2022-10-05 15:07:42
ቀን 25 /1/2015 ዓ.ም
በአዲስ አበባ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ሚሰጥባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች የቅድመ ዝግጅት ስራቸዉን በማጠናቀቅ ተማሪዎችን በመጠበቅ ላይ መሆናቸዉ ተገለጸ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ201 ትምህርት ቤቶች ዝግጅታቸዉን ሳደርጉ የቆዩ 49 ሺህ 2 መቶ 3 ተማሪዎች በአዲስ አበባ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ላይ በዘጠኝ ካንፓሶች የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ይወስዳሉ፡፡
በመጀመሪያዉ ዙር የሶሻል ሳይንስ እና በሁለተኛ ዙር የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና የሚወስዱ ሲሆን የሚፈተኑባቸዉ የመፈተኛ ክፍሎች እና ወንበሮች ፣ የማደሪያ ክፍሎቻቸዉ ፣ የመመገቢያ ቦታዎች እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች ሁሉ ተማልተዉ ዩኒቨርስቲዎች ዝግጁ ሆነዉ እየጠበቋቸዉ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛዉ ገብሩ ገልጸዋል፡፡
ሀላፊዉ አክለዉም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ5 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፣ በኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በፌደራል ቴክኒክና እልጠና ዩኒቨርሲቲዎች ለፈተናዉ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን ተናግረዋል፡፡ በነዚህ የፈተና ጣቢያዎች ላይ ተማሪዎችን ሊፈትኑ የሚችሉ 997 ፈታኞች ፣ ሱፐርቫይዘሮች እና የጣቢያ ሀላፊዎች ተዘጋጁተዉ ተማሪዎችን እየጠበቁ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎችን ከሚማሩባቸዉ ትምህርት ቤቶች ወደ ሚፈተኑባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያጋጉዙ 300 አውቶቢሶች መዘጋጀታቸዉንም ጨምረዉ የገለጹ ሲሆን የኒቨርሲቲዎችም ፈተናዉን ለመስጠት ሙሉ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ማጠናቀቃቸዉንም አሳውቀዋል፡፡
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube:
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
7.6K viewsAbebe Chernet, edited 12:07