Get Mystery Box with random crypto!

🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ wekitawi_meraja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ wekitawi_meraja — 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @wekitawi_meraja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.40K
የሰርጥ መግለጫ

This is national and international News and advertising channel
🇪🇹🇪🇹🇪🇹"ስለኢትዮጲያ ሳትሰማ ያሳለፍከው ቀን እንደባከነ ይቆጠራል" 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
⏭▶️➡️ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ዜናዎችን በፍጥነት ይደርሶታል።🔚

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-30 21:03:26
ከሱዳን ደብቀን ልናስገባ የነበረውን የጦር መሳሪያ የኢትዮጵያ አየር ሀይል አጋይቶብናል

He looks high
ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
3.1K views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:58:36 በኮምቦልቻ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የከተማችን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ሰፊው  ከመከረ በኋላ በቀጣዮቹ ነጥቦች ላይ ጥብቅ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም በኮምቦልቻ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ዉሳኔዎች ተላልፈዋል።

1ኛ የጠላትን ሀሳብና እንቅስቃሴ በመደገፍ አሉባልታ በማናፈስ በህብ ረተሰብ መካከል ሽብርና ውዥንብር በሚነዙ የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ላይ በህግ እንዲጠየቁ ተወስኗል ።

2ኛ  በከተማ ደረጃ  አገልግሎት የምትሰጡ  ታክሲዎች እስከ  11 ሰዓት  ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ  ውሳኔ ተላልፏል ።

3ኛ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተንተርሶ የከተማችን ነዋሪ ላይ ያለ አግባብ ዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ሸቀጦችን በመከዘን በገበያ ላይ እጥረትን  በመፍጠር ነዋሪውን ለተጨማሪ ወጭና የኑሮ ጫና የሚጥሉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ  ይወሰዳል።

4ኛ ከወቅታዊ የጸጥታ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በምግብ ቤቶች በመጠጥ ቤቶች በካፌዎችና በግረሶሪዎች ላይ እስከ 11 ስዓት ጀምሮ ማንኛውም አገልግሎት መሰጠት የተከለከለ ነው።

5ኛ  የአልጋ አከራይ ሆቴሎዎች የመኖሪያ ቤትና የመደብ አከራዮች የተከራዩን ማንነት የሚገልጽ  መረጃ  በመያዝ  እንድታስገለግሉና በአቅራቢያችሁ ለሚገኝ የጸጥታ ተቋማት ጋር በቅርበት በመስራት የተከራዩን መታወቂያ ኮፒ በማድረግ  ጭምር የመሰጠት ግዴታ አለባችሁ።

6ኛ በከተማው አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ወይም  ድርጊቶች ጸጉረ ልውጥ ሰዎች አጠራጣሪ ተሽከርካሪዎች ወዘተ ሲታዩ  ለጸጥታ ተቋማት መጠቆም እንደሚገባ ተገልጿል።

7ኛ በከተማው ውስጥ የሚገኙ DSTV ማሳያ ቤቶች ፣የቡና መሸጫ ቤቶች ፣የሺሻና የጫት ማስቃሚያ ቤቶች ውስጥ ተሰብስቦ  ጫት መቃም በህግ ያስጠይቃል።

8ኛ  በማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አላስፈላጊ ህዝብን ወደ አለመረጋጋት የሚወስዱ የተዛቡ መረጃዎችን መልቀቅ በህግ ያስጠይቃል።

9ኛ  የከተማችን የጸጥታ ኃይሎች ከመንግዜውም በላይ በመናበብ በመቀናጀት የተሰጣችሁን ኋላፊነት በብቃት በመወጣት  ህግ የማስከበር ሚናችሁን እንድትወጡ በጥብቅ እናሳስባለን። የከተማችን ነዋሪም በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በበሬ ወለደ በሀሰተኛ በሚለቀቁ  መረጃዎች  ሳይደናገር እና አላስፈላጊ ውዦብር ውሰጥ ሳይገባ በተረጋጋና በሰከነ መልኩ መደበኛ ሰራችሁን እንድታከናውኑ ተገልጿል።

10ኛ ከተፈቀደላቸው የከተማችን የፀጥታ ኃይሎች ወጭ የጦር መሳሪያ ይዞ በቡድንም ሆነ በግል  ይዞ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

11ኛ  መንግስት  ከሚሰራቸው የተቀናጀ ድጋፍ አሰባሰብ ስርዓት ውጭ ለመከላከያ ፣ ለልዩ ኃይል ድጋፍ በሚል ሰበብ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ግብዓቶችን ማሰባሰብ ፈጽሞ የተከለከለ ነዉ። ያለ ከተማ አስተዳደሩ ዕውቅና  በግልም ሆነ በቡድን ወደ ግንባር መንቀሳቀስ  የተከለከለ ነው።

13ኛ ማንኛውም ተቋማት ተሽርካሪዎችን  ለጸጥታ ሰራ በተፈለጉ ጊዜ የጸጥታ ተቋሙ ሲጠይቅ  ቀና ትብብር እንድታደርጉ ከተማ አስተዳዳሩ አሳስቧል።

14ኛ .ከዛሬ ነሀሴ 24/2014ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም የከተማችን ነዋሪ ከ11 ጀምሮ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። በቀጣይም የጸጥታ ምክር ቤቱ በየጊዜው የሚያወጣቸውን ውሳኔዎች እናሳውቃለን ሲል የከተማ መስተዳድሩ ማስታወቁን ብስራት ራዲዮ ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
3.2K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:35:52
የወልድያ ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ ዶክተር ዳዊት መለሰ የዛሬ ነሀሴ 24 የከተማዋ ነባራዊ እዉነት በቦታዉ ላይ ሆነዉ ይናገራሉ።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01
3.8K views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:25:05 የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በበ2015 ዓመት ቀጣይ አመት ለሙከራ ይሰጣል።

የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በ2015 ዓመት እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።አዲሱ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት በርካታ ደረጃዎችን አልፎ ለሙከራ ትግበራ የደረሰ መሆኑን የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ ለብስራት ሬድዮ ገልፀዋል ።

በስርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ላይ የተመረጡ የመማር ማስተማር የልህቀት ማዕከላት ዩኒቨርሲቲዎች እና ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በአማካሪነት እንደተሳተፉበት ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል ።ይህ ሥርዓተ ትምህርት ሀገር በቀል እውቀትን፣ ግብረ ገብነትን ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የተላበሰ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል ።

በመሆኑም በዚህ የሙከራ ትግበራ ወቅት ከመምህራንና ከባለድርሻ አካላት በርካታ ግብዓቶች እንደሚሰበሰቡ ጠቅሰው ወላጆችና ሌሎችም አስተያየት እዲሰጡበት በድረ ገፅ ይለቀቃል ተብላል።በሙከራ ትግበራው ወቅት የሚመጡ አስተያየቶች ተካተው በ2016 ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባም ተገልጿል ።

ቻናላችንን በመቀላቀል
ዓለም-አቀፋዊ እና አገር-አቀፍ መረጃዎችን በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።
@Merja01
3.7K views11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:09:50
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለአንድ ደቂቃ 50 ሳንቲም የአገልግሎት በማስከፈል ላይ ይገኛል

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ በ25 ከተሞች አገልግሎት እጀምራለሁ አለ።

ከሁለት ዓመት በፊት በወጣ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ጨረታ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በው ዕለት የመጀመሪያውን የደንበኞች የቴሌኮም አገልግሎቱን በድሬዳዋ አስጀምሯል።

ኩባንያው በመነሻ ኮዱ 07 በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች አካሂዷል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮች ለድሬዳዋ ደንበኞቹ በመሸጫ ሱቆች ይፋ ያደረገ ሲሆን ኔትወርኩን ለአንድ ወር የሚቆይ የሙከራ አገልግሎት ተጀምሯል።

ድርጅቱ የድምጽ አገልግሎቱን በደቂቃ ከሳፋሪ ኮም ስልክ ቁጥሮች ወደ ሳፋሪኮም እና ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዶች በደቂቃ 50 ሳንቲም የሚያስከፍል ሲሆን ለኢንተርኔት ደግሞ በ10 ብር 120 ሜጋ ባይት፣ 900 ሜጋ ባይቱን በ50 ብር እንዲሁም ሁለት ጌጋ ባይት መጠን ያለውን ኢንተርኔት ደግሞ በ100 ብር ለ30 ቀናት በመደበኛነት በመሸጥ ላይ ነው።

ኩባንያው አክሎም እስከ ቀጣዩ ሚያዝያ 2015 ድረስ ባሉት ስምንት ወራት ውስጥ በ25 የኢትዮጵያ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደሚጀምር ለአልዓይን አስታውቋል።

አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ኮምቦልቻ፣ ሀረር፣ አዳማ፣ ሀዋሳ፣ጅማ፣ ጅግጅጋ እና ሌሎች ከተሞች በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ አገልግሎቶቹ ከሚጀመርባቸው አካባቢዎች ዋነኞቹ ናቸውም ተብሏል።
ቻናላችንን በመቀላቀል
ዓለም-አቀፋዊ እና አገር-አቀፍ መረጃዎችን በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።
@Merja01
3.7K views11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:20:16
ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም

"........
የማንጨበጥ ነበልባል-እሳት ነን ለጠላታችን
ፍሙ ከርቀት ይፋጃል- ብረት ያቀልጣል ክንዳችን
ኢትዮጵያ በእኛ ደም ደምቃ-በአፅማችን ፍላጽ ተማግራ
እንደ ታፈረች እንድትኖር-ከዘመን ዘመን ተከብራ፤
.........."

ይህ ስንኝ ከጀግናው መከላከያ ሠራዊታች መሪ መዝሙር ላይ ተቀንጭቦ የቀረበ ነው!!

ሠራዊታችን የተሠጠውን ግዳጅ በአስደናቂ ብቃት ፈፅሞ የሚያሳይ፤ ከፍተኛ ወታደራዊ የማድረግ ብቃት ያለው፣ የዘመኑን የጦርነት አቅሞች በሚገባ ተጠቅሞ በድል ላይ የሚረማመድ፤ በስነ-ልቦናዊና ሞራላዊ ዝግጁነቱ ጠንካራ የአሸናፊነትን መንፈስ የታጠቀ ነው።

የውጭም ይሁን የውስጥ ጠላቶቻችን በከንቱ ይዳክራሉ እንጂ ከአይበገሬው ጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን እና የጥምር ኃይሎቻችን ፊት የሚቆም አንዳችም ምድራዊ ኃይል የለም።

የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት
#አሸናፊነት መለያችን ነው!!
ቻናላችንን በመቀላቀል
ዓለም-አቀፋዊ እና አገር-አቀፍ መረጃዎችን በቴሌግራም ገፃችን ይከታተሉ።
@Merja01
4.1K views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ