርዳጋ ጃርቴ ከተሞች ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል እና ኦነግ በአማራ ተወላጆች ላይ ተኩስ ከፍተውባቸው እንደዋሉና ህዝቡም ወደ ጫካ መሰደዱን ከስፍራው መረጃ ደረሶኛል።
3.9K views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 14:40:57
የዝግጅት ጥቆማ!

በጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ሙያ በታላላቅ ብሔራዊና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የብዙ ዓመታት ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች (ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ጋዜጠኛ አላዛር ተረፈ) የተቋቋመው ‹‹Arat Kilo Media አራት ኪሎ ሚዲያ››፤ ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ሙያዊና ልዩ በሆነ አቀራረብ ወደ አድማጭ/ተመልካቾች ለማድረስ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

‹‹Arat Kilo Media አራት ኪሎ ሚዲያ›› ከዝነኛውና ተፅዕኖ ፈጣሪው ጋዜጠኛና ደራሲ ተመስገን ደሳለኝ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ በቅርቡ ለአድማጭ/ተመልካቾች ያቀርባል፡፡

‹‹Arat Kilo Media አራት ኪሎ ሚዲያ››ን ሰብስክራይብ (SUBSCRIBE) በማድረግና ለሌሎች በማጋራት የሚዲያውን ዝግጅቶች ይከታተሉ፤ቤተሰብ ይሁኑ!

‹‹Arat Kilo Media አራት ኪሎ ሚዲያ››

https://www.youtube.com/watch?app=desktop&v=9KvP0QVLrew&feature=youtu.be

https://www.youtube.com/@AratKiloMedia
4.2K views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ