2022-08-31 14:15:08
ከጋዝጊብላ ወረዳ ፀጥታ ም/ቤት በወቅታዊ የፀጥታና ደህንነት ጉዳይ የተላለፈ ውሳኔ! 1ኛ. ማንኛውም እግረኛ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
2ኛ. የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታ በማናፈስ በህብረተሰብ መካከል ሽብርና ውዥንብር በሚነዙ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ላይ በህግ እንዲጠየቁ ተወስኗል።
3ኛ. ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ማለትም ምግብ ቤት፣ ሱቆች፣ ወፍጮ ቤቶች፣ባንክ ቤቶች እና ሌሎች መሠል የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋሞችን መዝጋት የተከለከለ ነው።
4ኛ. ወቅታዊ ሁኔታውን ምክንያት በማድረግ በምርትና አገልግሎት ላይ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ, ምርትን በመሠወር ዕጥረት እንዲከሰት ማድረግ በህግ ያስጠይቃል።
5ኛ. ለጸጥታ ስራ ስምሪት ከተሰጣቸው ተሸከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም ተሸከርካሪ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
6ኛ. ከጸጥታ መዋቅሩ ውጭ በየትኛውም ሰዓትና ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
7ኛ. በከተማችን የሚገኙ የመንግስትና የግል ታጣቂዎች መንግስት በሚያሰማራው የፀጥታ ስራ በቅንጅትና ቁርጠኝነት ተሳታፎ በማድረግ ህዝብና መንግስት የጣለባችሁን ሃላፊነት መወጣት ይኖርባችኋል፣ ሃላፊነታቸውን በማይወጡት ላይ አስፈላጊውን ርምጃ ይወሰዳል።
8ኛ. ማንኛውም ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ግለሰብ ሆነ ድርጅት የትኛውንም ሚዲያ ተጠቅሞ ስለጦርነት: ስለ ጥምር ጦሩ እንቅስቃሴ: ስምሪት: አቋምና የትጥቅ ሁኔታ መዘገብ መረጃዎችን ማሰራጨት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
9ኛ. ማንኛውም ግለሠብ በከተማው አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ወይም ድርጊቶች፣ ጸጉረ ልውጥ ሰዎች፣ አጠራጣሪ ግለሰብ ተሽከርካሪ ወዘተ ሲታዩ ለጸጥታ ተቋማት የመጠቆም ግዴታ አለበት።
10ኛ. በመንግስት ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም አካል የመከላከያ: የልዩ ሀይል: የፌዴራል እና የመደበኛ ፓሊስ መለዮ በከፊል ሆነ ሙሉ መልበስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፣ ለብሶ የተገኘ በህግ ይጠየቃል።
11ኛ. ማንኛውም የቤት አከራይ ወይም አልጋ ቤቶች ተከራዮቻቸውን ማንነታቸውን የሚገልፅ ህጋዊ መታወቂያ ስለመኖራቸው የማረጋገጥና መታወቂያውን ኮፒ በማድረግ ለፀጥታ ተቋም በወቅቱ የማሳወቅ ግደታ አለባቸው።
12ኛ. ከወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በምግብ ቤቶች፣ በመጠጥ ቤቶች፣ በካፌዎችና ፊልም ቤቶች ከምሽት 1:00 ሰዓት በኋላ ማንኛውም አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነዉ
13ኛ. በማህበራዊ ሚዲያ ሆነ በማናቸውም የግንኙነት አይነት ሀሰተኛ መረጃ፣ በሬ ወለደ ወሬ በመንዛት በህዝብ ላይ አላስፈላጊ ውዥንብርና ስጋት መፍጠር በህግ ያስጠይቃል። ህዝቡም መረጃዎችን ከትክክለኛ የመረጃ ምንጭ ብቻ በመውሠድ በበሬ ወለደ ወሬ ሳይደናገጥ መደበኛ ተግባሩን በተረጋጋ መንገድ እንዲያከናወን እናሳስባለን።
የጋዝጊብላ ወረዳ ፀጥታ ም/ቤት
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
2.1K views11:15