Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wekitawi_meraja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wekitawi_meraja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wekitawi_meraja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.40K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 21:51:49
የሸዋሮቢት ከንቲባ ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ

የሸዋሮቢት ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው አሁን ከመሸ 3:00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሀይሎች ጥቃት ተፈፅሞበት ህይወቱ እንዳለፈ ምንጮች ዘግበዋል

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
1.4K viewsedited  18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 21:19:57
በሁለት ህፃናት ላይ የተፈፀመ የግድያ ወንጀል

#Ethiopia | በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ (ኮምዶሚኒየም) በሁለት ህፃናት ላይ የተፈፀመው የግድያ ወንጀል፤ የተፈፀመው ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ነው፡፡

በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ በምትሰራ ወንጀል ፈፃሚ አማካኝነት ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ የሁለት ዓመትና የሦስት አመት ህፃናት ህይወት አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት ወንጀል ፈፃሚው በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡

ከአሰሪዎቿ ጋር በተፈጠረ ግጭት ነው ተብሏል።

"አስቸኳይ ፍትሕ ይሰጠን!" በማለት በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ቁጣቸውን ገልፀዋል።

የህፃናቱ ህይወት በወንጀል ፈፃሚዋ እንዴት እንዳለፈና ሌሎችንም መረጃዎች ፓሊስ ተጨማሪ መረጃ እያጣራ እንደሚገኝ እና ህብረሰተቡም እንዲረጋጋ ም/ ኮማንደር ማርቆስ አሳስበዋል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
1.8K views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:10:17
"ሕወሐት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሎበታል"

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ሕወሐት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰው እና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ ነው፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው።

አሁን እንደሚታየው አሸባሪውን ሕወሓት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ ወድቋል። ምክንያቱም:-

1. የሽብር ቡድኑ ሰላማችንን እንዳያደፈርስና ሀገራችንን እንዳያፈርስ መከላከል ስለሚገባ፤

2. ሕወሐት ወደ ትግራይ የሚላከውን ርዳታ ለተቸገረው ሕዝብ እንዳይደርስ፣ በተቃራኒው እርዳታው ለጦርነት እንዲውል እያደረገ በመሆኑ መንግሥት እርዳታው ለተረጂው ሕዝብ እንዲደርስና ትግራይ ውስጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሕዝቡን ከችግር የመከላከል ግዴታ ስላለበት፤

3. ሕወሐት በእኩይ ተግባሩ ሕዝብን በረሃብ ለመቅጣት አቅዶ ተደጋጋሚ ጦርነት የሚከፍተው በክረምት የግብርና ወቅት በመሆኑ መንግሥት ወረራውን እየተከላከለ ያለው ሕዝብን ከረሃብ የማዳን ግዴታ ስላለበት ጭምር ነው።

ይሁንና በሕወሓት የሽብር ቡድን እየደረሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም መንግሥት ለሰላማዊ አማራጭ ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባሉበት ሁኔታ፣ አሸባሪውን ሕወሓት መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።

በመሆኑም ሕወሓት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት ሃገራችንን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይላችን በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ ይገኛል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
2.5K viewsedited  16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 18:38:31 አሁን ነው መጠንቀቅ፤ አሁን ነው ማሰብ፤ አሁን ነው ጥበብ እሚያስፈልገው፡፡ ድሉ የኢትዮጵያ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡ ታዲያ ድል ተገኘ ተብሎ ወደ መቀሌ በፍጥነት መገስገስ አደጋ አለው፡፡ እናም ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ ጦርነቱ ከህውሃት ጋር እንዳልሆነ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ህወሀት ቅጥረኛ ወታደር ነው፡፡ ተቀጥሮ እሚዋጋ ሽፍታ ነው፡፡ የራሱ አላማና ግብ የለውም፡፡ አላማው ቀጣሪዎቹ ያሉትን መፈፀም ነው፡፡ ቀጣሪዎች ደግሞ ግብፅ እና አሜሪካ ናቸው፡፡ ይህ የፈጠራ ወሬ እሚመስለው እሚጠራጠር ብዙ ሰው አለ፡፡ ግን አውነት ነው፡፡ ህወሀት ለትግራይ ህዝብ አይደለም እሚታገለው፡፡ ይህን አውነት እመኑ፡፡ ተቀጣሪ ሽብርተኛ ነው፡፡ አሁን ጥበብ ነው እሚያስፈልገው፡፡ አሁን የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ምእራባውያን እየጠበቁ ያሉት የመንግስትን ስህተት ነው፡፡ ሁሉም ተናቦ ለመጮህ አቆብቁቧል፡፡ ማእቀብ ምናምን ለማለት የተጣደፉ ይመስላሉ፡፡ ከዚህ ጦርነት የመንግስትን ስህተት ነው እየፈለጉ ያሉት፡፡

እስካሁን መንግስት እየሄደበት ያለው መንገድ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ አሁን ጦርነቱ የአእምሮ ጨዋታ ሆኗል፡፡ ምእራባውያን ያሰቡት ሳይሆን ያላሰቡት እየሆነ ተቸግረው በአለም ፊት ሃፍረታቸውን እየተከናነቡ ነው፡፡ ሞያ በልብ ነው ኢንዲሉ ሁሉም ነገር በዝግ መሆኑ ደግሞ አስጨንቋቸዋል፡፡ እንደዚህ ጊዜ ምእራባውያን የቀለሉበትና የተናቁበት ጊዜ ያለ አይመስልም፡፡ የአለም ሃገራት ፊታቸውን አዙረውባቸዋል፡፡ ፍትሃዊ አይደላችሁም ብለዋቸዋል፡፡ ሴራቸው እና ሃፍረታቸው ተጋልጦ በአለም ህዝብ ፊት አለመታመንን፤ መቅለልን፤ ውርደትን እየተከናነቡ ነው፡፡ ለዚህ ደግመ የኢትዮጵያ ድርሻ ቀላል አይደለም፡፡ ሁሉም ባይባሉ በኢትዮጵያ ላይ ጥርሳቸውን የነከሱ አሉ፡፡ እናም ህወሃት መንግስትን ስህተት ውስጥ ለመክተት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ በምስራቅም በምእራብም በደቡብም እንዳበደ ውሻ እየተናከሰ ነው፡፡ መንግስትን በማሳሳት ያልተገባ እርምጃ እንዲወስድ እየተሟሟቱ ነው፡፡ እናም የመንግስት ውሳኔ ከስሜት የራቀ በጥበብ ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል፡፡ ቸኩሎ መቀሌ መግባቱ ምንም ጥቅም የለውም፡፡ እንደውም መንግስት መቀሌ ገባ ማለት ህወሀት ራስ ምታት የሆነበትን የህዝብ ጥያቄ አቃለለት ማለት ነው፡፡ እናም ህዝቡ ራሱ ሊያስወግደው ይገባል፡፡ በቃኝ ብሎ ህወሀትን ሊተፋው ይገባል፡፡ አሳልፎ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ህወሀት አሁን በጣም የተዳከመበት ወቅት ላይ ስለሆነ ህዝቡም ስለተሰላቸ ከበባውን እያጠበቡ መሪዎቹን ቀለበት ውስጥ መክተት እና እነሱን ከህዝብ ነጥሎ ማስወገድ/መምታት ብቻ ነው መፍትሄው፡፡ መቀሌ ምንም ነገር የለም፡፡ መሪዎቹ ያሉት በረሃ ዋሻ ውስጥ ነው፡፡ ዘመናዊ ቪላ የሆነ ዋሻ ሰርተው በረሃ ውስጥ ነው እሚኖሩት፡፡ ምናቸው ሞኝ ነው ከተማ ለዛውም መቀሌ እሚኖሩት፡፡ እና መቀሌ ተያዘች ማለት አለቀለት ማለት አይደለም፡፡ የጦርነቱ ግብ መቀሌን መያዝ መሆን የለበትም፡፡ የወያኔን መሪዎች ማስወገድ ነው ግቡ መሆን ያለበት፡፡ መቀሌን ስትይዝ ያኔ ህወሃት መስዋአት የሚያረጋቸው የተዘጋጁ ምስኪን ሰዎች አሉ፡፡ እሱ ራሱ እያረዳቸው በኢትዮጵያ መንግስት እያሳበበ/እየጮኸ አለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ እንዲዘምት ያደርጋሉ፡፡ ህወሀት የምእራባውያን እና የግብፅ ተቀጣሪ ጦር መሆኑን መርሳት የለብንም፡፡ ስለዚህ የምንወስናቸው ውሳኔዎች እነዚህን ሃይሎች ታሳቢ ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
2.6K views15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:36:01 ሰበር ዜና
ጀ/ል ጻድቃን ገ/ትንሳይ፣
ጀ/ል ታደሰ ወረደ (ወዲ ወረደ)፣
ጀ/ል ዩሃንስ (መዲድ)፣
ጀ/ል ከበደ ሸሪፎ፣
ጀ/ል አብረሃ ድንኩል እና ወዲ አባተ ስብሰባ ላይ እያሉ ባሉበት አካባቢ በድሮውን እርምጃ መወሰዱን ምንጮች ገልጸዋል እንግድህ ከነዚህ የህወሓት አመራሮች ውስጥ ማን ይሙት ማን ይትረፍ ሰሞኑን በቲቪያቸው መስኮት ብቅ ሲሉ ነው የምናውቀው:: ሌላው ባለፈው በጀት የተመታው አንቶኖቭ አውሮላን ውስጥ ለግዜው ስሙን እማልጠቅሰው ከፍሰሃ ማንጁስ በተጨማሪ ከፍተኛ የህወሓት አመራር እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል::
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
2.8K views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:21:54
ቅኔውን ይቀኙት የለ
3.2K views10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:14:41
ያማል ቅኔው አለች

ቻናላችንን በመቀላቀል
ዓለም-አቀፋዊ እና አገር-አቀፍ መረጃዎችን በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።
@Merja01
3.4K viewsedited  07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 08:41:38
#Breaking
የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ ጋር የነበረውን “የቪዛ ማመቻቸት ስምምነት” ሙሉ በሙሉ ለማቆም ወሰነ!!

ውሳኔው የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ በህብረቱና እና በሩሲያ መካከል የነበረው “የቪዛ ማመቻቸት ስምምነት” ለማቆም ሚያስችላቸውን እርምጃ ለመውሰድ ላለፉት ሁለት ቀናት በቼክ ሪፐብሊክ ከመከሩ በኋላ የተደረሰ ስምምነት ነው ተብሏል፡፡

ሚኒስተሮቹ በውይይታቸው ከሩሲያ ወደ አጎራባች ግዛቶች የሚደረጉ የድንበር ማቋረጦች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ትኩረት ሰጥተው የተመለከቱት አንኳር ነጥብ እንደነበር የአውሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል አስታውቋል፡፡ሚኒስትሮቹ የድንበር ማቋረቱ ሁኔታ በአውሮፓ ከፍተኛ የሆነ ደህንነት ስጋት መደቀኑን በተመለከተ መወያየታቸውም ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ ጋር የነበረውን “የቪዛ ማመቻቸት ስምምነት” ሙሉ በሙሉ ለማቆም መወሰኑ ጆሴፕ ቦሬል ከደቂቃዎች በፊት በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ ይፋ አድርገዋል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
3.5K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:00:56
የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረገው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ያለምንም ለውጥ እንዲቀጥል የተወሰነ መሆኑ የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታውቋል።

ቻናላችንን በመቀላቀል
ዓለም-አቀፋዊ እና አገር-አቀፍ መረጃዎችን በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።
@Merja01
3.9K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:53:51 ሰበር ዜና ህወሃት ሳያስብበት በከፈተው ጦርነት በርካታ አመራሮቹን እያጣ ይገኛል። በዚህም

1:- ጀነራል አስርተ
2:- ኮ/ል ጉዕፅ
3:- ኮ/ል በርሀ በጊዕ እና
4:- ኮ/ል ወርቂ የተባሉት አመራሮች በመከላከያ ሰራዊት መደምሰሳቸው ታውቋል

ቻናላችንን በመቀላቀል
ዓለም-አቀፋዊ እና አገር-አቀፍ መረጃዎችን በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።
@Merja01
4.0K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ