Get Mystery Box with random crypto!

#ስለ_ዳግም_ምፅዓት (አቶ አለሙ አጋ በገና) ቅኝት - ሰላምታ እንዲህ አርገን ሥራውን | መርጌታ ባምላኩ የባህል መዳኒት

#ስለ_ዳግም_ምፅዓት
(አቶ አለሙ አጋ በገና)
ቅኝት - ሰላምታ

እንዲህ አርገን ሥራውን ሁሉ አምነን
እናምናለን ዳግም ይመጣል ብለን
ነገር ግን ዳግም ይመጣል ስላልን
ከፃድቃን ከመላእክትም ቢሆን
የሚያውቅ የለም የሚመጣበት ቀኑን
ባላወቅነው ባልመረመርነው ሰዓት
ግሩም ሆኖ ይመጣል እንጂ ድንገት
መጀመሪያ የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ
ከያለበት ይሰበሰባል በአንድ አፍታ
አጥንታችን ትቢያ የሆነው አፈር
ጅብ የበላው የተበተነው ከዱር
የራስ ፀጉር የእግር ጥፍራችን ሳይቀር
ተሳስቶ የአንዱ ወደ አንዱ ሳይዞር
በየራሱ ይሰበሰባል ሁሉም
ይመታል የአዋጅ ነጋሪት ዳግም
ነፍስ የሌለው በድን ይሆናል ፍፁም
በሶስተኛው የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ
ይነሳሉ መልካም የሠሩ በእልልታ
የብርሃን ልብስ የብርሃን ቀሚስ ለብሰው
እንደ ፀሐይ እንደ ጨረቃ ደምቀው
እግዚአብሔርን ፈጣሪያቸውን መስለው
ይሰሙና በቀኙ ቆመው ፍርዱን
ከማያልፈው ተድላ ደስታ በቀር
ጠግቦ ቁንጣን ተርቦ ስስት ሳይኖር
ገብቶ መውጣት አግኝቶ ማጣት ችጋር
የሌለባት ደገኛይቱን ሀገር
ይወርሳሉ መልካም የሠሩ በምድር
ኃጥአንም እጅግ ከጭራ ቀጥነው
መልካቸውም እጅግ ከቁራ ጠቁረው
ከላይ ከታች የጨለማ ልብስ ለብሰው
ዲያብሎስን አለቃቸውን መስለው
ይሰሙና በግራ በኩል ቆመው
በመንቀጥቀጥ የሚፈርደውን ሰምተው
ከልቅሶና ጥርስ ማፋጨት በቀር
ተድላ ደስታ የሌለባትን ሀገር
ይወርሳሉ ክፉ የሠሩ በምድር
እንዲህ አርገው መጻሕፍት ሁሉ እንዳሉ
በየሥራው ይከፈለዋል ለሁሉ
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም አሜን

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur