Get Mystery Box with random crypto!

ሐራምን መዳፈር ኢስላም በማያሻማ መልኩ ከደነገጋቸው ህግጋቶች አንዱ የምስል ወይም ፎቶ ሐ | አል አዝካር AL AZKAR

ሐራምን መዳፈር

ኢስላም በማያሻማ መልኩ ከደነገጋቸው ህግጋቶች አንዱ የምስል ወይም ፎቶ ሐራምነት ነው ። ዛሬ ተውሒድ እናስተምራለን የሚሉ ወንድሞች ጭምር እየተዳፈሩትና እንደ ቀላል እያዩት ቻናላቸው የምስል ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ እስከሚመስል ድረስ የሴትና የወንድ ምስል ወይም የሚደንሱ ሴቶችን ምስል ማዥጎርጎሪያ እያደረጉት ነው ። ይህ ተግባር ሸሪዓን የሚፃረር የምናስተምረውን ተውሒድ የሚነካ ወደ ሽርክ የሚያዳርስን ሙንከር ማሰራጨት በመሆኑ አላህን ልንፈራ ይገባል ። ፎቶም ሆነ ምስል በየትኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑ የሰዎች ኢጅቲሃድ ሳይሆን ከልብ ወለዳቸው ከማይናገሩት የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – በወሕይ አማካይነት ለቁጥር በሚያታክቱ ሐዲሶች የተረጋገጠ ነው ። የተኛውም ምስል ይቻላል የሚል ዓሊም ምንም ነብያዊ ማስረጃ የለውም ። ምናልባት ደሩራ ነው የሚል ነው የሚሆነው ። ያ ደግሞ በደሩራው ልክ የሚታይ ነው ። የትኛውም አማኝ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ሲባል ሸኽ እገሌ እንዲህ ብለዋል ሊል አይገባም ። ይህን በተመለከተ የሰለፎችን ንግግር እንመልከት : –
قال ابن عباس – رضي الله عنه – :
" يوشك أن تنزل عليكم حجارة من السماء ، أقول: قال: رسول الله – صلى الله عليه وسلم – وتقولون : قال أبو بكر وعمر؟ "
أخرجه الإمام أحمد ( 3121 )
ዐብዱላሂ ኢብኑ ዓባስ እንዲህ አሉ: – ከሰማይ የድንጋይ ናዳ ሊወርድባችሁ የደረሰ ይመስላል , የአላህ መልእክተኛ ብለዋል እያልኳችሁ አቡበከርና ዑመር ብለዋል ትላላችሁን ? !!!!!!
ሱብሃናላህ ኢብኑ ዓባስ ዑመርና አቡበከር ብለዋል ስለተባሉ ነው ይህን ያሉት ። ባዮቹ መረጃውን ባለማወቃቸው ነው እንጂ የተነሳው የተመቱዕ መስአላ መረጃ የሌለው ሆኖ አይደለም ። ነገር ግን ከኢብኑ ዓባስ ጋር የተነጋገሩት መረጃውን ሳያቀርቡ አቡበከርና ዑመር ብለዋል ማለታቸው ነው ያስቆጣው ። አቡበከርንና ዑመርን እንድንከተል ታዘን እያለ ። ነገር ግን ነስ ከመጣ መቆም ግዴታ መሆኑን ለመግለፅ ነው ።
ሌላው አሰር እንዲህ ይላል : –
قال الإمام أحمد : عجبت لقوم عرفوا الإسناد وصحته ، ويذهبون إلى رأي سفيان ، والله تعالى يقول:
{ ۚفَلْيَحْذَرِ الَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنْ أَمْرِهِ أَن تُصِيبَهُمْ فِتْنَةٌ أَوْ يُصِيبَهُمْ عَذَابٌ أَلِيم ٌ}
النور ( 63 )
أتدري ما الفتنة ؟ الفتنة الشرك . لعله إذا رد بعض قوله أن يقع في قلبه شيء من الزغ فيهلك .
ኢማሙ አሕመድ እንዲህ ይላል : –
" የሰዎች ሁኔታ አስደነቀኝ ( አስገረመኝ) ሐዲስን ሶሒህነቱ ቃወቁ በኋላ ወደ ሱፍያን አስሰውሪ ረእይ ይሄዳሉ , አላህ እንዲህ እያለ
" እነዚያም ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ ፡፡"
ፈተና ( መከራ ) ማለት ምን እንደሆነ ታውቃለህን ? ፈተና ማለት ሽርክ ነው ። የነብዩን ከፊል ንግግር ከመለሰ በልቡ ላይ አንዳች ጥመት ይከሰትና እንዳይጠፋ ይፈራል "
ይህ ማለት ሐዲስ መጥቶለት እገሌ እንዲህ ብሏል ከሚል ሰው ጋር ሰለፎች የነበራቸው አቋም ነው ።
አሁን የአላህ መልእክተኛ በፎቶና ምስል ዙሪያ ከተናገሯቸው ሐዲሶች ጥቂቶቹን እንመልከት : –
روى البخاري ومسلم عن عائشة عن رسول الله صلى الله عليه وسلم أنه قال : «أشدّ الناس عذاباً يوم القيامة الذين يضاهئون بخلق الله "
ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡትና እናታችን ዓኢሻ ባወራችው ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ትላለች : –
" የቂያማ ቀን ብረቱ ቅጣት የሚያገኘው እነዚያ በአላህ አፈጣጠር የሚያመሳስሉ ናቸው "
روى البخاري ومسلم وأصحاب السنن أن النبي صلى الله عليه وسلم قال :
«إن اصحاب هذه الصور يعذبون يوم القيامة، يقال لهم: أحيو ما خلقتم».
ቡኻሪና ሙስሊም እንዲሁም የሱነን ባልተቤቶች በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላሉ: –
" የእነዚህ ምስል ባልተቤቶች የቂያማ ቀን ይቀጣሉ, የፈጠራችሁትን ህያው አድርጉ ይባላሉ "
روى البخاري ومسلم والنسائي عن ابن عباس رضي الله عنهما أن رجلاً قال له: إني أصوّر هذه الصور فأفْتني فيها، فقال له: ادن مني فدنا، ثم قال: ادن مني فدنا، حتى وضع يده على رأسه وقال: إنبئك بما سمعت من رسول الله صلى الله عليه وسلم، سمعته يقول: «كلّ مصوّر في النار، يُجعل له بكل صورة صوّرها نفس فيعذب به في جهنم».
وفي رواية أخرى عنه: سمعته يقول:
«من صوّر صورة فإنّ الله يعذبه حتى ينفخ فيها الروح وليس بنافخ فيها أبداً»
ቡኻሪና ሙስሊም እንዲሁም ኢማሙ ነሳኢ በዘገቡትና ዐብዱላሂ ኢብኑ ዓባስ ባወሩት ሐዲስ አንድ ሰው ለኢብኑ ዐባስ እንዲህ አላቸው እኔ ይህን ምስል እስላለሁ እስኪ ፈትዋ ስጠኝ ። ኢብኑ ዐባስም ወደኔ ቅረብ አለው ቀረበ አሁንም ቅረብ አለው ቀረበም እጁ በጭንቅላቱ ላይ እስከሚያደርግ ድረስ ከዛም ከአላህ መልእክተኛ የሰማሁትን እነግርሃለሁ አለው ። የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ : –
" ምስል የሚስል ሁሉ የእሳት ነው ። በየአንዳንዱ የሳለው ምስል ነፍስ ይደረግለታል በሱም በጀሀነም ይቀጣል ። " በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ እንዲ ብለዋል
" አንድን ምስል የሳለ ሰው ሩሕ እስከሚነፋበት ድረስ አላህ ይቀጣዋል ። እስከመጨረሻውም ሩሕ የሚነፋ አይደለም "
እነዚህ ሐዲሶች ከብዙ በጥቂቱ ናቸው ። እንደምታዩት እንደ ጠዋት ፀሀይ ፍንትው ብለው የሚታዩ የፎቶ ወይም ምስል በየትኛውም መልኩ ክልክልነት የሚያረጋግጡ ሲሆኑ እነዚህን ሐዲሶች ትቶ ከስሜት ጋር የሚሄድ የዑለማዎች ንግግር መፈለግ የሰለፍዮች መገለጫ አይደለም ። በተለይም ወደ ተውሒድ የሚጣራ ሰው የዚህ ዛቻ ማረፈያ የሆነውን ምስል ከማሰራጨትና ሐላል ነው ብሎ ከመሞገት ሊቆጠብ ይገባል ። እንኳን እንዲህ አይነት መረጃ የመጣበትን ጉዳይ አይደለም የሚያጠራጥር ነገር ከሆነ እንኳን መጠንቀቁ የዲንንም የራስንም ክብር መጠበቅ ነው ። አላህ ከስሜት ወጥተን ሐቅን የምንከተል ያድርገን ።