Get Mystery Box with random crypto!

በይስሐቅ ፈንታ የበገና መዝሙር በይስሐቅ ፈንታ ኢየሱስ ታረደ/2/ ደሙን ከፈለና አዳምን ታደገ/2 | መርጌታ ባምላኩ የባህል መዳኒት

በይስሐቅ ፈንታ
የበገና መዝሙር

በይስሐቅ ፈንታ ኢየሱስ ታረደ/2/
ደሙን ከፈለና አዳምን ታደገ/2/

ተጨነቀ ጌታ ተሰቃየ ጌታ
የኔ መድኃኔዓለም የአዳም ልጅ አለኝታ
እንደሚታረድ በግ ተነዳ ወደ ሞት
ንፁህ ኢየሱስ በደል የሌለበት

በማመን ሲሸከም የአዳምን መከራ
ስቃይ ተቀበለ ደሙ እየተዘራ
ለሚገርፋት ሁሉ ምህረትን ሲቸር
እርሱ ግን ሲገረፍ ብዙ ተቸገረ

የሰማነውን ድምፅ ማን ሰው እኮ አምኗል
የእግዚአብሔርስ ክንድ ለነማን ተገልጿል
ባየነው ጊዜ ህመም ተሸክሞ
ስለበደላችን ተገርፎና ታሞ

እጁ የታሰረው ይስሀቅ ተፈቶ
ኢየሱስ ቀረበ በሰው ልጆች ፈንታ
ንፁህ በግ ቀረበ በደል የሌለበት በደለኛ ሆኖ
ሊሰቀል ሊገደል መስቀሉን ተጭኖ

በእውነት ደዌያችንን እርሱ ተሰቀለ
በሰው ልጆች ፈንታ በእንጨት ተሰቀለ
እኛ ግን ከሰስነው እንደ ወንጀለኛ
ስለ እኛ ቢሰቀል ሰማያዊው ዳኛ

ለሰው ልጆች ህይወት የታሰበውን ሰይፍ
አይተናል ሰምተናል በኢየሱስ አንገት ሲያልፍ
የመስቀሉ ስዕል ኧረ እንዴት ይገርማል
እዩት ንፁህ በግ በአርምሞይነዳል

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur