Get Mystery Box with random crypto!

አል አዝካር AL AZKAR

የቴሌግራም ቻናል አርማ seid_islamic — አል አዝካር AL AZKAR
የቴሌግራም ቻናል አርማ seid_islamic — አል አዝካር AL AZKAR
የሰርጥ አድራሻ: @seid_islamic
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ብዙ ማዉሳትን አዉሱ።{አል አህዛብ፥41}
"አላህ አዋቂም ጥበበኛም ነው"🎨
☞ ኢስላም በራሱ ውበት ነው ፣ ጥበብም ነው።
♢አላህም ቆንጆ የሆኑ ነገሮቸን ሁሉ ይወዳል በሀዲስ ላይ ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዳሰፈሩት:-
 ❤“.. إن الله جميل يحب الجمال ..”♥ ☞
-
-
-
-
-

♡"ያ ረብ ለሰጠከኝ ፀጋ ሁሉ አመሰግናለሁ!"

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-16 15:04:31 አመጋገበዎን ያስተውሉ
=
1. ሐላል ብቻ ይመገቡ፡፡ ያለበለዚያ በሚመገቡት ይጠየቃሉ፡፡ ዱዐዎትንም አላህ ባይቀበለዎት አይደነቁ፡፡ ስለዚህ የሚመገቡት ነገር ምንጩ ሀላል መሆን አለበት፡፡ ከዚያ ባለፈ ለጤናም፣ ለዲንም፣ ለኢኮኖሚም፣ ለቤተሰብም፣ ለማህበረሰብም ጎጂ የሆነ ነገር ሁሉ ሀራም ነውና ይራቁ፡፡
2. አቀራረቦን ያስተካክሉ፡፡ አንዴ ሁለቴ ያጋጥም ይሁን፡፡ ሁሌ ግን ይበቃል ተብሎ ከሚገመተው በላይ እያቀረቡ ያለጥንቃቄ ነካክቶ መድፋት ከአላህ ዘንድ ያስጠይቃል፡፡ አባካኞች የሸይጧን ወንድሞች ናቸውና፡፡
3. ተስተካክለው ይቀመጡ፡፡ በምግብ ጊዜ ትራስ ላይ መደገፍ፣ መጋደም፣ ወይም ስርኣት የሌለው አቀማመጥ መቀመጥ ወይም ቆሞ መብላት ክልክል ነው፡፡
4. ቢስሚላህ ይበሉ፡፡
5. በቀኝ እጅዎት ይብሉ፡፡ በግራ መብላት የሸይጧን ስራ ነው፡፡ ሲጠጡም እንዲሁ፡፡ እቃው እንዳይጨማለቅ በሚል አጉል ምክንያት በግራ እንዳይጠጡ፡፡ ወይ አስተካክለው ይያዙ፡፡ ያለበለዚያ እቃው ኋላ ይታጠባል እንጂ የሸይጧን ስራ አይስሩ፡፡
6. በሶስት ጣት መብላት ከሱና ነው፡፡ (ግዴታ አይደለም።)
7. ከፊት ከፊቶ ይብሉ፡፡ እዚያም እዚህም መክለፍለፍ ከሱናም ከወግም ያፈነገጠ ነው፡፡
8. ከምግቡ አናት ወይም ከመሀሉ አይጀምሩ፡፡ መሀሉን ይደርሱበት የለ? ምን አናቱን/መሀሉን አስበረቆሰዎት? መናልባት ከመሀል ሳይደርሱ ከበቃዎትም ቀሪውን ሌላ ሰው ሊመገበው ይችላል፡፡ ከመሀል ሲጀመር ግን ለሌላ ሰው ደስ አይልም፡፡
9. በልክ ይብሉ፡፡ ሲበቃው ሳይሆን ሲያመው የሚያቆመው ህፃን ነው፡፡
10. ሲጨርሱ ጣትዎን ይላሱ፡፡ አንዳንድ በዚህ ሱና የሚያፍር አለ፡፡ ጠላ እሚጠጣ፣ አሳማ የሚበላ፣ እስቲንጃ የማያደርግ ሰው ሳቀብኝ ብሎ ሱናን መተው እንዴት አይነት አሳፋሪ ነገር ነው?! አንዳንዱማ ጭራሽ አስቂኝ ነው፡፡ “እጅን መላስ ያስጠላል” ይላል፡፡ የበላህበትን እጅ መላስ ከደበረህ በሪሞት ኮንትሮል ብላ ወይ ደግሞ ምግቡን ጭራሽ ቶወው፡፡ አጂነብይ ሲጨብጡ አያፍሩም አይደብራቸውም። ሲዘፍኑ፣ ሲያዳምጡ አያፍሩም አይደብራቸውም። ወለድ ሲበሉ አያፍሩም አይደብራቸውም። … ሱና ለመተግበር ግን ያፍራሉ፣ ይደብራቸዋልም፡፡ ከእንዲህ አይነት የተገለበጠ አሰተሳሰብ አላህ ይጠብቀን፡፡
11. ሲጨርሱ አላህን ያመስግኑ፡፡
12. ተጋብዘው ከሆነ ለጋበዘዎት ዱዐ ያድርጉ፡፡
13. ውሃ ሲጠጡ ይቀመጡ፡፡ ቆመው አይጠጡ፡፡
14. እንደማንቆርቆሪያ ባለ ነገር ሲጠጡ በጡቱ አይጠጡ፡፡ በጡቱ የሚመጣውን ውሃ ንፁህነት ማረጋገጥ አይቻልምና፡፡
15. የሚጠጡበት እቃ ውስጥ አይተንፍሱ፡፡ ለተመልካችም ያስጠላል። በሽታ የመተላለፍ እድሉም ሰፊ ነው፡፡ እንዲያውም በሶስት እስትንፋስ እያረፉ መጠጣት ሱና ነው፡፡ ሱናውን እኛ ካልሰራነው ማን ይስራው?
-
(ኢብኑ ሙነወር፣ 20/2/2005)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
1.5K views12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-25 20:07:01 ሐራምን መዳፈር

ኢስላም በማያሻማ መልኩ ከደነገጋቸው ህግጋቶች አንዱ የምስል ወይም ፎቶ ሐራምነት ነው ። ዛሬ ተውሒድ እናስተምራለን የሚሉ ወንድሞች ጭምር እየተዳፈሩትና እንደ ቀላል እያዩት ቻናላቸው የምስል ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ እስከሚመስል ድረስ የሴትና የወንድ ምስል ወይም የሚደንሱ ሴቶችን ምስል ማዥጎርጎሪያ እያደረጉት ነው ። ይህ ተግባር ሸሪዓን የሚፃረር የምናስተምረውን ተውሒድ የሚነካ ወደ ሽርክ የሚያዳርስን ሙንከር ማሰራጨት በመሆኑ አላህን ልንፈራ ይገባል ። ፎቶም ሆነ ምስል በየትኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑ የሰዎች ኢጅቲሃድ ሳይሆን ከልብ ወለዳቸው ከማይናገሩት የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – በወሕይ አማካይነት ለቁጥር በሚያታክቱ ሐዲሶች የተረጋገጠ ነው ። የተኛውም ምስል ይቻላል የሚል ዓሊም ምንም ነብያዊ ማስረጃ የለውም ። ምናልባት ደሩራ ነው የሚል ነው የሚሆነው ። ያ ደግሞ በደሩራው ልክ የሚታይ ነው ። የትኛውም አማኝ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ሲባል ሸኽ እገሌ እንዲህ ብለዋል ሊል አይገባም ። ይህን በተመለከተ የሰለፎችን ንግግር እንመልከት : –
قال ابن عباس – رضي الله عنه – :
" يوشك أن تنزل عليكم حجارة من السماء ، أقول: قال: رسول الله – صلى الله عليه وسلم – وتقولون : قال أبو بكر وعمر؟ "
أخرجه الإمام أحمد ( 3121 )
ዐብዱላሂ ኢብኑ ዓባስ እንዲህ አሉ: – ከሰማይ የድንጋይ ናዳ ሊወርድባችሁ የደረሰ ይመስላል , የአላህ መልእክተኛ ብለዋል እያልኳችሁ አቡበከርና ዑመር ብለዋል ትላላችሁን ? !!!!!!
ሱብሃናላህ ኢብኑ ዓባስ ዑመርና አቡበከር ብለዋል ስለተባሉ ነው ይህን ያሉት ። ባዮቹ መረጃውን ባለማወቃቸው ነው እንጂ የተነሳው የተመቱዕ መስአላ መረጃ የሌለው ሆኖ አይደለም ። ነገር ግን ከኢብኑ ዓባስ ጋር የተነጋገሩት መረጃውን ሳያቀርቡ አቡበከርና ዑመር ብለዋል ማለታቸው ነው ያስቆጣው ። አቡበከርንና ዑመርን እንድንከተል ታዘን እያለ ። ነገር ግን ነስ ከመጣ መቆም ግዴታ መሆኑን ለመግለፅ ነው ።
ሌላው አሰር እንዲህ ይላል : –
قال الإمام أحمد : عجبت لقوم عرفوا الإسناد وصحته ، ويذهبون إلى رأي سفيان ، والله تعالى يقول:
{ ۚفَلْيَحْذَرِ الَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنْ أَمْرِهِ أَن تُصِيبَهُمْ فِتْنَةٌ أَوْ يُصِيبَهُمْ عَذَابٌ أَلِيم ٌ}
النور ( 63 )
أتدري ما الفتنة ؟ الفتنة الشرك . لعله إذا رد بعض قوله أن يقع في قلبه شيء من الزغ فيهلك .
ኢማሙ አሕመድ እንዲህ ይላል : –
" የሰዎች ሁኔታ አስደነቀኝ ( አስገረመኝ) ሐዲስን ሶሒህነቱ ቃወቁ በኋላ ወደ ሱፍያን አስሰውሪ ረእይ ይሄዳሉ , አላህ እንዲህ እያለ
" እነዚያም ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ ፡፡"
ፈተና ( መከራ ) ማለት ምን እንደሆነ ታውቃለህን ? ፈተና ማለት ሽርክ ነው ። የነብዩን ከፊል ንግግር ከመለሰ በልቡ ላይ አንዳች ጥመት ይከሰትና እንዳይጠፋ ይፈራል "
ይህ ማለት ሐዲስ መጥቶለት እገሌ እንዲህ ብሏል ከሚል ሰው ጋር ሰለፎች የነበራቸው አቋም ነው ።
አሁን የአላህ መልእክተኛ በፎቶና ምስል ዙሪያ ከተናገሯቸው ሐዲሶች ጥቂቶቹን እንመልከት : –
روى البخاري ومسلم عن عائشة عن رسول الله صلى الله عليه وسلم أنه قال : «أشدّ الناس عذاباً يوم القيامة الذين يضاهئون بخلق الله "
ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡትና እናታችን ዓኢሻ ባወራችው ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ትላለች : –
" የቂያማ ቀን ብረቱ ቅጣት የሚያገኘው እነዚያ በአላህ አፈጣጠር የሚያመሳስሉ ናቸው "
روى البخاري ومسلم وأصحاب السنن أن النبي صلى الله عليه وسلم قال :
«إن اصحاب هذه الصور يعذبون يوم القيامة، يقال لهم: أحيو ما خلقتم».
ቡኻሪና ሙስሊም እንዲሁም የሱነን ባልተቤቶች በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላሉ: –
" የእነዚህ ምስል ባልተቤቶች የቂያማ ቀን ይቀጣሉ, የፈጠራችሁትን ህያው አድርጉ ይባላሉ "
روى البخاري ومسلم والنسائي عن ابن عباس رضي الله عنهما أن رجلاً قال له: إني أصوّر هذه الصور فأفْتني فيها، فقال له: ادن مني فدنا، ثم قال: ادن مني فدنا، حتى وضع يده على رأسه وقال: إنبئك بما سمعت من رسول الله صلى الله عليه وسلم، سمعته يقول: «كلّ مصوّر في النار، يُجعل له بكل صورة صوّرها نفس فيعذب به في جهنم».
وفي رواية أخرى عنه: سمعته يقول:
«من صوّر صورة فإنّ الله يعذبه حتى ينفخ فيها الروح وليس بنافخ فيها أبداً»
ቡኻሪና ሙስሊም እንዲሁም ኢማሙ ነሳኢ በዘገቡትና ዐብዱላሂ ኢብኑ ዓባስ ባወሩት ሐዲስ አንድ ሰው ለኢብኑ ዐባስ እንዲህ አላቸው እኔ ይህን ምስል እስላለሁ እስኪ ፈትዋ ስጠኝ ። ኢብኑ ዐባስም ወደኔ ቅረብ አለው ቀረበ አሁንም ቅረብ አለው ቀረበም እጁ በጭንቅላቱ ላይ እስከሚያደርግ ድረስ ከዛም ከአላህ መልእክተኛ የሰማሁትን እነግርሃለሁ አለው ። የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ : –
" ምስል የሚስል ሁሉ የእሳት ነው ። በየአንዳንዱ የሳለው ምስል ነፍስ ይደረግለታል በሱም በጀሀነም ይቀጣል ። " በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ እንዲ ብለዋል
" አንድን ምስል የሳለ ሰው ሩሕ እስከሚነፋበት ድረስ አላህ ይቀጣዋል ። እስከመጨረሻውም ሩሕ የሚነፋ አይደለም "
እነዚህ ሐዲሶች ከብዙ በጥቂቱ ናቸው ። እንደምታዩት እንደ ጠዋት ፀሀይ ፍንትው ብለው የሚታዩ የፎቶ ወይም ምስል በየትኛውም መልኩ ክልክልነት የሚያረጋግጡ ሲሆኑ እነዚህን ሐዲሶች ትቶ ከስሜት ጋር የሚሄድ የዑለማዎች ንግግር መፈለግ የሰለፍዮች መገለጫ አይደለም ። በተለይም ወደ ተውሒድ የሚጣራ ሰው የዚህ ዛቻ ማረፈያ የሆነውን ምስል ከማሰራጨትና ሐላል ነው ብሎ ከመሞገት ሊቆጠብ ይገባል ። እንኳን እንዲህ አይነት መረጃ የመጣበትን ጉዳይ አይደለም የሚያጠራጥር ነገር ከሆነ እንኳን መጠንቀቁ የዲንንም የራስንም ክብር መጠበቅ ነው ። አላህ ከስሜት ወጥተን ሐቅን የምንከተል ያድርገን ።
2.6K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-17 21:40:07
ሶላት ለማይሰግድ ሰው አሳሳቢ ምክር
==========================
ወንድሜ ሆይ!
«ሶላትን በፍጹም እንዳትተው። በዚህ ወቅት ከቀብር ስር ሁነው ህይዎት ወደነርሱ ብትመለስላቸው አንድትን እንኳ ሱጁድ ለአላህ ማድረግ የሚመኙ ሚሊዮኖች ይገኛሉ።»

ታዲያ አንተ ኋላ ከምድር ስር ሁነህ እንደነርሱ ከምትመኝ፤ ዛሬ ከምድር በላይ ሳለህ አላህ ከሰጠህ 24 ሰዓት ውስጥ 1 ሰዓት እንኳ ለርሱ መስጠት ለምን ከበደህ
ኋላ ከመለደም አስተንትን!
ኋላ ብትጸጸትም ትርጉም የለውም።
3.1K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-13 22:33:18


የአንድ ባራያ ወንጀል የቱንም ያህል ቢገዝፍ
የአሏህ መሃርታ ከባሪያው ወንጀል የበለጠ ግዙፍ ነው !
[ ኢብን ረጀብ ]
°
ወዳጄ ከሰራኸው ወንጀል በላይ
በአሏህ ላይ ተስፋ መቁረጥህ
የበለጠ ዋጋ ያስከፍልሃል ፡፡
°
ምክንያቱም ተስፋ መቁረጥ የሚመነጨው
የአሏህን መሃሪነት ከማስተባበል አልያም
የአሏህን መሃሪነት ካለማወቅ ነውና !
°
ለዚህም ነበረ አባታችን ኢብራሂም ( ዐለይሂ ሰላም ) ከሸበቱና ከጃጁ ወዲያ መላዕክቶች በልጅ ሲያበስሯቸው ...
" قَالَ أَبَشَّرْتُمُونِى عَلَىٰٓ أَن مَّسَّنِىَ ٱلْكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ "
« እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ » አለ ፡፡
[ ሱረቱል ሂጅር 54 ]

የዚህኔ መላዒካዎችም ቀበል አደረጉና
" قَالُوا۟ بَشَّرْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْقَٰنِطِينَ "
« በእውነት አበሰርንህ ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹን » አሉ ፡፡
[ ሱረቱል ሂጅር 55 ]
ከዚያም ደጉ አባታችን ኢብራሂም ( ዐለይሂ ሰላምም ) መለስ አሉና ....

" قَالَ وَمَن يَقْنَطُ مِن رَّحْمَةِ رَبِّهِۦٓ إِلَّا #ٱلضَّآلُّونَ "
« #ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው» አለ ፡፡
°
ተመለከታችሁ ....?
አባታችን ኢብራሂም ( ዐለይሂ ሰላም ) ተስፋ የሚቆርጥ አካል " መንገድ የሳተ ጠማማ ነው " እያሉን ነው ፡፡ ምክንያቱም ይህ አካል የአሏህን ትክክለኛ ማንነትን ( መሃሪነትን ) አላወቀምና ፡፡ የአሏህን ማንነት ያላወቀና አውቆም ያላመነ " መንገድ የሳተ " ይባላል !
°
እናም ............. ተስፋ አትቁረጡ !!
..
3.6K viewsانور فضلأ, 19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-13 15:21:09
ምስክርነት በራስ በቃ
وشهد شاهد من اهلها

ሙፍቲ ኡመር ገነቴ በራሳቸው አንደበት እውነታውን እንዲህ በማለት ይመሰክራሉ

መውሊድን የጀመረው መሊከል ሙዘፈር ነው !!

ትክክለኛው ሱና ሰኞ ሰኞ መፆም ነው

መብላት መጠጣት መሰብሰብ የነብዩ ሱና አደለም

ትክክለኛው ሱና ረሱልን መከተል የፈለገ መሰብሰብ መብላት መጠጣት አደለም ሰኞ ሰኞ መፆም ነው !

እኛም እንጠይቃል ታዲያ የማንን ሱና እንከተል የረሱልን ሱና ወይስ ረሱል ከሞቱ ከ 600 ዓመት በሃሏ የተፈጠረውን ?

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በየሳምንቱ ጁምኣ አደራቹን አዲስ ነገር በዲን ላይ ከመፍጠር ተጠንቀቁ ብለው አላሳሰቡም ለምን የረሱልን ቃል አናከብርም ?

አመት ጠብቆ ተሰብብቦ መብላት ፣ መጠጣት ፣ መጨፈር ይህ የረሱል ሱና ካልሆነ ለምን ይፈፀማል አላህ ያዘዘን ረሱልን አደንድንከተል አይደለምን ?

" የዛኔ (በሰሃባዋች ግዜ) ዲን ያልነበረ ነገር አሁን ዲን ሊሆን አይችልም " ኢማሙ ማሊክ
2.4K viewsانور فضلأ, 12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-07 22:21:49
2.1K viewsYa Allah أعطني الصبر, 19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-07 22:18:41 ‍ ‍ ዐቂቃ ሌላ ለመውሊድ ሌላ!
~ ~ ~ ~ ~ ~~~~ ~
ከዚህ ቀደም እንደገለፅኩት የመውሊድ ጨፋሪዎች የማይገናኘውን ሁሉ ለዚህ የቢድዐ ድግስ ማስረጃ ለማድረግ ሲውተረተሩ ማየት የተለመደ ነው። በዚህ ረገድ ክሚያነሷቸው ከሸረሪት ድር የደከሙ ብዥታዎች ውስጥ አንዱ ነብዩ ﷺ ከነብይነታቸው በኋላ ለራሳቸው “ዐቂቃ አድርገዋል” የሚል ነው። “ህፃን እያሉ አቡ ጧሊብ ዐቂቃ እንዳደረጉላቸው ስለሚታወቅ ይህኛው ልደታቸውን በማስመልከት አላህን ለማመስገንና ለተከታዮቻቸውም ይህንኑ ለማስተማር ያደረጉት እንደሆነ ይታሰባል” ይላሉ በድፍረት።

መልስ፡-

1. በመጀመሪያ ሐዲሡ ብዙሃን ዑለማእ ዘንድ ደካማ ነው። ይህንንም በርካታ ዑለማዎች አስረግጠው ጠቁመዋል። ለምሳሌ፦

1.1. የሐዲሡ ዘጋቢ የሆኑት በይሀቂ እራሳቸው ስለ ሐዲሡም ስለ ሰውየውም እንዲህ ብለዋል፡- “ዐብዱረዛቅ እንዲህ ብሏል፡ ዐብዱላህ ብኑ ሙሐረርን የተውት በዚህ ሐዲሥ ሁኔታ ነው። በርግጥ በሌላ በኩል ከቀታዳ ይዞ፣ በሌላ ደግሞ ከአነስ ዘግቦታል። ነገር ግን እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ውድቅ የሆነ ሐዲሥ ነው።” [አሱነኑል ኩብራ፡ 9/300] ተመልከቱ እንግዲህ ዘጋቢው እራሳቸው በዚህ መልኩ ያጣጣሉትን ጉዳይ ቁም ነገር አርገው የሚጠቅሱት። አንዳንዶቹማ አይናቸውን በጨው አጥበው በይሀቂ ይህንን ሐዲሥ ለመውሊድ ማስረጃ አድርገው ጠቅሰውታል ብለዋል። ይሄ የለየለት ቅጥፈት ነው።
1.2. ሐዲሡን ኢማሙ ማሊክም ደካማ እንዳሉት ኢብኑ ሩሽድ ገልፀዋል። [አልሙቀደማቱል ሙመሂዳት፡ 15/2]
1.3. ኢማሙ አሕመድ ይህንን ሐዲሥ ሙንከር እንዳሉት፣ ሰውየውንም ደካማ እንዳሉት ኢብኑል ቀዪም ገልፀዋል። [ቱሕፈቱል መውዱድ፡ 57]
1.4. ቡኻሪም ሰውየውን “የተተወ ነው” ብለውታል። [ፈትሑል ባሪ፡ 3/348]
1.5. አልበዛርም ሰውየው ደካማ እንደሆነ ገልፀዋል። [ከሽፉል አስታር ሚን ዘዋኢዲል በዛር]
1.6. ነወዊም “(ባጢል) ውድቅ የሆነ ሐዲሥ ነው” ብለዋል። [አልመጅሙዕ ሸርሑል ሙሀዘብ፡ 8/412]
1.7. ዘሀቢም የሐዲሡን አስተላላፊ ዐብዱላህ ብን ሙሐረርን በከባዱ ያብጠለጠሉ ሙሐዲሦችን ከዘረዘሩ በኋላ “ከጥፋቶቹ ውስጥ ከቀታዳ ከአነስ ብኑ ማሊክ ብሎ ነብዩ ﷺ ከተላኩ በኋላ ለራሳቸው ዐቂቃ አድርገዋል ማለቱ ነው።” ይላሉ፡- [ሚዛኑል ኢዕቲዳል፡ 2/500]
1.8. ኢብኑ ዐብዲል ሃዲ ደካማ እንደሆነ ገልፀዋል። [ሪሳለቱን ለጢፋህ፡ 54]
1.9. ኢብኑ ሐጀርም ሐዲሡ ደካማ እንደሆነ ገልፀዋል። [ፈትሑል ባሪ፡ 9/509]
1.10. ኢብኑል ሙለቀንም “ሐዲሡ በጣም ደካማ ነው ምክንያቱም ይሄ ዐብደላህ በምሁራን ኢጅማዕ በጣም ደካማ ነውና” ይላሉ። [አልበድሩ ልሙኒር፡ 9/339]
1.11. ሸውካኢም ዶዒፍነቱን ጠቁመዋል። [ነይሉል አውጣር፡ 5/228]
1.12. አልሙባረክፑሪም እንዲሁ ሐዲሡ ሶሒሕ እንዳልሆነ ገልፀዋል። [ቱሕፈቱል አሕወዚ፡ 5/97]
ይህ ሁሉ ሂስ ከመሰንዘሩም ጋር ሐዲሡን የተወሰነ ዋጋ የሰጡት አጋጥመዋል። ለምሳሌ ሸይኹል አልባኒ።

2. ነገር ግን ሶሒሕ ነው ብንል እንኳን ዛሬ ለሚፈፀመው የቢድዐ መውሊድ ፈፅሞ መረጃ መሆን አይችልም። ምክንያቱም በሐዲሡ የተጠቀሰው ዐቂቃ እንጂ መውሊድ አይደለምና!! ቃል በቃል ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰውን ጥሎ ያለ ተጨባጭ መረጃ በሌለበት “ድሮ አያታቸው ዐቂቃ ስላወጡላቸው ይሄኛው መውሊድ ነው” ማለት ከንፁህ ጥናት ያፈነገጠ ስሜት የተጫነው ድምዳሜ ነው። ከጥንት ጀምሮ ዑለማዎች ይህንን ሐዲሥ ያሰፈሩትና ያጠኑት ቀድሞ ዐቂቃ ያልወጣለት ሰው ኋላ በራሱ መፈፀም ይችላል ወይስ አይችልም በሚል ጉዳይ ላይ እንጂ ፈፅሞ ለመውሊድ አይደለም።

3. የሰነዱ አጠያያቂነት እንዳለ ሆኖ እሳቸው የፈፀሙት በህይወታቸው አንዴ ብቻ ነው። እናንተ መውሊድ ብላቸሁ የምትሰባሰቡት በያመቱ ነው። ምኑን ከምኑ ነው የምታገናኙት?

4. ደግሞስ ዐቂቃ የልደት በዓል ነውንዴ? ሰዎቹ ዐቂቃና መውሊድ አይለዩም ማለት ነው? ዐቂቃኮ አቅሙ የሚችልን ሙስሊም ሁሉ የሚመለከት እርድ እንጂ በነብዩ ﷺ ላይ የተገደበ አይደለም። ለመሆኑ ለህፃናት የሚታረደውን ዐቂቃ መውሊድ ብላችሁ ነው እንዴ የምትጠሩት? ዐቂቃውን የልጆቹን የልደት ቀናቸውን እየጠበቃችሁስ ነው የምትፈፅሙት? አንዴ ካረዳችሁ በኋላ በያመቱስ ነውንዴ የምታከብሩት?

5. ደግሞስ ነብዩ ﷺ ዐቂቃውን የፈፀሙት በልደት ቀናቸው ነው ወይም ረቢዑል አወል 12 ነው የሚለውን ከየት ነው ያመጣችሁት? እንዲህ አይነት ጥቆማ በሌለበት በምን ስሌት ነው ለመውሊድ ማስረጃ የሚሆነው?

6. እውነት እንደምትሉት ነብዩ ﷺ ዐቂቃውን ያደረጉት ተከታዮቻቸው መውሊድን እንዲያከብሩ ለማስተማር ከሆነ ምነው ታዲያ ሶሐቦች እርድ እየፈፀሙ በያመቱ መውሊዳቸውን ሳያከብሩት ቀሩ? መቼም እንደ ሺዐዎች ስላፈነገጡ ነው እንደማትሉ ተስፋ እናደርጋለን። ስላልተመቻቸው ነው ማለት የለየለት ቅጥፈት ነው። ከነብዩ ﷺ ሞት በኋላኮ አንድና ሁለት አመት አይደለም የኖሩት!! ያን ሁሉ ዘመን ሁሉም ሶሐባ አልተመቸውም ይባላል። ሁለቱን ዒዶች ሲያከብሩ አልነበር? ሌሎች ዲናዊ ተግባራትን ሲያከናውኑ አልነበር? እነሱም፣ ታቢዒዮቹም፣ አትባዑ ታቢዒንም፣ የሐዲሥ ምሁራንም፣ አራቱ ኣኢማዎችም አለማክበራቸው ምንድነው የሚያሳየው? “አክብረውትስ ቢሆን ምን አሳወቀን?” እንዳትሉ በነዚያ ነብዩ ﷺ ምርጥነታቸውን በመሰከሩላቸው ትውልዶች ዘመን መውሊድ የሚባል እንዳልነበረ ኢብኑ ሐጀር፣ ሰኻዊ፣ ሲዩጢ፣ ዒራቂ፣ ተዝመንቲ፣... መናገራቸውን አሳልፌያለሁ። ፈርተው ነው ያልፈፀሙት ማለትም አይን ያወጥዐ ቅጥፈት ነው። ምክንያቱ አንድና አንድ ብቻ ነው። መውሊድ የሸሪዐ መሰረት ስለሌለው ብቻ! ይህ ነው እነሱ ጋር የነበረው ግንዛቤ!! እንጂ የሸሪዐ መሰረት ቢኖረው ኖሮ ለእምነታቸው ሲሉ አገር ንብረታቸውን ጥለው የተሰደዱ፣ ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ፣ ከስጋ ዘመዶቻቸው ጋር የተሞሻለቁ፣ በሕቅ ላይ የወቃሽን ወቀሳ የማይፈሩ፣ የጀኝነት፣ የቆራጥነት፣ የተቅዋ፣ ... ተምሳሌቶች ናቸው። ለነብዩ ﷺ የነበራቸውም ወዴታ ወደር አልነበረውም። በጭፈራ ሳይሆን በተግባር የሚገለፅ ነበር። ከሳቸው በመከላከል ለነፍሶቻቸው ሳይሰስቱ እራሳቸውን ፊዳ በማድረግ ደረታቸውን ለቀስት የሚሰጡ የተመረጡ ትውልዶች ናቸው። ይልቅ በተዘዋዋሪም ቢሆን አጉል ከነሱ በላይ ነብዩን ﷺ እንወዳለን ከሚመስል እብሪት ብትርቁ ይሻላችኋል።
~~

ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/alazkare
https://t.me/alazkare
1.6K viewsYa Allah أعطني الصبر, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-30 22:38:00 ያቁት አልሐመዊ ከሙዞፈር ጋር አንድ ዘመን የኖሩ በመሆናቸው ዘግይተው መጥተው ስለ ንጉሱ አድናቆት ብቻ ከሰፈሩ ፀሐፊዎች በተሻለ ምስክርነታቸው ሚዛን የሚደፋ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ሙዞፈር ፃድቅ እንኳ ቢሆን፣ አይደለም እንጂ መውሊድ በሱ የተጀመረ ቢሆን እንኳ ይሄ ከቢድዐነት አያወጣውም፡፡ ከነቢዩ - ﷺ - ህልፈት በኋላ ስድስት መቶ አመታት ዘግይቶ የሚጀመር አዲስ ፈሊጥ ጥመት እንጂ ፈፅሞ ፅድቅ ሊሆን አይችልም፡፡ እምነታችን ከቁርኣንና ከሐዲሥ የሚቀዳ እንጂ እንደ ሌሎች እምነቶች ማንም እየተነሳ አዳዲስ ነገሮችን የሚለጥፍበት አይደለም፡፡

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
(ጥቅምት 08/2013)
የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋብዙ።
1.4K viewsሰኢድ የእናቱ ልጅ 🅂🄴🅈🄰 🄼🄴🄽, 19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-30 22:38:00 መውሊድ በማን ተጀመረ? በሙዞፈር ወይስ በ“ፋጢሚያ” ሺዐ?
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ሰሞኑን አሕባሾች መውሊድን በማስተዋወቅ ላይ ተጠምደው እያየን ነው። ከሚያነሷቸው ነጥቦች አንዱ መውሊድ “ታላቅ ዓሊም፣ ተቂይ፣ ሷሊሕና ጀግና በነበሩት” ንጉስ ሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚል ነው። ሙዞፈር የሞተው ከ812 አመት በፊት በ630 ሂጅሪያ ነው። ሰዎቹ ሙዞፈር ላይ ችክ የሚሉት እጅግ አፈንጋጭ በሆኑት “ፋጢሚያ” ሺዐዎች ነው የተጀመረው የሚለውን ለመሸሽ ነው። እርግጥ ነው መውሊድ የተጀመረው በሙዞፈር ነው ያሉ አሉ። ሌሎች ደግሞ የለም ትንሽ ቀደም ብሎ በሸይኽ ዑመር አልመላ (571 ሂ.) ነው የሚሉም አሉ። ሁለቱም ሃሳቦች ግን በማንም - እደግመዋለሁ - በማንም ቢጠቀሱ ፈፅሞ ስህተት ናቸው፡፡ ምክንያቱም ከዚያ በፊት በአፈንጋጭ ሺዐዎች እንደተጀመረ የሚያሳዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች አሉና፡፡ ማስረጃ ከቀረበ በኋላ ለማንም ሙግት እጅ አንሰጥም፡፡ ለሐቅ እጅ ለሚሰጡ፣ ከመንጋዊ አስተሳሰብ አግልለው ህሊናቸውን ለሚያከብሩ ሰዎች ብቻ ማስረጃዎቹን አሰፍራለሁ።

1. ኢብኑል መእሙን (587 ሂ.):—

በታሪክ ድርሳናት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መውሊድ ተጠቅሶ የተገኘው በኢብኑል መእሙን ስራ ነው። የኢብኑል መእሙን አባት የ“ፋጢሚያ” ንጉስ ከፍተኛ ባለሟል ነበር። የታሪክ ፀሐፊው አልመቅሪዚ (845 ሂ.) ኢብኑል መእሙንን በማጣቀስ በ517 ሂጅሪያ የተካሄደውን መውሊድ አስመልክተው እንዲህ የሚል መረጃ አስፍረዋል፡-
“የ‘ፊጢሚያ’ ገዢዎች በዓላትና ለተገዢዎቻቸው ነገሮችን ሰፋ የሚያደርጉባቸው እንዲሁም ችሮታ የሚበዘባቸው ዓውደ-አመታት” ካሉ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- ለፋጢሚያ ገዢዎች በአመቱ ውስጥ በዓላትና ዓውደ አመታት አሏቸው። እነሱም … የዓሹራእ ቀን፣ የነብዩ - ﷺ - ልደት (#መውሊድ) ቀን፣ የዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ ልደት ቀን፣ የሐሰን የልደት ቀንና የሑሰይን የልደት ቀን (ሰላም በነሱ ላይ ይሁንና)፣ የፋጢመቱ ዘህራእ ዐለይሃ ሰላም ልደት ቀን፣ ስልጣን ላይ ያለው ገዢ የልደት ቀን፣ … የገዲር ዒድ (የሺዐዎች ነው)” እያሉ ይዘረዝራሉ። ከውስጣቸው የፋርስ መጁሳዎች፣ የሺዐና ከክርስትና ደግሞ እንደ ገና እና ትንሳኤ ያሉ በዓላት የተካተቱበት ሲሆን ባጠቃላይ 28 በዓላት ናቸው የተዘረዘሩት። [አልኺጦጥ፡ 1/436]
መውሊድ ከምን አይነት በዓላት ጋር እንደተጀመረ ተመልከቱ። በሌላ ኪታባቸው ላይም “በረቢዐል አወል ላይ (የ“ፋጢሚዮቹ” ንጉስ) ሌሊት ላይ በጎዳናዎችና መንገዶች ላይ ጧፎች እንዲበሩ ያስገድድ ነበር” ይላሉ። [ኢቲዒዙል ሑነፋእ፡ 2/48] ሌላ ቦታ ደግሞ “ረቢዐል አወል ላይ የነብዩን - ﷺ - ክቡር ልደት መፈፀም ብሄራዊ ልምድ ሆኖ ቀጠለ” ይላል። [ኢቲዒዙል ሑነፋእ፡ 3/101] ልብ በሉ! ይህንን መረጃ የሰጠን ኢብኑል መእሙን የሞተው መውሊድን ጀመረ የሚባለው ንጉስ ሙዞፈር ገና በተሾመ በአመቱ ነው፡፡ እያስተዋላችሁ!!

2. ኢብኑ ጡወይር (617 ሂ.):—

ሌላኛው መውሊድን ከ“ፋጢሚዮች” ጋር በማያያዝ የጠቀሰው ጥንታዊ የታሪክ ፀሐፊ ኢብኑ ጡወይር ነው። ኢብኑ ጡወይር ለነዚህ “ለፋጢሚያ” መንግስት ፀሐፊ ሆኖ አገልግሏል። ኋላ በሶላሑዲን አልአዩቢ ሲደመሰሱም በአይኑ ተመልክቷል። በዚህኛው ስርኣትም ውስጥ ዳግም አገልግሏል። በ“ፋጢሚያዎች” መንግስት ስለሚዘጋጀው መውሊድና ስለተትረፈረፈ ምግቡ “ኑዝሀቱል ሙቅለተይን ፊ አኽባሪ ደውለተይን” በተባለ ኪታቡ ላይ በዝርዝር አትቷል። “ማን ያውራ የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ” ይላል ያገራችን ሰው። ለናሙና ያክል ቀንጨብ ላድርገው፡-
ذكر جلوس الخليفة في الموالد الستة في تواريخ مختلفة، وما يطلق فيها، وهي مولد النبي صلى الله عليه وسلم، ومولد أمير المؤمنين علي بن أبي طالب، ومولد فاطمة عليها السلام، ومولد الحسن، ومولد الحسين عليهما السلام، ومولد الخليفة الحاضر
“ኸሊፋው በተለያዩ ጊዜያት በስድስቱ መውሊዶች ላይ የሚያደርጋቸውን መስሰየምና ምን ተብለው እንደሚታወቁ ማውሳት፡- እነሱም የነብዩ- ﷺ - መውሊድ፣ የአሚረል ሙእሚኒን ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ መውሊድ፣ የፋጢማ ዐለይሃ ሰላም መውሊድ፣ የሐሰን መውሊድ፣ የሑሰይን - ዐለይሂመ ሰላም - መውሊድና የዘመኑ ኸሊፋ መውሊድ ናቸው፡፡ …” [ኑዝሀቱል ሙቅለተይን፡ 217-219]

3. አሕመድ ብኑ ዐሊይ አልቀልቀሸንዲ (821 ሂ.):—

ስለ “ፋጢሚያ” መሪዎች ጉባዔ ሲያወሩ “ሶስተኛው ጉባዔ በረቢዐል አወል ወር 12ኛ ቀን ላይ በነብዩ - ﷺ - መውሊድ ላይ የሚኖረው ጉባዔ ነው” ካሉ በኋላ ዝርዝር አፈፃፀሙን ይተርካሉ፡፡ [ሱብሑል አዕሻ፡ 3/576]

ስናጠቃልል የመውሊድ በዓል ጀማሪዎች “ፋጢሚያ” ሺዐዎች እንደነበሩ ለጥርጣሬ ቀዳዳ የማይሰጡ መረጃዎች አሉን ማለት ነው፡፡ ልብ በሉ! የመጨረሻው የ“ፋጢሚዮች” ንጉስ አልዓዲድ ሊዲኒላህ የሞተው በ 567 ሂጅሪያ ነው፡፡ ሱፍዮች “መውሊድ ጀመረ” የሚሉት ሙዞፈር የተሾመው ደግሞ ከ 19 ዓመታት በኋላ በ586 ሂ. ነው፡፡ ይህንን ተጨባጭ ታሪካዊ መረጃ እያየ “አይኔን ግንባር ያርገው” የሚል ካለ የለየለት ቂላቂል ነው፡፡ መውሊድ በሺዐዎች እንደተጀመረ የሚጠቁሙ ግልፅ ማስረጃዎች እየቀረቡ እያዩ “እከሌ እንዲህ ብለዋል” “እንቶኔ እንዲህ ብለዋል” እያሉ ነገር መዘብዘብ እራስን መሸወድ ብቻ ነው፡፡
“ሙዞፈር ነው የጀመረው” ያሉት እንደ ሲዩጢ ያሉ የኋለኛው ዘመን ሰዎች ከመሆናቸውም በላይ ያጣቀሱት ተጨባጭ ማስረጃ የለም፡፡ በነገራችን ላይ እነዚህ መውሊድ በሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚሉ አካላት ኢብኑ ከሢርን ሲያጣቅሱ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ኢብኑ ከሢር የሙዞፈርን መውሊድ ከመጥቀሳቸው ውጭ “ጀማሪ ነው” አላሉም፡፡
መቅሪዚ እንደጠቀሱት እነዚህ የሺዐዎቹ መውሊዶች ኋላ ላይ ለተወሰኑ ጊዜያት ተቋርጠው ነበር፡፡ [አልመዋዒዝ ወልኢዕቲባር፡ 1/432] ኋላ ላይ በተተካው የ“ፊጢሚዮቹ” ንጉስ አልኣሚር ቢአሕካሚላህ (524 ሂ.) ነው የተጀመሩት፡፡ ልብ በሉ! ይህ ዳግም የተጀመረው መውሊድ እራሱ ከሙዞፈር መውሊድ በዓል ብቻ ሳይሆን ከራሱ ሙዞፈር መወለድም የቀደመ ነው፡፡
በነገራችን ላይ ሱፍዮች መውሊድን ጀመረ የሚሉትን ሙዞፈርን ቅዱስ አድርገው የሚጠቅሱት ወይ ታማኞች ስላልሆኑ ነው፡፡ ወይ ደግሞ በሰውየው ላይ የቀረቡ ሂሶችን ያልተመለከቱ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ የሚያደርጉት ለገበያቸው የሚሆናቸውን እየመረጡ ማቅረብ ነው፡፡ ንጉሱ በከፊል የታሪክ ፀሐፊዎች ከመወደሱም ጋር የሰላ ሂስ የሰነዘሩበትም አሉ፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡-
ያቁት አልሐመዊ ይባላሉ፡፡ በ626 ሂ. የሞቱ ታዋቂ የታሪክ ምሁር ናቸው፡፡ ሙዞፈርን አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡-
“የዚህ ሰውየ ባህሪ እርስ በርሱ የሚቃረን ነው፡፡ እሱ ሲበዛ በዳይ፣ ህዝቦቹ ላይ ጨካኝ እንዲሁም አግባብ ባልሆነ መልኩ ገንዘቦችን የሚወስድ ነበር፡፡ ይህ ከመሆኑ ጋር ለድሃዎች የሚቸርና ለእንግዶች በብዛት የሚሰድቅ ነበር፡፡ እጅግ በርካታ ገንዘቦችን አፍስሶ ከከሃዲዎች እጅ ምርኮኞችን ነፃ ያወጣ ነበር፡፡ በዚህ ላይ ባለቅኔው እንዲህ ይላል፡-

‘ልክ እንደዚያች ወጥ ረገጥ
በብልቷ ነግዳ ለበጎ ስራ የምትሮጥ
መስሚያ ካለሽ ወዮ ላንቺ!
ምፅዋትሽ ይቅር ይልቅ አትዘሙቺ፡፡’ ” [ሙዕጀሙዑል ቡልዳን፡ 1/138]
1.3K viewsሰኢድ የእናቱ ልጅ 🅂🄴🅈🄰 🄼🄴🄽, 19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 19:43:30
«ልጄ ሆይ! ተውበትን አታዘግይ። ሞት በእርግጥም በቅፅበት ይመጣል።»
(ሉቅማን ለልጁ የመከረው ምክር)

[አ-ት'ተብሲራህ ሊብኒ-ል-ጀውዚይ: 34
1.6K viewsانور فضلأ, 16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ