Get Mystery Box with random crypto!

የእልቂት አዚም ' የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰ | ስንክሳር በየቀኑ

የእልቂት አዚም

" የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?" ገላ 3፥2

በሆኑ እና እየሆኑ ባሉ ነገም ሊሆኑ በሚችሉ የሰው ልጅን ጥፋት የኦርቶዶክሳውያንን እልቂት እንዳንረዳ አዚም ያደረገብን ምንድን ነው?

የማያጸድቅ ሞትን መላመድ ትልቅ በሽታ ነው፡፡ ሁላችን በስሁት ርዕዮት ታመናል ፈውሱ ግን ኦርቶዶክሳዊነት ነበር፡፡
መድኃኒታችንን አልተጠቀምንበትም፣ ለበሽተኞች ባለመድኃኒት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ክርስትና አካለ ክርስቶስ እንጂ ዘር አይደለም ቋንቋም መግባቢያ እንጂ ሰው አይደለም፡፡ የተወለድንበት ማሕፀነ ዮርዳኖስ አንድ ነው ፡፡ ሁላችንም የተቀበልነው ማዕድ አንድ የቀራንዮ ማዕድ ነው፡፡
ማዶ እና ማዶ ያለኸው ወንድሜ ሆይ
ማዶና ማዶ ያለሽው እኅቴ ሆይ
ሁላችሁም የወይኑ ግንድ ቅርንጫፎች የሆናችሁ፦እየተቆረጠ ያለው የወይኑ ቅርንጫፍ ነውኮ!!
የተከፋፈለ ክርስቶስን አልተቀበልነም አንዱን ክርስቶስ ነው እንጂ ባልተከፋፈለ ክርስትስ አንድ ሁነን በከፋፋይ ስሁት ፖለቲካ አንለያይም፡፡

ከማይጠፋ ዘር አብራከ መንፈስ ቅዱስ ተወልደን በሚጠፋ ስሁት ርዕዮት አንጋደልም፡፡
እናም የሐዋርያው ተግሣፃዊው ጥያቄ የህሊናን ስንፍና አዚም ይቀሰቅሳል ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሆይ የእልቂት አዚም ያደረገብን ማን ነው?
ተው ባይ አባት ተው ባይ ምእመን እንዴት ልናጣ ቻልን?
የሞት ነጋሪትን የሚደልቅብን በዝቷል ፡፡

የዋሐን ምእመናን ደግሞ የሚያውቁት ሳይኖር በታዛዥነት እንደ እሳት ራት እየሆኑ ነው፡፡
የውጪውም የውስጡም ዓላማ ፦ቤተክርስቲያንን አቅም አልባ ማድረግ እና ከሞት የተረፉት ከጥላ ያረፉት ዳግም እንዳይገናኙ የደም ድንበር መዘርጋት ነው፡፡
እኛም በዝምታችን ፣ በስንፍናች፣ በፍራታችን ምክንያት፦ከሁሉ በላይ ቤተ ክርስቲያንን ይዘን ከሁሉ በታች አደረግናት ፡፡

#ሼር/ለወዳጅዎ ያጋሩ

#በመ/ር ገብረ መድኅን እንየው