Get Mystery Box with random crypto!

ስንክሳር በየቀኑ

የቴሌግራም ቻናል አርማ sinksar — ስንክሳር በየቀኑ
የቴሌግራም ቻናል አርማ sinksar — ስንክሳር በየቀኑ
የሰርጥ አድራሻ: @sinksar
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.00K
የሰርጥ መግለጫ

የአመቱን ስንክሳር በየቀኑ የሚቀርብበት ማብራሪያው ላልቀረበበትም የበለጠ እንድናነብ የሚረዳን መማማሪያ ነው።
" ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ:: በዓለም ያለው ሁሉ: እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት: ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ: ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም:: ዓለሙም: ምኞቱም ያልፋሉ::" 1ዮሐ. 2:15
# ያጋሩ

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-07 06:16:28

134 views03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 06:15:37

116 views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 06:09:08

121 views03:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:27:38 † ስንክሳር ሰኔ 30 †

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!።

እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

። ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ።

ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
https://t.me/Sinksar

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

=>መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
+የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
+በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
+በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
+እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
+የጌታችንን መንገድ የጠረገ
+ጌታውን ያጠመቀና
+ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
+ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ: መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::

https://t.me/Sinksar

=>አምላካችን ከቅዱሱ ቤተሰብና ከጻድቁ በረከት ይክፈለን::

=>ሰኔ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ልደቱ)
2.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ (ወላጆቹ)
3.አባ ጌራን መስተጋድል (ሕንዳዊ)
4.ቅዱሳት ደናግል ማርያና ማርታ
(ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት-የአልዓዛር እህቶች)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

=>" ደግሞም አንተ ሕጻን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ:: መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና:: እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ:: ይሕም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው:: " (ሉቃ. 1:76)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

በዚህ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ።

ክፉውን ያርቅልን
https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
https://t.me/Sinksar
127 views19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:22:32

186 views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:22:05

173 views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:21:47

160 views04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 22:16:59 . ስንክሳር ሰኔ 29

. እንኩዋን ለቅዱሳን ነገሥታት "#ማርቆስ እና #ቴዎድሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ::

ማንኛውም ሰው
¤ቢጾም ቢጸልይ
¤መልካም ቢሠራ
¤ለእግዚአብሔር ቢገዛ
¤አልፎም ቢመንን ይደነቃል:: ይሕንን ሥራ ንጉሥ ሆነው ስለ ሠሩትስ ምን እንላለን? ማድነቅ የሚለው ቃል የሚገልጸው አይመስለኝም::

¤ወርቅና ብር በእግር እየተረገጠ
¤የሚበላውና የሚጠጣው ተትረፍርፎ ሳለ
¤አገር ምድሩ እየሰገደላቸው
¤ሁሉ በእጃቸው
¤ሁሉም በደጃቸው ሳለ...
ይህንን ሁሉ ስለ #ክርስቶስ ፍቅር የተውትን ጻድቃን ነገሥታት የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከእነዚህ መካከል ዛሬ የሚከበሩትን 2ቱን እናዘክር::

+*" ቅዱስ ማርቆስ ንጉሠ ሮም "*+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ቅዱስ ጻድቅ: የዋህ: ንጹሕና ገዳማዊ ብላ ትጠራዋለች:: ሮም እንደ ዛሬ ጠባብ ከተማ ሳትሆን ዓለምን በክንዷ ሥር ቀጥቅጣ የምትገዛ ኃያል ሃገር ነበረች:: ቅዱስ ማርቆስ የልዑላኑ ቤተሰብ ነውና በሮም ተወልዶ በእመቤታችን ቤተ መቅደስ ውስጥ አድጉዋል::

+የየዕለት ሙያው ጾምና ጸሎት: መጻሕፍትንም መመልከት ነበር:: ነባሩ ንጉሥ ሲሞት መሣፍንቱ ቅዱስ ማርቆስን በድንግልናው ገና ወጣት ሳለ በዚያች ታላቅ ሃገር ላይ አነገሡት:: ንጉሥ ቢሆንም ሙሉውን ሌሊት በእመቤታችን ፊት ሲጸልይና ሲያለቅስ ያነጋ ነበር::

+ስለ ፍቅርም ድንግል ማርያም ተገልጻ "ምን ላደርግልህ ትወዳለህ?" አለችው:: ቅዱስ ማርቆስም "ለሕዝቡ ፍቅር አንድነትን ሰላምን ስጪልኝ:: እኔ በማስተዳድርበት ቦታ ሁሉ ጠብ ክርክር ይጥፋልኝ:: ፍቅር ይንገስልኝ" ሲል መለሰላት:: ድንግል እመቤታችንም "እንደ ቃልህ ይሁን" ብላ አጋንንት ወደ ሃገሩ እንዳይገቡ ከለከለችለት:: በዚህም ቅዱስ ማርቆስ ከነገሠ ጀምሮ ለ5 ዓመታት ጠብ ክርክር: ክፋትና ችግር አልነበረም:: ሁሉም ተፋቅሮን ያጸና ነበር እንጂ::

+ከ5 ዓመታት በሁዋላ ግን ሕዝቡና ሹማምንቱ ተሠብስበው አንድ ነገርን መከሩ:: #ቅዱስ_ማርቆስን አጋብተው ለብዙ ጊዜ እንዲመራቸው ማለት ነው:: ምክንያቱም አኗኗሩ እንደ መነኮሳት ነውና ጠፍቶ እንዳይሔድ በመስጋታቸው ነው:: ከዚያም የሕዝቡ አለቆች ተመርጠው ሃሳባቸውን አቀረቡለት:: እርሱ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጭራሹኑ እንዲህ ዓይነት ሃሳብ መጥቶበት አያውቅም::

+"እስኪ በጸሎት ላስብበት" ብሎ መለሳቸው:: እነርሱ ግን ወደውታልና ድጋሚ ተሰብስበው ሌላ ነገርን መከሩ:: እርሱ ሳያውቅ መልካም ሴት መርጠው: ሥርዓተ ተክሊል አዘጋጅተው: ድግሱንም አዘጋጅተው በግድም ቢሆን ሊያጋቡት ቆረጡ:: ቅዱስ ማርቆስ የተደረገውን ሁሉ ፈጣሪ ገልጦለት በጣም ደነገጠ::

+ፈጥኖ ወደ #እመ_ብርሃን ስዕል ቀርቦ አለቀሰ:: "#እመቤቴ! እኔ ካንቺ ጋር እንጂ ከዚህ ዓለም ጋር መኖር አልችልም" አላት:: እመ ብርሃን ከሰማይ ወደ እርሱ ወርዳ "የምነግርህን ስማኝ:: በሌሊት ተነስተህ ወደ ማሳይህ በርሃ ሒድ" ብላው ተሠወረች:: ቅዱስ ማርቆስ ደስ እያለው የንግሥና ልብሱን ጥሎ: ቆሻሻ ጨርቅ ለብሶ በሌሊት ከቤተ መንግስቱ ወጣ::

+ወደ ሁዋላ አልተመለከተም:: እመቤታችን እየመራችው #ደብረ_ቶርማቅ የሚባል በርሃ ውስጥ ባሕር ተከፍሎለት ገባ:: ሕዝቡ መልካም እረኛ መሪን አጥቷልና በሮም ከተማ ታላቅ ለቅሶና ሐዘን ተደረገ:: ቅዱስ ማርቆስ ግን በደብረ ቶርማቅ በጾም: በጸሎትና በተጋድሎ ማንንም ሳያይ ለ60 ዓመታት ኖረ::

+በዚህች ቀንም ዐርፎ ወደ ወደደው ክርስቶስ ሒዷል:: ሥጋውን የሚቀብር አልነበረምና ከሰማይ 12ቱ ሊቃነ መላእክትና 12ቱ ሐዋርያት ወረዱ:: በዝማሬ ሲገንዙትም በድኑ ከመሬት 5 ክንድ ከፍ ብሎ ተንሳፈፈ::
መላእክቱና ሐዋርያቱም በማሕሌት እዚያው ደብረ ቶርማቅ ውስጥ ቀብረውታል::

+"+ #ቅዱስ_ቴዎድሮስ ንጉሠ ኢትዮዽያ +"+

=>በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት #ጻድቁ_ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል:: በርግጥ በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስን (1845-1860) ነው:: በበጎ ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ የምናስበው ቀዳማዊው ነው::

+ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ #ዐፄ_ዳዊት (#ግማደ_መስቀሉን ያመጡት) እና የተባረከችው ሚስታቸው #ፅዮን_ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ #ዘርዐ_ያዕቆብ ታላቅ ወንድም ነው::

+በኢትዮዽያ ለ3 ዓመታት (ከ1396-1399) ብቻ ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን
¤ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል: ፍርድ እንዳይጉዋደል ይታትር የነበር:
¤ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር:
¤ወገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ:
¤ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር::

+ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር:: በነገሠ በ3 ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሦ ሥጋውን ተሸክመው ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል:: ከመቃብሩም ላይ ጸበል ፈልቁዋል::

=>ቸር አምላክ መልካም መሪ ለሃገራችን: በጐ እረኛንም ለነፍሳችን ያድለን:: ከቅዱሳን ነገሥታቱም ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

=>ሰኔ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ማርቆስ ንጉሠ ሮም (ጻድቅ: ንጹሕና ገዳማዊ)
2.ቅዱስ ቴዎድሮስ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ኢትዮዽያዊ (ፍልሠቱ)
4."7ቱ" ቅዱሳን መስተጋድላን (አባ አብሲዳ: አባ ኮቶሎስ: አባ አርድማ: አባ ኒኮላስ: አባ ሙሴ: አባ እሴይ: አባ ብሶይ)
5.ቅዱሳን አባ ሖር: አባ ብሶይ: አባ ሖርሳና እናታቸው ቅድስት ይድራ (ሰማዕታት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅድስት አርሴማ ድንግል
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)

=>+"+ አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል::
በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል::
የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው::
የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም::
በበጐ በረከት ደርሰህለታልና::
ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ::
ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም::
ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ::
በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው:: +"+ (መዝ. 20:1-5)

<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>
163 views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 07:16:57

205 views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 06:31:11

190 views03:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ