Get Mystery Box with random crypto!

በሁለት ህፃናት ላይ የተፈፀመ የግድያ ወንጀል #Ethiopia | በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

በሁለት ህፃናት ላይ የተፈፀመ የግድያ ወንጀል

#Ethiopia | በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ (ኮምዶሚኒየም) በሁለት ህፃናት ላይ የተፈፀመው የግድያ ወንጀል፤ የተፈፀመው ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ነው፡፡

በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ በምትሰራ ወንጀል ፈፃሚ አማካኝነት ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ የሁለት ዓመትና የሦስት አመት ህፃናት ህይወት አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት ወንጀል ፈፃሚው በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡

ከአሰሪዎቿ ጋር በተፈጠረ ግጭት ነው ተብሏል።

"አስቸኳይ ፍትሕ ይሰጠን!" በማለት በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ቁጣቸውን ገልፀዋል።

የህፃናቱ ህይወት በወንጀል ፈፃሚዋ እንዴት እንዳለፈና ሌሎችንም መረጃዎች ፓሊስ ተጨማሪ መረጃ እያጣራ እንደሚገኝ እና ህብረሰተቡም እንዲረጋጋ ም/ ኮማንደር ማርቆስ አሳስበዋል፡፡

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01