Get Mystery Box with random crypto!

ምስክርነት በራስ በቃ وشهد شاهد من اهلها ሙፍቲ ኡመር ገነቴ በራሳቸው አንደበት እ | አል አዝካር AL AZKAR

ምስክርነት በራስ በቃ
وشهد شاهد من اهلها

ሙፍቲ ኡመር ገነቴ በራሳቸው አንደበት እውነታውን እንዲህ በማለት ይመሰክራሉ

መውሊድን የጀመረው መሊከል ሙዘፈር ነው !!

ትክክለኛው ሱና ሰኞ ሰኞ መፆም ነው

መብላት መጠጣት መሰብሰብ የነብዩ ሱና አደለም

ትክክለኛው ሱና ረሱልን መከተል የፈለገ መሰብሰብ መብላት መጠጣት አደለም ሰኞ ሰኞ መፆም ነው !

እኛም እንጠይቃል ታዲያ የማንን ሱና እንከተል የረሱልን ሱና ወይስ ረሱል ከሞቱ ከ 600 ዓመት በሃሏ የተፈጠረውን ?

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በየሳምንቱ ጁምኣ አደራቹን አዲስ ነገር በዲን ላይ ከመፍጠር ተጠንቀቁ ብለው አላሳሰቡም ለምን የረሱልን ቃል አናከብርም ?

አመት ጠብቆ ተሰብብቦ መብላት ፣ መጠጣት ፣ መጨፈር ይህ የረሱል ሱና ካልሆነ ለምን ይፈፀማል አላህ ያዘዘን ረሱልን አደንድንከተል አይደለምን ?

" የዛኔ (በሰሃባዋች ግዜ) ዲን ያልነበረ ነገር አሁን ዲን ሊሆን አይችልም " ኢማሙ ማሊክ