Get Mystery Box with random crypto!

Addis Ababa Education Bureau

የሰርጥ አድራሻ: @wwwaddisababaeducationbureau
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 106.72K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 76

2022-09-22 17:37:37
ቀን 12/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራና አጠቃላይ ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ለክፍለ ከተማና ክላስተር ሱፐር ቫይዘሮች ኦረንቴሽን ሰጠ።

ኦረንቴሽኑ በዋናነት የ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከትምህርት አጀማመር ጋር በተገናኘ በአፋን ኦሮሞ ትምህርት በትምህርት ቤቶችና በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት አድርጎ በተዘጋጀ ቼክ ሊስት ዙሪያ የተሰጠ ነው።

በመርሀ ግብሩ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንዳስታወቁት በ2014ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ተደራሽነትን ለማሳደግ በተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው በ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመንም አምና የተገ ኙ አበረታች ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የትምህርት አገልግሎቱን ለማስፋፋት የተለያዩ ተግባራት እንደሚከናወኑ አስረድተዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም የ2015 ዓ.ም ትምህርት በአብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች በአግባቡ ቢጀመርም አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ግን በሚፈለገው ደረጃ ወደ መማር ማስተማር ስራው እንዳልገቡ መረጃዎች መኖራቸውን ገልጸው በድጋፍና ክትትል ተግባሩ ተሳታፊ የሆኑ ሱፐር ቫይዘሮች በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት ከክፍለ ከተሞችም ሆነ ትምህርት ቤቶች ተገቢውን መረጃ ይዘው መመለስ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።
12.0K viewsAbebe Chernet, 14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 11:06:04
ቀን 12/1/2015 ዓ.ም

ማሰታወቂያ!

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
13.6K viewsAbebe Chernet, 08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 14:36:56 እና በግንባታ ላይ ያሉ ተጨማሪ ክፍሎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለመማር ማስተማር ስራው ዝግጁ ማድረግ የሚሉ አማራጮችን መሰረት በማድረግ ወደ አመቱ ትምህርት መገባቱን ጠቁመው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ለችግሩ ትኩረት በመስጠት 5 ሚሊየን ብር መድቦ 536 የተማሪ መቀመጫ ዴስኮች ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረጉን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
14.3K viewsAbebe Chernet, 11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 14:36:21
ቀን 11/1/2015 ዓ.ም

ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ2015 ዓ.ም የትምህርት አጀማመርን የተመለከተ ጉብኝት ተካሄደ።

የመስክ ምልከታው በዋናነት ከፍተኛ ተማሪ ተቀብለው ወደ መማር ማስተማር ስራው በገቡ ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ፣የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብሬ ዳኘው፣ የትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱን ጨምሮ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ናስር በምልከታው ተሳታፊ ሆነዋል።

ምልከታ የተደረገባቸው ትምህርት ቤቶች ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ተማሪ መቀበላቸውንና እስካሁን ምዝገባ ባለመቆሙ ተጨማሪ ተማሪዎችን በመመዝገብ ላይ በመሆናቸው የተማሪ ክፍል ጥምርታው ከስታንዳርድ በላይ እንዲሆን ማድረጉን የትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ ትምህርት ቤቶቻችን መቀበል ከሚችሉት በላይ ተማሪ ለመመዝገብ መገደዳቸውን ገልጸው በክፍለ ከተማው በቅርቡ ግንባታቸው የሚጠናቀቁ አዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች አገልግሎት መስጠት እስኪጀምሩ ትምህርት ቤቶቹ ተማሪዎቻቸውን ፈረቃን ጨምሮ የተለያዩ አማራጮችን ተጠቅመው ማስተማር እንደሚገባቸው በመጥቀስ ቢሮው ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውዋል።

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ናስር በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ያጋጠመውን የተማሪዎች የመማሪያ ክፍል እጥረት ለመቅረፍ የግለሰብ ህንጻ ተከራይቶ ከማስተማር ጀምሮ ተማሪዎችን በፈረቃ ማስተናገድ
12.9K viewsAbebe Chernet, 11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 14:01:09
ቀን 11/1/2015 ዓ.ም

የመስቀልና የኢሬቻ የአደባባይ በዓላትን አከባበር አስመልክቶ ውይይት ተደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በቀጣይ ቀናት ውስጥ የሚከበሩትን የመስቀልና የኢሬቻ የአደባባይ በዓላትን አከባበር በተመለከተ ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዳል፡፡ በዓላቱ በሰላም ተጀምረው በሠላም እንዲጠናቀቁ የሰራተኛውን ሚና አስመልከቶ ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱ ላይ ሰራተኞች በአላቱ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ የማድረግ ኃላፊነት መውስድ እንደሚገባቸዉ ተመላክቷል፡፡

በውይይቱ ላይ ሰራተኞች ሰላምን የሚያደፈርሱ ከወትሮ የተለዩ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከቱ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት እንዳለባቸው እንዲሁም ለሰላም ዘብ በመቆም ባዕላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ከመግባባት ላይ ተደርሳል ።

የውይይት መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ ፣ የቢሮ ሀላፊ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ እና የቢሮ ሀላፊ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ሲሆኑ በንግግራቸው በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች በበዓላቱ ተሳታፊ ስለሚሆኑ ሰራተኛዉ በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ የሚጠበቅባቸዉን ሀላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:

13.0K viewsAbebe Chernet, 11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 13:00:10 ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
16.8K viewsAbebe Chernet, 10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 12:59:27
ቀን 9/1/2015 ዓ.ም

የ2015 የትምህርት ዘመን የትምህርት ማስጀመሪያ ኘርግራም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በእሸት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በይፋ ተጀመረ።

በትምህርት ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ከወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ በተጨማሪ የብልጽግና ጽ/ቤት ሃላፊው አቶ ብርሃኑ አበራ፣ የተማሪ ወላጆች፣ መምህራን እንዲሁም ሌሎች የት/ቤት ማህበረሰብ አባላት የተገኙ ሲሆን የችቦ ርክክብና የአዲሱን ስርዓተ-ትምህርት መማሪያ መፅሃፍ ርክክብ ተደርጓል፡፡

በክፍለ ከተማ ደረጃ ከ191ሺ በላይ ተማሪወችን ተቀብለው ለማስተማር ወደ ተግባር መገባቱን የገለጹት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ ዘንድሮ የሚጀመረውን አዲስ ስርዓተ-ትምህርት በአዲስ አስተሳሰብና በአዲስ እይታ ተቀብለን ተግባራዊ ልናደርገው ይገባል ብለዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ በበኩላቸው ተማሪዎቻችን በስነ-ምግባር ታንፀው ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ተወዳዳሪ ይሆኑ ዘንድ ከሁሉም ባለድርሻዎች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልፀው እንኳን ለ2015 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

በእሸት ት/ቤት በተደረገው የትምህርት ማስጀመሪያ ላይ አመራሮቹ የተማሪዎችን ምገባም በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን በተመሳሳይ በአዲስ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2015 የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል፡፡
14.3K viewsAbebe Chernet, 09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 12:50:24
ቀን 9/1/2015 ዓ.ም

የ2015 የትምህርት ዘመን በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ሐምሌ 19/67 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ያስሚን ውሃብረዲን፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ ፣ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት የ2015 ትምህረት የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ያስሚን ውሃብረዲን ዘንድሮ ትምህርት የሚጀምረው በተዘጋጀው የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ስለሆነ ተማሪዎች በርትተው በመማር ብእቁ እውቀት እንዲገበዩና የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች መሆናቸውን አውቀው ከወዲሁ ራሳቸውን የተሻለ ትውልድ ለማድረግ በእውቅት ለመበልጸግ እንዲተጉ በመልእክታቸው አሳስበዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
12.7K viewsAbebe Chernet, edited  09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 11:51:01 መምህራንና ተማሪዎች በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በተለይም በማጠናከሪያ ትምህርት በንቃት ሲሳተፉ መቆየታቸውን የተናገሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ በአዲሱ የትምህርት ዘመንም በትምህርቱ ዘርፍ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ በባለቤትነት መንፈስ መንቀሳቀስ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
12.0K viewsAbebe Chernet, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 11:50:53
ቀን 9/1/2015 ዓ.ም

የ2015 የትምህርት ዘመን በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

በክፍለ ከተማው የትምህርት ዘመኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት በይፋ የተጀመረ ሲሆን፣ በለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር ባደረጉት ንግግር አገር የምትገነባው በተማረ ትውልድ መሆኑን አውስተው፣ "አገራችን በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም በሁሉም መስክ የጀመረችውን የስኬት ጉዞ ለማስቀጠል ትምህርት ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆችና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ድርሻውን በመወጣት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲረጋገጥ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው በበኩላቸው ትምህርት አገርን ወደብልጽግና ለማሸጋገር ቁልፍ መሣሪያ መሆኑን አውስተው፣ "የትምህርት ተግባሩ ሰላማዊ እንዲሆን በተለይም የአገራችንን ሰላም ለማደፍረስ የሚፈልጉ ኃይሎች ትምህርት ቤቶችን መጠቀሚያ እንዳያደርጉ የትምህርት ባለድርሻ አካላት የማይተካ ሚናችሁን እንደትናንቱ ዛሬም አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል" ብለዋል።
11.5K viewsAbebe Chernet, 08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ