Get Mystery Box with random crypto!

የሴት ቀስት/ ቀስተንቻ/ሰርቲ/ በቅንነት ሼር ሼር በማድረግ ለተቸገሩ ይድረስ              | መርጌታ ባምላኩ የባህል መዳኒት

የሴት ቀስት/ ቀስተንቻ/ሰርቲ/

በቅንነት ሼር ሼር በማድረግ ለተቸገሩ ይድረስ
                    በምዕራቡ ዓለም ለምግብነት እና ለመድኃኒትነት/
እኛው ዘንዳ ለቤት አጥር አውለን ዝቅ ያደረግናት ድንቅ ዕጽ።

#የሴት ቀስት
የሴት ቀስት በወይና ደጋ፤ በደጋ ፤እንዲሁም በቆላማ ፤አከባቢ በብዛት የሚገኝ ቁጥቋጦ መሳይ ቀጫጭን ቅጠል ያለው እንዲሁም በትንሹ እሾህ ያላት ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላት እጽ ናት።

ለፊንጢጣ ኪንታሮት ፦
#የሴት ቀስት ሥር እና ቅጠሏ ሰብስበው በማድረቅ በብረት ምጣድ አድርገው በእሳት እስኪ ከስል ድረስ ማቆየት ከዛ በኃላ እፅዋቷ ተቃጥላ ከከሰለች በኃላ አውጥቶ በማቀዝቀዝ 25 ግራም አልያም በሾርባ ማንኪያ 4 በመለካት በፀጉር ቅቤ በደንብ አድርገው የከሰለው ዕጽ መለወስ!(በድጋሚ የተለጠፈ)

ለድክመተ ወሲብ፦
#የሴት ቀስት ገና ሳያድግ ሙሽራውን በመልቀም አዘውትረው ልክ እንደ ፎሰልያ ጥብስ ቀንበጥ ቀንበጡን በወይራ ዘይት እንዲሁም ከማንኛውም የምግብ አትክልት ጋ አቀላቅለው በመጥበስ ከተማእንደምግብነት ቢጠቀሙ ፍትወት ያዘገያል እንዲሁም ያጸናል።

ሀብቱ ለተልከሰከሰ፦
#የሴት ቀስት፣፩በቀል ፍየለ ፈጅ፣ሞይደር፣በወርቀ ዘቦ ሰፍተህ አስቀምጥ እንዲሁም ያዝ!

ለማይድን ቁስል፦
#የሴት ቀስት ቅጠሏን አድርቀህ በቁስሉ ላይ በየቀኑ እያፀዳህ ነስንስበት ከሳልስት ጀምሮ ይደርቃል።

ለማንኛውም የሆድ ህመም፦ቁርጠት/መንፋት/ተቅማጥ/ይሆናል።
#የሴት ቀስ ቅጠል ወቅጠህ በሾርባ ማንኪያ አንድ በመለካት በአንድ ሊትር ንፁህ ውኃ በጥብጠው በሻሽ በደንብ አጥለው ጧት በባዶ ሆድ አንድ ቀን ይጠጡ።ፍቱን ነው።

ለዓይነ ጥላ/ለሴት ዛር መንፈስ፦
#የሴት ቀስት ሥር በንጽህና ማክሰኞ ቀን ቆርጠው አድርቀው ሸርከት አድርጎ በመደቆስ ማታ ማታ ከከርቤ ዕጣን ጋር ለ ሰባት ቀናት ያክል ማታ ማታ መታጠን ሕልመ ለሊትም ያቆማል።

ለስራ አጥ/አልያም ስራ አልሳካ ላለው፦
#የሴት ቀስት ሥር፤የሞይደር ሥር ፣ከከርቤ ዕጣን ጋር በማቀላቀል ጧት ጧት እየታጠነ ይሂድ ይሳካለታል።

ለቋቁቻ/ለባርሌ/
#የሴት ቀስት፣የመቅሞቆ የሥሩ ቅርፊት በንፅህና አዘጋጅተው  አንድ የሾርባ ማንኪያ የቀስተንቻ የስሩ ቅርፊት አንድ የሾርባ ማንኪያ የመቅሞቆ ሥር ለክተው በአንድ ስኒ የጸጉር ቅቤ ለውሰው ለ 3 ቀን ይቀቡ ጧት ተቀብተው ለ7 ሰዓታት ኣቆይተው ይታጠቡ ፍፁም ያድናል።ፍቱን።

ለሽንት ማጥ፦
#የሴት ቀስት ሥር አሁንም በንጽህና አዘጋጅተው አንድ አንድ የሾርባ ማንኪያ የሴት ቀስት የተፈጨ ሥር በመለካት ለ 7 ቀናት በግማሽ በግማሽ ሊትር ውኃ በሻይ መልኩ እያፈሉ ቀዝቀዝ አድርገው ይጠጡ።ፍቱን

ለሪህ በሽታ፦
#የሴት ቀስት ሥር አድርቀው ፈጭተው አንድ ኪሎ ገደማ ያዘጋጁ!ከዛ በመቀጠል ጧት ጧት አንድ አንድ የሾርባ ማንኪያ በመለካት ከ ሴት ዕሬት ጁስ ጋር በማቀላቀል ለ 20 ቀን ያለ ስኳር ቢጠጡ እጅጉን ድንቅ ፈውስ ያገኙበታል።

ማሳሰብያ፦
#ያለ እውቀት በድፍረት እንዲሁም የእጽዋቱ ማንነት ሳይረዱ በይሆናል ማንኛውም ነገር ወደ ሆድ ውስጥ እንዳይወስዱ።

ሼር  በማድርግ ለወዳጅዎ የእጽዋት ፈዋሽነትን ማድረስዎ እንዳይረሱ!!



ለበለጠ መረጃ
0974743707