Get Mystery Box with random crypto!

​​​​ ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት 1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46) 2. አባት ሆ | መርጌታ ባምላኩ የባህል መዳኒት

​​​​ ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት

1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30)

ሰባቱ ተዐምራት

ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት

1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ

አምስቱ ችንካሮች

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች

1. ሳዶር ፦ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. አላዶር ፦ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት
3. ዳናት ፦ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት
4. አዴራ ፦ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት
5. ሮዳስ ፦ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur