Get Mystery Box with random crypto!

መርጌታ ባምላኩ የባህል መዳኒት

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedon_enewek — መርጌታ ባምላኩ የባህል መዳኒት
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedon_enewek — መርጌታ ባምላኩ የባህል መዳኒት
የሰርጥ አድራሻ: @tewahedon_enewek
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.29K
የሰርጥ መግለጫ

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፈሪት ነው
ኑዉ ተፈወሱ ጥበብ በኛ አለ
በታማኝነት እንሰራለን ይደውሉ ያናግሩን
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
መልካም ቀን ተመኘሁ
መርጌታ ባምላኩ ነኝ

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-08-21 00:21:38 የሴት ቀስት/ ቀስተንቻ/ሰርቲ/

በቅንነት ሼር ሼር በማድረግ ለተቸገሩ ይድረስ
                    በምዕራቡ ዓለም ለምግብነት እና ለመድኃኒትነት/
እኛው ዘንዳ ለቤት አጥር አውለን ዝቅ ያደረግናት ድንቅ ዕጽ።

#የሴት ቀስት
የሴት ቀስት በወይና ደጋ፤ በደጋ ፤እንዲሁም በቆላማ ፤አከባቢ በብዛት የሚገኝ ቁጥቋጦ መሳይ ቀጫጭን ቅጠል ያለው እንዲሁም በትንሹ እሾህ ያላት ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላት እጽ ናት።

ለፊንጢጣ ኪንታሮት ፦
#የሴት ቀስት ሥር እና ቅጠሏ ሰብስበው በማድረቅ በብረት ምጣድ አድርገው በእሳት እስኪ ከስል ድረስ ማቆየት ከዛ በኃላ እፅዋቷ ተቃጥላ ከከሰለች በኃላ አውጥቶ በማቀዝቀዝ 25 ግራም አልያም በሾርባ ማንኪያ 4 በመለካት በፀጉር ቅቤ በደንብ አድርገው የከሰለው ዕጽ መለወስ!(በድጋሚ የተለጠፈ)

ለድክመተ ወሲብ፦
#የሴት ቀስት ገና ሳያድግ ሙሽራውን በመልቀም አዘውትረው ልክ እንደ ፎሰልያ ጥብስ ቀንበጥ ቀንበጡን በወይራ ዘይት እንዲሁም ከማንኛውም የምግብ አትክልት ጋ አቀላቅለው በመጥበስ ከተማእንደምግብነት ቢጠቀሙ ፍትወት ያዘገያል እንዲሁም ያጸናል።

ሀብቱ ለተልከሰከሰ፦
#የሴት ቀስት፣፩በቀል ፍየለ ፈጅ፣ሞይደር፣በወርቀ ዘቦ ሰፍተህ አስቀምጥ እንዲሁም ያዝ!

ለማይድን ቁስል፦
#የሴት ቀስት ቅጠሏን አድርቀህ በቁስሉ ላይ በየቀኑ እያፀዳህ ነስንስበት ከሳልስት ጀምሮ ይደርቃል።

ለማንኛውም የሆድ ህመም፦ቁርጠት/መንፋት/ተቅማጥ/ይሆናል።
#የሴት ቀስ ቅጠል ወቅጠህ በሾርባ ማንኪያ አንድ በመለካት በአንድ ሊትር ንፁህ ውኃ በጥብጠው በሻሽ በደንብ አጥለው ጧት በባዶ ሆድ አንድ ቀን ይጠጡ።ፍቱን ነው።

ለዓይነ ጥላ/ለሴት ዛር መንፈስ፦
#የሴት ቀስት ሥር በንጽህና ማክሰኞ ቀን ቆርጠው አድርቀው ሸርከት አድርጎ በመደቆስ ማታ ማታ ከከርቤ ዕጣን ጋር ለ ሰባት ቀናት ያክል ማታ ማታ መታጠን ሕልመ ለሊትም ያቆማል።

ለስራ አጥ/አልያም ስራ አልሳካ ላለው፦
#የሴት ቀስት ሥር፤የሞይደር ሥር ፣ከከርቤ ዕጣን ጋር በማቀላቀል ጧት ጧት እየታጠነ ይሂድ ይሳካለታል።

ለቋቁቻ/ለባርሌ/
#የሴት ቀስት፣የመቅሞቆ የሥሩ ቅርፊት በንፅህና አዘጋጅተው  አንድ የሾርባ ማንኪያ የቀስተንቻ የስሩ ቅርፊት አንድ የሾርባ ማንኪያ የመቅሞቆ ሥር ለክተው በአንድ ስኒ የጸጉር ቅቤ ለውሰው ለ 3 ቀን ይቀቡ ጧት ተቀብተው ለ7 ሰዓታት ኣቆይተው ይታጠቡ ፍፁም ያድናል።ፍቱን።

ለሽንት ማጥ፦
#የሴት ቀስት ሥር አሁንም በንጽህና አዘጋጅተው አንድ አንድ የሾርባ ማንኪያ የሴት ቀስት የተፈጨ ሥር በመለካት ለ 7 ቀናት በግማሽ በግማሽ ሊትር ውኃ በሻይ መልኩ እያፈሉ ቀዝቀዝ አድርገው ይጠጡ።ፍቱን

ለሪህ በሽታ፦
#የሴት ቀስት ሥር አድርቀው ፈጭተው አንድ ኪሎ ገደማ ያዘጋጁ!ከዛ በመቀጠል ጧት ጧት አንድ አንድ የሾርባ ማንኪያ በመለካት ከ ሴት ዕሬት ጁስ ጋር በማቀላቀል ለ 20 ቀን ያለ ስኳር ቢጠጡ እጅጉን ድንቅ ፈውስ ያገኙበታል።

ማሳሰብያ፦
#ያለ እውቀት በድፍረት እንዲሁም የእጽዋቱ ማንነት ሳይረዱ በይሆናል ማንኛውም ነገር ወደ ሆድ ውስጥ እንዳይወስዱ።

ሼር  በማድርግ ለወዳጅዎ የእጽዋት ፈዋሽነትን ማድረስዎ እንዳይረሱ!!



ለበለጠ መረጃ
0974743707
 
413 views21:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 00:21:07 #ጤና ይስጥልኝ ውድ #የኢትዮጵያ ልጆች እንዲሁም የዚህ ድህረገፅ ቤተሰቦች

በቅንነት ሼር ሼር በማድረግ ለተቸገሩ ይድረስ

# ዛሬ አንድ ወሳኝ የአባቶች መፍዝዝ ወይም እራስን ከጠላት የሚከላከል ፣የሚሰውር ጸሎት ላካፍላችሁ ወደድኩ።

#ቢስሚላሂ አቅየቱ አቤል ከቤል አውዙቢላሂ ወይዳኩል ገረመጁን  ገዳ አርመጁን  ከዋጁን ተሀረም  ተዋጁን ጋሬሩ ማቶ እንጅሩ  አናቄን  አፍጁንጁን  ማዴራሂር  አላተፈፊ አስፈሪደ አድህነኒ እምኩይናት ወነፍጥ እምበትር ወእምእብን  እመጥባይት ወእምሾተል ሊተ ለገብርከ እገሌ የራስን ክርስትና ስም እና መጠሪያ ስም ማስገባት 
#ገቢር

፩. #ነጭ እጣን
፪. #ከርቤ እጣን
፫. #የብር ቀለበት ወይም ድንብል
፬. #የጸጉር ቅቤ

#አሰራር እጣኖችን  ፈጭቶ አልሞ በቅቤው ለውሶ ቀለበቱን ወይም ድንብሉን ከእዚያው ላይ በማድረግ
ጥዋት በባዶ ሆድ ወደ ምስራቅ  አቅጫ ቁሞ ከተቻለ ከትክል ደንጋይ ላይ ቢሆን ይመረጣል ካልተቻለ እንዲሁ  ቁሞ ይህን ጸሎት አርባ ዘጠኝ ጊዜ ( 49 ) በተዘጋጀው ገቢር ላይ እፍ  እያሉ ጸልዮ   ሲጨርሱ ቀለበቱን መልበስ ወይም ድንብል ከሆነ በአንገት ማሰር በቅቤ የተለወሰውን ለ፯ ቀን (7) እራስን መቀባት  ነው።
#ይህን እየተቀቡ  ለ ፯ ቀን ከፆታዊ ግንኙነት ንጹሕ መሆን ያስፈልጋል  ።

#ይህ የተፈተነ የአባቶች ጥበብ  ነው።
ቢጠቀሙት መልካም ነው
እኔ ይህን ጥበብ ለማግኘት ከመምህሬ አሰግደው ብዙ ደጅ ጠንቸበት አለሁ እናም ሳቀርብላችሁ በቀና አዕምሮ ነው
ጥበብን ለጠቢባን

ሼር ሼር አድርጉ

ጥበብ  ታላቋን ታከብራለች!!!!

0974743707
          0974743707


ሐሳብ አስተያየት ካላችሁ
@Mnobd
403 views21:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 00:20:10 የግብረ ወሲብ ድክመት ኣይነቶች
፩ መንስኤ እስኪት /የሚይንሣሣ የሚያነቃቃ
፪ መጽንኤ አስኪት /የሚያጠነክር
፫ መፍትሔ እስኪት /የሚፍታ
፬ ዘኢይወርድ ገትር /የምያስወርድ የማያስቸኩል
፭ ጸላኤ ወሲብ /ዓይነጥላ /ፍራቻ ወይም ጥላቻ
6 በሴት ላይለሚደርስ የግብረ ሥጋ ጥላቻና ፍራቻ
7 የውሃ ሽንት ለሚንጠበጠብበትና ለሚከለክለው።
ከእነዚ መካክል የትኛው አንደሆነ እስተውሎ ምወቅና መረዳት
ያስፈልጋል።
ለምሳሌ። እንድ ሰው ብቻውን ተኝቶ ሳለ በእንቅልፍ ብልቱ የሚነሣ
ከሆነ በወሲብ ጊዜ የማይነሳ ከሆነ /የሚሰንፍ ከሆነ/ ይህ
አካላዊ ችግር ሳይሆን ልቦናዊ ወይም የግብረሥጋ/ጸልኤ
ወሲብ /ጥላቻ ነው
ሼር በማድረግ
ለሌሎችም ያጋሩ



ሐሳብ አስተያየትወን በዚህ ይጠይቁን
መርጌታ ባምላኩ


@Mnobd
405 viewsedited  21:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 12:44:17 የማንን ስብከት ማዳመጥ ይፈልጋሉ

የመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ

የመምህር ምህረተአብ አሰፋ

የመምህር ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

የመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳንን

የመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳንን

የመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ

የመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ትምህርቶች

የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን እይታ

የሊቀ ሊቃውን ዕዝራ ሐዲስ

እንዲሁም የሌሎችንም ሰባኪያን ትምህርቶች ለማግኘት ከስር JOIN የምትለውን ንኳት


https://t.me/Zemaryan
https://t.me/Zemaryan
https://t.me/Zemaryan
716 views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 19:55:50 ዘፈን ለምን ይከለከላል

➭ ዘፋኝነት የተከለከለበትን ምክንያት በግድ ማወቅ አለብኝ ለምን ትላለህ?

➨ ምክንያቱን ማወቅህ አያፀድቅህም አለማወቅህም አያስኮንንህም፡፡ ነገር ግን ዘፋኝ ብትሆን ትጠየቅበታለህ፡፡ ባትዘፍን ደግሞ ታዛዥ ተብለህ በእግዚአብሔር ዘንድ ትመሰገነበታለህ፡፡ ስለዚህ የሚመለከትህን ለምን አታደርግም?

➣ . . . ዘፈን ለምን እንደተከለከለ መዘርዘሩ ምስጢሩን እንደሚያጠበው መገለጹ ትክክል ነው፡፡ ቢሆንም ይሕ እንዳለ ሆኖ የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት የዘፈንን ጎጂ ገጽታ ማሳየት ይገባል፡፡

ሀ. ዘፈን የአጋንንት ስራ ነው፡፡ አጋንንት ይዘፍናሉና፡፡

➣ ለዚህ ምንም ማስተባበያ አያስፈልገውም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ›› በማለት ስለ አጋንንት ዘፋኝነት ይናገራል፡፡ ኢሳ 13፥21 አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን ተረዳ፡፡
ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል ‹‹ . . . እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር፡፡ አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር፡፡›› 1መቃ 36፡27-28 የዚህ ስፍራ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለውን አጋንንትን ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጎራ መሰለፋቸው ነው፡፡

➾ ዘፈን የአጋንንት ስራ መሆኑን ስታውቅ አይንህ ተገልጦ አንድ ምሥጢር መመርመር ይጀምራል፡፡ እስኪ ሀገራችንን ጨምሮ የጃማይካውያንንና የአንዳንድ የአፍሪካንና የሌሎችንም አህጉራት ዘፋኞችን ድርጊት ልብ ብለህ መርምር፡፡ ደግሞም ፀጉራቸውን አንጨብርውና በመናጥና በአሺሽ ጦዘው አንገታቸውን በማወናጨፍ የሚዘፍኑት ዘፈን መገኛውም እንደሆነ ማስተዋል ሞክር፡፡ የባለ ዛሮች ዝየራ አይተህ የምታውቅ ከሆነ ፍፁም ተመሳሳይ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡
ባለውቃቤዎችስ ሲደነፉ ተመልክተህ አታውቅምን? የባለ ውቃቤዎች ድንፋታ ደግሞ ቁርጥ እዋኽ፣ እዋኽ እየተባለ የሚዘፈነውን ባህላዊ ዘፈን ይመስላል፡፡ ፍከራው ቀረርቶውና በየብሄረሰብ የምትመለከተውን ዘፈንና ጭፈራ ብትመረምር ከዚህ የቀረበ መመሳሰል አታጣበትም፡፡ ቅዱስ ሐዊ እንደተናገረው ‹‹ዘፈንና ዳንስ ከሰይጣን የተገኘ›› ነውና፡፡

➨ አጋንንት ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ የዘፈንና የጭፈራ ዓይነት ሁሉ ምንጮች ናቸውና፡፡ ከዚህ በኋላ የእኔ ስጋት ዘፋኞች እና ጨፋሪዎች አዳዲስ የዘፈን እና ጭፈራ መንገድ (ስታየል) ለመኮረጅ ሲሉ አጋንንት ያደሩባቸው ሰዎች ፍለጋ በየፀበል ስፍራው መዞር እንዳይጀምሩ ነው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ሰዎች የሚሹት ገንዘብንና ዝናን ብቻ እንጂ ሃይማኖት እና ምግባርን አይደለምና፡፡

➲ ለ. ክርስትያን የሆነ ሁሉ ዘፋኝነት በቅዱሳን መጻሕፍት የተከለከለ ተግባር መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡

ዘፋኝነት እንደ መተዳደርያ ስራም ተደርጎ መታየት የለበትም፡፡ በዘፋኝነት ‹‹ሥራ›› የተሰማሩ ክርስትያኖች በሃይማኖት ለመኖር ከወደዱ በንስሐ እንደተመለሱ ዝሙት አዳሪዎችና ቀማኞች ሁሉ እነርሱም ሌላ የስራ አማራጭ መፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡

በዘመናችን የሐጢያት ተግባራት በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ገቢ ማግኛ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ገቢ ያስገኘ ተግባር በሙሉ ግን እንደ ሙያ (ፕሮፌሽን) መቆጠር የለበትም፡፡ ‹‹መተዳደሪያዬ ነው›› እያሉ ሕሊናን የሚቆጠቁጥና መንፈሳዊነትን የሚጋፋ ስራ ከመስራት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ አትስረቅ አታመንዝር ያለ እግዚአብሔር ‹‹አትዝፈን›› ደግሞ ብሏል፡፡ ታዲያ በመንፈሳዊ ጎዳና ለሚመለከተው ዘፈን ከስርቆትና ከምንዝር በምን ይለያል? ሁሉም የእግዚአብሔርን ሕግ በማፍረስ አንድ ናቸውና፡፡ ምን ላድርግ? መተዳደሪያዬ ነው እያሉ በዘፋኝነት ጸንቶ ከመኖር አማራጭ መሻት ይበጃል፡፡ በዚህ ዓለም ስጦታው ዘፋኝነት ብቻ የሆነና ሌላ ምንም ዓይነት ተውህቦ (ስጦታ) የሌለው ሰው የለም፡፡ እንዲህ ቢሆን ኖሮ ፈጣሪም ዘፋኝነትን ባላወገዘ ነበር፡፡ አንበሳ ምግቡ ሥጋ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ አንበሳ ሳር እንዲበላ ማድረግ እንደማያቻል ሁሉ ዘፋኞች እንደሌላው ሰው በሌላ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው መኖር የማይችሉ ቢሆኑ ኖሮ ፈጣሪ ዘፋኝ አትሁኑ የሚል ትእዛዝ አይሰጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ካሰቡበት እንደሌላው ሰው ሁሉ ዘፋኞችም ሌላ የስራ አማራጭ አላቸው፡፡

➼ ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ሥራን አስመልክቶ ሲናገር ‹‹ስለ ተግባረ እድ ግን በዓለም ከሚሠሩ ሥራዎች መንፈሳዊ ህግን ከሚቃወም ሥራ በቀር ሁሉንም ሊሰሩ ይገባል፡፡ . . . እንደ ዘፋኝነት፣ እንደ መጥፎ ጨዋታ፣ በእግር አንደማሸብሸብ (ዳንስና ጭፈራ) ካልሆነ በቀር፡፡›› ፍት.ነገ.መን.አን 23፡820 ይሕ የአበው ቃል ዘፋኝነት በመንፈሳዊ እይታ እንደስራ መቆጠር እንደሌለበት ያስረዳል፡፡

➲ ሐ. ዘፋኝነት ‹‹የስጋ ስራ›› በመሆኑ ሀጥያት ነው፡፡

➣ ገላ 5፡21 ስለዚህ ዘፈን መዝፈን በመጽሐፍ ቅዱስ በእጅጉ ይከለከላል፡፡ ክርስትያኖች በመንፈሳዊ ሀሳብ መመላለስ እንጂ እንደ ዘፈን ያለውን ስጋዊ ስራ መስራት የለባቸውም፡፡ በመንፈስ ተመላለሱ፤ የስጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ›› ተብሏልና፡፡ ገላ 5:21

➲ መ. ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል ዘፋኝነትም ተከልክሏል፡፡

➣ ሐመር መጽሔት ይህን ሲያስረዳ ‹‹ዛሬ የአለም ሕዝብ የሚያዘወትረውን ዘፈን ሐዋርያት በትምህርታቸው ደጋግመውና አጥብቀው ተቃውመውታል ይላል (ሐመር 2ኛ ዓመት ቁ 4 ገጽ 27) በእርግጥም ሐዋርያት በዲድስቅልያ ‹‹አትኩኑ ዘፋንያነ››፤ ‹‹ዘፋኝ አትሁኑ›› ብለዋል፡፡ ዲድስ አን7
ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በቀን እንደምንሆን በአግባቡ እንመላለስ፡፡ በዘፈንና በስካር አይሁን›› ብሏል፡፡ ሮሜ 13፡13 ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ << በስካር እና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል፡፡›› ይለናል 1ኛ ጴጥ 4፡3

➣ በላይኛው አንቀጽ በሰፈረው የሮም ክታቡ ቅዱስ ጳውሎስ ዘፋኝነትን ከዝሙትና ከስካር ጋር አስተካክሎ አስቀምጦታል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ ‹‹በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፡፡ ነውረኞችና ርኩሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፡፡›› በማለት ዘፋኝነትን የርኩሳንና የነውረኞች ተግባር አድርጎታል፡፡ 2ጴጥ 2፡13-15

➭ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እነዚህን የዘፈን ሰዎች በሌላ ማንነታቸው ሲገልጻቸው ደግሞ ‹‹ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትን የማይተዉ ዓይኖች አሏቸው፡፡ የማይፀኑትንም ነፍሳት ያታልላሉ፡፡ መመኘት የተለመደ ልብ አላቸው፡፡ የተረገሙ ናቸው፡፡›› ይላል 2ጴጥ2፡13-15
መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ ‹‹ከሰይጣን የተገኘ ነውና ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል፡፡›› ይለናል፡፡ መጽ ሐዊ አን50

➨ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን እንተው ዘንድ ‹‹ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችኋለሁ›› በማለት ይማፀናል (ተግ ዘዮሐ አፈ 28)

ዘፈንን አንተውም ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ "በዘፈን ፀንተው የሚኖሩ ይፈረድባቸዋል" በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን፡፡ መጽ ሐዊ አን 12 ይህ የሐዊ ቃል ሐዋርያው ‹‹የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው፡፡ እርሱም ዝሙት .. ስካር፣ ዘፋኝነት እንደነዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም›› ማለት በምን ይለያያሉ

Share በማረግ ትውልዱን እንታደግ

ሞዐ ተዋህዶ ቻናል
2.0K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 23:13:39
"ሥጋ ስንት ገባ"
ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!





12.8K views20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 08:56:09 ​​​​ ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት

1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30)

ሰባቱ ተዐምራት

ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት

1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ

አምስቱ ችንካሮች

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች

1. ሳዶር ፦ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. አላዶር ፦ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት
3. ዳናት ፦ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት
4. አዴራ ፦ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት
5. ሮዳስ ፦ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
13.1K views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 08:56:09 ​​ሰሙነ ሕማማት
ዓርብ

የስቅለት ዓርብ ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።
ዝርዝሩን -



መልካሙ ዓርብ ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
ዝርዝሩን -



#ሼር
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
7.3K views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 08:56:09 ​​​​​​"​​ሕማማት መስቀል" ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦

1. በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የኋሊት መታሰሩ
2. ከአፍንጫው ደም እስኪውጣ ድረስ 25 ጊዜ በጡጫ መመታቱ
3. 65 ጊዜ ከግንድ ማጋጨታቸው
4. 120 ጊዜ በድንጋይ ፊቱን መመታቱ
5. 365 ጊዜ በሽመል መደብደቡ
6. 80 ጊዜ ጽህሙን መነጨቱ
7. 6666 ጊዜ መገረፉ
8. አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ መደፋቱ
9. 136 ጊዜ በምድር ላይ መውደቁ
10. ሳዶር፡ አላዶር፡ ኤዴራ፡ ዳናትና ሮዳስ በሚባሉ 5ቱ ቅንዋተ መስቀልበችንካር መቸንከሩ
11. መራራ ሐሞትን መጠጣቱ
12. መስቀሉን ተሸክሞ መንገላታቱ
13. በመስቀል መሰቀሉ ናቸው።

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
6.4K views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 20:51:44 ​​​​ምን ሰጡህ ይሁዳ

ሙትን ልታስነሳ ድውይን ልትፈውስ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ
ልታስር ልትፈታ በነፍስም በሥጋ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር አልፋና ኦሜጋ

ምን ሰጡህ ይሁዳ አይሁድ ወገኖችህ
ለነርሱ አሳልፈህ ጌታህን የሰጠህ
ከሁሉ የሚበልጥ ሥልጣን ሰጥቶህ ሳለ
ብርን ለመቀበል ልብህ ተታለለ

ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ
እንዴት በመቃብር ሶሥት ቀን አደረ
አንተ የሰጠኸው አሳልፈህ ለሞት
ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ በሰንበት

#ሼር
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
6.1K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ