Get Mystery Box with random crypto!

አሁን ነው መጠንቀቅ፤ አሁን ነው ማሰብ፤ አሁን ነው ጥበብ እሚያስፈልገው፡፡ ድሉ የኢትዮጵያ እንደሚ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

አሁን ነው መጠንቀቅ፤ አሁን ነው ማሰብ፤ አሁን ነው ጥበብ እሚያስፈልገው፡፡ ድሉ የኢትዮጵያ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡ ታዲያ ድል ተገኘ ተብሎ ወደ መቀሌ በፍጥነት መገስገስ አደጋ አለው፡፡ እናም ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ ጦርነቱ ከህውሃት ጋር እንዳልሆነ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ህወሀት ቅጥረኛ ወታደር ነው፡፡ ተቀጥሮ እሚዋጋ ሽፍታ ነው፡፡ የራሱ አላማና ግብ የለውም፡፡ አላማው ቀጣሪዎቹ ያሉትን መፈፀም ነው፡፡ ቀጣሪዎች ደግሞ ግብፅ እና አሜሪካ ናቸው፡፡ ይህ የፈጠራ ወሬ እሚመስለው እሚጠራጠር ብዙ ሰው አለ፡፡ ግን አውነት ነው፡፡ ህወሀት ለትግራይ ህዝብ አይደለም እሚታገለው፡፡ ይህን አውነት እመኑ፡፡ ተቀጣሪ ሽብርተኛ ነው፡፡ አሁን ጥበብ ነው እሚያስፈልገው፡፡ አሁን የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ምእራባውያን እየጠበቁ ያሉት የመንግስትን ስህተት ነው፡፡ ሁሉም ተናቦ ለመጮህ አቆብቁቧል፡፡ ማእቀብ ምናምን ለማለት የተጣደፉ ይመስላሉ፡፡ ከዚህ ጦርነት የመንግስትን ስህተት ነው እየፈለጉ ያሉት፡፡

እስካሁን መንግስት እየሄደበት ያለው መንገድ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ አሁን ጦርነቱ የአእምሮ ጨዋታ ሆኗል፡፡ ምእራባውያን ያሰቡት ሳይሆን ያላሰቡት እየሆነ ተቸግረው በአለም ፊት ሃፍረታቸውን እየተከናነቡ ነው፡፡ ሞያ በልብ ነው ኢንዲሉ ሁሉም ነገር በዝግ መሆኑ ደግሞ አስጨንቋቸዋል፡፡ እንደዚህ ጊዜ ምእራባውያን የቀለሉበትና የተናቁበት ጊዜ ያለ አይመስልም፡፡ የአለም ሃገራት ፊታቸውን አዙረውባቸዋል፡፡ ፍትሃዊ አይደላችሁም ብለዋቸዋል፡፡ ሴራቸው እና ሃፍረታቸው ተጋልጦ በአለም ህዝብ ፊት አለመታመንን፤ መቅለልን፤ ውርደትን እየተከናነቡ ነው፡፡ ለዚህ ደግመ የኢትዮጵያ ድርሻ ቀላል አይደለም፡፡ ሁሉም ባይባሉ በኢትዮጵያ ላይ ጥርሳቸውን የነከሱ አሉ፡፡ እናም ህወሃት መንግስትን ስህተት ውስጥ ለመክተት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ በምስራቅም በምእራብም በደቡብም እንዳበደ ውሻ እየተናከሰ ነው፡፡ መንግስትን በማሳሳት ያልተገባ እርምጃ እንዲወስድ እየተሟሟቱ ነው፡፡ እናም የመንግስት ውሳኔ ከስሜት የራቀ በጥበብ ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል፡፡ ቸኩሎ መቀሌ መግባቱ ምንም ጥቅም የለውም፡፡ እንደውም መንግስት መቀሌ ገባ ማለት ህወሀት ራስ ምታት የሆነበትን የህዝብ ጥያቄ አቃለለት ማለት ነው፡፡ እናም ህዝቡ ራሱ ሊያስወግደው ይገባል፡፡ በቃኝ ብሎ ህወሀትን ሊተፋው ይገባል፡፡ አሳልፎ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ህወሀት አሁን በጣም የተዳከመበት ወቅት ላይ ስለሆነ ህዝቡም ስለተሰላቸ ከበባውን እያጠበቡ መሪዎቹን ቀለበት ውስጥ መክተት እና እነሱን ከህዝብ ነጥሎ ማስወገድ/መምታት ብቻ ነው መፍትሄው፡፡ መቀሌ ምንም ነገር የለም፡፡ መሪዎቹ ያሉት በረሃ ዋሻ ውስጥ ነው፡፡ ዘመናዊ ቪላ የሆነ ዋሻ ሰርተው በረሃ ውስጥ ነው እሚኖሩት፡፡ ምናቸው ሞኝ ነው ከተማ ለዛውም መቀሌ እሚኖሩት፡፡ እና መቀሌ ተያዘች ማለት አለቀለት ማለት አይደለም፡፡ የጦርነቱ ግብ መቀሌን መያዝ መሆን የለበትም፡፡ የወያኔን መሪዎች ማስወገድ ነው ግቡ መሆን ያለበት፡፡ መቀሌን ስትይዝ ያኔ ህወሃት መስዋአት የሚያረጋቸው የተዘጋጁ ምስኪን ሰዎች አሉ፡፡ እሱ ራሱ እያረዳቸው በኢትዮጵያ መንግስት እያሳበበ/እየጮኸ አለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ እንዲዘምት ያደርጋሉ፡፡ ህወሀት የምእራባውያን እና የግብፅ ተቀጣሪ ጦር መሆኑን መርሳት የለብንም፡፡ ስለዚህ የምንወስናቸው ውሳኔዎች እነዚህን ሃይሎች ታሳቢ ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01