Get Mystery Box with random crypto!

ስንክሳር በየቀኑ

የቴሌግራም ቻናል አርማ sinksar — ስንክሳር በየቀኑ
የቴሌግራም ቻናል አርማ sinksar — ስንክሳር በየቀኑ
የሰርጥ አድራሻ: @sinksar
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.00K
የሰርጥ መግለጫ

የአመቱን ስንክሳር በየቀኑ የሚቀርብበት ማብራሪያው ላልቀረበበትም የበለጠ እንድናነብ የሚረዳን መማማሪያ ነው።
" ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ:: በዓለም ያለው ሁሉ: እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት: ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ: ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም:: ዓለሙም: ምኞቱም ያልፋሉ::" 1ዮሐ. 2:15
# ያጋሩ

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 11:01:07
126 views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:39:15 የእልቂት አዚም

" የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?" ገላ 3፥2

በሆኑ እና እየሆኑ ባሉ ነገም ሊሆኑ በሚችሉ የሰው ልጅን ጥፋት የኦርቶዶክሳውያንን እልቂት እንዳንረዳ አዚም ያደረገብን ምንድን ነው?

የማያጸድቅ ሞትን መላመድ ትልቅ በሽታ ነው፡፡ ሁላችን በስሁት ርዕዮት ታመናል ፈውሱ ግን ኦርቶዶክሳዊነት ነበር፡፡
መድኃኒታችንን አልተጠቀምንበትም፣ ለበሽተኞች ባለመድኃኒት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ክርስትና አካለ ክርስቶስ እንጂ ዘር አይደለም ቋንቋም መግባቢያ እንጂ ሰው አይደለም፡፡ የተወለድንበት ማሕፀነ ዮርዳኖስ አንድ ነው ፡፡ ሁላችንም የተቀበልነው ማዕድ አንድ የቀራንዮ ማዕድ ነው፡፡
ማዶ እና ማዶ ያለኸው ወንድሜ ሆይ
ማዶና ማዶ ያለሽው እኅቴ ሆይ
ሁላችሁም የወይኑ ግንድ ቅርንጫፎች የሆናችሁ፦እየተቆረጠ ያለው የወይኑ ቅርንጫፍ ነውኮ!!
የተከፋፈለ ክርስቶስን አልተቀበልነም አንዱን ክርስቶስ ነው እንጂ ባልተከፋፈለ ክርስትስ አንድ ሁነን በከፋፋይ ስሁት ፖለቲካ አንለያይም፡፡

ከማይጠፋ ዘር አብራከ መንፈስ ቅዱስ ተወልደን በሚጠፋ ስሁት ርዕዮት አንጋደልም፡፡
እናም የሐዋርያው ተግሣፃዊው ጥያቄ የህሊናን ስንፍና አዚም ይቀሰቅሳል ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሆይ የእልቂት አዚም ያደረገብን ማን ነው?
ተው ባይ አባት ተው ባይ ምእመን እንዴት ልናጣ ቻልን?
የሞት ነጋሪትን የሚደልቅብን በዝቷል ፡፡

የዋሐን ምእመናን ደግሞ የሚያውቁት ሳይኖር በታዛዥነት እንደ እሳት ራት እየሆኑ ነው፡፡
የውጪውም የውስጡም ዓላማ ፦ቤተክርስቲያንን አቅም አልባ ማድረግ እና ከሞት የተረፉት ከጥላ ያረፉት ዳግም እንዳይገናኙ የደም ድንበር መዘርጋት ነው፡፡
እኛም በዝምታችን ፣ በስንፍናች፣ በፍራታችን ምክንያት፦ከሁሉ በላይ ቤተ ክርስቲያንን ይዘን ከሁሉ በታች አደረግናት ፡፡

#ሼር/ለወዳጅዎ ያጋሩ

#በመ/ር ገብረ መድኅን እንየው
492 views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:52:25 ስንክሳር ነሐሴ 26

† እንኳን ለእናታችን ብጽዕት ሣራ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

††† ቅድስት ሣራ ብጽዕት †††

† አበው እናታችን ሣራን " #ቡርክተ_ማሕጸን" ይሏታል:: (የቅዱሱ ዘር የይስሐቅ እናት ናትና) በዚያውም ላይ የደጉ ሰው የአብርሃም ሚስት ናት:: ልክ በዓለም ታሪክ "ከጠንካራና ስኬታማ ወንዶች ጀርባ ጠንካራ ሴቶች አሉ" እንደሚባለው ከአብርሃም አባታችን ስኬታማ የቅድስና ሕይወት ጀርባ ብጽዕት ሣራ አለች::

ለአብርሃም አባታችን መጽሐፍ የተናገረው ክብር ሁሉ ለቅድስት ሣራ ይገባታል:: አንድም ገንዘቧ ነው:: ቅድስቷ እናት ደጉ አብርሃምን ያገባችው ገና በከላውዴዎን (በ2ቱ ወንዞች መካከል) ሳለ ነው:: ገና ከልጅነቷ ጀምራ አብርሃምን "ጌታየ" እያለች ታገለግለው እንደ ነበር ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል:: (1ዼጥ. 3:5)

በዚህም ከብራበታለች: ገናበታለች እንጂ አልተጐዳችበትም:: አብርሃም ወደ ካራን ሲወጣ "ለምን?" አላላችም:: እንዲሁ ለፈቃደ እግዚአብሔር ታዘዘች እንጂ:: በካራን ታራን ቀብረው: በፈጣሪ ትዕዛዝ ወደ #ከነዓን ሲፈልሱም ቅድስት ሣራ አልተቃወመችም::

ለፈጣሪዋ ትዕዛዝና ለባሏ ስትል ርስቷን: ሃገሯን: ዘመዶቿን ሁሉ ትታ ሔዳለች:: ይሔውም በጐ ምናኔ ነው:: እናታችን ሳራ በከነዓን የተመቸ ነገር አልገጠማትም:: ከአንዴም ሁለቴ በረሃብና በድርቅ ምክንያት ወደ ግብጽ እና #ጌራራ ተሰደዋል::

በዚያም ፈርዖን "እነካለሁ" ቢል እግዚአብሔር ተቆጥቶ: ፈርኦንንና ግብጽን በደዌ መታ:: በዚህም ክብረ ሣራን ተመለከትን:: ከስደት መልስም በኬብሮን (በተመሳቀለ መንገድ ላይ) ድንኩዋን ሠርተው የወጣ የወረደውን ሲያበሉ: እንግዳ ሲቀበሉ ኑረዋል:: (ልብ በሉልኝ ይህን ትጋትና ደግነት ያሳየችውን ቅድስት ሣራን ልናከብራት ይገባል)

እድሜ ዘመኗን ያሳለፈችው እንግዳ በመቀበል: እግዚአብሔርን በማምለክ ነው:: ምንም እንኩዋ ማሕጸኗ ለጊዜው ቢዘጋ ተስፋ አልቆረጠችም:: ለአብርሃምም ከአጋር እንዲወልድ ፈቃድ ሰጥታለች::

ዕድሜዋ 89 ዓመት በሆነ ጊዜ ሰይጣን እንግዳ እንዳይመጣ ለ3 ቀናት ቢያስቀርባቸው እንደ ባሏ እርሷም 3 ቀናትን ያለ ምግብ አሣልፋለች:: በ3ኛው ቀን ሥላሴን በቤቷ አስተናግዳለች:: ስለ ክብሯም ከ3 መሥፈሪያ ዱቄት ለውሳ ያዘጋጀችውን እንጐቻ ሥላሴ በልተውላታል:: (ምንም ሥላሴ ምግብን ባይመገቡም)

የሥላሴ በዚያች ድንኩዋን ውስጥ መስተናገድ ታላቅ ምሥጢር አለው:: ከግብዣው በሁዋላም እግዚአብሔር አለ:- "አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ . . . እንዲሁ ከርሞ እመለሳለሁ: ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች" አለው::

ያን ጊዜ ሣራ በውሳጤ ሐይመት (በድኩዋኑ ውስጥ) ሆና ሰምታ ሣቀች:: ለምን ሳቀች ቢሉ:- እጅግ ደስ ቢላት! አንድም ቢገርማት:: ይሕስ በምን ይታወቃል ቢሉ:- ልጇ " #ይስሐቅ" የተባለው "ለእናቱ ሣቅን: ደስታን ያመጣ" ለማለት ነውና::

ሥላሴም:- "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ: እንዘ ትብል ዓዲየኑ እስከ ይእዜ: ወእግዚእየኑ ልሕቀ: ቦኑ ነገር ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር - ሣራን ምን አሳቃት? ለእግዚአብሔርስ የሚሳነው ነገር አለን" ብለዋል::

ቅድስት ሣራ በ90 ዓመቷ ይስሐቅን ወልዳ በቀሪ ዘመኖቿ በደስታ ኑራለች:: በዚህች ቀንም በመልካም ሽምግልና ዐርፋ: አባታችን #አብርሃም ከታላቅ ሐዘን ጋር ቀብሯታል:: ሐዋርያው #ቅዱስ_ዻውሎስ ብጽዕት ሣራን በበጐ ምሳሌ መስሏታል:: (ዕብ. 11:11)

† ቅዱሳን ሞይስስና ሣራ †

† እነዚህ ቅዱሳን ግብጻውያን የአንድ እናት: የአንድ አባት ልጆች ሲሆኑ የነበሩትም በዘመነ ሰማዕታት ነው:: ከወላጆቻቸው ጋር በሥርዓተ ክርስትና አድገው ዕድሜአቸው ለአካለ መጠን ሲደርስ ወላጆቻቸው ሞቱባቸው::

ያን ጊዜ ቅዱስ_ሞይስስ እህቱን ቅድስት ሣራን ጠርቶ "እህቴ! እኔ ወደ ገዳም መሔዴ ስለሆነ አንቺ ባል አግብተሽ: ሃብት ንብረቱን ወርሰሽ ኑሪ" አላት:: #ቅድስት_ሣራ ግን መልሳ "እንዴት እኔን በዚህ ዓለም ወጥመድ ውስጥ ትተወኛለህ? ሁለታችንም ከአንድ ማሕጸን ነን:: ስለዚህ ላንተ የምትፈልገው ሁሉ ለእኔም ያስፈልገኛልና እኔም መናኝ ነኝ" አለችው::

ቅዱስ ሞይስስ የልቡናዋን መጨከን ሲያይ ነዳያንን ሰበሰበ:: ገንዘቡን: ቤቱን: ሃብቱንና ንብረቱን ሁሉ በየስልቱ ለነዳያን አካፈለ:: ሳይዘገይም እህቱን ይዞ ወደ በርሃ ተጉዋዘ:: እርሷን ከደናግል ገዳም አስገብቶ እርሱ ከወንዶች ገዳም ውስጥ መነኮሰ::

ለ10 ዓመታት ሁለቱም ለፈጣሪያቸው በጾምና በጸሎት: ከስግደት ጋር ሲገዙ: ለአባቶችና እናቶች ደግሞ በትሕትና ሲታዘዙ ኖሩ:: በእነዚህ ሁሉ ዓመታት አንድም ቀን ተገናኝተው አያውቁም ነበር:: አንዱ ለሌላኛው ተግቶ መጸለይን ግን ቸል አላሉም::

ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ (የመከራ) ነውና መከራው እየገፋ ሲመጣ ቅዱስ ሞይስስ አንድ ነገር አሰበ:: በክርስቶስ ስም ደሙን ለማፍሰስም ወሰነ:: ወደ ከተማ ከመውጣቱ በፊት ግን ለቅድስት ሣራ መልዕክት ላከባት:: "እኔ ወደ ምስክርነት እየሔድኩ ስለሆነ ቸር ሁኚ" የሚል ነበር መልእክቱ::

እርሱ ይህንን ብሎ ወደ ከተማ ሲሔድ ግን መንገድ ላይ እህቱን አገኛት:: ገርሞት የፍቅር ሰላምታን ከተለዋወጡ በሁዋላ "እንዴት መጣሽ?" ቢላት "ወንድሜ! ቀድሞም ነግሬሃለሁ:: ላንተ የምትፈልገው የድኅነት መንገድ ሁሉ ለእኔም ያስፈልገኛል" አለችው::

ሁለቱም ተያይዘው ወደ መከራ አደባባይ ደረሱ:: በዚያም ስመ ክርስቶስን ሰብከው: ብዙ መከራንም ተቀብለው በዚህች ቀን ሰማዕት ሆነዋል::

† አምላከ ቅድስት ሣራ ደግነቷን: መታዘዟን ያሳድርብን:: ከበረከቷ: ከሌሎችም ቅዱሳን በረከትን ይክፈለን::

† ነሐሴ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ብጽዕት ሣራ (የአብርሃም ሚስት)
2.ቅዱሳን አባ ሞይስስና እህቱ ሣራ (ሰማዕታት)
3.ቅዱሳን አጋቦስና ቴክላ (ሰማዕታት)

† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †


ቤተሰብ ይሁኑ

https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
164 views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:55:29
ይሄ እድል እንዳያመልጠን!

የአክሲዮን ሽያጩ 6 ቀን ቀረው።

በተግባር ሥራ ጀምሮ የሚገኘው ከራድዮን የሆቴልና ቱሪዝም ንግድ አ.ማ በከራድዮን ካፌና ሬስቶራንት ጥራት ያለው አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ በውስጥ ማናገር ይችላሉ።
73 views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:55:57 † ስንክሳር ነሐሴ 25 †
https://t.me/Sinksar

እንኳን ለቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት እና ለታላቁ አባ ቢጻርዮን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

†በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† ቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት †

† ቅዱሱ በ3ኛው መቶ ክ/ዘ የነበረ አረማዊ ሰው ሲሆን ከከሃዲው መክስምያኖስ ወታደሮችም አንዱ ነበር:: "ሊቀ መሓዛት" ይሉታል: የጐበዛዝቱ አለቃም ነበር:: ይህ ሰው ምንም ክርስቲያን አይሁን እንጂ በልቡ ቅንነት ተገኝቶበታል:: እንደ አሕዛብ ልበ ድንጋይ አልነበረም::

በወጣትነቱም አንዲት ደመ ግቡ ሴት አግብቷል:: ይህች ሴት ' #ኤልያና' ስትባል የተባረከች ክርስቲያን ናት:: እርሱ ግን አያውቅም:: ከተጋቡ ከዓመታት በሁዋላ ጌታ እግዚአብሔር ስለ ሚስቱ ጸሎት በጐ ጐዳና ሊመራው ፈለገ::

እንድርያኖስ ሁሌም በየቀኑ ክርስቲያኖች ደማቸውን ሲያፈሱ ይመለከታል:: የትእግስታቸው መጠንም ይገርመው ነበር:: በተለይ አብዛኞቹ በመከራው ደስተኞች ነበሩ:: ነገሩ ግራ ቢያጋባው 24 ባለንጀሮች ሊገደሉ ወደ ታሠሩበት ቦታ ሒዶ ጠየቃቸው::

"ምን ልታገኙ ነው ግን ይሕንን ሁሉ ስቃይ በአኮቴት (በምስጋና) የምትቀበሉት?" ቢላቸው "በሰማይ በክርስቶስ ዘንድ የሚጠብቀንን የክብር ሕይወት ሥጋዊ አንደበት አከናውኖ መናገር አይቻለውም:: ዝም ብሎ 'ዕጹብ: ዕጹብ' እያሉ የሚያደንቁት ነው እንጂ" አሉት::

እርሱም ተደላድሎ ተቀምጦ "እስኪ በደንብ አስረዱኝ" አላቸው:: ከዓለም መፈጠር እስከ ጌታችን የማዳን ሥራ: አልፎም ስለ ፍርድ ቀን በጥዑም አንደበታቸው አስተማሩት:: ቅዱስ እንድርያኖስ በቅጽበት ልቡ ወደ ክርስቶስ ፍቅር ሸፈተ::

በፍጥነት ተነስቶ የራሱን ስም ከሰማዕታቱ 25ኛ አድርጐ አጻፈ:: ንጉሡ ይሕንን ሲሰማ "አብደሃል" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "የለም! ዛሬ ገና ከእብደቴ ተመለስኩ" በማለቱ ከ25ቱ ቅዱሳን ጋር ታሠረ:: ቅድስት ኤልያና (ሚስቱ) ነገሩን ስትሰማ ፈጽሞ ደስ አላት::

ወደ እስር ቤት ሒዳ "አይዞህ በርታ! ስለ ክርስቶስ የሞትክ ቀን ብቻ እኮራብሃለሁ" ብላ: እግራቸውን አጥባቸው ተመለሰች:: በሚገደሉበት ቀንም ልሰናበታት ብሎ ቅዱስ እንድርያኖስ ቢመጣ ቅድስት ኤልያና ቤቷን ዘግታ ገሠጸችው:: እርሷ ክዶ የመጣ መስሏት ነበር::

እርሱ ግን የሚስቱን የእምነት ጥንካሬ ተረዳ:: ቅዱሱና 24ቱ ቅዱሳን ለቀናት ብዙ መከራን እየተቀበሉ ሰነበቱ:: አካላቸውን እየቆራረጡ: ደማቸውን እያፈሰሱ ሆዳቸውንም እየቀደዱ መከራን አጸኑባቸው:: በመጨረሻው በዚህች ቀን ሲገደሉ ቅድስት ኤልያና "የእኔን ባል አስቀድሙት" አለች:: (የሌሎቹን አይቶ እንዳይደነግጥ ነው)

እንዳለችውም የእርሱንና የባልንጀሮቹን ጭን ጭናቸውን እየሰበሩ ገድለዋቸዋል:: ቅድስት ኤልያናንም መሣፍንቱ "ካላገባንሽ" እያሉ ሲያስቸግሯት ተሰዳ ሒዳ ከሰማዕታቱ መቃብር ላይ አለቀሰች:: ጌታም ጠርቷት እዚያው ዐረፈች::

††† ታላቁ አባ ቢጻርዮን †††

ታላቁ ገዳማዊ ሰው የመጀመሪያ መነኮሳት ከሚባሉ አባቶች አንዱ ሲሆን ዓለምን ንቆ ከመነነ በሁዋላ ከአባ #እንጦንስ ዘንድ መንኩሷል:: ከእርሳቸው ዘንድ በረድእነት ለብዙ ዓመታት አገልግሏል:: አገልግሎቱን በፈጸመ ጊዜም አስኬማን ተቀብሎ ወደ በርሃ ወጥቷል::

ምንም የራሱን ገዳም ባይመሠርትም በ4ኛው መቶ ክ/ዘ የምናኔ ሕይወት እንዲስፋፋ ካደረጉ አበው እርሱ ዋነኛው ነው:: በተጋድሎ ዘመኑም የሚታወቅባቸው ነገሮች አሉ:: ከእነሱም ጥቂት እንጠቅሳለን:: አባ ቢጻርዮን:-
1.ጾሙም ሆነ ጸሎቱ በ40 ቀናት የተወሰነ ነበር:: ጾምን ከጀመረ ያለ 40 ቀን እህል አይቀምስም:: ለጸሎት ከቆመም የሚቀመጠው ከ40 ቀናት በሁዋላ ነው::
2.ሁሌም በየበርሃው እየዞረ ያለቅሳል:: "ምነው" ሲሉት "ወገኖቼ አለቁብኝ: ደሃም ሆንኩ" ይላቸው ነበር:: እንዲህ የሚለው አጋንንት ብዙ ነፍሳትን እየነጠቁ ሲወስዱ ስለሚመለከት ነው::
3.በየገዳማቱ እየለመነ ለነዳያን ያከፋፍል ነበር::
4.ሐፍረቱን ከሚሸፍን ጨርቅ በቀር ምንም ልብስ አይለብስም ነበር::
5.ውዳሴ ከንቱን አምርሮ ይጠላ ነበር::
6.በባሕር ላይ ተራምዶ ሲሔድና እግሮቹ ሳይርሱ ሲቀሩ አበው ተመልክተዋል::
7.መርዝነት ያለውን ውሃም ጣፋጭ አድርጐታል::

††† ቅዱሱ ድውያንን ፈውሶ: አጋንንትን ከአካባቢው አሳዶ: ብዙ ፍሬ አፍርቶ: ገዳም ውስጥ በገባ በ57 ዓመቱ በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::

††† ቸር አምላክ በክብረ ቅዱሳን ይከልለን:: ከበረከታቸውም ያብዛልን::

††† ነሐሴ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት
2."24ቱ" ሰማዕታት (ማሕበሩ)
3.ቅድስት ኤልያና (ሚስቱ)
4.ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ
5.ቅዱስ ኤልያኖስና እህቱ አውዶክስያ (ሰማዕታት)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

††† "ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን: የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው:: #እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከእርሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና: በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር:: በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ:: እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን:: ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን::" †††
(2ቆሮ. 5:18)


† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †


ቤተሰብ ይሁኑ

https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
84 views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:13:36 +++ የነሐሴ 24 አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማኅሌት +++

መልክዐ ሥላሴ

ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ
ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤
ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤
ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤
ወተክለ ሃይማት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ፡፡
ዚቅ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤
ዘኢይነውም ትጉህ በውስተ ቅዱሳን ስቡሕ፤
ከመ ቀስተ ደመና የዓውዶ ሱራሄ ሎቱ ለባሕቲቱ ይደሉ ስባሔ፡፡

መልክአ ሚካኤል
1
ሰላም ለሕጽንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤
ጸሎተ ቅዱሳን ዉኩፍ፤
ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤
ለረዲኦትየ ከመ ዘይሰርር ዖፍ፤
እንዘ ትሰርር ነዓ በከልኤ አክናፍ፡፡
ዚቅ
ርድአኒ ወአድኅነኒ፤ ወሥመር ብየ፤
በከመ ሠመርኮሙ ለቅዱሳን አበውየ፡፡
2
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ . . .
ዚቅ
አመ ኖኅ ይእቲ መድኀኒት፤
እንተ ኮነት አንቀጸ ሕይወት ማርያም ቅድስት፡፡

መልክአ ተክለ ሃይማኖት
3
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘጥንተ ፊደሉ መስቀል፤
ስም ክቡር ወስም ልዑል፤
ተክለ ሃይማኖት ማቴዎስ በዓለ ቀዳማይ ወንጌል፤
ከመ እወድስከ መጠነ አውሥኦተ እክል፤
ማእሠረ ልሳንየ ትፍታሕ ማርያም ድንግል፡፡
ዚቅ
ወንጌለ መለኮት ሰበከ ስምዐ ጽድቅ ኮነ
ወበእንተዝ ተክለ ሃይማኖት ተሰመይከ
4
ሰላም ለአዕይንቲከ ዘአርአያሆን ሐዋዝ ፤
እለ ጽዱላት እማንቱ ከመ ሰርቀ ቤዝ፤
ተክለ ሃይማኖት ኅብዓኒ እሞተ ኃጢአት አዚዝ፤
ለከሰ አኮ ከመዝ፤
ኢይረክበከ ሞት ዳግመ እምዝ፡፡
ዚቅ
ዳግመ እምዝ ኢይረክቦ ሞት ከመዝ ዳግመ እምዝ፡፡
5
ሰላም ለኵልያቲከ ዘፈተኖን በትዕግሥት፤
ኢየሱስ ክርስቶስ አበ ብርሃናት፤
ተክለ ሃይማኖት ሰጋዲ ከመ መላእክት፤
ጸሎትከ ዘገበርካሃ እስከነ ኍልቈ ምእት ዓመት፤
መድኀኒተ ትኩነነ እምግሩም ቅሥት፡፡

ዚቅ
ተክለ ሃይማኖት ሰማዕት ሰባኬ መድኀኒት
ጸሎትከ ትኩነነ ፀወነ እመንሱት
ተክለ ሃይማኖት ሰባኬ መድኀኒት
6
ሰላም ለጸአተ ነፍስ በስብሐተ አእላፍ እንግልጋ፤
ለዓለም ዛቲ እምግብርናቲሃ ወፁጋ፤
ተክለ ሃይማኖት ቶማስ ለመርዓስ ዐቃቤ ሕጋ፤
ለእለ ገብሩ ተዝካረከ እንዘ ሀለው በሥጋ፤
ሀቦሙ እግዚእየ ሞገሰ ወጸጋ፡፡
ዚቅ
ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ፤
ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤
እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ፤
ወአብእዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ፡፡
7
ሰላም ለበድነ ሥጋከ ኤልሳዕ መምህር ዘገነዛ፤
በሠናይ ጼና መዓዛ፤
ተክለ ሃይማኖት ሰባኪ ፊሊጶስ ዘብሔረ ጋዛ፤
ለሥጋየ መሬታዊት አመ የኃልቅ ዕዘዛ፤
ስብረተ ዐጽምከ ይኩነኒ ቤዛ፡፡
ዚቅ
ሖረ ኀቤሁ ለተክለ ሃይማኖት ቀዲሙ ሌሊተ፤
ኤልሳዕ ስሙ መልአኮሙ ለአርድዕት፤
ውእቱኒ አምጽአ ከርቤ አፈዋተ፤
ገነዝዎ በሰንዱናት ለተክለ ሃይማኖት፡፡
7
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ በዘቦቱ ይትመሐፀኑ፤
ነገሥተ እስራኤል ኄራን ዘአስተሣነይዎ በበ ዘመኑ፤
ተክለ ሃይማኖት ሠዋዒ ለእግዚአብሔር ካህኑ፤
አድኅነኒ እምፀብአ ከይሲ ዘዐሥር ቀርኑ፤
ወእምብእሲ ዘክልኤ ልሳኑ፡፡
ዚቅ
መላእክት አእመሩ ሃይማኖተከ፤
ነገሥት ሐነፁ መካነከ፤
አባ ተክለ ሃይማኖት ክርስቶስ ዘአፍቀረከ፡፡
8
ሰላም ለመቃብሪከ እምቅድመ ትኑም ውስቴታ፤
ታቦተ ማርያም ድንግል ዘአንበርከ በውሳጢታ፤
ተክለ ሃይማኖት አቡየ ለወልድከ ዕጓለ ማውታ፤
ለበረከትከ ይከልለኒ ረድኤታ፤
ወይዑደኒ ዘጽድቅከ ወልታ፡፡

ዚቅ
ጸለየ ተክለ ሃይማኖት እንዘ ይብል ኀበ ተቀብረ ሥጋየ
ወተክዕወ ደምየ ህየ ይኩን በረከት፡፡
9
ሶበ አዕረፈ ተክለ ሃይማኖት ከዊኖ ህልወ በጾማዕቱ፤
እንዘ ርኁብ ወእንዘ ጽሙዕ ውእቱ፤
ላእካነ ማርያም አሜሃ እለ መጽኡ ለአፍልሶቱ፤
ተበሀሉ በአርጋኖን ወዘመሩ ሎቱ፤
አማን ለጻድቅ ክቡር ሞቱ፡፡
ዚቅ
ይቤሎ ኢየሱስ ለተክለ ሃይማኖት፤
ሰማዕኩ ጸሎተከ ወስዕለተከ፤
እምብዙኅ ፃማ አአርፈከ፤
ኀበ ሀሎ ፍሥሐ አነብረከ፡፡
+++
ምልጣን
አባ አቡነ፡ አቡነ መምህርነ እምአዕላፍ ኅሩይ፤
ሐውጽ እምሰማይ ብርሃነከ ከመ ንርአይ፡፡
ወይም
ሞቶሙሰ ለጻድቃን ሕይወቶሙ ውእቱ፤
እስመ ለጻድቅ ይትሌዓል ቀርኑ በክብር
ጻድቃን እለ አሥመርዎ ለእግዚኦሙ ምድረ ብርህተ ወጽዕዱተ ይወርሱ፡፡
+++
እስመ ለዓለም
ደሪዖሙ ተዓጊሦሙ መጠዉ ነፍሶሙ ለሞት፤
እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ እም ፀሐይ ይበርህ ገጾሙ፤
እለ አጥረይዋ በትዕግሥት
ኦ እፎ አምሰጥዎ ለሞት ለመጽብብ ከመ ይባዕዎ ለመርህብ
ኦ እፎ አምሰጥዎ ለሞት ዓደዉ እሞት ውስተ ሕይወት
ኦ እፎ አምሰጥዎ እለ ጸውዖሙ ወይቤሎሙ ንዑ ለአቡየ ቡሩካኑ
እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ
አመ ያቀውም አባግዓ የማኑ ወአጣሌ በጸጋሙ
ኦ እፎ አምሰጥዎ ለሞት አሜሃ ይቤሎ እለ በየማኑ ንዑ ለአቡየ ቡሩካኑ
ወያወርሶሙ ምድረ ሐዳሰ እንተ ታውኅዝ ሐሊበ ወመዓረ
ኦ እፎ አምሰጥዎ ለሞት ገነተ ትፍሥሕት ኪያሃ አውረሶሙ ወአቀቦሙ ከመ ብንተ ዐይን ለጻድቃን እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ፡፡
+++
130 views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:13:12 ስንክሳር ነሐሴ 24

† እንኩዋን ለታላላቁ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት: ቅድስት ክርስቶስ ሠምራና ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †

† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ †

*ልደት*

=>መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ: ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::

+በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ ሚካኤል: ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በሁዋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::

+ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24 ቀን በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታሕሳስ24 ቀን በ1207 ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::

*ዕድገት*

=>የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁናም ከወቅቱ ዻዻስ አባ ጌርሎስ ተቀብለዋል::

*መጠራት*

=>አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮስ ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::

+የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:: "ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: ከዚህ በሁዋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::

*አገልግሎት*

=>ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያን ጊዜ ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት::

+1ኛ ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::
+2ኛው ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::

+ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::

*ገዳማዊ ሕይወት*

=>ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::

+እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል::

+በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በሁዋላም ወደ ምድረ ሽዋ (ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::

*ስድስት ክንፍ*

=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

+የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::

+ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
-በቤተ መቅደስ ብስራቱን
-በቤተ ልሔም ልደቱን
-በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
-በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
-በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

+የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው::

+በዚያም:-
-የብርሃን ዐይን ተቀብለው
-6 ክንፍ አብቅለው
-የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
-ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
-ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
-ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
-"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

*ተአምራት*

=>የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
*ሙት አንስተዋል
*ድውያንን ፈውሰዋል
*አጋንንትን አሳደዋል
*እሳትን ጨብጠዋል
*በክንፍ በረዋል
*ደመናን ዙፋን አድርገዋል::

+ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

*ዕረፍት*

=>ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን በወዳጆቹ ምልጃ ክብራቸውን ያድለን:: በረከታቸውም በዝቶ ይደርብን::

=>ነሐሴ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት)
2.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ (ጻድቅት)
3.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
4.አበው አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
4."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
5.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም

=>††† ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ††† (ማቴ.10:40)


† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †


ቤተሰብ ይሁኑ

https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
93 views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:12:56 †ስንክሳር ነሐሴ 23 †

እንኳን ለሰላሳ ሺ ግብጻውያን ሰማዕታት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ሠለስቱ እልፍ ሰማዕታት †††

† ዘመነ ሰማዕታት አርባ ሰባት ሚሊየን ክርስቲያኖችን በአርባ ዓመታት ከበላ በኋላ በ305 (312) ዓ/ም ቢጠናቀቅም ስለ ሃይማኖት መሞት ግን እስከ ምጽዓት ድረስ ይቀጥላል:: ለእያንዳንዱ ክርስቲያን ከሚቀርቡ ፈተናዎች ሁሉ እጅግ ከባዱ ይሔው ሰማዕትነት ነውና ሊቀበለው ያለው (ያደለው) ይቀበለዋል::

ቤተ ክርስቲያን በባሕር ላይ ያለች መርከብ ናትና ዘወትር በፈተና ውስጥ መኖሯ የሚጠበቅ ነው:: ዘመነ ሰማዕታትን ተከትሎ የመጣው የመናፍቃን ዘመን ሲሆን ለመቶ ሃምሳ ዓመታት ያህል መናፍቃን እንደ አሸን ፈልተዋል:: በዚያው ልክ ከዋክብት ቅዱሳን ሊቃውንት ነበሩና በየጊዜው ጉባኤያትን እየሠሩ: መናፍቃንን አሳፍረዋል:: ምዕመናንንም አጽንተዋል::

በ451 ዓ/ም የተፈጸመው ድርጊት ግን ዛሬም ድረስ ጠባሳው የሚለቅ አልሃነም:: ንጉሡ መርቅያንና ጳጳሱ ልዮን የንስጥሮስን ትምሕርት አለባብሰው ሊያስተምሩ ሲሞክሩ ግጭት በመፈጠሩ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሁለት ተከፈለች::

በጉባኤው የነበሩ ስድስት መቶ ሰላሳ ስድስት ጳጳሳት ስቃይና ሞትን ፈርተው በኑፋቄ መጽሐፍ ላይ በመፈረማቸው "መለካውያን" (ከእግዚአብሔር ይልቅ ለንጉሥ የሚታዘዙ) ተባሉ:: ጉባኤውም "ጉባኤ ከለባት" (የውሾች ስብሰባ): "ጉባኤ አብዳን" (የሰነፎች ጉባኤ) ተብሏል::

የወቅቱ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ግን "በኑፋቄው ላይ አልፈርምም::" ከማለቱ አልፎ መናፍቃኑን አወገዛቸው:: በዚህ ምክንያት ጽሕሙን ነጭተው: ጥርሱንም አርግፈው: ወደ ጋግራ ደሴት ከሰባት ደቀ መዛሙርቱ ጋር አሳደዱት::
በዚያም ለሦስት ዓመታት ቆይቶ በ454 ዓ/ም ዐረፈ::

እግዚአብሔር ፈርዶባቸው ንጉሡ መርቅያን እና ንግሥቲቱ ብርክልያ (ክፉ ሴት ናት) ድንገት ሞቱ:: ፈተናው ግን በዚህ አላበቃም:: በዙፋኑ የተተካው ሌላኛው ጨካኝ ልዮን ነበር:: መንፈሳዊውን አርበኛ አባ ዲዮስቆሮስን በሞት ያጡት የግብጽ ክርስቲያኖች ደቀ መዝሙሩን "አባ ጢሞቴዎስን እንሾማለን::" ቢሉ ንጉሡ ከለከለ::

የሚሾመው መለካዊ ነው ብሎ አብሩታርዮስ የሚባል መናፍቅ ጳጳስ በላያቸው ላይ ሾመባቸው:: ይህንን መታገስ ለሕዝቡና ለካህናቱ ከባድ ነበር:: ተኩላ እንኳን በበጐች ላይ በይፋ ተሹሞ: ተደብቆም ቢሆን እየነጠቀ መብላት ልማዱ ነው:: መናፍቁ ጳጳስ በተለያየ መንገድ ሕዝቡን ለመሳብ ሞክሮ ነበር::

ለምሳሌ አውጣኪን (የክርስቶስን ሰው መሆን ምትሐት የሚል 'የቱሳሔ' አስተማሪ መናፍቅ ነው::) አወገዘው:: እነሱ ግን ተረድተውታልና ቦታ አልሰጡትም:: ምክንያቱም አውጣኪ ከቀድሞም የተወገዘ መናፍቅ ነውና:: የሚገርመው ከሕዝቡ አንድስ እንኳ ከመናፍቁ ጳጳስ የሚባረክ አልነበረም:: ሥጋውን ደሙንም ከእውነተኛ ካህናት በድብቅ ይቀበሉ ነበር::

አንድ ቀን ግን መናፍቁ ጳጳስ አብሩታርዮስ ተገድሎ ተገኘ:: (መልአክ ቀሥፎት ነው የሚሉ አሉ:: እስካሁን ድረስ የገዳዩ ማንነት አልታወቀም::) ግብጻውያን ክርስቲያኖች ግን የእርሱን ሞት ሲሰሙ ደጉን እረኛ አባ ጢሞቴዎስን ሾሙ:: ችግሩ የመጣው ከዚህ በኋላ ነው::

የመናፍቁ ተከታዮች ለንጉሡ ልዮን "አንተን ንቀው: የሾምከውን ገደሉ:: ሌላ ጳጳስም ሾሙ::" ብለው መልዕክት ላኩለት:: በዚህ የተበሳጨው ልዮን ኦርቶዶክሳውያንን ባገኛችሁበት ሁሉ ግደሉ የሚል አዋጅ አወጣ:: ይህን አዋጅ ተከትሎ ሰላሳ ሺ ሰዎች በእስክንድርያ ከተማ ተጨፈጨፉ::

ገዳዮቹ ወንድ: ሴት: ሕፃን: ሽማግሌ ሳይመርጡ የክርስቲያኖችን ደም አፈሰሱ:: ለሦስት ቀናትም ግድያው ቀጥሎ እንደ ነበር ይነገራል::
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት "ወኀጥኡ ዘይቀብሮሙ" እንዳለ ቀባሪም አጡ::

ገዳዮቹ ቀጥለውም አባ ጢሞቴዎስን አስረው አጋዙት:: ለአሥር ዓመታትም አሰቃዩት:: ከእነዚህ ዓመታት በኋላ ግን ንጉሡ ተጸጽቶ አባ ጢሞቴዎስን ወደ መንበሩ መልሶታል:: ወገኖቻችን የግብጽ ክርስቲያኖች እንኳን ያኔ ዛሬም በጽናታቸው አብነት ልናርጋቸው የሚገቡ ናቸው::

† አምላከ ሰማዕታት በቸርነቱ ይጠብቀን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

††† ነሐሴ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ሰላሳ ሺ የእስክንድርያ (ግብጽ) ሰማዕታት
2.ቅዱስ ድምያኖስ ሰማዕት

† ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል

† "በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት:: በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ:: ነገር ግን በየውሃነትና በፍርሃት ይሁን::" †††
(፩ጴጥ. ፫፥፲፫-፲፮)


† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †


ቤተሰብ ይሁኑ

https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
110 views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 05:04:38   ነሐሴ  22 

†. እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሚክያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ

ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር): መጻዕያትን (ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን) የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: (ሐዋ. 11:27) ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::

ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::

የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ::" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: (ዮሐ. 4:36)

ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ፈለጉ::" እንዳለ ጌታ በወንጌል::(ማቴ. 13:16, 1ጴጥ. 1:10) ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት
አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት:
አራቱ ዐበይት ነቢያት:
አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያትና
ካልአን ነቢያት ተብለው በአራት ይከፈላሉ::

አሥራ አምስቱ አበው ነቢያት የሚባሉት ቅዱስ አዳም አባታችን፣ ሴት፣ ሔኖስ፣ ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣ ኄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ ኖኅ፣ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ ሙሴ እና ሳሙኤል ናቸው::
አራቱ ዐበይት ነቢያት ደግሞ
ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል፣ ቅዱስ ኤርምያስ፣ ቅዱስ ሕዝቅኤል እና ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

አሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት:- ቅዱስ ሆሴዕ፣ አሞጽ፣ ሚክያስ፣ ዮናስ፣ ናሆም፣ አብድዩ፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ኢዩኤል፣ ዕንባቆም፣ ዘካርያስ እና ሚልክያስ ናቸው::

ካልአን ነቢያት ደግሞ:-ኢያሱ፣ ሶምሶን፣ ዮፍታሔ፣ ጌዴዎን፣ ዳዊት፣ ሰሎሞን፣ ኤልያስና ኤልሳዕ . . . ሌሎችም ናቸው::

ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::
*የይሁዳ (ኢየሩሳሌም):
*የሰማርያ (እሥራኤል)ና
*የባቢሎን (በምርኮ ጊዜ) ተብለው ይጠራሉ::

በዘመን አከፋፈል ደግሞ:-
፩)ከአዳም እስከ ዮሴፍ (የዘመነ አበው ነቢያት):
፪)ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል (የዘመነ መሳፍንት ነቢያት)
፫)ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት (የዘመነ ነገሥት ነቢያት)
፬)ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ (የዘመነ ካህናት ነቢያት) ይባላሉ::

ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህን ካልን በዛሬው ቀን የምናስታውሰውና የምናከብረው
ቅዱስ ሚክያስ ቁጥሩ ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ.ል. ክርስቶስ በ800 ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው::
አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ አሥራ አራት ምዕራፍ: ሲያንስ አንድ ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል:: ሚክያስ አባቱ ሞራት (ሞሬት) ይባላል:: ሚክያስ ማለት "መኑ ከመ አምላክ - እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!" ማለት ነው:: አንድም "መልአከ እግዚአብሔር" ማለት ነው:: የአባቶቻችን ሁሉ ስማቸው እግዚአብሔርን የሚሰብክ ነው::

ቅዱሱ ነቢይ ገና ልጅ እያለ መላእክት ያነጋግሩት ነበር:: በዚህ ምክንያት ከሰው አይቀርብም:: ትክ ብለው ሲያዩት በፊቱ ላይ ብርሃን ቦግ ቦግ እያለ ይታይ ነበር:: በወጣትነት ዘመኑ እግዚአብሔር ለትንቢት ሲጠራው በእሺታ ታዘዘ:: በሦስቱ ነገሥታት (በኢዮአታም: አካዝና ሕዝቅያስ) ዘመንም ትንቢቶችን ተናግሯል:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን: ነገሥታቱን አስተምሮ ገስጿል::

አንድ ቀን በቤተ ልሔም ሲያልፍ የዳዊት ከተማ ፈት ሁና: ዳዋ በቅሎባት ቢመለከት አዘነ:: ወዲያውም ትንቢት ተናገረላት::
"አንቺም የኤፍራታ ምድር ቤተ ልሔም: የይሁዳ ነገሥታት ከነገሡባቸው ከተሞች ከቶ አታንሺም:: ወገኖቼን እሥራኤልን የሚጠብቃቸው ንጉሥ (መስፍን) ካንቺ ዘንድ ይወጣልና::" አለ::

ይኸውም አልቀረ ለጊዜው ከሚጠት በኋላ ደጉ ዘሩባቤል ነግሦባታል:: በፍጻሜው ግን የባሕርይ ንጉሠ ነግሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ከንጽሕት ድንግል ማርያም ተወልዶባታል::

ቅዱስ ሚክያስ ወገኖቹን ሲያስተምርና ሲመራ ኑሮ: ሰባት ምዕራፎች ያሉትን ሐረገ ትንቢት ተናግሮ: በመልካም ሽምግልና: በንጉሡ ሕዝቅያስ ዘመን ዐርፏል:: ወገኖቹ ቀብረውታል:: ጌታም በክብረ ነቢያት ከልሎታል::

ቸር አምላከ ነቢያት የነቢያቱን መከራ አስቦ ከመከራ: በእንባቸውም ከእንባ ይሰውረን:: ከተረፈ በረከታቸውም አያጉድለን::

ነሐሴ 22 ቀን የሚከበሩ
ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ

ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
5.አባ ጳውሊ የዋህ

"ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መስዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን? እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጐች: ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? . . . ሰው ሆይ! መልካሙን ነግሮሃል:: እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ: ምሕረትንም ትወድ ዘንድ: ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሔድ ዘንድ አይደለምን?" (ሚክ. ፮፥፮)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
(ይህ የቴሌግራም ቻናላችን ነው ይቀላቀሉን)

https://t.me/Keradiyon77Books
https://t.me/Keradiyon77Books
https://t.me/Keradiyon77Books

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

              
ቤተሰብ ይሁኑ

       https://t.me/Sinksar
       https://t.me/Sinksar
       https://t.me/Sinksar
247 views02:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:32:40
የማኅበረ ቅዱሳን 15ኛ ጠቅላላ ጉባኤ መርሐ ግብረ መከናወን ጀመረ!!
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
(ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ)

ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ እና አፋር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት መርሐ ግብሩ በጸሎተ ወንጌል ተጀምሯል፡፡

በመርሐ ግብሩም የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ፣ በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ዓለምፀሐይ መሠረት ጨምሮ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ነሐሴ 21-2014ዓ.ም
224 views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ