Get Mystery Box with random crypto!

መርጌታ ባምላኩ የባህል መዳኒት

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedon_enewek — መርጌታ ባምላኩ የባህል መዳኒት
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedon_enewek — መርጌታ ባምላኩ የባህል መዳኒት
የሰርጥ አድራሻ: @tewahedon_enewek
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.29K
የሰርጥ መግለጫ

የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፈሪት ነው
ኑዉ ተፈወሱ ጥበብ በኛ አለ
በታማኝነት እንሰራለን ይደውሉ ያናግሩን
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
መልካም ቀን ተመኘሁ
መርጌታ ባምላኩ ነኝ

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-03-11 20:56:21 ​​የብፁዕ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሥርዓተ ጸሎትና ሥርዓተ ቀብርን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ፤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሰብሳቢነት የመከረው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥርዓተ ቀብራቸውን የሚያስፈጽም ዐቢይ ኮሚቴ አቋቁሟል።

የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ ከአምስት ያላነሡ ንዑሣን ኮሚቴዎችን በማቋቋምና ሥራዎችን በየዕለቱ እየተከታተለ፣ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ሥራዎችን በወጣው መርሐ ግብር መሠረት እያከናወነ ይገኛል። በዚህም መሠረት፦

ከሐሙስ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ ይፋዊ የኃዘን ቀናት ታውጆ፥ የእምነት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መሪዎችና ተወካዮች፣ የውጭ ሀገራት ኤምባሲ አምባሳደሮች፣ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና ምእመናት በመንበረ ፓትርያርክ ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በመገኘት በተዘጋጀው የኃዘን መግለጫ መዝገብ ላይ በጽሑፍ ኀዘናቸውን እየገለጹ ይገኛል።

በቀጣይ ቅዳሜ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ የቅዱስነታቸው አስከሬን ከሃሌ ሉያ ሆስፒታል በክብር ወደ መስቀል አደባባይ ያመራል፤ በመስቀል አደባባይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት፣ መላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየድርጅትና የመምሪያ ኃላፊዎች፣ ምእመናንና ምእመናት ለዕለቱ የተዘጋጀው መርሐ ግብር ተከናውኖ ከተጠናቀቀ በኋላ በክብር ታጅቦ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጉዞ በማድረግ ያርፋል።

በመንበረ ፓትርያርክ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ፣ ልዩ ልዩ የሐዘን መግለጫና መንፈሳዊ መልእክቶች ከተላለፉ በኋላ፥ ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የክብር ሽኝት ይደረጋል።

በዚያም ሌሊቱን በሙሉ ስብሐተ እግዚአብሔር፣ ከነግህ ጀምሮ ጸሎተ ቅዳሴ ከደረሰ በኋላ፤ በመርሐ ግብሩ መሠረት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከውጭ ሀገራት የሚመጡ የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች፣ የእምነት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግሥት ባለ ሥልጣናትና ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ይፈጸማል።

ምንጭ፡-የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
9.5K views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 23:52:53 በይስሐቅ ፈንታ
የበገና መዝሙር

በይስሐቅ ፈንታ ኢየሱስ ታረደ/2/
ደሙን ከፈለና አዳምን ታደገ/2/

ተጨነቀ ጌታ ተሰቃየ ጌታ
የኔ መድኃኔዓለም የአዳም ልጅ አለኝታ
እንደሚታረድ በግ ተነዳ ወደ ሞት
ንፁህ ኢየሱስ በደል የሌለበት

በማመን ሲሸከም የአዳምን መከራ
ስቃይ ተቀበለ ደሙ እየተዘራ
ለሚገርፋት ሁሉ ምህረትን ሲቸር
እርሱ ግን ሲገረፍ ብዙ ተቸገረ

የሰማነውን ድምፅ ማን ሰው እኮ አምኗል
የእግዚአብሔርስ ክንድ ለነማን ተገልጿል
ባየነው ጊዜ ህመም ተሸክሞ
ስለበደላችን ተገርፎና ታሞ

እጁ የታሰረው ይስሀቅ ተፈቶ
ኢየሱስ ቀረበ በሰው ልጆች ፈንታ
ንፁህ በግ ቀረበ በደል የሌለበት በደለኛ ሆኖ
ሊሰቀል ሊገደል መስቀሉን ተጭኖ

በእውነት ደዌያችንን እርሱ ተሰቀለ
በሰው ልጆች ፈንታ በእንጨት ተሰቀለ
እኛ ግን ከሰስነው እንደ ወንጀለኛ
ስለ እኛ ቢሰቀል ሰማያዊው ዳኛ

ለሰው ልጆች ህይወት የታሰበውን ሰይፍ
አይተናል ሰምተናል በኢየሱስ አንገት ሲያልፍ
የመስቀሉ ስዕል ኧረ እንዴት ይገርማል
እዩት ንፁህ በግ በአርምሞይነዳል

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
6.6K views20:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 20:13:18 ወዴት ወድቆ ይሆን
የበገና ዝማሬ

እንክርዳድ ኑፋቄን ገበሬው ለይቶ
መልካም ዘር ሲዘራ ወደ ማሳው ወጥቶ
ለአጨዳው ምጽአት ለበጋው አዝመራ
ወዴት ወድቆ ይሆን ክረምት የተዘራ /2/

ዘወድቀ ውስተ ፍኖት ሲዘራ ያለቀው
አእዋፍ ሰማይ መሳጤ ነጠቀው
ዘወድቀ ዲበ ኮክሕ ጥልቅ አፈር ከሌለው
በደስታ እየሰማ በችግር የካደው
ዘወድቀ ውስተ ሦክ ተጨንቆ እንዳይወጣ
በዓለም ትካዜ በስፍጠተ ብዕል ታንቆ ፍሬ አጣ

ውስተ ምድር ሠናይ የወደቀም ነበር
ዘወሀበ ፍሬ ሰምቶ ሚተገብር
ጌታዬ ከአራቱ ስፍራዎች በምሳሌ ካልከው
ወዴት ወድቆ ይሆን ከእኔ ልብ የላከው
እባክህ ጎተራ አበጅተህ ለአጨዳ ስትመጣ
ከፍሬያማው ክምር ዕድል እንዳላጣ

ከእሾህ ከጭንጫ ላይ ከመንገድ እንዳልቀር
ልቤ ልብ አግኝቶ በምግባር እንዲኖር
ራሴን መስማት ትቼ ላንተ ፈቃድ ልደር

ዲ/ን ቀዳሜጸጋ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
5.8K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 12:59:05 #ስለ_ዳግም_ምፅዓት
(አቶ አለሙ አጋ በገና)
ቅኝት - ሰላምታ

እንዲህ አርገን ሥራውን ሁሉ አምነን
እናምናለን ዳግም ይመጣል ብለን
ነገር ግን ዳግም ይመጣል ስላልን
ከፃድቃን ከመላእክትም ቢሆን
የሚያውቅ የለም የሚመጣበት ቀኑን
ባላወቅነው ባልመረመርነው ሰዓት
ግሩም ሆኖ ይመጣል እንጂ ድንገት
መጀመሪያ የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ
ከያለበት ይሰበሰባል በአንድ አፍታ
አጥንታችን ትቢያ የሆነው አፈር
ጅብ የበላው የተበተነው ከዱር
የራስ ፀጉር የእግር ጥፍራችን ሳይቀር
ተሳስቶ የአንዱ ወደ አንዱ ሳይዞር
በየራሱ ይሰበሰባል ሁሉም
ይመታል የአዋጅ ነጋሪት ዳግም
ነፍስ የሌለው በድን ይሆናል ፍፁም
በሶስተኛው የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ
ይነሳሉ መልካም የሠሩ በእልልታ
የብርሃን ልብስ የብርሃን ቀሚስ ለብሰው
እንደ ፀሐይ እንደ ጨረቃ ደምቀው
እግዚአብሔርን ፈጣሪያቸውን መስለው
ይሰሙና በቀኙ ቆመው ፍርዱን
ከማያልፈው ተድላ ደስታ በቀር
ጠግቦ ቁንጣን ተርቦ ስስት ሳይኖር
ገብቶ መውጣት አግኝቶ ማጣት ችጋር
የሌለባት ደገኛይቱን ሀገር
ይወርሳሉ መልካም የሠሩ በምድር
ኃጥአንም እጅግ ከጭራ ቀጥነው
መልካቸውም እጅግ ከቁራ ጠቁረው
ከላይ ከታች የጨለማ ልብስ ለብሰው
ዲያብሎስን አለቃቸውን መስለው
ይሰሙና በግራ በኩል ቆመው
በመንቀጥቀጥ የሚፈርደውን ሰምተው
ከልቅሶና ጥርስ ማፋጨት በቀር
ተድላ ደስታ የሌለባትን ሀገር
ይወርሳሉ ክፉ የሠሩ በምድር
እንዲህ አርገው መጻሕፍት ሁሉ እንዳሉ
በየሥራው ይከፈለዋል ለሁሉ
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም አሜን

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
5.5K views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-31 22:57:17
አጫብር "ሖረ ኢየሱስ" በጽርሐ ጽዮን ሰንበት ት/ቤት - Achabir "Hore eyesus"
ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

ዝማሬውን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!





7.3K views19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-31 12:02:50
"ይብቃህ በለኝ" ሊያደምጡት የሚገባ ድንቅ አስተማሪ ግጥም በወንድማችን ዲ/ን ገብረኪዳን
ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!





7.0K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-11 14:14:22
8.5K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-09 00:36:51
8.4K views21:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ