Get Mystery Box with random crypto!

አል አዝካር AL AZKAR

የቴሌግራም ቻናል አርማ seid_islamic — አል አዝካር AL AZKAR
የቴሌግራም ቻናል አርማ seid_islamic — አል አዝካር AL AZKAR
የሰርጥ አድራሻ: @seid_islamic
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ብዙ ማዉሳትን አዉሱ።{አል አህዛብ፥41}
"አላህ አዋቂም ጥበበኛም ነው"🎨
☞ ኢስላም በራሱ ውበት ነው ፣ ጥበብም ነው።
♢አላህም ቆንጆ የሆኑ ነገሮቸን ሁሉ ይወዳል በሀዲስ ላይ ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዳሰፈሩት:-
 ❤“.. إن الله جميل يحب الجمال ..”♥ ☞
-
-
-
-
-

♡"ያ ረብ ለሰጠከኝ ፀጋ ሁሉ አመሰግናለሁ!"

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-09-29 19:40:39 “መውሊድ”፣ “ክሪስማስ”፣ አሹራ….?
***************************************
ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው በላይ አውቀው ነው ወይ?
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ነብይ ተደርገው በተላኩ ጊዜ ነሷራዎችም (ክርስትያኖች) ይሁዳዎችም ነበሩ፡፡ ነሷራዎች የኢሳንም ልደት ሲያከብሩ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የወንድማቸውን ኢሳ ልደት አንድም ቀን አክብረው አያውቁም፡፡ ምክንያቱም በአላህ አልታዘዙምና፡፡ የነብይም ይሁን የሌላ ግለሰብ የልደት በዓል ማክበር የነብያቶች እምነት እስልምና በፍፁም የሚያውቀው አይደለም፡፡ ልደት ማክበር የእስልምና አካልም አይደለም፡፡በሌላ በኩል ሌላኛው ወንድማቸው ነብየላህ ሙሳን (አለይሂ ሰላም) አስመልክቶ የሁዳዎች አሹራን ሲፆሙ አዩ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሁዳዎችን ለምን እንደሚፆሙ ጠየቁ “አላህ ሙሳን እና የእስራኢል ልጆችን ከፊርዐውን ነፃ ያወጣበት ቀን ነው” ሲሉ መለሱላቸው፡፡ ነብዩም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “እኛ በሙሳ ጉዳይ ከናንተ የበለጠ የተገባን ነን” ብለው አሹራን ፆሙ እንዲፆምም አዘዙ፡፡ እንዲያውም ረመዳን ከመደንገጉ በፊት አሹራ በሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነበር፡፡ ከረመዳን በኋላ ይሀው እኛም የሳቸውን ፈለግ በመከተል እንፆመዋለን፡፡ ልክ እንደዚሁ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ሰኞ ለምን እንደሚፆሙ” ሲጠየቁ “የተወለድኩበት ቀን ስለሆነ እና ቁርዐን እኔ ላይ የወረደበት ቀን ስለሆነ ነው” ብለዋል፡፡ ታድያ ግዴታ ያልሆነ የሱና ፆም አሹራን በአመት አንዴ እንድንፆመው፣ እሳቸው የተወለዱበትን ቀን እና ቁርዓን የወረደበትን ቀን ሰኞ እንዲሁ በሳምንትን አንዴ ሱና ፆም እንድንፆም ነግረውናል፡፡ የሚያሳዝነው አብዛኛው “መውሊድን” አከብራለሁ የሚል ሰው የታዘዘውን በየሳምንቱ የሚፆመውን ሱና ሲፆም አይታይም፡፡ ይልቁንስ ለምሳሌ “የኢስነይን ሰዎች ነን” እያሉ ሰኞ ሰኞ ጉንጫቸውን በአንደንዛዡ ቅጠል ጫት ወጥረው ሲቅሙ እና ሲጨፍሩ የሚውሉ ሸይጧን የተጫወተባቸው አሉ፡፡ በአመት አንዴ ግን ያልታዘዙትን “መውሊድ” ብለው በማክበር “የኢሳ ልደት” ብለው ከሚያከብሩት ሰዎች ጋር ተመሳስለዋል፡፡ የታዘዙትን ትተው ያልታዘዙትን በመስራት ወደ አላህ እዝነት ሳይሆን ቁጣውን ወደሚያከናንባቸው የሰይጣን መንገድ የሚንደረደሩ ሰዎች ምን አለ ቆም ብለው ቢያስቡ?
አላህ እኮ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) በመከተል እንጂ ውዴታውን እና ምህረቱን ቃል የገባልን ያላዘዙትን በመስራት አይደለም፡፡ ሸይጧን ደግሞ እንዲህ አሳቢ መስሎ ነው ከጥንት እስከዛሬ ሰዎችን ሲያጠም የነበረው፡፡ አላህ ከተንኮሉ ይጠብቀን፡፡
ሌላው ሰሃባዎች አላህ አማኝ፣ እውነተኞች፣ ወድጃቸዋለሁ እያለ ያወደሳቸው….. ከነሱ መንገድ ውጭ ያለን የሚከተል መንገድ የሳተ፣ ጀሀነምም እንደሚገባ አላህ እና መልክተኛው ነግረውን ሲያበቁ፡፡ ለምን ይሆን መውሊድንም ይሁን ሌሎች ተግባራትን በተመለከተ ሰሃባዎች የቆሙበት ቦታ የማንቆመው?
ሰሃባዎች ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በህይወት በነበሩ ግዜም ይሁን ሞተው አንድም ቀን የማንንም ነብይ ይሁን የረሱልን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደት አክብረው አያውቁም፡፡
ታድያ እኛ ማን ሆነን ነው ሰሃባዎች ያልሰሩትን የምንሰራው? የአላህን ዲን፣ ንፁሁን የነብዩ ሱና በቢድዐ ለማቆሸሽ፣ የሰይጣንን ተልኮ “ነብዩን መውደድ” በሚል ስም ለማሳካት ደፋ ቀና የሚባለው?
እውነት ሰሃባዎች ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሳይወዱ ቀርተው ነው የነብዩን መውሊድ ያላከበሩት?
ወይንስ እነሱ ለነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላቸው ውዴታ ሸሪዐ በደነገገው መልኩ በገንዘብ፣ በህይወት መስዋትነት እና በሌላም ስለገለፁ ነው?
እውነታው እነሱ ስለስርዐት አላቸው፡፡ ይህንን ከሰማይ የወረደ ዲን “እኔ እንደሚመስለኝ” እያሉ ሳይዳፈሩ ያንን ንፁህ ምንም ጭማሪ የማይፈልግ ዲን ለእኛ በሰላም አድርሰዋል፡፡ አላህም ወዷቸዋል፡፡ ዛሬ አላህ ዘንድ ገና ፍርድ ያልተሰጠባቸው ሰዎች ይህን ዲን መጥተው በፈለጉ ጊዜ በቀያየሩት ቁጥር እኛ አብረን የምንቀያየረው አላህን ነው የምናመልከው ወይንስ እነዚህ አላህ ያልደነገገውን የሚደነግጉ ዲን አፍራሾች?
መውሊድ የሸሮች ሁሉ መጠራቀሚያ፣ የሙስሊሞችን አንድነት ማፍረሻ፣ የድሆችብ ንብረት መብያ….. እርኩስ ተግባር ነው፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! ራቁት፡፡
አይ ሸይጧን በየዘመኑ መጥፎውን ነገር ጥሩ አስመስሎ ስም እየቀያየረ የአደም ልጆችን ያጠማቸዋል፡፡ ወደ እሳትም ይመራቸዋል፡፡ ተመልከቱ አደም እና ሀዋን ያቺን ዛፍ ስሟን አሳምሮ እንዳትበሉ የተባሉትን አስበላቸው ከዛም ስህተት ውስጥ ጣላቸው፡፡ የኑሕን (አለይሂ ሰላም) ህዝቦች በሞቱት 5 ደጋግ ሰዎች ያዘነ መስሎ መቀማመጫቸው ላይ ሀውልት አሰርቶ ገደል ከተታቸው፡፡ የጠፉበትን እርኩስ ተግባር ሽርክ ውስጥ ዘፈቃቸው፡፡ አሁንም ይህን ኡመት “ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላችሁን ውዴት ልደቱን አክብሩለት” የሚመስል የሰይጣን ሹክታ እዚህ ኡማ ላይ ተሰራጭቶ የሽርክ መነሃርያ የሆነውን መውሊድ እያከበሩ ወደ እሳት ሲነዱ ይታያሉ፡፡ መውሊድ ላይ ከባባድ የሽርክ ቃላትን ከእስልምና አስፈንጥረው የሚያስወጡ የሽርክ ተግባራት ይታያሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ አላህን ትቶ ፍጡራንን መለመን፣ እነሱን ድረሱልን ብሎ መጣራት፣ አላህን ትቶ ለፍጡራን ስለት መግባት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
አሳዛኙ ደግሞ ጥመቱን እንደሃቅ፣ ሃቁን እንደ ጥመት ቆጥረው “ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ሰሀባዎቻቸው፣ ታቢኢኖች፣ አትባኡታቢኢን፣ 4 አኢማዎች፣ ሙሐዲሶች፣ 3 ምርጥ ክፍለ ዘመን እና ትውልድ አላከበረውም” ሲባሉ ሃቁን ከመቀበል ይልቅ ያልታዘዝነውን አንሰራም ያሉትን “ነብዩን የማይወዱ፣ የነብዩ ጠላቶች፣ ወሃብዬች እና ሌላም” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡
ከድጡ ወደ ማጡ ይሉሃል ይህ ነው፡፡ ሸይጧን ግን ዛሬ ጥፋታቸውን እያሸበረቀላቸው ዲንን በዲን ስም እንዲንዱ እየገፋፋቸው ነው፡፡
ነሷራችን በነብየላህ ኢሳ (አለይሂ ወሰለም) ላይ ድንበር አልፈው “የአላህ ልጅ ነው” እንዲሉ ያደረጋቸው የሰው እና የጂን ሰይጣናት ናቸው፡፡ ነሷራች ኢሳን ድንበር ያለፉበት ጠልተውት ሳይሆን ወደውት ነው፡፡ ግን ድንበር አለፉ፡፡ ከልክ በላይ ከፍ ከፍ አደረጉት፣ ያላታዘዙትን ልደቱን አከበሩለት፡፡ ከዚህም ኡማ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመውደድ ስም ሸይጧን መንገድ አስቷቸው ልክ እንደነሷራች ያልታዘዙትን ልደት ማክበር፣ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “መጣ ያለፈው ወንጀላችንን ማረ”፣ “የሁሉ ቀላቢ”፣ “ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ” እና የመሳሰሉትን የብቸኛ ፈጣሪና ተመላኪ አላህ መብት አሳልፈው ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመስጠት ታላቁን ማጋራት እና ቢድዐ ሲሰሩ ይታያል፡፡
ሸይጧን መቼም ለሰው ልጎች ከባድ ጠላታቸው ነው፡፡ አላህ ድንበር ከማለፍ፣ ከሽርክ፣ ከቢድዐ እና አላህ ከጠላው ሁሉ ይጠብቀን፡፡ አላህ ወደ ተውሒድ፣ ሱና፣ የሰለፉነ ሷሊሂን አረዳድ፣ እሱ መልካም ወዳለው ሁሉ ይምራን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
1.6K viewsانور فضلأ, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-27 21:01:27 ጥናተ መንዙማ ክ 3
1.5K viewsانور فضلأ, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-27 20:07:00 ነብዩን አትወዳቸውም?
1.4K viewsانور فضلأ, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-25 17:57:57 ማን ነው የከፋው?
አንዳንድ ሰዎች መውሊድ በኢስላም የሌለ የፈጠራ መንገድ ነው፡፡ መውሊድ ሸር ነው፡፡ ኸይር ቢሆን ኖሮ አላህ እና መልክተኛው ይደነግጉልን ነበር፡፡ ሰሃባዎች፣ ታቢእዬች፣ አትባኡ ታቢኢን፣ አራቱ አኢማዎች ፉቀሃዎች (አቡ ሀኒፋ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ ኢማሙ ሻፊኢይ፣ ኢማሙ አሕመድ)፣ ሙሐዲሶች (ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ ነሳኢ፣ አቡ ዳውድ ኢብን ማጃእ…..) ያውቁት ነበር፡፡ እነዚህ ሁሉ ምርጦች አያውቁትም ሲባሉ እሺ አናከብርም ፈጠራ ስለሆነ ከማለት ፋንታ “በሳቸው መወለድ ሰይጣን እና ወሃቢ ብቻ ነው ያለቀሱት” ሲሉ እየተደመጡ፣ ሲፅፉም እየታዩ ነው፡፡
እውነታው በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መወለድ የመካ ሙሽሪኮች አልተቆጡም ነበር፡፡ የመካ አጋሪያን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ከነብይነት በፊት “ሙሐመዱል አሚን (ታማኙ ሙሐመድ)” እያሉ ነበር የሚጠሯቸው፡፡ ነብይ ሆነው “ህዝቦቼ ሆይ! ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ የለም በሉ ትድናላችሁ” ሲሉ የመጀመሪያው ጠላታቸው በሳቸው መወለድ አይደለም ሊቆጣ ተደስቶ የነበረው አቡ ለሃብ “እልም ያድርግህ ለዚህ ነው ወይ የሰበሰብከን” ሲል ግልፅ ጥላቻውን ይፋ አደረገ፡፡ ከዛም አጋሪያን ታማኙ ሙሐመድ እንዳላሉ “ድግምተኛ፣ እብድ፣ አባትና ልጅን የሚለያይ፣ ገጣሚ….” እያሉ ይሰድቧቸውና ስማቸውን ያጠፉ ጀመር፡፡ አለ የሚባል ሁሉ ፈተና ደረሰባቸው፡፡
ጥያቄ አለኝ ሰሃባዎች መውሊድን አላከበሩም ነበር ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ስለሚጠሉ ወይንም በሳቸው መወለድ ስለተናደዱና ስለበሸቁ ነበርን?
በፍፁም፡፡ ሰሃባዎች ማለት በጣም ስነስርኣት ያላቸው ትውልድ ነበሩ፡፡ አደለም መልክተኛው በህይወት እያሉ መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከሞቱም በኋላ የሳቸውን ትእዛዝ ታዘው ለሁለት አገር ድል በቅተዋል፡፡ ዛሬ ይህ ኡመት አላህ ካዘነለት ውጭ ሱና እንከተል እየተባለ ወደ ቢድኣ ይሮጣል፡፡ ይህም ኡማዋ ላለበት ውርደት ሰበብ ሆኗል፡፡ አላህ የሳቸውን ሱና አጥብቀው፣ የሱናን ባንዲራ ከፍ አድርጎው ለድል ከሚጎናፀፉት ያድርገን፡፡
ዛሬ ዛሬ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንደገለፁት “የማይሰሩትን የሚናገሩ፣ ያልታዘዙትን የሚሰሩ” ሰዎች ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎችን ከቻልን በእጃችን እንድናስቆም፣ ካልቻልን በምላሳችን እንናገር፣ ካልቻልን በቀልባችን እንድንጠላ ነግረውናል፡፡
አላህ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መወለዳቸውን ሳይሆን መላካቸውን ነው ፀጋ፣ ልገሳ ብሎ የጠራው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
لَقَدْ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ إِذْ بَعَثَ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ يَتْلُوا۟ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتِهِۦ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَإِن كَانُوا۟ مِن قَبْلُ لَفِى ضَلَٰلٍ مُّبِينٍ
አላህ በምእምናን ላይ ከጎሳቸው የኾነን፤ በእነርሱ ላይ አንቀጾቹን የሚያነብ፣ የሚጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልእክተኛ በውስጣቸው በላከ ጊዜ፤ በእርግጥ ለገሰላቸው፡፡ እነርሱም ከዚያ በፊት በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ፡፡
እኛ እዚህ ዲን ላይ ያለን ድርሻ መከተል ብቻ ነው፡፡ መጨመር እና መቀነስ ለእሳት ይዳርጋል፡፡ አላህ ኢድ እና አረፋን እንድናከብር እንደ ደነገገልን መውሊድን እንድናከብር ቢያዘን እንሰራ ነበር፡፡ ነገር ግን የሃይማኖቱ ባለቤት አላህ አላዘዘንም እኛም ስነስርኣት ይዘን ሰይጣን የሚያመጣልንን ወጥመድ አንቀበልም ብለን ይሀው በሱና ላይ ሰሃባዎች በነበሩበት መንገድ ላይ ፀንተናል፡፡ አልሐምዱሊላህ፡፡
ሰይጣን በነብዩ ውዴታ ስም አላህ ያላዘዘውን እንዳያሰራን ወጥመዶቹን ጠንቅቀን እንወቅ፡፡ ነሷራች ኢሳን (አለይሂ ሰላም) ያመለኩት ወደውት እንጂ ጠልተውት አይደለም፡፡ ስለዚህ የአላህ ባሪያ የሆኑትን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስንወድ አላህና መልክተኛው ያዘዙንን ብቻ በመታዘዝ ከከለከሉን በመራቅ ብቻና ብቻ ነው፡፡ አላህ እና መልክተኛው ያላዘዙንን ሰርተን “ለነብዩ ያለኝን ውዴታ ለመግለፅ ነው” ብንል ምክንያት አይሆነንም፡፡
አይደለም መልክተኛውን አላህን መውደዳችን እንኳን የሚረጋገጠው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) በመከተል ነው፡፡ መከተል ሲባል የሰሩትን በመስራት የከለከሉትንና ያልሰሩትን ከመስራት በመራቅ፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በመልክተኛ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ አሚን፡፡
1.7K viewsانور فضلأ, 14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-25 17:49:30 የሲድቅ ( የእውነተኝነት ) ደረጃው

ሲድቅ ከላኢላሃ ኢለ ላህ ሸርጦች አንዱ ሲሆን ታላቅ የቀልብ ዒባዳ ነው ። የቀልብ ዒባዳዎች ባጠቃላይ ከሱ ነው የሚመነጩት ። የመልካም ስራ ሩሕ ነው ማለት ይቻላል ። የኢማን ባለቤቶች ከሙናፊቆች የጀነት ሰዎች ከጀሀነም ሰዎች የሚለዩት በሱ ነው ። ሲድቅ የዲን መሰረት ነው ። የእውነተኛ ሰው ደረጃ ከነብያቶች ደረጃ ቀጥሎ ነው የሚመጣው ። ይኀውም በሚቀጥለው የአላህ ቃል ማየት እንችላለን : –
" وَمَن يُطِعِ اللَّهَ وَالرَّسُولَ فَأُولَٰئِكَ مَعَ الَّذِينَ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِم مِّنَ النَّبِيِّينَ وَالصِّدِّيقِينَ وَالشُّهَدَاءِ وَالصَّالِحِينَ ۚ وَحَسُنَ أُولَٰئِكَ رَفِيقًا "
النساء ( 69 )
" አላህንና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃንም ፣ ከሰማዕታትም፣ ከመልካሞቹ ጋር ይኾናሉ ፡፡ የእነዚያም ጓደኝነት አማረ ፡፡ "
ለዚህም ነው አላህ አማኞችን ከእውነተኞች ሁኑ ብሎ ያዘዘው ። ይህንንም በሚቀጥለው የአላህ ቃል እናገኘዋለን : –
" يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَكُونُوا مَعَ الصَّادِقِين َ"
التوبة ( 119 )
" እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ ፤ ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ ፡፡ "
አላህ የመልካም ስራ ባልተቤቶችን ሲነግረን መልካም ስራቸውን ዘርዝሮ ካወደሳቸው በኋላ እውነተኞች መሆናቸውን መስክሮ አላህን የሚፈሩት እነርሱ ናቸው ብሎ ነው የዘጋው ። የሚቀጥለውን አንቀፅ እንመልከት : –
" لَّيْسَ الْبِرَّ أَن تُوَلُّوا وُجُوهَكُمْ قِبَلَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ وَلَٰكِنَّ الْبِرَّ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَالْمَلَائِكَةِ وَالْكِتَابِ وَالنَّبِيِّينَ وَآتَى الْمَالَ عَلَىٰ حُبِّهِ ذَوِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينَ وَابْنَ السَّبِيلِ وَالسَّائِلِينَ وَفِي الرِّقَابِ وَأَقَامَ الصَّلَاةَ وَآتَى الزَّكَاةَ وَالْمُوفُونَ بِعَهْدِهِمْ إِذَا عَاهَدُوا ۖ وَالصَّابِرِينَ فِي الْبَأْسَاءِ وَالضَّرَّاءِ وَحِينَ الْبَأْسِ ۗ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ صَدَقُوا ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُتَّقُون َ"
البقرة ( 177 )
" መልካም ሥራ ፊቶቻችሁን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም ፡፡ ግን መልካም ሥራ በአላህና በመጨረሻው ቀን ፣ በመላእክትም ፣ በመጻሕፍትም ፣ በነቢያትም፣ ያመነ ሰው ገንዘብንም ከመውደዱ ጋር ለዝምድና ባለቤቶችና ለየቲሞች ለምስኪኖችም ፣ ለመንገደኞችም ፣ ለለማኞችም ፣ ለጫንቃዎችም (ማስለቀቅ) የሰጠ ሰውና ሶላትንም ደንቡን ጠብቆ የሰገደ ፣ ዘካንም የሰጠ ፣ ቃል ኪዳንም በገቡ ጊዜ በኪዳናቸው የሞሉ (ሰዎች ሥራ) ነው ፡፡ በችግር በበሽታና በጦር ጊዜም ታጋሾችን (እናወድሳለን) ፡፡ እነዚህ እነዚያ እውነትን የያዙ ናቸው ፡፡ እነዚያም ተጠንቃቂዎቹ እነርሱ ናቸው ፡፡ "
ሸኹል ኢስላም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –
" والصدق والإخلاص هما في الحقيقة تحقيق الإسلام والإيمان ، فإن المظهرين للإسلام ينقسمون إلى مؤمن ومنافق ، والفارق بين المؤمن والمنافق هو الصدق . فإن أساس النفاق يبنى عليه هو الكذب ، ولهذا إذا ذكر الله حقيفة الإيمان نعته بالصدق كما في قوله تعالى : –
" ሲድቅና ኢኽላስ የኢማንና የእስልምና ማረጋገጫ ናቸው ። እስልምናን የሚያሳዩ ሰዎች ወደ ሙእሚንና ሙናፊቅ ይከፈላሉ, በሙእሚንና በሙናፊቅ መካከል የሚለየው ሲድቅ ነው ። የንፍቅና መሰረቱና መገንቢያው ውሸት ነው ። ለዚህ ነው አላህ አውነተኛን ኢማን ሲገልፅ በሲድቅ የሚገልፀው በሚቀጥለው የአላህ ቃል እንደመጣው : –
" قَالَتِ الْأَعْرَابُ آمَنَّا ۖ قُل لَّمْ تُؤْمِنُوا وَلَٰكِن قُولُوا أَسْلَمْنَا وَلَمَّا يَدْخُلِ الْإِيمَانُ فِي قُلُوبِكُمْ ۖ وَإِن تُطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ لَا يَلِتْكُم مِّنْ أَعْمَالِكُمْ شَيْئًا ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيم ٌ"
الحجرات ( 14 )
የዐረብ ዘላኖች «አምነናል» አሉ ፡፡ «አላመናችሁም ፤ ግን ሰልመናል በሉ ፡፡ «እምነቱም በልቦቻችሁ ውስጥ ገና (ጠልቆ) አልገባም ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ብትታዘዙ ከሥራዎቻችሁ ምንንም አያጎድልባችሁም ፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው ፡፡
" إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ "
الحجرات ( 15 )
(እውነተኛዎቹ) ምእምናን እነዚያ በአላህና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶ ቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው ፡፡ እነዚያ እነሱ እውነተኞቹ ናቸው ፡፡
" لِلْفُقَرَاءِ الْمُهَاجِرِينَ الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِمْ وَأَمْوَالِهِمْ يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّنَ اللَّهِ وَرِضْوَانًا وَيَنصُرُونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ أُولَٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُون َ"
الحشر ( 8 )
" ለእነዚያ የአላህን ችሮታና ውዴታውን የሚፈልጉ ፣ አላህንና መልክተኛውንም የሚረዱ ኾነው ከአገሮቻቸውና ከገንዘቦቻቸው ለተወጡት ስደተኞች ድኾች (ይስሰጣል) ፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው ፡፡"
فأخبر أن الصادقين في دعوى الإيمان هم المؤمنون الذين لم يتعقب إيمانهم ريبة وجاهدوا في سبيله بأموالهم وأنفسهم ."
التحفة العراقية ، ص ( 20 – 21 )
" አላህ በኢማናቸው እውነተኛ የሆኑት እነዚያ ኢማናቸው ጥርጣሬ ያልተከተለው በገንዘባቸውና በነፍሳቸው በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት መሆናቸውን ተናገረ ። "
በመቀጠልም አንድ ባሪያ የቂያማ ቀን ከእሳት ቅጣት የሚጠብቀው ሲድ ብቻ መሆኑን አላህ ሲነግረን እንዲህ ይላል : –
" قَالَ اللَّهُ هَٰذَا يَوْمُ يَنفَعُ الصَّادِقِينَ صِدْقُهُمْ ۚ لَهُمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ "
المائدة ( 119 )
1.6K viewsانور فضلأ, 14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 21:41:43 ጥናተ መንዙማ ክ 2
1.5K viewsانور فضلأ, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-12 08:04:37 ጥናተ መንዙማ ክ 1
2.0K viewsانور فضلأ, 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-12 08:02:21 ኮርስ፡- በአላህና በመጨረሻው ቀን ላመኑ ሁላ፡፡

አርእስት፡- ትውልዱን ከመንዙማ ማስጠንቀቅ፡፡

ሼር በማድረግ ማህበረሰቡ ትምህርቱን እንዲሳተፍ ሰበብ ሁኑ፡፡
ለወጣቶች በክረምት 100 ሀዲስ ተማምረን መጨረሳችን ይታወቃል፡፡ በአላህ ፍቃድ መንዙማ ውስጥ ያሉትን ሺርኮች ትውልዱ ይረዳቸው ዘንድ ዛሬ ማታ ከመግሪብ እስከ ኢሻ ስንኞቹን እያነሳን ከቁርዓን እና ሀዲስ መልስ ይሰጥባቸዋል፡፡ የቴሌግራም ላይቭ ሊንክም ይለቀቃል፡፡ ልጆቾን ተሳታፊ ያድርጉ፣ እርሶም ይከታተሉ፡፡ እስልምናችንን ለማፍረስ ከውስጥ ቆርጠው የተነሱ አካላት በሰለዋት ስም ምን አይነት ከኢስላም የሚያስወጣ ንግግሮች እንዳሏቸው በማስረጃ በአላህ ፍቃድ እንማማራለን፡፡
ፓምፍሌቱን ከዚህ ሊንክ ያውርዱና ፕሪንት አድርገው ይከታተሉ፡- https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/3512
በሞባይላችሁ ለመከታተል የምትፈልጉ ከዚህ ሊንክ አውርዱት፡- https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/3511
በአላህ ፍቃድ ተውሒድ ከፍ ብላ ትውለበለባለች፡፡ ሺርክ ከነባለቤቶቻቸው ይከስማሉ፡፡
2.0K viewsانور فضلأ, 05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-03 23:13:40 አየተል ኩርስይ ከፈርድ ሶላት በኋላ


【عن أبي أُمامةَ الباهليِّ رضيَ اللهُ عنه قال رسول الله صلى الله عليه وسلم من قرأ آية الكرسي في دبر كل صلاة مكتوبة لم يمنعه من دخول الجنة إلا أن يموت】
(رواه النسائي وصححه الألباني)

አቢ ኡማመተ አልባሂልይ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል።
【ግድ ከተደረገበት ፈርድ ሶላት በኋላ አየተል ኩርስይ የሚቀራ ሰው፧ጀነት ለመግባት የሚከለክለው ነገር የለም ሞት ቢሆን እንጂ】
ነሳእይ ዘግቦታል ኢማሙ አልባንይ ሶሂህ ብለውታል።

የሀዲሱ መልእክት ባጭሩ

ከፈርድ ሶላት በኋላ አየተልኩርስይ በሚቀራ ሰውና በጀነት መካከል ያለው ግርዶሽ ሞት ብቻ ነው ማለት ነው። ነገር ግን ይህ ትልቅ ምንዳ የሚረጋገጠው ተውሂድ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። በአላህ ላይ የሚያጋራ ሰው የፈለገ መልካም ስራ ቢሰራ ተቀባይነት አያገኝምና።

አየተል ኩርስይ ከአጭር ትርጉም ጋር

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْحَىُّ ٱلْقَيُّومُ
አላህ ከእርሱ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡
لَا تَأْخُذُهُۥ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ
ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡
لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ
በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ የአላህ ብቻ ነው፡፡
مَن ذَا ٱلَّذِى يَشْفَعُ عِندَهُۥٓ إِلَّا بِإِذْنِهِۦ
ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?
يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ
አላህ (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡
وَلَا يُحِيطُونَ بِشَىْءٍ مِّنْ عِلْمِهِۦٓ إِلَّا بِمَا شَآءَ
በሻውም ነገር ቢሆን እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡
وَسِعَ كُرْسِيُّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ
ኩርስዩን ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡
وَلَا يَـُٔودُهُۥ حِفْظُهُمَا
ጥበቃቸውንም አያቅተውም፡፡
وَهُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْعَظِيمُ
እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡
2.1K viewsانور فضلأ, 20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-03 23:03:34 የምሽት ግብዣ
============
የዚህ ወጣት ብቃት በጣም ነው ያስገረመኝ። ማሻ አላህ! አይመን ጦይብ ይባላል። ከነገ በኋላ እሁድ ከሚመረቁት የመርከዝ ኢብኑ ዐባስ ተማሪዎች መካከል አንዱ ነው።ይህን ጉሮሮ የሰጠው ጌታ አላህ ምስጋና የተገባው ነው።

①, ቃሪእ መውላና ኩርተሽ፣
②, በአስቀሪው ድምፅ፣
③, ቃሪእ አቡበክር አ-ሽ'ሻጢሪ፣
④, ቃሪእ ዐብዱ-ር'ረሕማን መስዑድ
⑤, ቃሪእ ዑመረ-ል-ሒሻሚይ (አዲስ ቃሪእ)
⑥, ቃሪእ ሰልማነ-ል-ዐቲቢይ
⑦, ቃሪእ ያሲር አል-ዱሰሪይ
⑧, ቃሪእ ሰዕደ-ል-ጛሚዲይ
⑨, ቃሪእ ኻሊደ-ል-ጀሊል
10, ቃሪእ ዐብዱ-ል-ባሲጥ ዐብዱ-ስ'ሶመድ

ገና ያላስደመጠን እስከ 5 ድምፆች አሉት!


አላህ ይባርክልህ። አምሳያህንም ያብዛልን። ጠቃሚ እውቀትም ይጨምርልህ!

(ከመርከዙ ገፅ የተገኘ!)
1.5K viewsانور فضلأ, 20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ